1 month ago
በኦሮሚያ 42 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት 3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በጀት ተፈቀደ
✍️ በ2019 ዓ.ም ከ13 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ይገባሉ
የትምህርት ዘመን ከ13 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንደሚገቡ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
በ3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በጀት 42 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አዲስ ግንባታ መፈቀዱ ተገልጸዋል።
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) የ2018 ዓ.ም አፈጻጸምና የ2019 የትምህርት ዘመን ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ በክልሉ 13 ሚሊዮን 521 ሺህ 861 ተማሪዎችን በ37 ሺህ 121 የትምህርት ተቋማት ውስጥ ለማስተማር ዕቅድ መያዙን ገልጸዋል።
የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል በሚከናወነው ሥራ 14 ሺህ 150 አዳዲስ መምህራን እንደሚቀጠሩ የጠቆሙት ኃላፊው፤ ከ20 ሚሊዮን በላይ መጻሕፍት ታትመው ለተማሪዎች እየቀረቡ እንደሚገኝና ተጨማሪ የክፍል ደረጃዎች እንዲሁም ሞዴል ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ መሆኑን ተናግረዋል።
በትምህርት ቤቶች የተጀመሩት የፍራፍሬ ችግኝ ተከላዎች፣ የዶሮና የከብት እርባታ ሥራዎች እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
Via ጋዜጣ_ፕላስ

3 months ago
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ አስገባ
#ethiopia | የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በማዕድን ዘርፍ እያስመዘገበ ያለውን አስደናቂ ስኬት በመቀጠል በ2018 በጀት ዓመት እስከ ሰኔ ወር ድረስ 8 ሺህ 985 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረጉን የክልሉ ማዕድን ቢሮ አስታውቋል።
ይህ አስደናቂ ውጤት በ2017 በጀት ዓመት ገቢ ከተደረገው 4 ሺህ 779 ነጥብ 71 ኪሎ ግራም የወርቅ ምርት ጋር ሲነጻጸር የ4 ሺህ 205 ኪሎ ግራም ታላቅ ብልጫ ያለው ሲሆን የክልሉን የወርቅ ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን አመላካች ሆኗል።
በሀገር ደረጃ ከወርቅ ማዕድን ኤክስፖርት ከተገኘው 5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ውስጥ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድርሻ 1 ነጥብ 18 ቢሊዮን ዶላር ወይም 21 ነጥብ 44 በመቶ መሆኑ ደግሞ ክልሉ ለሀገር ኢኮኖሚ እያበረከተ ያለውን ወሳኝ ሚና በግልጽ ያሳያል።
ይሁን እንጂ በክልሉ በስፋት የሚስተዋለው ባሕላዊ የወርቅ አመራረት ዘዴ አሁንም ለከፍተኛ የሀብት ብክነት ምክንያት እየሆነ እንደሚገኝ የቢሮው ኃላፊዎች ጠቁመዋል።
በጋዜጣ ፕላስ ዘገባ መሠረት ወርቁ በአግባቡ ሳይጠራ ከተረፈ ምርት ጋር አብሮ የሚወገድበትን ይህንን አሳሳቢ ችግር ለመቅረፍ፣ አሁን ላይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም ሰፊ ጥረት እየተደረገ ነው።
ይህንን ውድ የተፈጥሮ ሀብት በዘመነ መንገድ በማምረት ማኅበረሰቡም ሆነ መንግሥት ከዘርፉ የሚገባቸውን ያህል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል እንደ ቤጉ-ሚድሮክ ካሉ የግል ፕሮጀክቶች ጋር በቅንጅት መሥራት ለቀጣዩ ምርታማነት ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11 ነጥብ 5 በመቶ ሆኖ ተወሰነ
የውል እድሳት ምዝገባም ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ጀምሮ ይካሄዳል
የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅ መሠረት፣ ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበረው ፍትሐዊ የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11 ነጥብ 5 በመቶ ሆኖ መጽደቁን የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል ዕድሳት ምዝገባ ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት በይፋ መተግበር ይጀምራል።
የዋጋ ማስተካከያ ውሳኔ ጥናት ተካሂዶ የነዋሪውን የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ የተዘጋጀ ነው ብሏል።
ይህ አሰራር አከራዮች ወቅቱንና የኢኮኖሚ ሁኔታውን ያገናዘበ ፍትሐዊ ገቢ እንዲያገኙ የሚያረጋግጥ፤ ተከራዮች ከገቢያቸው ጋር የተመጣጠነ ኪራይ በመክፈል የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ያደርጋል።
ውሳኔው በከተማዋ ያለውን የኑሮ ውድነት ጫና በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ ረገድ የጎላ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና መልካም አስተዳደር ፋይዳዎች እንዳሉት የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አሰታውቋል።
ጋዜጣ_ፕላስ

ኢትዮጵያ በጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ኢንዶኔዥያ አዳዲስ የባህር ትራንስፖርት መስመሮች ጀመረች
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በበጀት ዓመቱ ወደ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ኢንዶኔዥያ አዳዲስ የጉዞ መስመሮችን በመክፈት የንግድ ትስስሩን እያጠናከረ እንደሚገኝ አስታውቋል።
የተቋሙ የኮርፖሬት ማርኬቲንግ መምሪያ ኃላፊና የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ተወካይ አቶ ደምሰው በንቲ፣ በኢንዶኔዥያና በጃፓን መስመሮች ላይ ከባድ ማሽነሪዎችን፣ ተሽከርካሪዎችንና የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን የማጓጓዝ ሥራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ለጋዜጣ ፕላስ ገልጸዋል።
ኃላፊው አክለውም፣ ወደፊትም የደንበኞችንና የሀገሪቱን ጥቅም ማዕከል ያደረጉ አዳዲስ መዳረሻዎችን የማስፋፋት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
እነዚህ አዳዲስ የባህር መስመር ጉዞዎች መጀመራቸው የሀገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ያሻሽላል ያሉት አቶ ደምሰው፣ የወደብ ጭነቶች በአጭር ጊዜ ወደተፈለገው ቦታ እንዲደርሱ በማስቻል ጊዜንና ወጪን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቆጥብ አስገንዝበዋል።
Seledadotio

