Logo
Getu Temesgen
አርሰናል ባየር ሙኒክን 3 ለ 1 አሸንፏል
#ethiopia | በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 5ኛ ዙር ጨዋታ አርሰናል ባየር ሙኒክን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡

በኤምሬትስ በተደረገው ጨዋታ ጁሪየን ቲምበር፣ ኖኒ ማዱኬ እና ጋብርኤል ማርቲኔሊ የመድፈኞቹን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡

ሌናርት ካርል የባየር ሙኒክን አንድ ግብ አስገኝቷል፡፡

የጀርመኑ ክለብ በውድድር ዓመቱ በሁሉም ውድድሮች ለመጀመርያ ጊዜ የተሸነፈበት ሆኗል፡፡

አርሰናል አምስቱንም የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች በማሸነፍ በ15 ነጥብ እየመራም ይገኛል፡፡

ሊቨርፑል በሜዳው እና ደጋፊው ፊት የ4 ለ 1 ከባድ ሽንፈት ገጥሞታል፡፡

በአንፊልድ በተደረገው ጨዋታ ኢቫን ፔርሲች፣ ጉስ ቲል፣ ዴ ኬትሌር እና ድሪዎች የፒኤስቪን አራት ግቦች አስቆጥረዋል፡፡

ዶሚንክ ሶቦዝላይ የሊቨርፑልን አንድ ግብ አስገኝቷል፡፡

ከሜዳው ውጭ ከኦሎምፒያኮስ የተጫወተው ሪያል ማድሪድ 4 ለ 3 አሸነፏል፡፡

ፈረንሳዊው አጥቂ ኬሊያን ምባፔ አራት ግቦችን አስቆጥሯል፡፡

ችኩኒሆ፣ ታርሚ እና ኤል ካቢ የኦሎምፒያኮስን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ፒኤስጅ ቶተንሃምን 5 ለ 3 አሸንፏል።

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.