ጌታችን ከሐዋርያት አስቀድሞ የመረጠው ደቀ መዝሙር እንደሆነ መጽሐፈ ስንክሳር ይናገራል፡፡
እርሱም በየአገሩ እየተዘዋወረ ወንጌልን በመስበክ ከአይሁድና ከአረማውያን ወገን ብዙዎችን ወደ ክርስትና መልሶ አጥምቋል፡፡ በማቴዎስ 10÷3 እንደተጻፈው አባቱ እልፍዮስ ይባላል፡፡ በሉቃስ 6÷16 ደግሞ ሐዋርያው “ታዴዎስ ልብድዮስ”፣ “የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ” እየተባለም ተብሎ ሲጠራ እናያለን፡፡ አንድ ቀን ወደ ሀገረ ስብከቱ ወደ ሦርያ ለስብከተ ወንጌል ሲሔድ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጐልማሳ አምሳል ተገልጦ “ወዳጄ ታዴዎስ ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ” ብሎ ሰላምታ ሰጥቶት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስም እንደ አባትነቱ ወደ ሦርያ አብሮት ሔዶ ነበረ፡፡ ከከተማዋ አጠገብ ሲደርሱም አንድ ሽማግሌ በሮችን ጠምደው ሲያርሱ አገኙ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ሽማግሌውን ምግብ ለመናቸው፡፡
“በሬዎቼን ጠብቁ” ብላዋቸውም ሊያመጡላቸው ወደ ቤታቸው ሔዱ፡፡ ሽማግሌው እስኪመለሱ ቅዱስ ጴጥሮስ ሠላሳ ትልም ካረሰ በኋላ ቅዱስ ታዴዎስ በዚያ የነበረውን የሥንዴ ዘር ዘራበት፡፡ የተዘራውም ወዲያዉኑ በቅሎ፣ አድጎ፣ እሸት ኾነ፡፡ ሽማግሌው ምግብ ይዘው ከቤታቸው ሲመለሱም ሐዋርያት ያደረጉትን ተአምር አይተው ደነገጡ፡፡ ከእግራቸው ሥር ወድቀውም “እናንተ ከሰማይ የወረዳችሁ አማልክት ናችሁን?” አሏቸው፡፡ እነርሱም “እኛ የእግዚአብሔር ባሮች እንጂ አማልክት አይደለንም” አሉ፡፡ ሽማግሌውም ስላደረጋችሁልኝ በጎ ሥራ በምትሔዱበት ቦታ ኹሉ ልከተላችሁን? አሏቸው፡፡ እነርሱም “በሬዎቹን ለጌታቸው መልስና በቤትህ የምንበላውን ታዘጋጅልን ዘንድ ለባለቤትህ ንገራት ወደ ከተማዋ ገብተን የላከን አምላካችን እግዚአብሔር እስከሚጠራን ጊዜ ድረስ እንቆያለንና” አሏቸው፡፡
ሽማግሌውም የሥንዴው እሸት ይዘው፣ በሬዎቻቸውን እየነዱ ወደ ከተማ ሲሔዱ ሰዎች ወቅቱ የእርሻ እንጂ የእሸት ጊዜ ስላልነበረ እየተገረሙ “እሸቱን ከወዴት አገኘኸው?” አሏቸው፡፡ ሽማግሌው ግን መልስ አልሰጧቸውም፡፡ ሐዋርያት እንደዘዟቸው በሬዎቹን ለጌታቸው መልሰው ሚስታቸው ራት እንድታዘጋጅላቸው ነገሯት፡፡ የከተማው መኳንንት ስለ እሸቱ ሲሰሙ “በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ከወዴት እንዳገኘኸው ንገረን” አሏቸው፡፡ ሽማግሌውም ሐዋርያት ያደረጉትን ሁሉና ወደ እርሳቸው ቤት ቢመጡ ሊያገኟቸው እንደሚችሉ ነገሯቸው፡፡ መኳንንቱም ሰይጣን ልቡናቸዉን አነሳስቶታልና ሐዋርያቱን ለመግደል ወሰኑ፡፡ ሌሎች ግን “አምላካቸው ኢየሱስ የሚሹትን ሁሉ ያደርግላቸዋልና ልንገድላቸው አንችልም፡፡ ይልቅ በከተማው በር አመንዝራ ሴት ርቃኗን ብናስቀምጥ ወደ ከተማችን አይገቡም” አሉ፡፡ በከተማዋ መግቢያ በር እንደተባባሉት ሴቲቱን እርቃኗን አስረዋት ጠበቋቸው፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያቱ ግን በሰዎቹ ልብና በሴቲቱ ላይ ያደሩትን ርኩሳን መንፈስ አስወጥተው በማስተማር በሥላሴ ስም አጥምቀው አገልጋዮችን ሾሙላቸው፡፡ ያቺንም ሴት ዲያቆናዪት አደርጎ ሾማት፡፡ ብዙ ድንቅና ተአምራትም አደረጉ፡፡ ሕዝቡም በእግዚአብሔር አመኑ፡፡ ከዚህ በኋላ አንድ ሰይጣን ያደረበትና ገንዘብ የሚወድ ጐልማሳ ባለጸጋ ቅዱስ ታዴዎስን በበዙ ተፈታተነው እርሱም ጌታችን እንደተናገረ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ስትሾልክ አሳየው፡፡ ያ ባለጸጋም ከቅዱስ ታዴዎስ እግር ስር ወድቆ ይቅርታ ጠየቀ ገንዘቡንም ሁሉ ለድሆች አከፋፈለ፡፡ ተምሮና አምኖም ተጠመቀ፡፡ ቅዱስ ታዴዎስ በየአገሩ እየተዘዋወረ ወንጌልን ሲሰብክ ቆይቶ ከአይሁድና ከአረማውያን ዘንድ ብዙ መከራ ከደረሰበት በኋላ አገልግሎቱን ፈጽሞ ሐምሌ 2 ቀን ዐርፏል፡፡ በብዙ ስጋዊ መከራ ውስጥ የሚያልፉ ቅዱሳን ገዳማውያንም የሐዋርያትን ፈለግ ተከትለው ዓለምን ንቀዋል፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

12 months ago