Logo
FastMereja
አዋሽ ካፒታል አ.ማ በይፋ ሥራ ጀመረ
#fastmereja I ​የአዋሽ ባንክ ተቀጥላ ኩባንያ የሆነው አዋሽ ካፒታል አ.ማ. በኢትዮጵያ አዲስ ለተጀመረው የካፒታል ገበያ ማዕቀፍ ሙሉ የኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት አጠናቆ ዛሬ ታኅሣሥ 09 ቀን 2018 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል በይፋ ሥራ መጀመሩን አብስሯል።

​ተቋሙ ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) ሙሉ የኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎት ፈቃዱን ሕዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም. ተረክቧል።

በ200 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ሥራውን የጀመረ ሲሆን፣ ወደፊት ካፒታሉን ወደ 400 ሚሊዮን ብር ለማሳደግ ዕቅድ ይዟል። አዋሽ ባንክ የተቋሙ የ95 በመቶ ባለድርሻ ነው።

​ዶ/ር አንዱአለም ኃይሉ የአዋሽ ካፒታል አ.ማ. ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሰይመዋል።

አዋሽ ካፒታል አ.ማ. ​የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፦
📌 ​የድርጅት ፋይናንስ እና የማማከር አገልግሎት።
📌 ​የዋስትና ሰነዶች (Securities) ንግድ እና የማገናኘት ሥራ።
📌 ​የገበያ ጥናትና ምርምር (Research and Market Intelligence)።
📌 ​የአረንጓዴ ፋይናንስ እና የESG (ከባባዊ፣ ማኅበራዊና አስተዳደራዊ) የማማከር አገልግሎት።

​የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የአዋሽ ካፒታል የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ባደረጉት ንግግር የተቋሙ መቋቋም በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍትና ለቢዝነስ ዘርፉ ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥር ነው ብለዋል።
#ቢዝነስ መረጃ

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.