የወለደችውን ልጅ ወንዝ ዳር ጥላ ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገችው ግለሰብ በእስራት ተቀጣች
በሰሜን ጎንደር ዞን አብነት ወረዳ አብነት ከተማ ነዋሪ የሆነቸው መሰሉ ንጉሴ የተባለች የሃያ አንድ አመት ወጣት የወለደችው ልጅ ጥላ ህይወቱ እንዲጠፋ በማድረጓ በቁጥጥር ስር ዉላለች።
ግለሰቧ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ በእንግድነት በመምጣት የቆይችበት ቤት አካባቢ ከአንድ ወጣት ጋር ተቀራርባ እንደነበረ ተገልጿል ።ወደ አረብ ሀገራት ወጥታ የመስራት ፍላጎት እንዳላት እና ለዚህም እንዲረዳት ስትነግረው በዚህ ጉዳይ የሚሰሩ ደላሎች እንደሚያውቅ እና እንደሚረዳት ነግሯት ግንኙነታቸውን ወደ ፍቅር አድጎ ነፍሰጡር መሆኗን ትረዳለች፡፡ይሁን እና እርግዝናዋን ስትነግረው ከአካባቢዉ ይሰወራል፡፡ መሰሉ የተፈጠረውን ነገር ተቀብላ ቀጥታ ስራ ፍለጋ ወደ ሻሸመኔ ከተማ በመሄድ ነገሌ አርሲ ስራ ተገኝቶላት ነገሌ ከተማ ቀርሣ መጂ ቀበሌ በአንድ ግለሰብ ቤት በሰራተኛነት የአራት ወር እርጉዝ ሆና መቀጠሯን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።
መሰሉ የቤት ሰራተኛ ሆና ስትቀጠር ምንም አይነት የእርግዝና ምልክቶች እና የሰውነት ለውጥ ሰይታይባት መቆየቷን የነገሌ አርሲ ወረዳ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ ኢንስፔክተር ወርቁ ሁሪሳ ገልጸዋል።ሃምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም መሰሉ ሳይታሰብ የመውለጃዋ ምጥ ሲመጣባት ምሽት 12 ሰዓት ላይ በከተማው ወደሚገኝ አዋዴ የተባለ ትልቅ ወንዝ በመሄድ ለብቻዋ ወንድ ልጅ ትገላገላለች።
የተገላገለችውን ወንድ ልጅ ማንም ሳያያት ወንዝ ዳር አስቀምጣ ለሁለት ሰዓታት ከወንዙ አካባቢ ሳትርቅ ቆይታ በአካባቢው ሰዎች አማካይነት ወንዝ ዳር የተጣለውን ልጅ የሚያነሳ ሰውን ስትከታተል በቁጥጥር ስር ውላለች።ፖሊስም ወዲያው የተጣለውን ልጅ ሲመለከት መሞቱን በመረጋገጡ ወደ ኩዮራ ሆስፒታል የህፃኑን አስክሬን በመላክ የምርመራ ውጤት ተቀብሎ የምርመራ መዝገቡን በበቂ ሁኔታ በማስረጃ በማጠናከር ለአቃቢ ህግ ልኳል።
አቃቢ ህግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ ህፃን ልጅን ወልዶ በመጣል ወንጀል ክስ መስርቷል።በአቃቢ ህግ የተመሰረውን ክስ ሲከታተል የቆየው የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድቤት ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ መሰሉ ንጉሴ በቀረበባት ክስ ሙሉ በሙሉ ጥፋተኛ መሆኗ በመረጋገጡ 15 ዓመት እስራት እንድትቀጣ ወስኖባታል።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል

12 months ago