ሜሲን ለማየት ጓጉተው ሿሿ የተሰሩት
የሕንድ እግር ኳስ ቤተሰቦች ...
በትሪቡን ስፖርት
#ethiopia | ነገሩ የንጉሱ የሕንድ ጉብኝት ነው ። የእግር ኳስ ውበት ሞናሊዛው ከMLS ገድሉ ማግስት አትላንቲክን አቋርጦ እነ ሻሩክ ሀገር ደርሷል ። የቅርብ ጓደኞቹ ዴፖልና ሱዋሬዝ አብረውት አሉ ።
ከ1.4 ቢሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ሕንድ በእግር ኳስ አስቂኝ የአፍዝ አደንግዝ የማጂክ ታሪኳ ብቻ ብትታወቅም ምትሃተኛዋን አርጀንቲናዊ ኮኮብ ሊዮኔል ሜሲ ከእልፍ አድናቂዎቹ ልታገናኝ በዛውም የበለጠ ገፅታዋና ቱሪዝሟን ልታነቃቃ በወጠነችው ዕቅድ በኮልካታ ከተማ የሚገኘው 80 ሺህ በላይ ተመልካች የሚይዘው የሳልት ሌክ ስቴዲየሟን እስከ አፍንጫው ሞልታለች ።
የሜሲ 70 ጫማ 21 ሜትር የሚረዝመው በአድናቂዎቹ የተሰራ ሀውልትም በካልካታ ከተማ ግዛት ይመረቃል ።
የኳስ ምትሃተኛው ከቦሊውድ ዝነኛው ሻሩክም ይገናኛል ። ከአርጀንቲና ሮዛሪዮ ሳንታፌ በመነሳት በምትሃቱ ላለፉት 20 ዓመታት የዓለም እግር ኳስን የወረረው ኮኮብ የሶስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ሕንድ ደርሷል ።
በሳልት ሌክ ስቴዲየም በተዓምሩ ምክንያት በአድናቆት ጨርቅ እያስጣለ በደስታ ያስፈነጠዛቸውን የሚወዱት ኮኮብ በህይወት ዘመናቸው አንዴ ዕንኳ በዐይናቸው ለመመልከት ከ1,900 ኪሎ ሜትሮች በላይ አቋርጠው ያላቸውን ነገር ሁሉ አሲይዘው ገና ካልሰሩበት ቀጣይ የወር ደሞወዛቸው ጭምር ቀድመው ተበድረው የሰርግ ቀናቸውን ጭምር ሰርዘው ከ1,500 ዶላር በላይ በጥቁር ገቢያ የተቸበቸበው ትኬትን ተሻምተው ገዝተው ስቴዲየም የተሰባሰቡ ሕንዳዊያን የእግር ኳስ ቤተሰቦች ግን ብዙ መስዋትነት በከፈሉለት የናፈቃቸው ቀን ያልተደራጀ መሰናዶ ተበሳጩ ።
የሚወዱትን ለዓመታት ያስጨፈራቸውን ኮኮብ ለደቂቃዎች ብቻ በሩቁ አይተው እንዲሰናበታቸው መደረጉ አበገናቸው ። በአዘጋጆቹ ቅጥፈት የተበሳጩ ደጋፊዎች የሳልት ሌክ ስቴዲየምንም አወደሙ ። ከፍተኛ ተቋውሞ በማስነሳት ከፀጥታ ኋይሎችም ተፋጠጡ ።
ተከድተናል ። ከፍተኛ ቅጥፈት ተፈፅሞብናል ። ሜሲን በአግባቡ ሳናየው ተለየን ። 20 ደቂቃ ሜዳው ላይ አልቆየም ። ምንም ዐይነት ከአድናቂዎቹ የሚገናኝበት ዝግጅት ሜዳው ላይ አልነበረም ። ኳስ ሲገፋ ፔናሊቲ ሲመታ አንዴ ዕንኳን ሜዳውን ዞሮ ሰላምታ እንዲሰጥ ከአድናቂዎቹ ጋር በቅርብ ርቀት እንዲገናኝ አልተደረገም ። አዘጋጆቹ ይሄንን ሁሉ ደጋፊ ሰብስበው አንድም የተዘጋጁበት ነገር አልነበረም ።
ሜሲ ኳስ እንደሚጫወት ጭምር ነው የተነገረን ! ይህ የለየለት ቅጥፈት ነው ። እራሱ ሜሲ በሁኔታው ሳይገረም አይቀርም ። የሚገርመው አዘጋጆቹ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች የባለስልጣናቱ ልጆች እና የፀጥታ ኋይሎች ወደ መሃል ሜዳው አጅበው አስገብተው እራሳቸው ብቻ ተሻምተው ከሜሲ ፎቶ ተነስተው እንዳጀቡት ይዘውት ወጡ ። ተመልሶ ይመጣል ስንል በዛው ቀረ ። ጉዳዩ ከፀጥታ የደህንነት ስጋት ጋር እንደሆነም ያልተደራጀውን ዝግጅት ለማስተባበል ሲባል ተገለፀ ።
ሜሲ ድንቅ ነው ። ትሁትና የኳስ ምትሃተኛ ነው ። በዛች ውስን ደቂቃ ዕንኳ ለህንድ እግር ኳስ እልፍ አድናቂዎቹ ለተደረገለት አቀባበል ሁሉ ግራሲያስ India እያለ ምስጋናውን አቅርቦ በጥድፊያ ሜዳውን ፎቶ ለመነሳት በሚሻሙ አጀቦች መሃከል ለቀቀ ።
