Logo
Getu Temesgen
#urgent
ደራሲ ስለሺ አምባው በፅኑ ታሟል እናሳክመው
#ethiopia | ደራሲ ስለሺ አምባው የሙሉ ጊዜ አንባቢና ጸሐፊ ነው:: ከድርሰት ውጭ ሌላ መተዳደሪያ የለውም:: ለዚህ የጥበብ ሙያው ሲል ለስምንት ዓመታት የቆየበትን የዩኒቨርሲቲ መምህርነት እስከ መተው ደርሷል::

የግጥም፣ የትያትር፣ የልቦለድ፣ የፊልም እና የአጫጭር የቴሌቪዥን ድራማዎች ደራሲ ስለሺ ባሳለፍነው ዓመት ምርጥ የፊልምና የትያትር ደራሲ በሚል በክልል ደረጃ እውቅናና ሽልማት ተበርክቶለታል::

ከስራዎቹ መካከልም ‹‹ገዳይ ሲያረፋፍድ›› የተሰኘው የሙሉ ጊዜ ፊልም፣ ‹‹ችሎት››፣ በመታየት ላይ ያለ ‹‹የጉድ ጀንበር›› ‹‹ በሕግ ›› እና ሌሎች የቴሌቪዥን አጫጭር ድራማዎቹ ይጠቀሳሉ::

ደራሲ ስለሺ አምባው ስራዎቹና ድርሰቶቹ በርካታ ናቸው።

12ኛ ክፍል ሲያጠናቅቅ ከ20 ዓመት በኋላ በባህር ዳር ጊዮን ሆቴል በር እንገናኝ በሚል ከተማሪዎቹ ጋር በመቀጣጠር እንዲገናኙ የሃሳቡ ጠንሳሽ ነው። ብዙ ሚዲያዎች ተቀባብለውታል። የድርሰት እና የትርጉም መጽሐፍት ጽፏል። የተከታታይ ፊልሞችን በመድረስና በማዘጋጀት ታዋቂ አርቲስቶችን አፍርቷል።

ደራሲ ስለሺ አምባው ለሰው ልጅ ሰዕብና የሚሟገት እና የሚያግዝ እንዲሁም አቅጣጫና መፍትሔ ለማንም ሰው የሚሰጥ የሰው መውደድ ያለው ደራሲ ነው።

ትናንት በመኖሪያ ቤቱ በደረሰበት የመውደቅ አደጋ መቆም እና መንቀሳቀስ አልቻለም።

የሕክምና ባለሙያዎችም የተጎዳው የእግሩ አጥንቶች ከፍተኛ ችግር ስለገጠማቸው የቀዶ ህክምናና የአጥንት ለውጥ በአስቸኳይ መታከም ካልቻለ ለህይወቱ እንደሚያሰጋውና ህክምናውም እስከ 1,400,000.00 (አንድ ሚሊየን አራት መቶ ሺ) ብር እንደሚያስፈልግ ተነግሮታል።

ስለዚህ ደራሲ ስለሽ አምባው መታገዝና መረዳት ስላለበት በውጭ ሃገርና በሃገር ውስጥ ያላችሁ የጥበብ ወዳጆች እጃችሁን እንድትዘረጉ ተጠይቃችኋል።

የገንዘብ አሰባሳቢና አሳካሚ ኮሚቴዎች በመዋቀር ላይ ስላሉ አካውንት ከፍተው ይፋ እስከሚያደርጉ ድረስ በደራሲ ስለሺ አምባው ስም ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000158103331
ስለሺ አምባው

የስለሺ ሥራዎች
የመድረክ ቴአትሮች
ስውሩ ክርን
የመጨረሻው መንገደኛ እና የመሳሰሉት

አጫጭር ልቦለዶች
ከእጓላማውታን መልስ
ስደተኛወና የመሳሰሉት

ፊልሞች
ገዳይ ሲያረፋፍድ
የቄሳር ዲናሮችና የመሳሰሉት

የቴሌቪዥን ድራማዎች
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከአምስት ዓመት በላይ በየሳምንቱ ችሎት ድራማን በድርሰት ሰርቷል

በአማራ ቴሌቪዥን መስታውት በተሰኘ የድራማ ዝግጅት ላይ ከ50 በላይ ድርሰቶች ሰርቶ ተላልፎለታል

ለህትመት ባይበቁም ከ100 በላይ ግጥሞች ሰርቷል

በበኩር ጋዜጣ ላይ ለረዥም ጊዜ አምደኛ ሆኖ አርቲክሎችን በመፃፍ ታትመውለታል።

የክልሉ ባህልና ቱሪዝም በስነ ፅሑፍ ላበረከተው አስተዋፅኦ ዕውቅናና ሽልማት አበርክቶለታል።

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.