ኢትዮጵያን ጨምሮ የብሪክስ አገራት ግዙፍ የባሕር ኃይል ልምምድ በደቡብ አፍሪካ ተጀመረ
በቻይና መሪነት የሚካሄደውና የብሪክስ ፕላስ አባላትን የሚያሳትፈው “Exercise Will for Peace 2026” የተሰኘው ታላቅ የባሕር ኃይል ወታደራዊ ልምምድ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ የባሕር ክልል በይፋ ተጀምሯል።
🔹 ተሳታፊዎች፦ በቻይና መሪነት እና በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን፤ የሩሲያ እና የኢራን ግዙፍ የጦር መርከቦች በስፍራው መድረሳቸው ተገልጿል።
🔹 ቆይታ፦ ልምምዱ ከዛሬ ጥር 1 እስከ ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ይቆያል።
🔹 ዓላማ፦ “የመርከብ ጉዞዎችን ደኅንነት እና የባሕር ላይ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በጋራ ማረጋገጥ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን፤ የንግድ መስመሮችን ደኅንነት መጠበቅና የአገራቱን ወታደራዊ ቅንጅት ማጠናከር ላይ ያተኩራል።
የደቡብ አፍሪካ መከላከያ ኃይል (SANDF) ዝግጅቱ መጠናቀቁን ያረጋገጠ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት የኢራን ትልቁ የጦር መርከብ በኬፕ ታውን የባሕር ዳርቻ እንደሚገኝና የቻይና እና የሩሲያ መርከቦችም በልምምዱ ላይ እየተሳተፉ መሆኑ ተዘግቧል።
ይህ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የብሪክስ አገራት በዓለም አቀፍ የባሕር መስመሮች ላይ ያላቸውን ተሰሚነት ለማሳደግ የሚያደርጉት ጥረት አካል ተደርጎ ተወስዷል።

9 months ago