Logo
Getu Temesgen
የቢቢሲ የዜና ኃላፊ በትራምፕ ንግግር አርትዖት ቅሌት ከሥልጣን ለቀቁ
#ethopia | በብሪታንያ ሕዝብ የገንዘብ ድጋፍ የምትተዳደረው የብሔራዊ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ አገልግሎት ቢቢሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት እና የዜና ክፍል ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ዴቦራ ተርነስ ከድርጅቱ መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።

የኃላፊዎቹ መልቀቅ የተከሰተው የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ንግግርን በሚመለከት በተደረገው 'የአርትዖት ቅሌት' ምክንያት በቢቢሲ ላይ የፖለቲካዊ ገለልተኝነት የጎደለው አሠራር አለ በሚል ሰፊ ትችት ሲቀርብ ከቆየ በኋላ ነው።

ቅሬታው የተነሳው ቢቢሲ በዶናልድ ትራምፕ ንግግር ላይ አርትዖት በማድረግ በተመልካች ላይ የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲፈጠር አድርጓል በሚል ነው።

የዜና ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ዴቦራ ተርነስ በሰጡት መግለጫ ላይ፣ በግጭቱ ምክንያት ተቋሙን የሚወዱት ቢቢሲ "ጉዳት ላይ መድረሱን" ገልጸው፣ "እንደ ቢቢሲ ዜና እና ወቅታዊ ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ፣ ኃላፊነቱ ከእኔ ጋር ያበቃል" ("As the CEO of BBC News and Current Affairs, the buck stops with me.") በማለት የሥራ መልቀቂያቸውን አረጋግጠዋል።

የብሪታንያ የሕዝብ ብሮድካስት ኩባንያ የሆነው ቢቢሲ በቻርተሩ መሰረት በዘገባዎቹ ውስጥ ገለልተኛነትን የመጠበቅ ግዴታ ያለበት ሲሆን፣ የቅርቡ ክስተት ከፍተኛ ጫና የፈጠረ ከመሆኑም ባሻገር ተቋሙ ለተጨማሪ ምርመራና ትችት እንዲጋለጥ አድርጎታል ሲል መናኸሪያ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.