Logo
Getu Temesgen
በአሜሪካ የተፈቀደው የኤች አይ ቪ መከላከያ በ2 የአፍሪካ ሀገራት በጥቅም ላይ ሊውል ነው
#ethiopia | የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ቢሮ "Gilead sciences" በተሰኘው የመድኃኒት አምራች የበለፀገውና እራሷ አሜሪካ ከአምስት ወራት በፊት ፈቃድ የሰጠችው "lanacapavir" የተሰኘውን የኤች አይ ቪ መከላከያ ክትባት እስዋቲኒ እና ዛምቢያ መውሰዳቸውን ገልጿል።

ሁለቱ ሀገራት በዓመት ሁለት ጊዜ በመውሰድ ከኤች አይ ቪ ይከላከላል የተባለውን ክትባት 500 ዶዝ መውሰዳቸውን ነው አሜሪካ ያስታወቀችው።

ኤች አይ ቪን ጨምሮ እንደ ቲቢና ወባ ያሉ በሽታዎችን ለመዋጋት ድጋፍ የሚያደርገው ግሎባል ፈንድ ከአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤትና ከአምራቹ ጋር በመሆን በ2028 ክትባቱን በብዛት በአፍሪካ በሚገኙና በርካታ ተጠቂዎች ባሉባቸው ሀገራት ቢያንስ 2 ሚሊየን ዶዞችን ለማዳረስ እየሰራ ስለመሆኑም ተገልጿል።

ለሁለቱ ሀገራት የሚሰጡት 500 ዶዞች ያለ ምንም ትርፍ የወጣባቸውን ወጪ ብቻ በመሸፈን የሚሰጡ መሆኑ ሲገለፅ፥ አምራቹ ሀገራት ፈቃድ ከሰጡ የመከላከያ መድኃኒቱን ለመላክ የሚያስችል አቅርቦት እንዳለ ገልጿል።

በአሜሪካና በአለም ጤና ድርጅት ፈቃድ የተሰጠው መድኃኒቱ በአፍሪካ በደቡብ አፍሪካና ዛምቢያ ፈቃድ ሲሰጠው አምራቹ ድርጅት በኬንያ፣ ሩዋንዳና ኡጋንዳ እንደዚሁም ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ፈቃድ እንዲሰጠው ጠይቋል።

አክሎም መድኃኒቱን ለማዳረስ ቅድሚያ የሚሰጣቸው 70% የሚሆኑ የዓለም የኤድስ ተጠቂዎች ያሉባቸውን 18 ሀገራት እንደሆነም ገልጿል።
#npr #tm

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.