28 days ago
#ጤናመረጃ
የደም ኮሌስትሮል መጠንን አመጋገባችንን በማስተካከል እንዴት መቀነስ እንችላለን!
1-በፋይበር የበለጸጉ ምግቦችን ማዘውተር፡- እነዚህም ፡- የተፈጨ አጃ፣ አደንጓሬ፣ ፖም፣ ሸክኒት፣ በቆልት..የመሳሰሉት ናቸው፡፡
2-በኦሜጋ 3 የበለጸጉ 'fatty acid' ያላቸውን ምግቦች መመገብ፡- እነዚህ ምግቦች ከላይ ከተጠቀሰው ጥቅም በተጨማሪ የደም ግፊት መጠን ይቀንስልናል፡፡እነዚህም፡- ሳልመን የአሳ ዘር፣ ተልባ፣ለውዝ..
3-Trans-fat በውስጣቸው የያዙ ምግቦች በደማችን ዉስጥ ያለውን ኮሌስትሮል መጠን ስለሚጨምሩ መጠቀም የለብንም ፡፡ ለምሳሌ፡-የዳቦቅቤ፣ብስኩት፣ ኬክ፣ችብስ፣ ዶናት፣ ቺዝ በርገር….እነዚህ ምግቦች ባለም የምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን የተከለከሉ ናቸው፡፡
4-በSaturated fat የበለጸጉ ምግቦችን መቀነስ ፡ ለምሳሌ፤-ስጋ፣ አይስ ክሬም፣ ቅቤ፣ቸኮሌት፣ ቺዝ፣… እነዚህ የምግብ አይነቶች ለብዙ የጤና እክሎች ያጋልጣሉ፡፡
5-አመጋገባችንን ከማስተካከል በተጨማሪ የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች ያስፈልጉናል፡-ሲጃራ አለማጨስ፣ የሰውነት ክብደት መቀነስ
ከመጠን በላይ አልኮል አለመጠቀም፣ ቢያንስ በሳምንት 5 ጊዜ ለ30 ደቂቃ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠቀሳሉ፡፡
ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ!
seledadotio

1 month ago
#ጤናመረጃ
ብጉርን መከላከያ እና ማስለቀቂያ ዘዴዎች!
ብጉር የሚከሰተው በቆዳችን የሚመነጭ ቅባት ወይንም የሞቱ ሴሎች የጸጉር መውጫ ቀዳዳዎቻችን ሲደፍኑ ነው። በአብዛኛው በጉርምስና ጊዜ የሚመጣው ብጉር የሆርሞን መለወጥን ተከትሎ ነው።
ብጉርን የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
*የሆርሞኖች በሰውነታችን መለዋወጥ
*መድሃኒቶች በተለይም ሆርሞኖችን የያዙ ከሆኑ
*ቅባትነት ያላቸውን መዋቢያዎችን መጠቀም
*ጭንቀት እና የወር አበባ መምጣት ናቸው።
*በዘር የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው።
ብጉር እንዳይባባስ ምን እናድርግ?
*ብጉር የወጣበትን ቦታ በስሱ ማጽዳት በውሃና በሳሙና መታጠብ (በቀን 2 ጊዜ)።
*ቅባታማ የሆኑ የመዋቢያ ውጤቶችን መጠቀምን ያስውግዱ።
*በብጉር የተጎዳ ቆዳዎን በእጅዎ አይነካኩ።
*ከባድ የጉልበት ስራ ከሰሩ በሗላ ገላዎንና ፊትዎን ይታጠቡ።
ቡጉርን በ1 ሳምንት ውስጥ የማስለቀቂያ ዘዴዎች!
