Logo
Getu Temesgen
ልዑል ዓለማየሁ ከአረፉ ከ146 ዓመት በኋላ
#ethiopia | በኢትዮጵያ እና በብሪታንያ መንግሥታት መካከል በተፈጠረው የዲፕሎማሲ ስብራት ምክንያት የመቅደላው ጦርነት ሚያዝያ 3 ቀን 1860 ዓ. ም. መካሄዱ ይታወቃል::

በወቅቱም አፄ ቴዎድሮስ ለጠላት እጅ ላለመስጠት እና ለመጭውም ትውልድ የታሪክ ጠባሳ ላለማውረስ እጃቸውን ለእጃቸው ሰጥተው መቅደላ አምባ ላይ ማረፋቸው ይታወቃል::

የሰባት ዓመት ዕድሜ የነበሩት ልጃቸው ልዑል ዓለማየሁም ተግዘው ከአገራቸው እንዲወጡ ተደርጓል::

በባዕድ ሀገር 11 ዓመት ከኖሩ በኋላም በ18 ዓመት ዕድሜያቸው ህይወታቸው አልፎ ኢንግላንድ በሚገኘው ዊንዘር ቤተመንግሥት በክብር ተቀብረዋል::

ይህም የተከናወነው በኢንግላድ ቤተክርስቲያ ሥርዓትና ወግ መሠረት ነበር::

ልዑል ዓለማየሁ ከአረፋ ከ146 ዓመት በኋላ ትላንት አርብ ህዳር 5 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት በዩናይትድ ኪንግደም እና በአካባቢው ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከአንጋፋው የኢትዮጵያዊያን ተራድኦ ማህበር በብሪታንያ ጋር በመተባበር የልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ አፅም ከአረፈበት ቤተመንግሥ በመገኘት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓትና ደንብ መሠረት ፀሎተ ፍትሐት እንዲደረግላቸው አድርገዋል::

አሁን እየተከታተላችሁ ያላችሁትም የዚሁ መታሰቢያ ዝግጅት አካል የሆነ ሕዝባዊ ስብሰባ ነው::

በዚህ ዝግጅት ላይም የታሪክ ተመራማሪዎች: የሥነ-ልቦና እና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የባይተዋሩን ልዑል የግዞት ሕይወት በተመለከተ ምልክታቸውን እያካፈሉን ነው::

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.