Logo
FastMereja
ዛሬ ምሽት ዐይኖች ኹሉ ሲዳማ ላይ ናቸው!!!
====================
ህዳር 5 እና 6 ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት ይጠብቁን።
በቋንቋዬ ነሽ ሚዲያ
በመንክር ሚዲያ
በነጋሽ ሚዲያ
በተአምኖ ሚዲያ
በአዛሔል ሚዲያ
በሎዛ ሚዲያ
በ 21 ሚዲያ

የአረንጃ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የሚገኘው በሲዳማ ሀ/ስብከት በሸበዲኖና ቦርቻ ወረዳ ቤተክነት ከሀዋሳ ከተማ በ48ኪ ሜ ርቀት ላይ የሚገኝና ጥንታዊና ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ነው::

የመድኃኔዓለም ታቦተ ህጉ በአፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት በደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ በ1874 ዓ ም በሲዳማ ክልል ከበሌላ ከተማ በ4 ኪ ሜ ርቀት ላይ ኢቲሳ በሚባል ቀበሌ ገበሬ ማህበር አነስተኛ መቃኖ በመስራት ታቦቱን አስገቡት። ሆኖግን ቦታው አመቺ ካለመሆኑ የተነሳ በድጋሚ በአረንጃ ቀበሌ አዲስ መቃኞ ቤት ሰርተው በ1876 ዓ ም ራስ ባልቻ አባ ነፍሶ ከአከባቢው ሀገር ሽማግሌዎችና ምዕመናን ጋር በአጀብና በሆታ በእልልታ አስገቡ። አሁን በቤተክርስቲያኑ በስጦታ ከራስ ባልቻ አባ ነፍሶ የተበረከተ የብርና የነሀስ መስቀሎች መጎናፀፊያዎች የብራና መጽሐፌት ይገኛሉ።

ከእነዚህም መካከል ወደ እንግሊዝ የተወሰደ አንድ የብራና መጽሐፍ በቦታው ተወላጅ የሆነች አንዲት እህት በሙዚየም ውስጥ ለጉብኝት በገባችበት ወቅት ይህን መጽሐፍ ተመልክታ ስታነበው ከኢቲሳ የመጣ የሚል ጽሑፍ ተመልክታ ይሄማ የአገሬ የመድሃኒአለም መፅሀፍ ነው ብላ ተከራክራ ተፃፅፋ ልታስመልስ ችላለች አሁን በዚህ ይገኛል ።

ቤተክርስቲያኑ አሁን ላይ 144ዓመት ያስቆጠረና ብዙ ገቢረ ታዕምራት የሚደረግበት ቦታ ነው የአከባቢው ምዕመን የለ ዕምነት ልዮነት እሚጠብቁትና እሚማፀኑት ዝናብ ቢዘገይባቸው በህብረት በቦታው ተማፅነው ዝናብ እሚያገኙበት ቦታ ነው ከዚህም የተነሳ የአከባቢው ምዕመን ያለ ሀይማኖት ልዩነት የመድኃኔዓለም አባታችንን ስም እንዃ ከፍቅራቸው የተነሳ መድዬ ብለው ነው የሚጠሩት።

ከተለያዮ ዓለማት መጥተው ብዙ የተደረገላቸው ምዕመናን በምስክርነታቸው ሲደመጡ ተሰምቷል ።
እኛም የዚህ ታላቅ በረከት ተሳታፊ እንሆን ዘንድ ቤተክርስቲያኗ ጥሪዋን ለልጆቿ ታስተላልፋለች።
ወስብሃት ለእግዚአብሔር ወወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር።አሜን።

ቤተክርስቲያኑን ለመርዳት
ንግድ ባንክ_ 1000726667188
አቢሲንያ _241419592
አዋሽ _01352167694720

የውጪ አካውንት
$Net7818523 Cash up account
Zel=+1 2407818523

ስልኮች
0916583334
0911369366
0927067797
0913107659

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.