1-የፈረንጅ እርሾ (baking soda)፦ የፈረንጅ እርሾ የቆዳዎን የሞቱ ሴሎች ያስወግዳል፡፡
ሁለት የሻይ ማንኪያ የፈረንጅ እርሾ ከትንሽ ውሀ ጋር አደባልቀው ይቀቡ። ከዚያም ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ይታጠቡ፡፡
2- ገብስ፦ ወዝ የበዛበትን ቆዳ በማፅዳት የሞቱ ሴሎችን ያስወግዳል፡፡
በ1 የሻይ ስኒ ዱቄቱ የበሰለ ገብስ ላይ አንድ የሻይ ማንኪያ ማር ና ግማሽ የሎሚ ጭማዊ መደባለቅ፣ ድብልቆቹን በቆዳ ላይ ማሸት፣ ለ30 ደቂቃ በማቆየት ለብ ባለ ውሀ መታጠብ፣ ይሄንን በሳምንት አንዴ ወይም ሁለቴ ያድርጉት
3- የሎሚ ጭማቂ፦ በሎሚ ውስጥ ያለው አሲድነት ብጉርን ለማስወገድ ጥሩ ጠቀሜታ አለው።የተቆረጠ ሎሚ ቆዳዎትን ይቀቡ ከትንሽ ደቂቃም በኋላ ይታጠቡት።
በተጠቀሱት መከላከያ መንገዶች የማይሻሻል ከሆነ ወደ ሀኪም በመሄድ ያማክሩ።

«ጥርት ያለ የፊት ቆዳ ለማግኘት ምን እናድርግ?»
የፊት ቆዳችንን በአግባቡ ካልተንከባከብነው በቀላሉ የሚጎዳ ሲሆን ቀጥሎ ያሉትን የፊት ቆዳን መንከባከቢያ መንገዶች ይመልከቱ።
1) ፊትን በቀን ሁለቴ መታጠብ
2) የፊት ሳሙና ወይም ሌላ ቅባት ሲቀቡ የፊትዎን ቆዳ ከመፈተግ ይቆጠቡ ይልቁንም በለስላሳና ክባዊ እንቅስቃሴ ቀስ ብለው ይቀቡት።
3) ለፊት ቆዳዎት የሚስማማ ማርጠቢያ ክሬሞችን ይጠቀሙ ከመተኛትዎትም በፊት ሊጠቀሙት ይችላሉ
4) የፊት ቆዳ ቀዳዳን ከሚደፍኑ ዘይታማ ከሆኑ ሜክአፖችና የቆዳ ክሬሞች ይራቁ
5) የቆዳችን ንፅህና መጠበቅ በተለይ ብጉር የሚያስቸግረን ከሆነ ቤንዞይል ፐርኦክሳይድ፣ ፊዞርሲኖል፣ ሳሊክሊክ አሲድ ወይም ሰልፈር ያለው ለፊትዎ የሚስማማ ሳሙና መጠቀም ብጉሩ በዚህ ካልቀነሰ ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል።
በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መድሃኒት
በተለያየ ምክንያት የፊትና ሌላ የቆዳ አካል ላይ የቀረን ምልክትን ለማጥፋት ከፈለጉ የሚከተለውን በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ ህክምናን ሊጠቀሙ ይችላሉ።
መድሃኒቱን በቤት ውስጥ ለማዘጋጀት፦
• አራት የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጁስ
• አራት የሻይ ማንኪያ ማር
• አንድ አስኳሉ የወጣለት እንቁላል
አዘገጃጀት
• ፊትዎ/ቆዳዎ ንፁህና ደረቅ መሆን ስላለበት ይታጠቡት
• በመቀጠልም ከላይ የተዘረዘሩትን በንፁህ እቃ ውስጥ በደንብ ያደባልቁ
• ከዚያም ምልክት ባለበት የቆዳዎ ክፍል ላይ ይቀቡት
• ከ15 ደቂቃ ቆይታ በኋላ ይታጠቡት
ጥሩ ውጤት ለማግኘት በሳምንት ሁለት ጊዜ እንዲጠቀሙት ይመከራል።

10 አስገራሚ የአቮካዶ የጤና ጥቅሞች!
