በፈረንሳይ የተሰጥኦ ውድድር ላይ የደመቀው ኢትዮጵያዊ
#ethiopia | ኢትዮጵያዊው የሰርከስ አርቲስት ዳግም አይተን በፈረንሳይ የተሰጥኦ ውድድር (France Got Talent) በአስደናቂ ብቃት ወደ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ተሸጋግሯል።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሰርከስ ትርዒት ኢትዮጵያን በዓለም ትላልቅ መድረኮች እና ውድድሮች ላይ የሚያስተዋውቁ የሰርከስ አርቲስቶች ቁጥር እየጨመረ ነው።
የአፍሪካ ድሪምስ ሰርከስ አባል የሆነው ዳግም አይተን የደቡብ ኦሞ ዞን በና ማኅበረሰብ ልዩ ጥበብን አዝናኝ በሆነ መንገድ ባቀረበው የሰርከስ ትርዒት ከዳኞች ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል።
ዳግም አይተን ለሩብ ፍፃሜ ውድድር ከቀረቡ 14 ተወዳዳሪዎች መካከል አንዱ መሆን የቻለ ሲሆን ለግማሽ ፍፃሜ የፊታችን ማክሰኞ ውድድር እንደሚያደርግ የአፍሪካ ድሪምስ ሰርከስ መሥራች የኔነህ ተስፋዬ ገልጿል።
በአሸናፊ እንዳለ
#ebc #ethiopia #francegottalent #talent

10 months ago