Logo
FIDEL POST NEWS
"መጻሕፍትን ማንበብ መኖር ያስተምረናል፤ የመኖር ጥንካሬ ይሰጠናል። በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ባለው በዚህ አስከፊ ጊዜ ውስጥም ቢሆን፣ ማንበብ ያፅናናል "ይሉናል የኖቤል አሸናፊው ላስሎ ክራስናሆርካይ

በጣም ዝምተኛ፣ ሆኖም በጥልቅ የነቃ ሰው – ላስሎ ክራስናሆርካይ። እ.ኤ.አ. በ2025፣ በአንድ የጥቅምት ወር ጠዋት፣ ፍራንክፈርት ውስጥ በሚገኝ አንድ የታመመ ጓደኛቸው አፓርታማ ውስጥ ተቀምጠው ሳለ፣ ለሥነ ጽሑፍ የኖቤል ሽልማት እንደተጠሩ ሰማ ። ዜናው ወዲያውኑ እንዳስደነገጣቸውና ዝም እንዳሰኘው ታወቀ።

ክራስናሆርካይ ከኖቤል ኮሚቴ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ስለብቸኛ ጽሑፋ፣ ከመራርነት ስለሚወለደው መነሳሳት፣ እንዲሁም ሰዎችን መኖር ስለሚያስተምሩ፣ በጨለማ ጊዜም ቢሆን ስለሚያቆዩ ስለ መጻሕፍትና ምናብ ኃይል ተናግረዋል።

ቃለ ምልልሳቸው ይሄን ይመስል ነበር;

'እንደነዚህ ያሉ እጅግ አስደናቂ ገጣሚዎችና ጸሐፊዎች ወደሚገኙበት ረጅም ሰንሰለት መቀላቀሌ በእውነት ያስኮራኛል።' አዲሱ የሥነ ጽሑፍ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ላስሎ ክራስናሆርካይ በዚህ ቃለ ምልልስ ደስታቸውን አካፍለዋል። ይህ ሽልማት ለእሳቸው ፈጽሞ ያልተጠበቀ እንደነበር ተናግረዋል። በንግግራቸውም ለጽሑፋቸው ዋነኛው አንቀሳቃሽ ኃይል 'መራርነት' እንደሆነ ገልጸዋል። ከመጎዳት፣ ከቁስልና ከሕይወት ኩራት መነሳሳትን ያገኛሉ። ሆኖም፣ ለእሳቸው ከሁሉ በላይ አስፈላጊው ነገር ምናብ (ምናባዊ አስተሳሰብ) ነው። 'ምናብ ከሌለ ሕይወት ፈጽሞ የተለየ ይሆን ነበር' ብለዋል። 'መጻሕፍትን ማንበብ መኖር ያስተምረናል፤ የመኖር ጥንካሬ ይሰጠናል። በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ባለው በዚህ አስከፊ ጊዜ ውስጥም ቢሆን፣ ማንበብ ያፅናናል።

ጄኒ ራይደን (የኖቤል ሽልማት ፋውንዴሽን): ሄሎ?
ላስሎ ክራስናሆርካይ: ሃሎ
ጄኒ: ጄኒ ራይደን እባላለሁ፣ ከኖቤል ሽልማት ፋውንዴሽን ነው ምደውለው
ክራስናሆርካይ: ኦ፣ እሺ
ጄኒ: ላስሎ ክራስናሆርካይ ኖት ?
ክራስናሆርካይ: አዎ፣ እኔ ነኝ።
ጄኒ: በመጀመሪያ እንኳን ደስ ያለዎት፣ የሥነ ጽሑፍ የኖቤል ሽልማት አሸንፈዋል።
ክራስናሆርካይ: በጣም አመሰግናለሁ። በጣም አመሰግናለሁ።
ጄኒ: አሁን ምን እየተሰማዎት ነው?
ክራስናሆርካይ: (ይስቃሉ) አንድ ዓይነት ጥፋት ነው! (ይስቃሉ) አሁን ስለ ሳሙኤል ቤኬት እያሰብኩ ነው፣ እሱም የኖቤል ሽልማት ሲቀበል። ዘገባው እንደገለጸው ማንም ምንም አልጠየቀውም ነበር፣ እሱ አንድ ነገር ብቻ ነው ያለው: 'ምን አይነት ጥፋት ነው!' እኔ የምለው ደግሞ፣ ከዚያም የበለጠ ትልቅ ጥፋት ነው። ምክንያቱም በአንድ በኩል እጅግ በጣም ትልቅ ደስታ ነው፣ በሌላ በኩል ደግሞ አንድ እንግዳ የሆነ ፍርሃት። ኩራት ይሰማኛል፣ ደስተኛ ነኝ። በጣም ብዙ አስደናቂ ገጣሚዎች፣ ደራሲያን፣ የሰውን ነፍስ ተርጓሚዎች ወዳሉበት ንቅናቄ መቀላቀል መቻሌ በአፍ መፍቻ ቋንቋዬ ለመጻፍ አዲስ ኃይል ይሰጠኛል። በሀንጋሪኛ ነው የምጽፈው፣ ትንሽ ቋንቋ ነው፣ ነገር ግን ዓለሜን በውስጡ አገኛለሁ። በዚህ ቋንቋ የመጻፍ ዕድል በማግኘቴ ኩራት ይሰማኛል፣ አመስጋኝ ነኝ። ከሁሉም በላይ ደግሞ መጻሕፍትን አሁንም ለሚያነቡ፣ ምናባዊ አስተሳሰብን አሁንም ለሚያውቁ አንባቢዎች ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ። ሰዎች ምናባቸውን መልሰው እንዲያገኙ እፈልጋለሁ። ምክንያቱም ያለ ምናብ ሕይወት ሙሉ በሙሉ የተለየ ይሆናል። መጻሕፍትን ማንበብ የመኖር ጥንካሬ ይሰጠናል፣ ያበለጽገናል – በገንዘብ ሳይሆን በስሜት። መጻሕፍትን ማንበብ በችግር ዓለም ውስጥ በጥሩ ሁኔታ እንድንኖርና እንድንተርፍ ይረዳናል።