4 months ago
ያከበረንን አክብረን የመረጠንን ሰርተንለት የምናልፍ ከሆነ ሁላችንም አሸናፊ እንሆናለን" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#ethiopia | ግንቦት 24፣ 2018 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትውልድ ቀያቸው በሻሻ ድምፅ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ለመገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ከማለዳ ጀምሮ በመውጣት በሰልፍ ምርጫ እያካሄደ ይገኛል።
ይህም የሚሻውን ለመምረጥ መካሪ እንደማያስፈልገው ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። እኔ ዛሬ የሚያሳስበኝ ከመራጩ በላይ ተመራጩ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ህዝብ በቁርጠኝነት የሚሻውን ወስኖ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ከመረጠ በኋላ የተመረጡት ሰዎች በዚያ ልክ ታምነው እጃቸውና ልባቸው ንጹህ ሆኖ ደከመን ታከተን ሳይሉ ሰርተው የሀገር ታሪክ ለመቀየርና የህዝቡን ውለታ ለመክፈል ዝግጁነታቸው ምን ያክል ነው የሚለው ነው ሲሉ ተናግረዋል"
በምርጫው ሂደት ያሸነፉ በታማኝነት ማገልገል የተሸነፉ ደግሞ ውጤቱን በጸጋ ሊቀበሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ጋዜጣ-ፕላስ
#የ7ኛውጠቅላላምርጫ #ምርጫ2018 #ሻሻ #ጠቅላይሚኒስትርዐቢይ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Sponsored by
Surafel
5 months ago
በአማራ ክልል ከ99 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ይወስዳሉ
በአማራ ክልል ከ99 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ ጥላሁን ወርቅነህ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ፈተና 99 ሺህ 900 ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ዘርፈ ብዙ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
ተማሪዎች የስነ ልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው በስነ ልቦና ምሁራን የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ፤ ከመደበኛው የክፍል ትምህርት በተጨማሪ የማካካሻ ትምህርቶችንና ሞዴል ፈተናዎችን የመስጠት ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
ፈተናውን መቶ በመቶ በበይነ-መረብ ለመስጠት የታቀደውን ሀገራዊ ግብ ለማሳካት ክልሉ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።
በዚህም መሠረት በየደረጃው ያሉ ኮምፒውተሮችን የመጠገን፣ አዳዲስ ግዢዎችን የመፈጸምና የኢንተርኔት መሠረተ-ልማት የማሟላት ስራዎች በስፋት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
በፈተና ወቅት የኤሌክትሪክ ኃይልና የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥ እንዳያጋጥም ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና ሌሎች አጋር አካላትን ያካተተ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱንም አመላክተዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመማሪያ መጽሐፍ አቅርቦት ለአንድ ተማሪ አንድ መጽሐፍ በሚል ደረጃ ተደራሽ መደረጉ ለተማሪዎቹ ዝግጅት ትልቅ አቅም ፈጥሯል ሲሉ አስረድተዋል።
#ጋዜጣፕላስ

ከ87 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 1 ሺህ 452 ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ ነው
ከ87 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አንድ ሺህ 452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በስድስት ቢሊዮን ብር ወጪ ሊገነቡ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት በሌለባቸው ወረዳዎች 1 ሺህ 452 አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት እንቅስቃሴ ተጀምሯል።
የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ በትምህርት ሚኒስቴርና በክልሎች ትብብር የሚከናወን ይሆናል ብለዋል።
ይህ የግንባታ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ 87 ሺህ 120 ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፤ ይህም በከተማና በገጠር ለሚገኙ የኢትዮጵያ ልጆች እኩል የትምህርት ዕድልን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን አስታውቀዋል።
የግንባታ ስራው ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ በሁሉም ክልሎች ይተገበራል። በዛሬው ዕለትም በትምህርት ሚኒስቴርና በክልል ትምህርት ቢሮዎች መካከል የስምምነት ፊርማ ተፈርሟል።
#ጋዜጣ_ፕላስ

6 months ago
ምክር ቤቱ የተጓደሉ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አመራሮችን ሹመት አፀደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 16ኛ መደበኛ ጉባኤ የተጓደሉ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አመራሮችን ሹመት መርምሮ አጸደቀ።
ምክር ቤቱ አመራሮቹን ለመሾም በመስፈርቱ መሠረት ምልመላ ሲያካሄድ ቆይቶ የአራት አመራሮችን ሹመት መርምሮ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
በዚሁ መሠረት ሚዛኔ አባተ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር፣ ወ/ሮ አሸነፈች አበበ የሴቶችና ሕፃናት ጉዳዮች ዘርፍ ኮሚሽነር፣ አቶ መሃመድ አህመድ የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ጉዳዮች ዘርፍ ኮሚሽነር እንዲሁም አቶ በዳሳ ለሜሳ የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

