Logo
YenetaTube
የኒኮላስ ማዱሮ የፖለቲካ ጉዞ ከባስ አሽከርካሪነት እስከ ፕሬዝዳንትነት

ኒኮላስ ማዱሮ ለብዙ ዓመታት በቬንዙዌላ ፖለቲካ ውስጥ ቁልፍ ሰው የነበሩ ሲሆን ወደ ስልጣን ማማው የወጡት እና ፖለቲካ ከመጀመራቸው በፊት በካራካስ ከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት (ባስ) አሽከርካሪ ነበሩ በወቅቱ በነበራቸው ጠንካራ የተቃውሞ እና የንግግር ችሎታ የሰራተኞች ማህበር መሪ በመሆን ታዋቂነትን አትርፈዋል።

የማዱሮ የፖለቲካ ህይወት የተቀየረው የቀድሞውን የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ሁጎ ቻቬዝን ካወቁ በኋላ ነው።

እ.ኤ.አ. በ1992 ቻቬዝ በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ታስረው በነበረበት ወቅት ማዱሮ እና የወደፊት ባለቤታቸው ሲሊያ ፍሎሬስ (ጠበቃ ነበሩ) ቻቬዝ እንዲፈቱ ከፍተኛ የቅስቀሳ ስራ ሰርተዋል።

ቻቬዝ እ.ኤ.አ. በ1998 ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ በኋላ ማዱሮ በፍጥነት በስልጣን እርከኖች ላይ ወጡ፦

* እ.ኤ.አ. 2000-2006፦ የብሔራዊ ምክር ቤት (ፓርላማ) አባል እና በኋላም አፈ-ጉባኤ ሆኑ።

* እ.ኤ.አ. 2006-2012፦ የቬንዙዌላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ለ6 ዓመታት አገልግለዋል።

* እ.ኤ.አ. 2012፦ በፕሬዝዳንት ቻቬዝ ተወካይ (ምክትል ፕሬዝዳንት) ሆነው ተሾሙ።

ሁጎ ቻቬዝ በካንሰር በሽታ ምክንያት ህይወታቸው ከመለፉ በፊት ማዱሮ ተተኪያቸው እንዲሆኑ በይፋ ተናግረው ነበር።

እ.ኤ.አ. መጋቢት 2013 ቻቬዝ ሲያርፉ ማዱሮ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሆኑ።

ከአንድ ወር በኋላ በተካሄደው ልዩ ምርጫ ተቃዋሚያቸውን ሄንሪኬ ካፕሪሌስን በጠባብ ውጤት በማሸነፍ በይፋ ፕሬዝዳንት ሆኑ።

ማዱሮ እ.ኤ.አ. በ2018 ለሁለተኛ ጊዜ መመረጣቸውን ቢያውጁም አሜሪካን ጨምሮ በርካታ የምዕራብ ሀገራት ምርጫው ፍትሃዊ አይደለም በማለት ሳይቀበሉት ቀርተዋል።

በቅርቡ እ.ኤ.አ. በ2024 በተካሄደው ምርጫም በተመሳሳይ ውዝግብ ውስጥ የቆዩ ሲሆን በመጨረሻም እ.ኤ.አ. ጥር 3 ቀን 2026 በአሜሪካ ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.