በሾፌር አልባው ታክሲ ውስጥ የተወለደ ህፃን
#ethiopia | ሾፌር አልባ ታክሲዎችን ለደምበኞች በማቅረብ የሚታወቀው ዋይሞ ኩባንያ አንዲት ሴት ወደ ሆስፒታል በማቅናት ሳለች በመኪና የኃለኛ ወንበር ልጅ መገላገሏን አሳውቋል።
የዋይሞ ኩባንያ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት አገልግሎት ፈላጊዋ እንስት ሾፌር አልባ ታክሲ (ሮቦት ታክሲ) ያዘዘችው ወደ ጤና ተቋም ለመሄድ አንደነበር እና ጉዞ ሲጀምሩም በመኪናው የኃላ መቀመጫ ያልተለመደ እንቅስቅሴ በጉዞ አስተባባሪ ቡድኖች መታዘባቸውን ተከትሎ ለፖሊስ የአስቸኳይ እርዳታ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ለኬቲቪዩ ፎክስ 2 ቻናል ተናግረዋል።
ዩፒአይ በበኩሉ እናት መኪና ውስጥ ካለ ሰው እርዳታ ልጇን በሰላም የተገላገለች ሲሆን ሰው አልባው መኪናም በመዳረሻነት ወደታዘዘው ሳንፍራንሲስኮ ዩኒቨርስቲ የህክምና ማዕከል ለተጨማሪ የህክምና እርዳታ አድርሷታል።
እናት እና ልጅን ለድንገተኛ ህክምና የተረከበው የዩኒቨርስቲው የህክምና ማዕከልም እናት እና በታክሲ ውስጥ የተወለደውን አዲሱ ህፃን በመልካም ሁኔታ እንደተረከባቸው ማረጋገጫ ሰጥቷል።
#etventertainment

6 months ago