“ስለ ትግራይ ሕዝብ እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው የማለት አባዜ መስተካከል አለበት”
- አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል
የትግራይን ሕዝብ “እኔ ብቻዬን ካልወከልኩኝ” የማለት አካሄድ ተቀባይነት እንደሌለውና ሕወሓት ሕዝቡን ለመወከል የሚያስችል የሕግም ሆነ የሞራል አግባብ የሌለው መሆኑን አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል አስታወቁ።
አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል ከጋዜጣ ፕላስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ “ስለ ትግራይ ሕዝብ እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው” የሚለው አባዜ መስተካከል ያለበት ሲሆን፣ በተለይም በአሁኑ ወቅት ሕወሓት መጠየቅ ያለበት ወንጀለኛ እንጂ ትግራይን የሚያክል ትልቅ ሕዝብ ሊወክል አይችልም።
ድርጅቱ የትግራይን ሕዝብ ችግር እንደማይፈታ በተግባር መታየቱንና ይልቁንም ሕዝቡን ወደ ባሰ ችግር ውስጥ እያስገባው ያለ አካል መሆኑን አብራርተዋል።
አጥፊው አካል ራሱ በመሆኑ ከሕወሓት ጋር በመሆን ለትግራይ ሕዝብ ችግር መፍትሔ መፈለግ እንደማይቻልና ተጠያቂ መሆን እንዳለበት አቶ ነብዩ አስረድተዋል።
ይሁን እንጂ ድርጅቱ ለመወያየት ዝግጁ ከሆነ መወያየት እንደሚችል ጠቅሰው፤ “እኛ እናውቅልሃለን፣ እኛ ካልወከልንህ” የማለት አምባገነናዊ ችግር ግን ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ጠቁመዋል።
የሕዝቡን ጥቅም የሚያስከብርና ዘላቂ መፍትሔ የሚያመጣ አካሄድ መከተል እንደሚገባ የገለጹት አቶ ነብዩ፤ የትግራይ ሕዝብ ውክልና በአንድ ወገን ብቻ ተይዞ መቆየት እንደሌለበት አሳስበዋል።

ለፋሲካ በዓል አንድ ኪሎ ሥጋ በ650 ብር እንዲሸጥ ተወሰነ
ለትንሣኤ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ አንድ ኪሎ ሥጋ በ650 ብር እንዲሸጥ መወሰኑንና ገበያውን ለማረጋጋት 600 ሺህ የቁም እንስሳት ወደ ከተማዋ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ ሃቢባ ሲራጅ በሰጡት መግለጫ፤ በበዓል ግብይት ወቅት ምንም ዓይነት የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይኖር ሰፊ ዝግጅት ተደርጓል።
ለበዓሉ ፍጆታ የሚውሉ 600 ሺህ የሚሆኑ የቁም እንስሳት ወደ ከተማዋ እንዲገቡ መደረጉንና ይህም ገበያውን ለማረጋጋት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
በበዓሉ ምክንያት በከተማዋ የሸቀጦች እጥረት እንዳይከሰት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የጠቀሱት ኃላፊዋ፤ በተለይ የሥጋ ምርት በአንድ ኪሎ በ650 ብር እንዲሸጥ መወሰኑን ይፋ አድርገዋል።
ይህ ውሳኔ ኅብረተሰቡ በዓሉን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያከብር ታስቦ የተደረገ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።
ከዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ሕገወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር የቁጥጥር ባለሙያዎች በየደረጃው መሰማራታቸውን አስታውቀዋል።
ሕገወጥ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉና ገበያውን በሚያናውጡ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድም አስገንዝበዋል።
ጋዜጣ ፕላስ

"የአፍሪካ ታሪክ በአፍሪካውያን እጅ እንጂ በሌሎች ሊጻፍ አይገባም"
- ፕንገተራይ አን ሙጓጓ
#ethiopia | የአፍሪካ ታሪክ በሌሎች ሳይሆን በራሳቸው በአፍሪካውያን እጅ ሊጻፍ እንደሚገባና ወጣቶች ለዚህ ትብብራቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ተገለጸ።
ይህ የተገለጸው 6ኛው የአፍሪካ ወጣቶች የዲፕሎማሲ ኮንፈረንስ በተካሄደበት ወቅት ነው።
ኮንፈረንሱ እያንዳንዱ ወጣት ድምፁ ዋጋ እንዳለውና ሀሳቡ ኃይል እንደሆነ እንዲያውቅ የሚደረግበት መድረክ መሆኑን የአህጉር አቀፍ የወጣቶች ትስስር ተወካይ ፕንገተራይ አን ሙጓጓ ገልጸዋል።
ለረጅም ጊዜ የአፍሪካ ድምፅ በዓለም መድረክ ዳር ላይ ተገፍቶ መቆየቱን ያነሱት ተወካይዋ፤ ዛሬ ግን በአንድነት ቆመን የራሳችንን ታሪክ በራሳችን እንጂ በሌሎች እጅ ሊጻፍ አይገባም ብለን በአንድ ድምፅ ልንናገር ይገባል ብለዋል።
ወጣቶች ትውልዶችን የሚያገናኙ ድልድይ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የምንመኛት ሰላማዊና የበለጸገች አፍሪካ ከሰማይ የምትወርድ ሳትሆን በገዛ እጃችን የምንገነባት ናት ሲሉ አስገንዝበዋል።
ከፖሊሲ ወደ ተግባር የምንሸጋገርበት ወቅት አሁን በመሆኑ፣ ቋንቋና ባህል ሳይለየን ከተለያዩ የአህጉሪቱ ክፍሎች የመጣን ወጣቶች ትብብራችንን ማጠናከር ይጠበቅብናል ሲሉም አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ውይይት ለሰላም ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ጫላ አሰፋ በበኩላቸው፤ አፍሪካውያን ወጣቶች አንድነታቸውን በማጠናከር የአህጉሪቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በራስ አቅም ለመወሰን መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
አፍሪካ ከአሁን በኋላ በችግር የምትታወቅ ሳትሆን የቴክኖሎጂ እና የኢኮኖሚ ማዕከል እየሆነች ያለች አህጉር መሆኗን ያነሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ የአህጉሪቱን ዕድገት አጠናክሮ ለማስቀጠል የወጣቶች ትብብር እና አንድነት ወሳኝ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጋዜጣ_ፕላስ #africa #weareone #ethiopia #adwa

