የእርስዎ ምርጫ ማነው?
የፌደራል ጠበቆች የፕሬዝዳንትነት ምርጫ በመራጮች ሚዛን
ጦማሪው ጠበቃ እንደከተበው
#ethiopia | አንድ ነገር ወዳጄ በቴሌግራም ሹክ አለኝ!
"መሠረት ናት የምታሸንፈው!"
"መሠረት የቷ ሁለት እኮ ናቸው" አልኩት
እንዲህም አለኝ " አንተ በቃ ሰው አታውቅም ማለት ነው!! የሴቶቾ ኮኮብ ከኮኮብም የንጋት የሆነችው በየሄደችበት የምትፈካ በጨለማ አብሪ በንጋትም የማትጠፋ ውብ ደማቅ የመብት ነጋሪ ከሀገር ውስጥ እስከ አለም መድረክ የፍትህን ጉዳይ ፍንትው አድርጋ እውነቱን የምትገልጥ አቀራረቧ ማራኪ አመራርዋ አስደናቂ ልምድዋ በግምባርዋ ብእርዋ ከእጆችዋ የማይለያት ረጅም ልምድ ያላት እሷ ናት መሠረት የምጠቅም ብትመረጥ ለሀገር ጥቅም የምትበጅ ማህበሩን የምትማግር ዋልታ ሆና በምሰሶ ችግር አርቃ መፍትሄ የምታቀርብ ፥ ከቅርብ እሩቅ ስልት ነድፋ የታጠቀች ጠበቃውን ቀልብ የሳበች በአመራሩ የተካነች በአለሞች አይን ልብ የሆነች በህግ ሙያ በእውቀቱ የረቀቀች እሷ ናት መሠረት ፥ መሠረት ስዩም ገባህ አደለ 🤩" አለኝ የሳቅ ምልክቶችን በሳቅ በመደርደር
ባይገባኝም ገብቶኛል አልኩትና እሺ እካ ተቀበል አልኩት የቴሌግራም መጻፊያ ኪይቦርዱን በልብ ማንጠልጠያ መገናኛ እያነጣጠርኩበት...
1..2...ተጀመረ የአመራርነትን ካባ የለበሰችው የአነጋገርን ለዛ የታጠቀችው ገና ከጅምሩ የውጭ ሀገር አጋጣሚውን የህግ ክርክር በአለም መድረክ ባታገኝም በዚህ በሀገር ውስጥ ባላት ከፌደራል ፍትህ አካላት በወሰደችው ልምድ ምግባር ዲስፕሊን በመጀመሪያ ባገኘችው የህግ ድግሪ የህግ አጠቃላይ ክህሎትን ዝናሯ ያደረገች ከአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ባገኘችው የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት በሳል የአመራርነትን ክህሎት የተጎናጸፈች በህግ ባለሙያዎች ማህበር ቀንደኛ የመሪነትን ቁንጮ የታጠቀች በፊቷ ግምባሯ ላይ የቆራጥ አመራርነት ስልት የታቀፈች ለእያንዳንዱ ችግር መፈትሄን ለመዘየድ የምታትር በፌደራል ፍርድቤት ብሎም በሌሎች የፍትህ ስረአት አካሄድ በልኩ የተረዳች የጠበቆችን ሙያዊ መብት ለማስጠበቅ ዘዴዎቹን በእጆቿ መዳፍ ጨብጣ የያዘች እሷ መ..ሰ..ረ..ት አያሌው ናት " ብዬ ላኩለት
በዚህ የጹህፍ ምስክርነታችን የብልጫ ድምጽ ድጋፍ ለማገኘት ወዳጄ ወደ አንድ ወዳጁ በቴሌግራም ቻት ይልክለታል ይደግፈው ይመስል ጠብቋል ነገሩ ግን ተገለባብጧል።
" ሁለት አይናቹ ሰነድ ቢያነጣጥር ልባችው ታሪክ ቢያመሰጥር የከበረውን ፋሲል በዳኝነትና በብዙ የጥብቅና አገልግግሎት ልምድ ላይ የቆየውን ወንድማችንን ወዴት አድርጋችሁት??! ቆፎጠን ያለ የችሎት አመራርነቱን ጥበብ ፣ የዳበረ የእውቀትና የምግባር ክህሎት ፣የአስተዳደር ጹሁፎች የምንባብ ልምድና ስራዎቹ ፣ የፍርድ ቤት አገልግሎት ዘመንና የዚህ ትሩፋቶች የተረጋጋ ማንነት ካለው የማህበሩ ተቆርቋሪነትና የጠበቃዎች ሙያዊ መብት መጠበቅ ልዩ ስትራቴጂካዊ እቅዶችን ስትመለከት ማን እንደ ፋሲል!! ደግሞስ አሁን ላይ ለውድድሩ ያቀረባቸውን ማህበሩ ለጠበቃውም ሆነ ለፍትህ ስረአቱ ሊያስገኝ የሚችለውን አበርክቶት በተጋበዙበት የማህበራዊ ሚዲያ ቴሌቨዥን ስንሰማ ከእሳቸው የጥንካሬ ስብእና ጋር ተደምሮ ለመፈጸም የበቁ ቆራጥ እጩ ፕሬዝዳንት ናቸው ከመረጥንማ እንዲጠቅሙን እሳቸውን😘" ብሎ የመለሰለትን ወደ እኔ አሸቅቦት ኖሯል
አሀ ብዬ የኔ መመዘኛ ሀሳብ ሚዛን እንዲደፋለኝ እኔም ወደ አንዱ ባልደረባዬ ብልክለት "ሊመረጥ የሚገባውንማ ለይተን እንወቅ " ካለኝ በኋላ ደቂቃ አስጠበቆኝ" ግን አቶ በሻዳ እያሉ እንዴት ሌላው ይታሰባል?! በህግ አገልግሎት ዘርፍ ረጅም ዘመን የቆዩ በጥብቅና አገልግሎት ረጅም ልምድ እወቀትን ያካበቱ በጠበቆች ማህበር ፕሬዝዳንትንተና ምክትል ፕሬዝዳንትነት የሰሩ እና ታዲያ እሳቸው ያላቸውን ልምድ ያህል ያለው ማን ይኖራል ተብሎ ይታሰባል!? ማህበሩ እንዲጠነክርና እና እንዲጎለብት የጠበቆች ሙያዊ መብትና የማህበሩ አወቃቀር ከሀገሪቱ የፍትህ ስረአት ጋር አዳምሮ ሊመጥን የሚችል ስትራቴጅካዊ ንድፍ በማስቀመጥ የማህበሩን እና የጠበቆችን እድገት ብልጽግና ሊያስጠብቁ የሚችሉት አቶ በሻዳ ብቻ ናቸው " በማለት መልእክቱን አጫረብኝ፥ አቤት የሠው እይታና የድጋፍ ምክንያት አስደማሚ መሆኑን በዚህ ምርጫ እየታዘብኩ ሳለ" ይመረጥ ከተባለማ ተስፋዬ ደረሰ ነው" የሚል የቴሌግራም ሹክሹክታ ተላከበኝ " በሳል ናቸው በዳኝነታቸው ብዙ ያገለገሉ ረጋ ሰከን ብለው ጉዳዮችን በጥበብ፣በእውቀት መመርመር ልማዳቸው ነው።
ውሳኔያቸው ደግሞ የሚፈጸም እንጂ የሚያስደግም አይደለም። አጠቃላይ ስብእናቸው ከአጠቃላይ ረጅም የዳኝነት እና የጥብቅና አገልግሎት እንዲሁም ከጥብቅ ትስስር የፍትህ አካላት ቁርኝት ጋር ተያይዞ እሳቸው የጠበቃውን መብት የሚያስጠብቁ የማህበሩን እድገት እና የፍትህ አስተዋጽኦ ከፍ የሚያደርጉ ከጊዜው ጋር የሚሄዱ ዘመናዊ ሰው ናቸው እሳቸው በጥብቅናውም ሆነ በዳኝነቱ አለም መቆየታቸው በጠበቆች ማህበርም አባል ሆነው መቆየታቸው እንዲሁም ከኢትዮጲያ ፍትህ ስረአት ጋር ቅርብ ትስስር ያላቸው በመሆኑ የማህበሩን ስትራቴጅካዊ እቅድ ፣ ስልት፣አወቃቀር፣ የጠበቆችን አገልግሎትና መብት በላቀ ደረጃ ከፍ በማድረግ ረገድ እሳቸውን የሚስተካከል የለም እሳቸው በፕሬዝዳንትነት ሊመረጡ ይገባል "የሚለውን ንባብ አይኖቼን ያለእርግቢት አንብቤ ከጨረስኩ በኋላ "ማን ይመረጥ" ስል ወደ ልቦናዬ ዳግም አቃጨልኩኝ💀
ማን ይመረጥ 💀💀💀
ጦማሪው ጠበቃ መራጩን ሊወስን ዳግም የአምስቱን እጩ ተወዳዳሪ መለያ ነጥቦችን ነድፎ ከመዘነ በኋላ አንዱ ድምጽ ለማን እንደሚጥል ሊወስን ለዛሬ ምሽት 4:00 ሰአት ቀጠሮ ይዞል።
የጠበቃው ምናባዊ አጥር ያለ ንባቢት የታህሳስ 04/2018 ዓ.ም የትውስታው አካል እንድትሆንለት ይህችን ክታብ አስቀመጠ

10 months ago