ጄኒ ራይደን: እንግዲህ፣ አሁን የት እንዳሉ ትንሽ ይንገሩን? ዜናውን የሰሙበት ቅጽበት ምን ይመስል ነበር?
ላስሎ ክራስናሆርካይ: አሁን ያለሁት ፍራንክፈርት ውስጥ፣ አንድ ጓደኛዬ ቤት ነው። ታሟልና ልጠይቀው መጣሁ። የኖቤል ሽልማት ማግኘቴን አሁንም ማመን አልቻልኩም። አንድ ሰው ስህተት የሰራ ይመስላል! ግን በጣም ደስተኛ ነኝ።
ጄኒ ራይደን: በጭራሽ አልጠበቁም ነበር?
ላስሎ ክራስናሆርካይ: ፈጽሞ አልጠበቅኩም። አስቤው አላውቅም። ሙሉ በሙሉ ተደንቄያለሁ።
ጄኒ ራይደን: ለጽሑፍዎ ትልቁ መነሳሳት ከየት ነው የሚመጣው?
ላስሎ ክራስናሆርካይ: ከመራርነት። ስለ ዓለም ወቅታዊ ሁኔታ ሳስብ፣ በጥልቅ ሐዘን እሞላለሁ። ያ ሐዘን ነው የጽሑፌ ኃይል የሚሆነው። ምናልባት ይህ መራርነት ለቀጣዩ ትውልድም፣ በጨለማ ጊዜ ውስጥም ቢሆን የመኖርን ፍላጎት ለመጠበቅ አንድ ዓይነት መነሳሳት ሊሆን ይችላል። አሁን የምንኖረው መኖር ከመቼውም ጊዜ በላይ ትልቅ ጥንካሬን በሚጠይቅበት ዘመን ነው።
ጄኒ ራይደን: እንግዲህ፣ ጽሑፍ በጨለማ ጊዜ ውስጥ ለመኖር እንዴት እንደሚረዳዎት እየተናገሩ ነው?
ላስሎ ክራስናሆርካይ: ጽሑፍ በእርግጥም በጣም የግል ጉዳይ ነው። ስለ ሥራዬ አብዛኛውን ጊዜ በፍጹም አወራውም፣ ለሌሎች ጸሐፊ-ጓደኞቼም አላሳይም። አንድ መጽሐፍ እጽፋለሁ፣ ከዚያ ለአሳታሚ አስረክባለሁ፣ ከዚያ ለጥቂት ቀናት ዝም እላለሁ። ከዚያም አንድ ቀን እንደገና እጀምራለሁ፣ ከበፊቱ የተሻለ ነገር ለመጻፍ እሞክራለሁ። ሕይወቴ እንደዚያ ነው የሚጓዘው።
ጄኒ ራይደን: በአንድ ቦታ ላይ እንደማይኖሩ ሰምቻለሁ አይደል? ከአንድ በላይ ከተማ ውስጥ መኖሪያ አለዎት?
ላስሎ ክራስናሆርካይ: አዎ፣ በትክክል ሰምተዋል። ሀንጋሪ ውስጥ እኖራለሁ – ቡዳፔስት አቅራቢያ በኮረብታ ላይ ያለ ትንሽ ቤት። ትሪዬስቴ (ጣሊያን) ውስጥም እኖራለሁ፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቪየና ውስጥ። በድሮው ኦስትሮ-ሃንጋሪ ግዛት ውስጥ እዞራለሁ ማለት ይቻላል።
ጄኒ ራይደን: ይህንን ደስታ እንዴት ያከብራሉ?
ላስሎ ክራስናሆርካይ: በእውነቱ ዛሬ አስተዳደራዊ ሥራ ነበረብኝ፣ አዲሱን አድራሻዬን በጀርመን ልመዘግብ ነበር። (ይስቃሉ) ስለዚህ ዜናውን ከሰማሁ በኋላም ዕቅዶቼን መለወጥ አልቻልኩም። ምናልባት ማታ ላይ ፍራንክፈርት ውስጥ ካሉ አንዳንድ ጓደኞቼ ጋር እራት እበላለሁ፣ ትንሽ ፖርት ወይን እና ሻምፓኝ እጠጣለሁ።

ጄኒ ራይደን: በጣም ጥሩ። እጅግ አመሰግናለሁ። ከእርስዎ ጋር ማውራት ደስ ብሎኛል።
ላስሎ ክራስናሆርካይ: እኔም አመሰግናለሁ።
ጄኒ ራይደን: በድጋሚ እንኳን ደስ አለዎት።
ላስሎ ክራስናሆርካይ: አመሰግናለሁ፣ በጣም አመሰግናለሁ።
ጄኒ ራይደን: ደህና ሁኑ።
12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.