7 months ago
የከተማ አውቶቡሶች ሞተር ቀይረው ተፈጥሮ ጋዝ ሊጠቀሙ ነው
የከተማ አውቶቡሶችን ሞተር በመቀየር ወደ ተፈጥሮ ጋዝ (Natural Gas) አጠቃቀም እንዲገቡ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን አስታወቀ።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ለነዳጅ እጥረት እንደ መፍትሔ እየተወሰዱ ያሉ አማራጮች ውጤታማነታቸው እየታየ ነው።
በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ የቤንዚን ሰልፍ የቀነሰው በኤሌክትሪክ መኪኖች መበራከት መሆኑን ጠቅሰው፤ ቀጣዩ ምዕራፍ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ አጠቃቀም መግባት መሆኑን አብራርተዋል።
ለዚህም በቅርቡ በቃሊቲ፣ በአዳማ እና በድሬዳዋ የጋዝ ማደያዎች ሥራ እንደሚጀምሩ ተጠቁሟል።
እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ የከተማ አውቶቡሶችን ሞተር በመቀየር ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ማስገባት በዘርፉ ላይ ትልቅ እፎይታ ይፈጥራል።
ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ ደግሞ የሀገር ውስጥ የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ሲጠናቀቅ 80 በመቶ የሚሆነውን የሀገር ውስጥ ፍላጎት መሸፈን እንደሚቻል ተገልጿል።
ለዚህም ጋዝ የማምረት እና ኤሌክትሪክ የማመንጨት ፕሮጀክቶች በቢሊዮን ዶላሮች በጀት ሥራ መጀመራቸውን አውስተዋል።
ትልቁ የባለሥልጣኑ ግብ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዘርፎች በነዳጅ እጥረት እንዳይቆሙ ማድረግ መሆኑን የጠቀሱት ደስታው (ዶ/ር)፤ በተለይም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች፣ የኤክስፖርት ኢንዱስትሪዎች እና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች በትኩረት ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ለአብነትም አዲሱ የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ግንባታ በአንድ ወር ብቻ 15 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ እንደሚፈልግ ጠቁመዋል።
በመጨረሻም በዘርፉ የሚታየውን ሕገወጥ ዝውውር ለመግታት ኅብረተሰቡ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።
መንግሥት በከፍተኛ ድጎማ የሚያቀርበውን ይህን ውድ ሀብት ለመጠበቅ በቴክኖሎጂም ሆነ በአስተዳደራዊ እርምጃ ሕገወጥ ድርጊቶችን ለመግታት ወደኋላ እንደማይሉ አረጋግጠዋል።

“የሲዳማ ዘመን አቆጣጠር ከሳይንሳዊ አካሄድ ጋር የተጣጣመ የጥንት የሲዳማ አባቶችን እምቅ እውቀት የሚያሳይ ነው”
የሲዳማ ዘመን አቆጣጠር ከሳይንሳዊ አካሄድ ጋር የተጣጣመ የጥንት የሲዳማ አባቶችን እምቅ እውቀት የሚያሳይ መሆኑን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ተናገሩ።
የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል በሐዋሳ ጉዱማሌ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በበዓሉ ላይ እንደተናገሩት፤ የሲዳማ ዘመን አቆጣጠር የጥንት የሲዳማ አባቶችን እምቅ እውቀት የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ትውልድም በሳይንስና ምርምር በርትቶ የአባቶቹን ሀገር በቀል እውቀት ለማበልፀግ መሥራት እንደለበት ተናግረዋል።
ፊቼ ጫምባላላ በውስጡ ሰላምን የሚያጎለብቱ የአብሮነትን የሚያጠናክሩ ከአምላክ ጋር የሚያስታርቁ እንዲሁም ትውልድ ነገን በተስፋ እንዲያይ የሚያነሳሱ በርካታ እሴቶች የያዘ ነው ብለዋል።
በፊቼ ጫምባላላ በምድር ከሰው ልጆች ጋር፤ በሰማይ ደግሞ ከአምላክ ጋር ሰላምና እርቅ የሚደረግበት ለሰው ልጆች ሁሉ የሚተርፍ ቱባ እሴትን የያዘ መሆኑን አንስተዋል።
ይህ የሐገር እውቀትና እሴት ልዩነቶችን በመፍታት አንድነትን በማጠናከር በሰላም አብሮ መኖር እንደሚቻል ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።

