14ኛው ኢትዮ የዶሮ እርባታ ኤክስፖ እና 1ዐኛው የአፍሪካ የእንስሳት እርባታ ኤግዚብሽንና ኮንግረስ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
#fastmereja :- በእንስሳት መኖ፣ በእንስሳት ጤና፣ በዶሮ እርባታ፣ በወተት፡ በስጋ በእንቁላል እንዲሁም በንብ እና በአሳ ሃብት ልማት ዘርፎች ለይ ትኩረት ያደረጉት 14ኛው ኢትዮ የዶሮ እርባታ ኤክስፖ (ETHIOPEX) እና 1ዐኛው የአፍሪካ የእንስሳት እርባታ ኤግዚብሽንና ኮንግረስ (ALEC) የአሳ ሃብት፣ የንብ እርባታና የባዮ ኢነርጂን ዘርፎችን ጨምሮ ዓውደ-ርዕዮች ሊዘጋጁ መሆኑ ተገልጸ።
በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የንግድ ትርዒቶች አዘጋጅ በሆነዉ በፕራና ኢቨንትስና አጋሮቹ አዘጋጅነት እና መቀመጫዉን ሱዳን ባደረገዉ አጋሩ ኤክስፖ ቲም ትብብር ከጥቅምት 2ዐ – ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ የሚዘጋጅ ሲሆን ከ5ዐዐዐ በላይ የንግድ ጎብኚዎችን እንደሚያስተናግድ በዛሬዉ እለት በስካይ ላይት ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
ከዚህ በፊት በነበሩት መርሀ-ግብሮች ዓውደ-ርዕዩ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ በዘርፉ ተዋንያን መካከል ለመቀራረብ ምቹ መድረክ በመሆን፣ ልምድና ተሞክሮ ለመጋራት በማስቻል የአቻ ለአቻ የንግድ ትስስር መርሀ-ግብሮችን በማዘጋጀት የላቀ ሚና ተጫውቷል።
በዘንድሮው መርሃ - ግብር ከ14 ሀገራት የተወጣጡ ከ8ዐ በላይ ዓለምዓቀፍ የቴክኖሎጂ እና ግብዓት አቅራቢዎች እንዲሁም ገናና የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት እንደሚሆን ተገልጿል።
ለ3 ቀናት በሚካሄደው ዓውደ ርዕይና ጉባዔ አጠቃላይ የእሴት ሰንሰለቱን የሚወክሉ መሰረታቸውን በቻይና፣ ቼክ ሪፕብሊከ፡ ኢትዮጵያ፣ ፈረንሳይ፡ ጀርመን፣ ህንድ፤ ታንዛኒያ፣ ግብጽ፣ ጣሊያን፣ ብራዚል፣ ኬኒያ፡ ኔዘርላንድሰ፣ ቱርክ፣ እና ሲሪያ ያደረጉ ዓለም ዓቀፍ የዘርፉ መሪዎች እና ጠንካራ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ከንግድ ጎብኚዎች ጋር ጠንካራ የስራ ግንኙነት ለመፍጠር ዝግጅታቸውን ጨርሰው እየተጠባበቁ እንደሆነም አክለዉ ገልፀዋል።
#ኹነት

12 months ago