Logo
SeledaPost
በሙሽሪት አለመገኘት ምክንያት ሰርጉ ተሰረዘ‼️

በአዲስ አበባ ከተማ ሰሞኑን የተሰማውና ብዙዎችን ያነጋገረው የሰርግ ታሪክ፣ በወጪ ብዛት ሳይሆን በፍጻሜው አስደናቂነት መነጋገሪያ ሆኗል።

ሁሉም ነገር ተሰናድቶ፣ የሰርግ አዳራሹ አሸብርቆ፣ ምግብና መጠጡ ሞልቶ የተጠበቀው ሰርግ፣ በሙሽሪት አለመገኘት ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።

ኖር ሬድዮ ታሪኩን እንዲህ ይነግራችኋል ለዓመታት በትውውቅ የቆዩትና ሙሽራው በውጭ ሀገር የሚኖረው እነዚህ ጥንዶች፣ ጋብቻቸውን ለመፈጸም የለፋ ወጪ አውጥተው ነበር።

ለምሳሌ ያህል ለክትፎ ብቻ 450 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ (Advance) ተከፍሎ ነበር። ዲኮሩም ከትናንትናው ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ተሰርቶ አልቋል።

​ነገር ግን በሰርጉ ዋዜማና በዕለቱ በተፈጠረ አለመግባባት ነገሮች ተበላሹ። ሙሽሪት "ከጋብቻ በፊት የጤና ምርመራ ማድረግ አለብን" የሚል ጥያቄ ታነሳለች። ሙሽራው በበኩሉ ይህንን ጥያቄ ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም ወይም ጊዜው አልፈቀደም ተብሏል።

በዚህ መሃል "ሙሽራው ከዚህ በፊት ትዳር ነበረው፣ አምስት ልጆችም አሉት" የሚሉ ወሬዎችና ጥርጣሬዎች መፈጠራቸው ችግሩን አባብሶታል ተብሏል። ሽማግሌዎች ገብተው ለማስማማት ያደረጉት ጥረትም ሳይሳካ ቀርቷል።

​በመጨረሻም በሰርጉ ቀን ሙሽራውና ሚዜዎቹ ዘንጠው ተዘጋጅተው ቢጠብቁም፣ ሙሽሪት ግን "አልመጣም" በማለት ቀረች።

ተጋባዥ እንግዶችም አንዳንዶቹ ጉዳዩን ሰምተው ሳይመጡ ቀርተዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠር ወጪ የፈሰሰበት ይህ ሰርግ፣ ሙሽራው ብቻውን ከሚዜዎቹ ጋር በባዶ አዳራሽ ፎቶ ተነስቶ ወደ ቤቱ በመመለሱ ተጠናቋል። ምንጭ- ኖር ሬዲዮ

seledadotio
seledadotio
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.