በብዙ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶች የተገኘ የወርቅ ሜዳልያ
📌የዶክተር ሜሮን ለገሰ ድል
#ethiopia | አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በተለያዩ የሕክምና ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 263 አዳዲስ ባለሙያዎችን ሲያስመርቅ፣ የአንድ ወጣት ጥረትና ጽናት በክብር አዳራሹ ውስጥ በልዩ ድምቀት ተስተጋብቷል።
ለዓመታት የዘለቁ አድካሚ የጥናት ሌሊቶች፣ እረፍት የሌላቸው ቀናትና ፈታኝ ፈተናዎች ዛሬ በደስታ እንባና በድል አክሊል ተተክተዋል። በዚህ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከመላው ተመራቂዎች የላቀ 3.95 ውጤት በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ለመሆን የበቃችው ዶክተር ሜሮን ለገሰ የዕለቱ ደማቅ ኮከብ ሆናለች።
የስኬቱ ምስጢር፡ ትጋትና ድጋፍ
ዶክተር ሜሮን ስኬቷን አስመልክቶ ለጋዜጣ ፕላስ በሰጠችው ቃል፣ መንገዱ አልጋ በአልጋ እንዳልነበረ ገልጻለች። "ፈተናው ቢነገር አያልቅም" የምትለዋ ሜሮን፣ ለዚህ ክብር እንድትበቃ የሚከተሉት ወሳኝ ነበሩ ብላለች፦
* የፈጣሪ እገዛ፡ በሁሉም እርምጃዎቿ አጋዥ እንደነበራት።
* የቤተሰብና የመምህራን ድጋፍ፡ ከጎኗ ያልተለዩዋት የቤተሰቧ አባላትና ዕውቀት ያጋሯት መምህራኖቿ።
* የጊዜ አጠቃቀም፡ ሰፊ ንባብና ከፍተኛ ትኩረት የሚጠይቀውን የሕክምና ትምህርት በብቃት ለመወጣት ጊዜዋን በአግባቡ የመጠቀም ጥበቧ።
"ትምህርቱ ሰፊ የማንበብ ጊዜና ትኩረት የሚጠይቅ ነበር፤ ነገር ግን ያን ጊዜ በአግባቡ መጠቀሜ ዛሬ ለዚህ ስኬት አብቅቶኛል" — ዶክተር ሜሮን ለገሰ
የተስፋ ብርሃንና የቀጣዩ ጉዞ
ዶክተር ሜሮን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሴት ተማሪዎች ውጤታማነት እየጨመረ መምጣቱ ለሌሎች ተነሳሽነት እንደሚፈጥር ጠቅሳለች። ትምህርቷን አጠናቃ ስትመረቅ ግን የያዘችው ትልቁ ራዕይ ሜዳልያውን ማጥለቅ ብቻ አይደለም፤ ሕዝቧንና ሀገሯን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል ነው።
በዛሬው ዕለት ቤተሰቦቿና ወዳጅ ዘመዶቿ በተገኙበት የተከበረው ይህ የድል ቀን፣ ለዶክተር ሜሮን የአገልግሎት ዘመን መጀመሪያ እንጂ የጥረት ማብቂያ አይደለም።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጋዜጣ + #የህክምና_ምረቃ #ዶክተር_ሜሮን_ለገሰ #የአዲስ_አበባ_ዩኒቨርሲቲ #የሴቶች_ስኬት #ወርቅ_ሜዳልያ #ኢትዮጵያ

ሁለት ቢሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ወጪ ለሚያደርጉ ሦስት ኩባንያዎች የማዕድን ምርት ፈቃድ ተሰጠ
ማዕድን ሚኒስቴር ሁለት ቢሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ወጪ በማድረግ በተለያዩ የማዕድን ምርት ለሚሰማሩ ሦስት ኩባንያዎች የምርት ፈቃድ ሰጥቷል።
የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኘ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት፤ ፈቃድ የተሰጠው ስትራቴጂካዊ ለሆኑ የኢትዮጵያ ሀብቶች ሲሆን፣ ይህም ብረትን በጥሬው በኢትዮጵያ ለማምረት ያስችላል።
ፕሮጀክቶቹ በተለያየ ምዕራፍ የሚከናወኑ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ሦስቱ የማዕድን ምርቶች 2 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ወጪ ይደረግባቸዋል።
ፈቃድ የተሰጣቸው ኩባንያዎች በፖታሽ፣ በብረትና በወርቅ ምርቶች የሚሰማሩ ናቸው።
በዚህም መሠረት በፖታሽ ምርት ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ፣ በብረት ምርት ለዜድዋይቲ ቢዲአይኤም (ZYT BDIM)፣ እንዲሁም በወርቅ ምርት ለቤሮ ማይኒንግ የማዕድን ምርት ፈቃድ ተሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ በበኩላቸው፤ በአፋር ክልል የሚገኘው የኢትዮጵያ የፖታሽ ሀብት በዓለም ላይ ካለው ሀብት በከፍተኛ ደረጃ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የፖታሽ ሀብቱ ለኢንዱስትሪ ግብዓት ከመሆኑ ባሻገር ለማዳበሪያ ምርት ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለውም ጠቁመዋል።
መንግሥት ለኢንዱስትሪ ግብዓት በሚሆኑ ትላልቅ ማዕድናት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝም ተመላክቷል።