አቮካዶን መመገብ ከሚያስገኛቸው ብዙ ጥቅሞች ዋነኞቹን እናያለን።
1) የደም ግፊትንና የደም ዝውውርን የሚያስተካክለውን ፖታሲየም የተሰኝውን ንጥረ ነገር በብዛት ይዟል፡፡በአቮካድ ውስጥ የሚገኝው ፖታሲየም ሙዝ ውስጥ ከሚገኝው በ10% ይበልጣል።
2) ፎሌት የተባለ ንጥረነገር ያለው ሲሆን ለእርጉዝ ሴቶች በጣም ጠቃሚና ለህፃኑ የአእምሮና አካላት እድገት ወሳኝ ሚና
ይጫወታል።በተጨማሪም በእርግዝና ወቅት የሚመጣውን ማቅለሽለሽ የሚከላከል ቫይታሚን ቢ6 ይዟል።
3) በአቮካዶ ውስጥ ያለው ሞኖሳቹሬትድ ፋት ለልብ ህመም የሚያጋልጠንን ኮሌስትሮል በመቀነስ ጤናን ያስተካክላል።በተጨማሪም ለስኳር በሸተኞች በደም ውስጥ ያለውን ትራይግላይሴራይድ በመቀነስ ይጠቅማል።
4) አቮካዶ ኦሊይክ አሲድ በውስጡ ይዟል።
ይህ አሲድ የጡት ካንሰርን ይከላከልልናል።
5) አቮካዶ ሊየቲን የተባለ ቫይታሚን ሲኖረው የካሮቲን ቫይታሚን ከሆነው ቫይታሚን ኤ ዝርያ የሚመደብ ሲሆን ለአይን ጤንነት በጣም ጠቃሚ ነው።
6) አቮካዶ ከፕሮስቴት ካንሰር የሚከላከሉና የተጐድ ሴሎችን የሚጠግኑ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች በውስጡ ይዟል።
7) አቮካዶ የአፍ ካንሰርን ከመከላከሉ ባሻገር ለመጥፎ የአፍ ጠረን አይነተኛ መፍትሄ ነው።
8) በአቮካዶ ውስጥ ያሉት ኢንዛይምና የምግብ ንጥረ ነገሮች የተጐዳ የጨጓራና የትንሽ አንጀት ግድግዳዎችን በማለስለስ ወደር አይገኝላቸውም።
9) በአንቲ ኦክሲዳንት የበለፀገ ስለሆነ ከእርጅና ጋር ተያይዘው የሚመጡ ምልክቶችን ይከላከላል።ሰውነታችን በሽታን የመከላከል አቅምን ይጨምራል የነርቭ ስርዓት ጤናማ እንዲሆን ያደርል።
10) በቫይታሚን የበለፀገ ሲሆን ቆዳችንን ከፍሪራዲካልስ ይከላከላል።
ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!

ሙዝ ለጤናችን የሚሰጠን 12 አስደናቂ ጥቅሞች!
ሙዝ በንጥረ ነገር ይዘታቸው ከበለፀጉ ፍራፍሬዎች አንድ ሲሆን በውስጡ በርከት ያሉ እንደ ማግኒዚየም ፣ ፓታሲየም ፣አይረን፣ ዚንክ፣ አዮዲንና ቫይታሚን ኤ፣ቢ፣ኢ፣ኤፍን ይዛል።
1- የሀይል ምንጭ ነው:- ሙዝ በውስጡ ቫይታሚን፣ሚኒራል እና ካርቦሀይድሬት በመያዙ ሀይል ለማግኘት ይጠቅማል፡፡
2- ለምግብ መንሸራሸር ይጠቅማል:- ይህም የሚሆነው ሙዝ በውስጡ የቃጫ ባህሪ(ፋይበርነት) ስላለው ነው፡፡
3- የጨጓራ ህመምን ያስታግሳል:- ጨጓራ ጠንካራ ግድግዳ እንዲኖረው እና በጨጓራ ውስጥ ያለውን አሲድነት በመቀነስ ህመምን ያስታግሳል፡፡
4- የልብን ጤንነትን ይጠብቃል:- ሙዝ በፖታሲየም የበለፀገ ስለሆነ ይህም ለልብ ጤንነት አስፈላጊ ነው፡፡
5- ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል:- ሙዝ በውስጡ አነስተኛ ቅባት እንደዚሁም ብዙ ፋይበር ሰለያዘ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
6- አኔሚያን ለማከም ይረዳል:- ሙዝ በውስጡ በዛ ያለ የብረት ማእድን ስለያዘ ይህም የቀይ የደም ሴልን ማነስ ይከላከላል፡፡
7.ነብሰጡሮችን ከህመም ይታደጋል:- ነብሰጡር ሴቶችን የሚያጠቃ የጠዋት ህመም የሚባለውን ለማከም ይረዳል፡፡
