Logo
Getu Temesgen
ሥልጣኔ ወይስ ኃላቀርነት ለግጭት ...

( የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ ሀሳብ )
#ethiopia | በአለምአቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ እንዲሁም በፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት ቤት ውስጥ በአቀራረቡ እና በምልከታው በተጨማሪም በልዩ ምርምር ውጤት ከሚስገርሙኝ መፃህፍት መካከል በሳሙኤል ፒ ሀንቲንግተን የተፃፈውና እጅግ አነጋጋሪ የሆነው ("The Clash of Civilizations and the Remaking of World Order")የተሰኘው መጽሐፍ፤ ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት በኋላ ያለውን የዓለም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በአዲስ መነጽር የሚተነትን ስራ ነው።

ደራሲው በመጽሐፋቸው የሚከራከሩት፣ በቀጣዩ ዘመን ለዓለም ግጭቶች መንስኤ የሚሆኑት እንደ ድሮው የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለም ወይም የኢኮኖሚ ሽኩቻዎች ሳይሆኑ፣በሥልጣኔዎች መካከል የሚፈጠሩ የባህልና የሃይማኖት ልዩነቶች ናቸው በሚል ጭብጥ ነው።

🔴ሀንቲንግተን ዓለምን በስምንት ዋና ዋና ሥልጣኔዎች :-

1️⃣ምዕራባዊ፣
2️⃣ኦርቶዶክስ፣
3️⃣እስላማዊ፣
3️⃣የቻይና፣
4️⃣ሂንዱ፣
5️⃣የጃፓን ፣
6️⃣የላቲን
7️⃣የአሜሪካ እና የአፍሪካ) ብሎ የዓለም ስልጣኔ ያስቀምጣቸዋል ።

🖊እንደ ማጠቃለያ ⁉️

እንደ ደራሲው እይታ፣ ግሎባላይዜሽን ዓለምን እያቀራረበ በመጣ ቁጥር ሰዎች ከሌላው ባህል ጋር ያላቸው ንክኪ ስለሚጨምር፣ ይህ ሁኔታ የራሳቸውን ማንነት ይበልጥ እንዲጠብቁና ከማይመስሏቸው ጋር የሥልጣኔ ግጭት ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል።

በተለይም የምዕራባውያን ዓለም አቀፋዊ የበላይነት (Hegemony )እየቀነሰ ሲመጣ፣ እንደ እስላማዊና ቻይናዊ ያሉ ሥልጣኔዎች የራሳቸውን እሴቶችና የበላይነት ለማስከበር ከምዕራቡ ዓለም ጋር ከፍተኛ ሽኩቻ ውስጥ እንደሚገቡ ይተነብያሉ።

ደራሲው ግጭቶች ይበልጥ የሚበረቱት በተለያዩ ሥልጣኔዎች አዋሳኝ ድንበሮች ወይም "Fault Lines" ላይ እንደሆነ ያስረዳሉ። ምንም እንኳን መጽሐፉ የዓለምን ውስብስብ ሁኔታዎች ቀለል አድርጎ በማቅረቡና አንዳንድ ትንቢታዊ ትንታኔዎቹ (እንደ September 11 attacks, colloquially known as 9/11ጥቃት እና የቻይና መነሳት) እውነት በመሆናቸው ቢደነቅም፤ በሌላ በኩል ግን ሥልጣኔዎችን እንደ የማይለወጡና ወጥ አካላት አድርጎ መውሰዱ፣ እንዲሁም በሥልጣኔዎች ውስጥ ያሉ የውስጥ ልዩነቶችንና ሰላማዊ ግንኙነቶችን ችላ ማለቱ በብዙ ምሁራን ዘንድ ለከባድ ትችት ዳርጎታል።

በአጠቃላይ መጽሐፉ የሰው ልጅ በቀጣይ ለምን ሊጋጭ እንደሚችልና የዓለም ሥርዓት በማንነት ላይ ተመስርቶ እንዴት ዳግም ቅርጽ ሊይዝ እንደሚችል ጥልቅ ግንዛቤ የሚሰጥ ስራ ነው።

የፖለቲካ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መፃህፍት የማንበብ ፍላጎት ያላችሁ ይህን ድንቅ ሥራ እንድታነቡ እጋብዛለሁ !
#ethiopia 🇪🇹

ለበለጠ ወዳጅነት የፃሃፊውን የኤክስ(X) እና የፌስቡክ ገፅ ይከታተሉ :-

🔗የኤክስ(X)ገፅ:-https://x.com/HDebasu?t=eR...

🔗የፌስቡክ:-https://www.facebook.com/s...

መልካም ቅዳሜ 🙏

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.