ከህግ ውጪ ከሥራቸው የተሰናበቱ 942 ሰራተኞች ወደ ሥራ ገበታቸው ተመለሱ
ከህግ ውጪ ከሥራቸው የተሰናበቱ 942 ሰራተኞች ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ፡፡
“የዳኝነትና የዲሞክራሲ ተቋማት እመርታ፤ ለተሳካ ሀገረ መንግስት ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ ሀገራዊ የዳኝነትና የዲሞክራሲ ተቋማት የሪፎርም ጉዞን የሚዳስስና ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚመለከት ኮንፈረስ ተካሂዷል፡፡
የተቋሙ ዋና ዕንባ ጠባቂ ወይዘሮ ስመኝ ውቤ በኮንፈረንሱ ላይ እንደገለጹት፤ የህዝብ አስተዳደር እንዲሻሻልና የመንግስት ተጠያቂነት ለማሳደግ ይሰራል፡፡
አስተዳደራዊ በደል የደረሰባቸው ግለሰቦች የሚያቀርቧቸውን ቅተሬታዎችና አቤቱታዎች በመከታተል መምርምሮ እልባት እንዲያገኙ እየሰራ ይገኛል፡፡ በቀጣይም የአቤቱታ ምላሽ አሰጣጡን ከ78 በመቶ ወደ 85 በመቶ ለማድረስ መታቀዱን ገልጸዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት በተሰሩ ሥራዎች ወደ ተቋሙ ከሚመጡ አቤቱታዎች መካከል 78 በመቶው እልባት እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን፤ ለአስተዳደራዊ በደል ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የቁጥጥር ሥራዎችን በመስራት 87 በመቶ መፍትሔ እንዲያኙ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡
እንደዋና ዕንባ ጠባቂዋ ገለጻ፤ መሬታቸው ያለአግባብ የተወሰደባቸው 828 አቤቱታ አቅራቢዎች ጉዳያቸው ተመርምሮ ምትክ ቦታ እንዲሰጣቸውና 14 ሚሊየን ብር ካሳ እንዲከፈላቸው ተደርጓል፡፡ ከህግ ውጪ ከሥራቸው ተሰናብተው የነበሩ 942 ሰራተኞች ደግሞ ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ መደረጉን አብራርተዋል፡፡
አቤቱታ አቅራቢዎች ከህግ አግባብ ውጪ የተከለከሉትን ልዩ ልዩ መንግሥታዊ አገልግሎቶች እንዲያገኙ መደረጉን ጠቅሰው፤ ዜጎች መረጃ የማግኘት፤ የመጠየቅ፣ የማዘጋጀት መብታቸው እንዲከበርና የመረጃ ነጻነት ህጉ እንዲተገበር ክትትል እያደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡፡
የተጠናከረ የቁጥጥርና የምርመራ ሥርዓትን መዘርጋት፤ የአስተዳደራዊ በደል እንዲቀንስ መስራት የተቋሙ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
የህዝብ አስተዳደር በግልጽነትና በተጠያቂነት መርህ እንዲመራ ለማድረግና ህገ መንግሥታዊነትን ለማስፈን እንደሚሰራ በመግለጽ፤ ተቋማት የሚሰጧቸው ፍትሃዊነት የጎደለው ውሳኔዎችና ትዕዛዞች በወቅቱ ለማረምና ለመከላከል እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

አሜሪካ በነዳጅ አምራቾች ላይ የተጣሉ አንዳንድ ማዕቀቦችን ልታነሳ ነው
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት አስተዳደራቸው በነዳጅ አምራች ሀገራት ላይ የተጣለውን አንዳንድ ማዕቀብ እንደሚያነሱ አስታወቁ።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በማያሚ ፍሎሪዳ በሚገኘው የጎልፍ ክለባቸው ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት፤ በአንዳንድ ሀገሮች ላይ የተጣሉትን ማዕቀቦች የነዳጅ ዋጋ እስኪስተካከል ድረስ እናነሳለን ብለዋል።
አሜሪካ በአሁኑ ወቅት በሩሲያ፣ በኢራን እና በቬንዙዌላ የነዳጅ ዘርፎች ላይ ማዕቀብ የጣለች ሲሆን፤ ትራምፕ የትኞቹ ሀገሮች የማዕቀብ እፎይታ እንደሚደረግባቸው አልገለጹም።
የሪዮተርስ የዜና ወኪል በርካታ ስማቸው ያልተጠቀሰ ምንጮችን በመጥቀስ ሰኞ ዕለት እንደዘገበው ትራምፕ የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ ባቀዱት እቅድ መሰረት በሩሲያ ላይ የተጣሉትን ማዕቀቦች ለማቃለል እያሰቡ መሆኑን አስታውቋል።
የአሜሪካ የግምጃ ቤት ሚኒስትር ስኮት ቤሴንት ባለፈው ሳምንት የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት ለህንድ የሚሸጠው የሩሲያ ነዳጅ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ለ30 ቀናት እንደሚተዉ አስታውቀዋል።
በጦርነት ሳቢያ ክፉኛ ንሮ የነበረው የዓለም የነዳጅ ዋጋ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በወሰዱት አዲስ አቋም ምክንያት ድንገተኛ ቅናሽ እያሳየ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
ይህም የመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስ በኋላ ከታየው የ50 በመቶ የዋጋ ጭማሪ አንጻር ትልቅ መረጋጋት የታየበት ነው ተብሏል።
ይሁን እንጂ የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ መዘጋቱ እና የባህር ትራንስፖርት መቆሙ አሁንም ለዓለም የነዳጅ ገበያ ትልቅ ስጋት ሆኖ ቀጥሏል።

“በኢ-ፍትሐዊነት የተዘጋብንን የባህር በር በማስከፈት የራሳችንን ታላቅ ታሪክ ሰርቶ ለማለፍ በቁጭት እንነሳ”
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
#ethiopia | በኢ-ፍትሐዊነት የተዘጋብንን የባሕር በር በማስከፈት የቀድሞ አርበኞቻችንን ታሪክ ከመዘከር ባለፈ ይህ ትውልድ የራሱን ታላቅ ታሪክ ሠርቶ ለማለፍ በቁጭት ሊነሳ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት 130ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ” በሚል መሪ ቃል በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት እየተከበረ በሚገኝበት ወቅት ሲሆን፤ ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦችና የአፍሪካውያን የነፃነት ፋና መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያን በውስጣዊ ጉዳዮች ልዩነት ቢኖራቸውም፣ በሀገር ሉዓላዊነትና በብሔራዊ ክብር ላይ ግን በጋራ መቆም እንዳለባቸው ዓድዋ ትልቅ ቁምነገር ያስተማረበት መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍንም በበኩላቸው፤ በደምና በአጥንታቸው ሀገርን ላቆዩ ጀግኖች ተገቢውን ክብር መስጠት እንደሚገባ ገልጸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #ዓድዋ #የባሕር_በር #ጀግንነት #አዳነች_አቤቤ #ዳንኤል_ጆቴ #አርበኝነት