8.የአይንን ጤና ያሻሽላል:- ሙዝ ቫይታሚን ኤን ስለያዘ የአይን በሽታን ይከላከላል፡፡
9.በወባ ትንኝ የተነደፈን ይፈውሳል:- የተነደፈበት ቦታ በሙዝ ልጣጭ በማሸት ከህመሙ ይፈውሳል፡፡
10.ጥርስን ያነጣል፦ በሙዝ ልጣጭ ጥርስዎን ሁልጊዜ ጥርስዎን ሲፍቁ ለአስደናቂ ፈገግታ ይኖርዎታል።
11.የተጎድ የሰውነት ቆዳን ያስተካክላል፣ የፊት መሸብሸብ እና የቆዳ መሰንጠቅን ይከላከላል።
12.ክንታሮትን ያድናል:- ሙዝ በፓታሲየም የበለጸገ ስለሆነ ክንታሮትን የማዳን አቅም አለው።
ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር

ኩላሊት የሚጎዱ ልማዶች
አሳሳቢ የሆነው የኩላሊት ህመም ቀድሞ መከላከያ መንገዶችን ያውቃሉ ? ብዙ ልማዶች ለኩላሊት ህመም ምክንያት ናቸው እነዚህም
1. ሽንትን መቋጠር
ሽንት በፊኛ ውስጥ ረጅም ሰአት ሲቆይ በውስጡ የሚያድጉት ባክቴሪያዎች ይበራከታሉ። እንዚህ ባክቴሪያዎች የሽንት ቧንቧ ወይም የኩላሊት ኢንፌክሽን ሊያመጡ ይችላሉ። ሽንትን መያዝ ኩላሊት ላይ በሚያደርሰው ጫናም ኩላሊት ተጎድቶ ሽንትን የመቆጣጠር ችሎታችንን ሊያጠፋ ይችላል።
2. በቂ ውሃ አለመጠጣት
አንድ ሰው በቀን ቢያንስ ከ10 እስከ 12 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት አለበት።
3. ጨው ማብዛት
ብዙ ጨው መመገብ ኩላሊታችን ላይ ከፍተኛ ጉ በምንመገበው ጨው የሚገኘውን ሶዲየም 95% ያህሉ በኩላሊታችን ነው የሚቀየረው። ጨው ስናበዛ ኩላሊታችን ጨውን ለማጣራት ይበልጥ መስራት ይኖርበታል።
4. የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ማዘውተር
የኩላሊት ህመም ካለብዎ ዶክተርዎን ሳያማክሩ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን አይጠቀሙ።
5. ፕሮቲን ያላቸው ምግቦች ማብዛት
6. መጠጥ ማብዛት
መጠጥ ሲበዛ ኩላሊታችን አደጋ ላይ ይወድቃል። መጠጥ ኩላሊታችን እና ጉበታችን ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል።
7. ሲጋራ ማጨስ
8. ቀላል ኢንፌክሽኖችን በግዜው አለመታከም።
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የኩላሊት ህመም ዋና ዋና ምክንያቶች ሆነው ይጠቀሳሉ። ከነዚህ ልምዶች ራሳችሁን በመቆጠብ የኩላሊት በሽታን መከላከል ይቻላል።

2 months ago
#ጤናመረጃ
የአብሽ 10 የጤና ጥቅሞች!! ሼር
አብሽ ለጤና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ያውቃሉ?
ለልብ ድካም፣ ለደምግፊት፣ ኮሌስትሮል ለመቀነስ፣ ለጨጓራና በስካር በሽታ ለሚሰቃዩ ፍቱን መድሃኒት ነው::ገና ለወለዱ እናቶችም የጡታቸውን መጠን የተወሰነ ለመጨመር ይጠቅማል።
ጥቅሞቹ በዝርዝር ቀጥሎ ቀርበዋል፦
※የስኳር በሽታን ለመቆጣጠር ይረዳል፦ አብሽ ደም ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን በመቆጣጠር ኢንሱሊን መቋቋምን ይቀንሳል።
※የልብ በሽታን ያስወግዳል፦የልብ ጉዳትን ለመከላከልና ኦክሲዳቲቭ ውጥረት ለማስወገድ ይረዳል።
