Logo
SeledaPost
የመጀመሪያዋ ከማርበርግ ቫይረስ ያገገመችው የ15 ዓመት ታዳጊ ከቫይረሱ ነፃ በመሆኗ ከህክምና ማአከል ወጣች

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩ እንደገለፁት ታማሚዋ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምልክት በማሳየቷ ህክምና ሲደረግላት ቆይቶ፣ በላቦራቶሪ ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መሆኗ በመረጋገጡ ከህክምና ማዕከል እንድትወጣ መደረጉን አስረድተዋል።

የበሽታው ታማሚ ታዳጊ በአምላክ ምትኩ 15 ዓመቷ ሲሆን በሽታው መኖሩ በላቦራቶሪ ምርመራ ተረጋግጦ፣  በተደረገላት ህክምና ከበሽታው ማገገም ችላለች፡፡

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምልክቱ በሚታይበት ወቅት ወዲያውኑ ወደ ጤና ተቋም የሚመጡ አካላት የማገገም ዕድላቸው ሰፊ በመሆኑ ሁሉም ሰው ሳይዘናጋ የቫይረሱ  ምልክቶች ሲኖሩ ፈጥኖ ወደ ህክምና ማዕከል መምጣት በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ያስችላል መባሉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

በቀጣይ ቀናት ከማርበርግ ቫይረስ በሽታ አገግመው የሚወጡ ታማሚዎች ስለመኖራቸውም የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ገልጿል።

seledadotio
seledadotio
10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.