ያኔ messi messi messi በሚል ድምፆች በአድናቆት የደስታ ዕንባ ጭምር የቀለጠው የሳልት ሌክ ስቴዲየም በፍጥነት ወደ ጦር አውድማ ተቀየረ ።
ደጋፊዎች ያገኙትን ንብረት ሁሉ ይሰባብሩ ጀመር ። ወንበሮች የስቴዲየሙ ንብረቶች ሁሉ ወደሙ ። ሜሲን እናያለን ብለን ከፀጥታ ሀይሎች ተፋጠን ተጭበርብረን ከስረን በፖሊስ ተገርፈን ጭምር ወደ ቤታችን ተመለስን ።
አዘጋጆቹ ከፍተኛ ዝርፍያ ፈፅመውብናል ። ቃላቸውን አላከበሩም ። እንዴት ከ80ሺህ በላይ ደጋፊ ስቴዲየም አሰባስበው ሜሲን 20 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ በሩቁ በብዙ አጀብ መሃከል ሰለምታ ሲሰጠን ብቻ እንድናየው አድርገው ይሸውዱናል ። በስሜታችን ቀልደዋል ። ለህይወት ዘመን ደስታችን አልተጨነቁም ። ለእግር ኳስ ባለን ፍቅር ገንዘባችንን ከስረናል ።
ጊዜያችንን አጥፍተናል ። ወደ ስቴዲየም ለመግባት ትኬት በጥቁር ገቢያ እስከ 1,500 ዶላር ተሽጧል ። ይህ ሜሲን ለማየት የሰርግ ቀኑን ጭምር ሰርዞ ዕድሜ ዘመኑን የሚያደንቀው ኮኮብን ለመመልከት ከመቶሺዎች ተጋፍቶ በርካታ ኪሎሜትሮችን አቋርጦ የነገ የትዳር የህይወት አጋሩን በደስታዋ ቀን አሳዝኖ ስቴዲየም ከተገኙ ደጋፊዎች መሃከል አንደኛው አስተያየየት ነው ። ሜሲን በማየት ከማገኘው የህይወቴ ደስታ የሚበልጥ ነገር ስለሌለ ዛሬ የነበረው የሰርግ ቀኔን ጭምር ሰርዣለሁ ።
ብዙ ዋጋ የከፈልኩበት ፕሮግራም ግን ያልተደራጀና በደጋፊዎች ስሜት ላይ ያላገጠ የቀጣፊዎች ነበር ። የነገ የትዳር አጋሬ ባለቤቴንም አሳዝኜ ዕድሜ ዘመኔን በኳስ ፍቅሬ ያስደሰተኝ ሜሲንም ለአንድ ደቂቃ ዕንኳ በአግባቡ ሳላይ ቀርቻለሁ ። ሜሲን ለማየት ዕዚህ ስቴዲየም ለመግባት የሰርግ ቀኔን ጭምር በመሰረዜ ምክንያት ስለ ደረሰብኝ የገንዘብ ኪሳራ ማስታወስ አልፈልግም ሲል በብስጭት ተናግሯል ።
የሕንድ ፖሊስ ከፍተኛ ንብረት ካወደሙ የተበሳጩ ደጋፊዎችን ድርጊት ካረጋጋ በኋላ ሜሲን ለማስመጣት ስራውን በሃላፊነት የወሰዱ የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪዎችን ለፈፀሙት ያልተቀናጀ ደጋፊዎችን የማታለል ተግባር በቁጥጥር ስር በማዋል መጠየቅ ጀምሯል ።
ለተፈፀመው ገፅታን የሚያበላሽ ተግባር ደጋፊዎችንም ሊዮኔል ሜሲንም ይቅርታ ጠይቋል ። ነገሩ የዓለም ሚዲያዎችን ጭምር እያነጋገረ ይገኛል ። የአርጀንቲናዊው ጥበበኛ ሊዮኔል ሜሲ India tour ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከስቴዲየሙ ብጥብጥ በኋላ ከዝነኛው የቦሊውድ አክተር ሻሩክም መገናኘቱ ተገልጿል ። ሜሲ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ጭምር እንደሚያገኝ ተነግሯል ።
ታላቁን የዘመናዊው እግር ኳስ የማይደገም ምትሃተኛ ኮኮብ ለማየት ኪሣቸውን አራቁተው ስራቸውን ትተው የሰርግ ቀናቸውንም ጭምር ሰርዘው ከየአቅጣጫው የተመሙ የሕንድ እግር ኳስ ቤተሰቦች ግን ብዙ ዋጋ በከፈሉለት አጋጣሚ የተመኙትን ሳያገኙ የሚያደንቁት ኮኮብ ሜሲ ሲጫወት ለማየት የጓጉለለት አርጀንቲናዊው ምትሃተኛን ለደቂቃዎች ብቻ ሜዳ ላይ አሳይተው የነሷቸው ሿሿ የሰሯቸው የዝግጅቱ አስተባባሪዎችን እየረገሙ የሳልት ሌክ ስቴዲየምን አውድመው ከፀጥታ ሀይሎች ግርፍያ ጋር ወደ መጡበት በሀዘን ተመልሰዋል ።

10 months ago