※የወር አበባ ቁርጥማትን ያስታግሳል፦አብሽ ከቁርጥማት በተጨማሪ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽና ድካምን ለመቀነስ ይረዳል።
※የጡት ወተት ምርትን ያሻሽላል፦አብሽን መጠጣት የወተት ምርትን የሚጨምር ውህድ ስላለው፤ ለሚያጠቡ እናቶች ይረዳል።
※የምግብ መፍጨት ችግርን ይረዳል፦የሆድ ድርቀትንና ከጨጓራ መቆጣት የተነሳ ለሚከሰት የምግብ መፍጨት ችግርን ለመከላከል ይረዳል።
※የጸጉር መሳሳትን ለመከላከልና ለፀጉር እድገት ጠቃሚ ነው።የተፈጨ አብሽን ሳይወፍር በብርጭቆ ውሀ በማዋሀድ መቀባት።
※ አብሽ መጠጣት አቅም ማጣትን ለማከምና የወሲብ ችሎታን ለመጨመር ይረዳል።
※አብሽ መጠጣት ብጉርን ለመከላከል ይረዳል።
※ፀረ-እርጅና ጥቅም አለው፦ለቆዳችን አስደናቂ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን እንደ የቆዳ መጨማደድና ቀጫጭን መስመርን ያስወግዳል።
※ቆዳን ለማርጠብ፦ የአብሽ የሚሙለጨለጨው በሀሪ የደረቁ ቆዳዎችን በማስወገድ ቆዳችን እንዲረጥብ ይረዳናል።
አጠቃቀሙ፣ በ1ብርጭቆ ውሃ ውስጥ 2 የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ አብሽ በማዋሀድ መጠጣት።ተፈጥሯዊ ስለሆነ ምንም አይነት ጉዳት የለውም።ክብደት እንዳይጨምሩ በመጠኑ ይጠቀሙ።

Sponsored by
Surafel
2 months ago
#ጤናመረጃ
ለፈጣን የፀጉር እድገት የሚረዱ ተፈጥሯዊ ዘዴዎች!
1- ሩዝ መጠቀም
2 የቡና ስኒ ሩዝ በ2 ኩባያ ዉኃ ለ5 ደቂቃ ያህል ማፍላት፣ዉኃዉን አጥልለን ለብ ሲል ፀጉራችንን አዳርሰን በመቀባት ለጥቂት ደቂቃዎች ቆዳችንን ማሳጅ ማድረግ፣ ከ30-45 ደቂቃ ያህል አቆይተን መታጠብ ለፀጉር እድገትና ልስላሴ ተመራጭ ነዉ፡፡
2- ቀይ ሽንኩርት
ሽንኩርት ዉኃ ዉስጥ በመቀቀል በዉኃዉ ፀጉሮን መታጠብ እና አቆይቶ በንጹህ ዉኃ ማለቅለቅ፣ ከዛም ውጤቱን መመልከት፡፡
3- የኮኮናት ዘይት
በየቀኑ የኮኮናት ዘይት በማሞቅ የፀጉርን ቆዳ አዳርሶ በመቀባት የፀጉርን ቆዳ ለ1 ደቂቃ በማሸት ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ዉጤቱን ማየት ይችላሉ፡፡ የፀጉርን ቆዳ በሞቀ የኮኮናት ዘይት ማሸት ሴሎቹ እንዲነቃቁ ያደርጋል፡፡
4- እንቁላል መጠቀም
እንቁላል ነጩን ብቻ በመምታት ፀጉርን በመቀባት ፀጉርዎ ፈጣን እድገት እንዲኖረዉ ማድረግ ይቻላል፡፡ ፀጉርዎን እስከ ጫፉ ድረስ በመቀባት ጠንካራና ጤናማ ፀጉር እንዲኖሮዎት ያድርጉ፡፡
5- የኮክ ቅጠል
100 ግራም የኮክ ቅጠል በ1ሊትር ዉኃ ለ15 ደቂቃ ያህል መቀቀል፣ አዉርደን ለብ ሲል ፀጉራችንን በዉኃዉ መታጠብና ቆዳችንን በማሸት በላስቲክ ሸፍነን ከ1ሰዓት ቡኋላ በንጹህ ዉኃ ማለቅለቅ ለፀጉር እድገትን ያፋጥናል፣ የፀጉር መሳሳትን ይከላከላል፡፡
6- እሬት(ኦሊቬራ) ለፀጉር እድገት
1 የኦሊቬራ ቅጠል በመሰንጠቅ ዉስጡ ያለዉን ዝልግልግ ፈሳሽ በማዉጣት ፀጉራችንን እስከ ስሩ በማዳረስ መቀባት፣ ቆዳችንን ለጥቂት ደቂቃ ማሳጅ ማድረግ፣ ለ30-45 ደቂቃ ያህል በላስቲክ ሸፍኖ ማቆየት፣ ከዛ መታጠብ፡፡
ለፀጉር እድገት፣ ለፀጉር መነቃቀል እና መሳሳት እንዲሁም ለፎረፎር እሬት(ኦሊቬራ) መድኃኒት ነዉ፡፡

