በአዲስ አበባ ያለው የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭት ምጣኔ በአገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው በእጅጉ ከፍ ያለ ነው ተባለ‼️
በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር 600 ሺሕ አልፏል።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባካሄደው ጥናት፣ በአዲስ አበባ ያለው የስርጭት መጠን 3 ነጥብ 14 በመቶ ሆኖ ሲገኝ፤ የሀገር አቀፉ ምጣኔ ደግሞ 0 ነጥብ 83 በመቶ እንደሆነ አስቀምጧል።
የቫይረሱ ስርጭት ከ0 እስከ 14 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሕጻናት 16 በመቶ፣ ከ15 እስከ 24 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣቶች 34 በመቶ እንዲሁም፤ 25 ዓመት እና ከዛ በላይ የሆኑ አዋቂዎች ደግሞ 51 በመቶ የሚሆነውን ቁጥር ይሸፍናሉ።
እ.ኤ.አ በ2024/2025 በጀት ዓመት አዲስ በኤች አይ ቪ ተይዘዋል ተብለው የተገመቱ ዜጎች ቁጥር 7 ሺሕ 962 ሲሆን፤ በየዓመቱ በአማካይ 9 ሺሕ 560 ሰዎች በኤች አይ ቪ/ኤድስ ምክንያት ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ተገልጿል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጋር እንደሚኖሩ ከሚገመተው ሰዎች መካከል 94 በመቶ የሚሆኑት ተመርምረው ራሳቸውን አውቀው መድኃኒት እንደጀመሩ በጥናቱ ተረጋግጧል ተብሏል፡፡
seledadotio

10 months ago