በስዊዘርላንድ በሚገኝ ታዋቂ መጠጥ ቤት ውስጥ የደረሰ ፍንዳታ ዓለምን አስደነገጠ
በታዋቂው የበረዶ መንሸራተቻ ስፍራ በበዓሉ መክፈቻ ላይ የደረሰው ፍንዳታ የሰዎችን ሕይወት ሲቀጥፍ ሌሎችን ደግሞ ለአካል ጉዳት ዳርጓል።
በስዊዘርላንድ ከሚገኙ እጅግ ታዋቂ የበረዶ መንሸራተቻ ስፍራዎች (Ski resort) በአንዱ የተከበረው የ2026 የፈረንጆች አዲስ ዓመት ዋዜማ ወደ አስከፊ የቅዠት ሌሊት ተቀይሯል።
በክራንስ-ሞንታና በሚገኘው "ኮንስታሌሽን" የተሰኘ መጠጥ ቤት ውስጥ በደረሰ ኃይለኛ ፍንዳታ፣ በርካታ ሰዎች አዲሱን ዓመት እየተቀበሉ በነበረበት ወቅት ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ፍንዳታው የተከሰተው በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከለሊቱ 7:30 አካባቢ፣ የአዲስ ዓመት አቀባበል በደመቀበት ወቅት ነው።
በቱሪስቶች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለው ይህ መጠጥ ቤት በወቅቱ በሰዎች ተጨናንቆ ነበር። የቫሌይስ ግዛት ፖሊስ እንደገለጸው፣ የሟቾች እና የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር በይፋ ባይረጋገጥም "በርካታ የሞቱ እና የቆሰሉ ሰዎች" እንዳሉ አስታውቋል።
የፖሊስ ቃል አቀባይ ጋልታን ላቲዮን "ምንነቱ ያልታወቀ ፍንዳታ ተከስቷል" ሲሉ ገልጸው፣ የነፍስ አዳን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አረጋግጠዋል።
በአካባቢው የሚገኙ የእሳት አደጋ መከላከል፣ የአምቡላንስ እና የፖሊስ ኃይሎች በቦታው ተሰማርተው አካባቢው በቁጥጥር ስር ውሏል።
የስዊዘርላንድ መገናኛ ብዙኃን ያሰራኟቸው ምስሎች የሚቃጠል ሕንጻ፣ ጥቅጥቅ ያለ ጭስ እና የነፍስ አዳኝ ቡድኖች ተጎጂዎችን ለመርዳት በሚረባረቡበት ወቅት የሚታይ ከፍተኛ መደናገጥን ያሳያሉ። የፍንዳታው መንስኤ እስካሁን ግልጽ ባይሆንም ምርመራው ገና መጀመሩ ተገልጿል።

9 months ago