ድንቅ የሕክምና ስኬት በአገው ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል
#ethiopia | በናዳ ምክንያት ወገቡ ተሰብሮ ተስፋው ጨልሞ የነበረው ወጣት፣ በሆስፒታላችን የሕክምና ባለሙያዎች ብቃት ዳግም ወደ ሕይወት ተመልሷል።
አንድ ወጣት በስራ ላይ እያለ በደረሰ የናዳ አደጋ የአከርካሪ አጥንቱ በከፍተኛ ሁኔታ ተሰብሮ ነበር።
የጭንቅላት፣ የሕብለሰረሰር እና የአከርካሪ አጥንት የሕክምና ቡድኑ ለ4 ተከታታይ ሰዓታት የፈጀ እጅግ ውስብስብ ቀዶ ሕክምና አከናውነዋል።
ቀዶ ሕክምናው በስኬት ተጠናቆ ታካሚው በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል።
ይህ ስኬት ሆስፒታላችን ዘመኑ የደረሰበትን የሕክምና ቴክኖሎጂና ጥበብ በመጠቀም ለወገኑ የሚሰጠውን አገልግሎት በተግባር ያሳየበት ነው። "ችግር ቢኖርም፣ መፍትሔው እኛ ጋር አለ!" የሚለውን መመሪያችንን በተግባር አረጋግጠናል።
በናዳና መሰል አደጋዎች ከሚመጡ ጉዳቶች ራስዎን ይጠብቁ። ድንገት አደጋ ቢከሰት እንኳ ወደ ሆስፒታላችን ፈጥነው በመምጣት አስፈላጊውን ሕክምና ማግኘት እንደሚችሉ እናሳስባለን።
አገው ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል
- እንጅባራ፣ ኢትዮጵያ
የጤንነትዎ ቋሚ ካፒታል!
#agewmidirhospital #medicalsuccess #spinesurgery #injibara #ethiopiandoctors #healthexcellence #hoperestored #ethiopia #የጤናመረጃ #አገውምድር #ሕክምና

3 months ago
በኢትዮጵያ በየዓመቱ 41 ሺህ ህጻናት ከአፈጣጠር ችግር ጋር እንደሚወለዱ ተገለጸ፤ መፍትሄውስ ምን ይሆን?
#ethiopia | በኢትዮጵያ በየዓመቱ 41 ሺህ የሚጠጉ ህጻናት ከተለያዩ የአፈጣጠር የጤና ችግሮች ጋር እንደሚወለዱ የጤና ባለሙያዎች አስታወቁ። ከእነዚህ ችግሮች መካከል «ስፓይና ቢፊዳ» (Spina Bifida) እና ተያያዥነት ያለው የጭንቅላት ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት ወይም «ሃይድሮሴፋለስ» (Hydrocephalus) በዋናነት ይጠቀሳሉ።
የሴንትራል መላ ሮተሪ ክለብ፣ ሪችአናዘር ፋውንዴሽን፣ አሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት እና የጤና ሚኒስቴር በመተባበር «የአፈጣጠር ችግሮችን መቆጣጠርና መንከባከብ» በሚል ርዕስ ባዘጋጁት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ እንደተገለጸው፥ እነዚህ የጤና እክሎች ሕጻናትን ለዕድሜ ልክ የአካል ጉዳትና ብሎም ለሞት ያጋልጧቸዋል።
የችግሩ ዋነኛ መንስኤ ምንድነው?
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እስከ 70 በመቶ የሚሆነው የስፓይና ቢፊዳ (የአከርካሪ አጥንትና የህብለ ሰረሰር ክፍተት) ችግር የሚከሰተው በእናቶች የፎሊክ አሲድ (Folic Acid) እጥረት፣ በሌሎች ተጓዳኝ የጤና ችግሮች፣ እንዲሁም እናቶች በሚጠቀሟቸው አንዳንድ መድኃኒቶች ምክንያት ነው።
እንዴት መከላከል ይቻላል?
