በጌዴኦ ዞን የሚገኙ የአልኮል መጠጥ ቤቶች ከምሽቱ 12 ሰዓት በኃላ እንዳይሰሩ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉ ተነገረ‼️
መጠጥ ቤቶችና ሰዓት እላፊ ገበያ በጤና ፣በኢኮኖሚ ፣በትምህርት ፣በሰላምና ፀጥታ ፣በሴቶችና ህፃናት ፣በባህል እሴት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ በመሆኑ በጌዴኦ ዞን የሚገኙ መጠጥ ቤቶች እና ገበያዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት በኃላ እንዳይሰሩ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዷለም ማሞ ተናግረዋል።
መጠጥ ቤቶች ለፀጥታና ለከፉ ወንጀሎች 80 በመቶ መነሻ ከመሆናቸዉ በዘለለ እንደ ኤችአይቪ ፣ቲቪ ፣አባላዘር ፣ጉበት ፣ካንሰርና ለተለያዩ ተላላፊ እና አስከፊ በሽታዎች ተጋላጭ በማድረግ ለከፋ ሞት እየዳረጉ እንደሚገኙ ተገልጿል ። ከወንጀል አንጻር ግዲያ ፣አስገድዶ መድፈር ፣ስርቆት ፣ዝርፊያና አደንዛዥ ዕጽ ዝውውር እንዲበራከት ዋንኛው መንስኤ መሆኑን ተጠቁሟል ።
በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ መጠጥ ቤቶች ፣ሺሻ እና ቁማር ቤቶች ሙሉ ለሙሉ እንዳይኖሩ ይደረጋል ሲሉ አቶ አንዷለም ከጣቢያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል ። የአረቄ መጠጥ ወደ ዞኑ እንዳይገባ ማገድ እንዲሁም በተለይም በገጠሩ ማህበረሰብ ዘንድ በጤናማነት የሚዘጋጁትን ሳይሆን አሁን ላይ ባዕድ ነገር ተቀላቅሎባቸዉ የጤና ዕክል የሚያመጡትንና አስክረዉ የወንጀል ድርጊት ለመስራት ሀይል የሚሰጡ ጠላ ቤቶች እንዲዘጉ ይሰራል ተብሏል ።
የአልኮል መጠጥ የጤና አስከፊነት የኃይማኖት ተቋማት ፣ትምህርት ቤቶችንና የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል ።
#ዳጉ_ጆርናል
seledadotio

11 months ago