የኢትዮ-እስራኤል ኢኖቬሽን ሳምንት በአዲስ አበባ ተጠናቀቀ
#ethiopia | ለሶስት ቀናት ሲከናወን የነበረው የ2025 የኢትዮ-እስራኤል ኢኖቬሽን ሳምንት በትናንትናው ዕለት ተጠናቀቀ። ከጥቅምት 12 እስከ 14 2018 ዓ.ም. በተከናወነው በዚህ ዝግጅት ላይ ለወጣቶች ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከእስራኤል ኤምባሲ፣ ከአዲሰ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ፣ ከስቲም ፓወር፣ ከዩኒስትሪም ድርጅት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የኢኖቬሽን ሳምንቱ የተከናወነ ሲሆን፣ በዚህም ክንውን በፈጠራ ላይ ትኩረታቸውን አድርገው በሚሰሩና ከእስራኤል በመጡ የዩኒስትሪም ድርጅት ባለሞያዎች ስልጠና መሰጠቱ ተነግሯል። በዚህ የስልጠና መርሐ ግብር ላይ 120 ያህል ወጣቶች መሳተፋቸው ታውቋል፡፡
በመዝጊያ ዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ዶ/ር አብርሃም ንጉሴ፣ ይህ ዝግጅት እስራኤል በኢኖቬሽን ላይ ያላትን የካበተ ልምድ ለማጋራት ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ሁለገብ ትብብር ቁልፍ አካል የሆነው የኢትዮጵያን የጀማሪ ኩባንያዎችና የፈጠራ ስነ ምህዳር፣ የእስራኤል ኤምባሲ በቋሚነት ከሚያደርገው ድጋፍ አንዱ መሆኑንም ገልጸዋል።
አምባሳደሩ በተጨማሪም፣ ወጣቶች በፈጠራ ራሳቸውን በማብቃት ችግር ፈቺ ሃሳቦችን ማቅረብ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።
የአዲሰአበባ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደጀኔ ዕንግዳ በበኩላቸው፣ በዩኒቨርስቲው በሳይንስና ቴክኖሎጂ ተማሪዎችን የሚያግዝ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የስቲምፓወር የኢትዮጵያ ተወካይ ዳይሬክተር ዶ/ር ስሜነህ፣ የእስራኤልን የኢኖቬሽን ልምድ መጋራት ጠቃሚ መሆኑን አስገንዝበው፣ በዘርፉ የሚመለከታቸው አካላት ሰፊ ርብርብ እንዲያደርጉበትም ጥሪ አቅርበዋል።
ይህ የፈጠራ ስልጠና ከስቲምፓወር ኢትዮጵያ (STEMpower Ethiopia) ጋር በመተባበር እየተካሄደ ሲሆን፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችና ከአገር ውስጥ የተውጣጡ (Startup) መስራቾችን በ"ጀማሪ አገር" አስተሳሰብ እና በፈጠራ የስራ ፈጠራ ክሕሎቶች ማሰልጠኑም ተገልጿል።

11 months ago