በመድረኩ ላይ የተገኙት የጤና ባለሙያዎች እና ፖሊሲ አውጪዎች የሚከተሉትን የመፍትሄ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል
* የአመጋገብ ዘይቤ፡ እድሜያቸው ከ15 እስከ 49 ዓመት የሆኑ ሴቶች በተፈጥሮ ፎሊክ አሲድ ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር አለባቸው።
* ቅድመ ዝግጅት፡ እርግዝና ከማቀድ 3 ወራት በፊት ጀምሮ እና በእርግዝና ወቅት የፎሊክ አሲድ እንክብሎችን መውሰድ እጅግ አስፈላጊ ነው።
* የበለፀጉ ምግቦች፡ በፎሊክ አሲድ የበለፀጉ የስንዴ ዱቄቶችን እና ዘይቶችን መጠቀም ችግሩን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሰዋል።
ይህ አገር አቀፍ መድረክ፤ ከአፈጣጠር ችግር ጋር የሚኖሩ ህጻናትን የህይወት ጥራት ለማሻሻል የሚያስችሉ ስልቶች ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ተጠናቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #healthnews #ethiopianhealth #ministryofhealth #spinabifidaawareness #folicacid #healthypregnancy #addisababa #የጤናመረጃ #ኢትዮጵያ

ቲማቲም ለፊት ጥራት ያለው አስደናቂ ጥቅም!!
ቲማቲም ለቆዳችን እጅጉን ጠቃሚ ነው፡፡ ቲማቲም ከፍተኛ መጠን ያለው ቤታካሮቲን፣ ላይኮፔን እና ፍላቮኖይድስን አለው፤ ይህን ንጥረ ነገር ደግሞ ለፊት ጥራት ተብለው በውድ ዋጋ የሚሸጡ መዋቢያዎች ይጠቀሙበታል፡፡
በቀላሉ የምናገኘው ቲማቲምን በመጠቀም ቡጉርን፣ የቆዳ ጥቁረትንና ጥቁር ነጠብጣቦችን ከፊታችን ላይ ለማጥፋት ይረዳናል፣ በተጨማሪም ቲማቲም የቆዳን እርጅና እና መሸብሸብ ፍጥነትን የመቀነስ ችሎታ አለው፡፡
ለማዘጋጀት አስፈላጊ ነገሮች -
- 1 ቲማቲም
- 2 የሻይ ማንኪያ ስኳር
- 2 የሻይ ማንኪያ ማር
- 1 መለስተኛ የቡና ሲኒ >>
አዘገጃጀት
1) በመጀመርያ የፊታችን የቆዳችን ቀዳዳዎች መከፋፈት ስላለባቸው ፊታችንን በሙቅ ውሀ እንፋሎት መታጠን፡፡
2) ቲማቲሙን ይቆርጡና በሲኒ ላይ ይጨምቁታል፡፡
3) ጭማቂው ላይ ቅድሚያ ስኳሩን ቀጥሎ ማሩን ይጨምሩና ያዋህዱታል፡፡
4) ውህዱን ፊትዎ ላይ በስሱ ይቀቡታል ፡፡
5) ለ 2 ደቂቃ በዝግታ ያሹታል፡፡
6) ለተጨማሪ 2 ደቂቃ ደግሞ ባለበት ይተውታል፡፡
7) ባጠቃላይ ከ 4 ደቂቃ በኋላ በ ቀዝቃዛ ውሀ ይታጠቡታል፡፡ ማስጠንቀቂያ:- ለቲማቲም ሆነ ከላይ ለተጠቀሱት ውህዶች አለርጂክ ከሆኑ እንዲጠቀሙት አይመከርም፡፡
......
በተጨማሪም ቲማቲም ለቆዳ ጤንነት ያለውን ጥቅም በቀላሉ ሞክሮ ማየት ካስፈለገ የሚከተለውን ማድረግ ይቻላል።
👉ከ8 እስከ 12 የሚሆኑ ቲማቲሞችን ልጦ የልጣጩን የውስጠኛ ክፍል ፊት ላይ መለጠፍ፡፡ ቢያንስ ከ10 ደቂቃዎች በኋላ ልጣጮቹን አንስቶ ፊትን መታጠብ፡፡ ከዛም ይህንን በተደጋጋሚ በማድረግ ለውጡን ማስተዋል እንችላለን።

4 months ago
"ልጄ ቀኝ እና ግራ እግሩ እኩል አደሉም ወይም ሲራመድ ይስበዋል ምን ሊሆን ይችላል?"
