Logo
SeledaPost
ትራምፕ በአሜሪካ ከሶማሊያ ሀገር የሚመጡ ሰዎችን ማየት እንደማይፈልጉ ተናገሩ

👉 ትራምፕ የሶማሊያ ስደተኞችን ቆሻሻ ማለታቸውን ኢልሃን ኦማር ተቃውማለች

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሶማሊያ ስደተኞችን በአሜሪካ ማየት እንደማይፈልጉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። "ወደ መጡበት ይመለሱ" እና። "ሀገራቸው በምንም ምክንያት አይጠቅምም" ሲሉ ትራምፕ ተደምጠዋል። የካቢኔ ስብሰባ ላይ ትራምፕ እንደተናገሩት "እውነት ለመናገር ያህል በእኛ ሀገር ላያቸው አልፈልግም" ብለዋል።

ትራምፕ በጥላቻ ንግግራቸው “ቆሻሻን ወደ አገራችን ብንወስድ አሜሪካ በተሳሳተ መንገድ ትሄዳለች” ብለዋል። ይህንን አሳፋሪ አስተያየት ትራምፕ የሰጡት በሚኒሶታ ሰፊውን የሶማሊያ ማህበረሰብ የማባረር ዘመቻ ለማድረግ ማቀዳቸውን ተከትሎ ነው።የግዛቱ ባለስልጣናት እቅዱን ከምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር የመጡ አሜሪካዊያን ዜጎችን ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሊያጠፋ ይችላል ሲሉ አውግዘዋል።

መንትያ ከተሞች በመባል የሚታወቁት ሚኒያፖሊስ እና ሴንት ፖል በዓለም ላይ ከፍተኛው ከሶማሊያ ሀገር የሚመጡ ዜጎች በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩበት ነው። ለሰዓታት የዘለቀው የካቢኔ ስብሰባ ማብቂያ ላይ ማክሰኞ እለት ትራምፕ በሰጡት አስተያየት “በእኛ ሀገር አልፈልጋቸውም። እውነት እላችኋለሁ “ በፖለቲካዊ መልኩ ትክክል ባልሆን እንኳን”  ምንም አይመስለኝም በአገራችን አልፈልጋቸውም ሲሉ ተደምጠዋል።

በመቀጠልም ኢልሀን ኦማርን ተችተዋል። የዲሞክራት ተወካይ እና የመጀመሪያዋ የሶማሊ-አሜሪካዊ በኮንግረሱ ከተመረጠችው ኢልሀን ኦማር ጋር ትራምፕ ደጋግመው ሲጋጩ ቆይተዋል። "ሁልጊዜ እመለከታታለሁ" ያሉት ትራምፕ ኢልሀን ኦማት "ሁሉንም ሰው ትጠላለች እናም እሷ ብቁ ያልሆነ ሰው ነች ብዬ አስባለሁ" ብለዋል። ኢልሃን ኦማር በማህበራዊ ድህረ ገጿ ላይ በሰጠችው የአፀፋ ምላሽ "በእኔ ላይ ያለው ስሜት በጣም አሳፋሪ ነው" ብላለች። በጣም የሚፈልገውን እርዳታ እንደሚያገኝ ተስፋ አደርጋለሁ ስትል አክላለች።

seledadotio
seledadotio
10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.