Logo
YenetaTube
" ሀቢቢ Come to Afghanistan "

የአሜሪካኑ መሪ ዶናልድ ትራምፕ ትናንትና አፍጋኒስታን ባግራም የጦር ሰፈርን በፀባይ ካልመለሰች ነገሮች ጥሩ አይሆኑም ሲል ለማስፈራራት ሞክሯል ።
............
አሜሪካ አፍጋንን ለመቆጣጠር በሞከረችባቸው ሀያ አመታት በተለያየ ጊዜ ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ወታደሮች አሰማርታ ነበር ።

እንዲሁም ፡ ከሁለት ትሪሊዮን ሶስት መቶ ቢሊየን ዶላር በላይ አውጥታለች ፡ የሰው ሀገር ሊወሩ የሄዱ በሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮቿን አጥታለች ።
....
ሆኖም አሜሪካን ይህን ሁሉ አድርጋ ፡ ለሀያ አመታት በእጇ አስገብታው የነበረውን የባግራም ጦር ሰፈርን ይዛ መቆየት አልቻለችምና የዛሬ አራት አመት ለቅቃ ወጥታለች ።
........
በዚህ ወቅትም አሜሪካ ወደ አፍጋኒስታን ይዛቸው መጥታቸው የነበሩት የቢሊየን ዶላር መሳሪያዎች አፍጋኒስታን ትታ በመውጣቷ ፡ አሁን ላይ ጣሊባን ማለት እጅግ ዘመናዊና በማታ የሚያሳዩ የጦርሜዳ መነፅሮች ፡ ጀምሮ ብላክ ሃውክን የመሰለ ዘመናዊ ሄሊኮፕተሮች ባለቤት ነው ።
...
በወቅቱ አሜሪካን ትታቸው ሄዳ በጣሊባን እጅ የገቡ የጦር መሳሪያዎች ዝርዝር

22,174 ............ humvee ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች ፡
634 ..............ባለጎማ ታንኮች
155 .................ማክስ ፕሮ ማይን ፕሩፍ ተሽከርካሪዎች
169 ................. MII17 ታንክ
42 ሺህ. ...............ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች
8ሺህ ................ ከባድ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች

162,043 ..........የማይጠለፉ ወታደራዊ የሬዲዮ መገናኛዎች
16,035 ............በምሽትም የሚያሳዩ ወታደራዊ የጦር ሜዳ መነፅሮች ።

358,530 ...........ቀላል ጠመንጃዎች
64,363 .............አውቶማቲክ ጠመንጃዎች
126,295 ........... ሽጉጥ
176 ...............መድፍ

33 .................MI ሄሊኮፕተሮች
33 .................. black hawk ዘመናዊ የጦር ሄሊኮፐተሮች
43. ............. MD 530 ዘመናዊ ሄሊኮፕተሮች
4 - ...........C130 ወታደራዊ መጓጓዣ አውሮፕላኖች
23 .............. EMB አውሮፕላኖች
28 .............. ሴሲና አውሮፕላኖች
10................. ሴስና ተዋጊ አውሮፕላኖች በሙሉ አሁን የታሊባን ናቸው
........
አሁን ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ፡ አሜሪካ ትሪሊዮን ዶላሮችን ፈጅታ የቢሊዮኖች መሳሪያ ትታ ወደ ሄደችው ወደ አፍጋኒስታን በውድም ሆነ በጉልበት እመለሳለሁ ብላለች ።
........
ጣሊባን በበኩሉ ይህንን የትራምፕን ንግግር ከሰማ በኋላ ዳግም ልታስታጥቀው እንደምትመጣ በማሰብ ሀቢቢ come to Afghanistan እያለ ነው ።
....
አፍጋኖች ከትናንቱ የትራምፕ ፉከራ በኋላ ፡ አደለም አሁን በራሷ በአሜሪካን ይህን ያህል ታጥቀን ፡ በሩሲያ ክላሽንኮቭ ለሀያ አመታት ለአሜሪካን አልተንበረከክንም ፡ የአፍጋን ምድርን ትርገጥና እንተያያለን ሲል ተናግሯል ።

Via wasihun tesfaye

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.