#ethiopia | ይህ ከአንድ ወላጅ የተጠየቅኩት ጥያቄ ነው:: መራመድ በጀመሩ ህፃናት የእግር ቁመት እኩል አለመሆን ወይም አንዱ መሰለል ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም አንደኛው ከነርቭ መወጠር ጋ የተገናኘ ነው::
በእግር ላይ ያለው ምልክት ቆይቶ ከወራት ወይም ዓመታት በሁአላ ቢሆንም የሚታየው ችግሩ ግን የሚከሰተው ቀድሞ ነው:: በአብዛኛው በተፈጥሮ ነው የሚከሰተው:: ቀድሞ ማወቅም ይቻላል::
በተፈጥሮ የሚከሰት የህብለሰረሰር መወጠር (Tethered cord) ወደ እግር የሚሄድ የነርቭ መልክት መዛባት ስለሚያመጣ አንደኛው እግር ከሌላኛው እኩል አያድግም:: ልጁም እግሩን በነፃነት ማዘዝ እየከበደው ይመጣል:: ይሄንንም ለማካካስ ሲል በተርከዝ መርገጥ ትቶ በ ግር ጣቶች ብቻ ለመርገጥ ይሞክራል:: እግሩም እየተወጠረ መሄድ ስለሚከብደዉ እየሳበው ይሄዳል::
ከዚህ ባለፈ የነርቭ መልክት መተላለፍ መዛባት ወደ ሽንት ፊኛ ሲደርስ ሽንት መቆጣጠር አለመቻል ይሄም በልጆች ቀኑን ሙሉ ዳይፐር አንደረጠበ መቆየት ይኖራል:: ሽንት በፊኛ እየተጠራቀመ ሲመጣ ወደ ኩላሊት እየተመለሰ ኩላሊት ዉስጥ መጠራቀም እና ተደጋጋሚ የኩላሊት እንፈክሽን ያመጣል አለፍ ሲልም ኩላሊት ስራ ሊያቆም ይችላል::
ወደ ታችኛው የአንጀት ክፍል የሚሄድ የነርቭ መልክት መዛባት ደግሞ ድርቀት ያመጣባቸዋል:: ይህ መወጠር ከአርከካሪ ጎን ያሉ ጡንቻዎችን በማዛባት የአከርካሪ መጣመም ሁሉ ያመጣል::
እንዴት ማወቅ ይቻላል?
ችግሩ ከዉስጥ ቢሆንም ከቆዳ ላይ የሚያሳየው ምልክት አለ:: ለምሳሌ ከጀርባ ላይ ያለ አንድ ቦታ ችምችም ያለ ፀጉር: መሃል ወገብ ላይ ያበጠ ወይም የተከማች ስብ: መሃል ወገብ ላይ ያለ Dimple (መሰርጎድ) : የአከርካሪ መጣመም እና የመሳሰሉት::
ሕክምና አለው?
አዎ መታከም ይችላል:: ነገር ግን ሕክምናው ህመሙ እንደታወቀበት ጊዜ ይወሰናል:: ተጨማሪ የMRI ምርመራ ያስፈልጋል:: በዋነኘት የተወጠርዉን ህብለሰረሰር በማላቀቅ ያንን ተከትሎ የሚመጣዉን መዘዝ መቀነስ ነው:: አንዴ የደርሰዉን ጉዳት መመለስ ግን እጅግ አዳጋች ነው ሲሉ ለሐኪም ገጽ ተናግረዋል::
N.B ለእያናዳንዱ ታካሚ የራሱ የህክምና እና የክትትል plan ያስፈልጋል:: ሁሉም አንድ አይነት ስላልሆነ::
References
1. Guggisberg, D., et al. (2004). Skin markers of occult spinal dysraphism in children: a review of 54 cases. Child's Nervous System
2. International Survey on the Management of Skin Stigmata and Suspected Tethered Cord. Child's Nervous System, Vol. 26
3. Kulkarni, A. V., et al. (2017). Evaluation and management of tethered cord syndrome in occult spinal dysraphism. Child's Nervous System.
ቸር ያሰማን!
ዶ/ር ሱራፌል መኮንን: ረዳት ፕሮፌሰር
የህፃናት አንጎል ህብለሰረሰር ነርቭ ቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሺያሊስት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#የጤናመረጃ #hakimpage #የህፃናትጤና #የነርቭህክምና #ዶክተርሱራፌል #የህብለሰረሰርመወጠር #ethiopiahealth #parentingtips #pediatricneurosurgery