Logo
FIDEL POST NEWS
የጉራጌ ክትፎ ወደ ዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት! 🇪🇹🍲✨

​ታዋቂው የጉራጌ ክትፎን ጨምሮ አራት የጉራጌ ባህላዊ እሴቶችን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (UNESCO) በዓለም የማይዳሰሱ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ ለማስመዝገብ ጥናት መጀመሩን የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ።

​🔹 ለምን ክትፎ ቅድሚያ ተሰጠው?
ክትፎ ከምግብነቱ ባለፈ የጉራጌ ማህበረሰብ መገለጫ፣ የእንግዳ መቀበያ እና የማህበራዊ ትስስር እሴት በመሆኑ ነው። በአሁኑ ወቅት የክትፎ አዘገጃጀት፣ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች (እንደ ቆጮ፣ ሚጥሚጣ እና ንጥር ቅቤ) ያላቸውን ጥበብ በማካተት ሰፊ ጥናት እየተደረገ ይገኛል።

​🔹 ሊመዘገቡ የታጩ አራት እሴቶች፦

1️⃣ የጉራጌ ክትፎ አዘገጃጀት፦ ልዩ የሆነው የማክተፍ እና የቅመማ ቅመም ጥበብ።
2️⃣ ባህላዊ የቤት አሰራር (ክብ ቤት)፦ ያለ ሚስማር የሚገነባውና ለዘመናት የሚቆየው የቤት አሰራር ጥበብ።
3️⃣ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት (የጎርደና ስርአት)፦ ማህበራዊ ሰላምን ለማስፈን የሚጠቀሙበት ጥንታዊ የፍትህ ስርአት።
4️⃣ የጉራጌ መንደር (ጀፎረ) አሰራር፦ ለጋራ መስተጋብር በሚመች መልኩ የሚሰሩ ሰፋፊ መንገዶችና የመንደር አወቃቀር።

​📍 የጥናቱ ሂደት
የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመረጋ እንደገለጹት፣ ለኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል። ጥናቱ እንደተጠናቀቀም ሰነዱ ለዩኔስኮ ዋና መስሪያ ቤት ለውሳኔ ይላካል።
​🔹 ሌሎች የሚጠበቁ ቅርሶች
በዞኑ የሚገኙ ታሪካዊ ዋሻዎች፣ በዕድሜ ጠገብ መስጂዶች የሚገኙ ጥንታዊ ኪታቦች እና በገዳማት የሚገኙ ንዋየ ቅድሳት ለቱሪስት መስህብነት እንዲውሉና ጥበቃ እንዲደረግላቸው በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ብስራት ራዲዮ
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.