8 months ago
"የትግራይ ሕዝብ ሀገሩን ከሚወጉት ጋር ተሰልፎ የመዋጋት ጥቁር ታሪክ የለውም"
- ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም
የትግራይ ሕዝብ ሀገሩን ከሚወጉት ጋር ተሰልፎ የመዋጋት ጥቁር ታሪክ የለውም ሲሉ የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ኬርያ ኢብራሂም ገለጹ፡፡
የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ኬርያ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የሕወሓት ቡድን ግን የተሰለፈው ከትግራይ ሕዝብና ከሀገሪቱ ጠላት ጋር ነው።
የትግራይ ሕዝብ ሀገሩን የሚወድ እንጅ ከሕዝብና ከሀገሩ ጋር ተቃራኒ ሆኖ የሚሰለፍበት ምንም ዓይነት ሁኔታ የለም፤ እንደዚህ ዓይነት ታሪክም የለውም ብለዋል።
እንደ ወይዘሮ ኬርያ ገለጻ፤ የትግራይ ሕዝብና የትግራይ ምድር የጦር ሜዳ እንዳይሆን ህዝቡ ሊጠነቀቅ ይባል፡፡
ይህ እንዳይከሰት አሰላለፋችንን ማስተካከል እና ከጥፋት ኃይሎች በተቃራኒ መቆም አለብን ሲሉ መክረዋል።
ለትግራይ ሕዝብ ሲባል የጦርነት በር መዘጋት አለበት ያሉት ወይዘሮ ኬርያ፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ለሰላም ግፊት ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የትግራይ ሕዝብ ጥያቄዎች መመለስ የሚቻለው ከፌዴራል መንግሥት ጎን በመሰለፍ በሰላማዊ እና በዲሞክራሲያዊ መንገድ እንጅ በጦርነት አይፈታም ሲሉም አስረድተዋል።
@ጋዜጣ-ፕላስ

“የካቲት 12 ኢትዮጵያውያን የቅኝ ግዛት ቀንበርን የማይቀበሉ ሕዝቦች መሆናቸውን ያስመሰከሩበት ቀን ነው”
- ሌተናል ኮሎኔል በላይነህ ታዬ
የካቲት 12 ኢትዮጵያውያን የቅኝ ግዛት ቀንበርን የማይቀበሉና አልደፈር ባይነታቸውን ዳግም ያስመሰከሩበት ቀን መሆኑን የቀድሞ የሠራዊት አባል ሌተናል ኮሎኔል በላይነህ ታዬ ገለጹ።
ሌተናል ኮሎኔል በላይነህ ታዬ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የአድዋ ሽንፈት ያቆሰለው የጣሊያን ወራሪ ኃይል ከ40 ዓመታት በኋላ በቂም ተነሳስቶ በፈጸመው ዳግም ወረራ ወቅት፣ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በማርሻል ሩዶልፍ ግራዚያኒ ላይ የግድያ ሙከራ ማድረጋቸውን ተከትሎ ጭፍጨፋው ተከስቷል።
በዚህም ከ30 ሺህ የሚልቁ ንጹሐን ላይ ጭፍጨፋ መፈጸሙን አስታውሰዋል። አሁን ያለው ትውልድ ከቀደሙት የኢትዮጵያ ጀግኖች የደም ዋጋ ተከፍሎባት የተረከባትን ሀገር በልማትና በሰላም የማጽናት ኃላፊነት እንዳለበትም አመልክተዋል።
በወቅቱ የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዘርና በቋንቋ ሳይከፋፈል ለሀገሩ ሉዓላዊነት ሲል አንገቱን እስከ መስጠት ድረስ ዋጋ መክፈሉን ገልጸዋል።
ከዚህም አሁን ያለው ትውልድ የሀገር ፍቅርን፣ የመንፈስ ጽናትንና ቁርጠኝነትን ሊማር እንደሚገባ ሌተናል ኮሎኔሉ አስገንዝበዋል።
ትውልዱ "ሀገሬ ምን አደረገችልኝ" ሳይሆን "እኔ ለሀገሬ ምን አደረግኩላት" ብሎ ራሱን ሊጠይቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በተጨማሪም ትውልዱ የተፈጠሩለትን ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም የሀገርን ልማትና ሰላም ለማጽናት ቁርጠኛ መሆን እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የነዳጅ ምርት መፈተሻ ላብራቶሪ በድሬዳዋ ልትከፍት ነው
ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የነዳጅ ምርት መፈተሻ ላብራቶሪ በድሬዳዋ ከተማ በቅርቡ ልትከፍት መሆኑን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አስታወቀ።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ላብራቶሪው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የነዳጅ ምርቶችና ዘይቶች የተቀመጠውን የጥራት መስፈርት ማሟላታቸውን ለመፈተሽ የሚያስችል ነው።
አገልግሎቱ በቅርበት መሰጠቱ አምራች ድርጅቶችና ተቋማት በተቀላጠፈ መንገድ ጥራት ማረጋገጥ እንዲችሉ የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ለዚህም ዘመናዊ መሣሪያዎችና የሰለጠኑ ባለሙያዎች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።
ተቋሙ በድሬዳዋ፣ በአዳማ፣ በሐዋሳና በባሕር ዳር ተጨማሪ የፍተሻ ላብራቶሪዎችን በማደራጀት ላይ እንደሚገኝም ነው ያስገነዘቡት።
@ጋዜጣ_ፕላስ

"ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ቤት በመሆኑ ወደ ባህሩ መመለሳችን አይቀሬ ነው"
ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ቤት በመሆኑ ወደ ባህሩ መመለሳችን አይቀሬ መሆኑን የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ገለጹ።
ፕሮፌሰር ብሩክ ለጋዜጣ ፕላስ በሰጡት መረጃ እንዳመለከቱት፤ ቀይ ባህር የቀድሞው የኢትዮጵያ አካልና ቤቷ በመሆኑ ወደ ባህሩ መመለሳችን የታሪክ ግዴታ ነው።
ቀደም ሲል በተፈጸሙ ስህተቶች የሀገሪቱ ሕዝብና ኢኮኖሚ እየተጎዳ መቀጠል ስለሌለበት የቀይ ባህር ተደራሽነት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ግብፅ ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳይኖራት ከጎረቤት ሀገራት ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር ሴራ እየሸረበች መሆኑን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ ግን ይህንን ሰንሰለት በመበጣጠስ ፍላጎቷን ማሳካቷ እንደማይቀር አብራርተዋል።
ኤርትራ ለኢትዮጵያ ጠላቶች መረማመጃ ከመሆን ወጥታ ከሰሜን እስከ ደቡብ ያሉ ተቃዋሚ ኃይሎችን መደገፍ ማቆም እንዳለባት ፕሮፌሰር ብሩክ አሳስበዋል።

ለመራጮች ምዝገባ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ለመላክ ዝግጅት ተደርጓል
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመራጮች ምዝገባ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ለመላክ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የመራጮች ምዝገባ ወደ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም መራዘሙን ገልጸዋል፡፡
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የመራጮች ምዝገባ የካቲት 7 እንደሚጀመር ተገልጾ የነበረው ወደ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓም ተራዝሟል፡፡
ቦርዱ 2018 ዓም ለሚያከናውነው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የቅድመ ምርጫ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል።
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመራጮች ምዝገባና ለምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ሙሉ በሙሉ ወደ ሀገር ማስገባቱን ገልጸው፤ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ለመላክ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ ነው ብለዋል።
የምርጫ ክልል ጽህፈት ቤት ለመክፈት የሚያስችሉ የምርጫ ክልል አስፈጻሚዎች ምዝገባ ቦርዱ ማካሄዱን ጠቁመው፤ በዚህም የምርጫ ክልል ጽህፈት ቤት መክፈት መቻሉን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ቦርዱ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች ምልመላ እና ቅጥር በማከናወን ለፖለቲካ ፓርቲዎች መላኩንም ሰብሳቢዋ ጠቁመዋል።

9 months ago
“ለትግራይ ሕዝብ አማራጭ ፖሊሲ ይዤ በ7ኛው አገራዊ ምርጫ ለመወዳደር ዝግጅት እያደረግሁ ነው”
- የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) በሰላም፣ በኢኮኖሚ እና በግብርና ላይ ትኩረት ያደረገ አማራጭ ፖሊሲና ማኒፌስቶ በመያዝ በ7ኛው አገራዊ ምርጫ ለመወዳደር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።
የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ፅጋቡ ቆባዕ ለአዲስ ዘመን ዕለታዊ ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ፓርቲው ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ሕጋዊ መመሪያዎችንና የምዝገባ መስፈርቶችን የማሟላት ሥራ እየሠራ ይገኛል።
ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ከማንኛውም ጫና ነፃ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ግዴታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የትግራይ ሕዝብ ለተሻለ የሐሳብ አማራጭ ያለው ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን ምክትል ሊቀመንበሩ ጠቁመዋል።
ብዙኃን መገናኛዎች ሁሉንም ፓርቲዎች በእኩል እንዲያስተናግዱና መራጮች ያለ ሥጋት ድምፅ እንዲሰጡ ሁኔታዎች ሊመቻቹ ይገባል ብለዋል።
በክልሉ ከጦርነቱ ወዲህ ያለው የፖለቲካና የጸጥታ ሁኔታ ለምርጫው እንቅፋት እንዳይሆን ጊዜያዊ አስተዳደሩና የፖለቲካ ኃይሎች በመግባባት በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል። ይህም ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ዕድገት ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።

ቻይና በ2025 ከፍተኛ የንግድ ትርፍ አስመዘገበች
እ.ኤ.አ. በ 2025 የቻይና የንግድ ትርፍ ወደ 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ዶላር በመጠጋት አዲስ ታሪካዊ ክብረወሰን ማስመዝገብ ችሏል፡፡
ይህ ውጤት የተመዘገበው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቻይና ምርቶች ላይ ከፍተኛ የታሪፍ ጭማሪ ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡
የቻይና የወጪ ንግድ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በ5 ነጥብ 5 በመቶ በማደግ 3 ነጥብ 77 ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል። በአንፃሩ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው ምርቶት ባለበት በመቆሙ፣ ሀገሪቱ የ1 ነጥብ 19 ትሪሊዮን ዶላር የንግድ ትርፍ እንድታገኝ አስችሏታል።
ወደ አሜሪካ የሚላኩ የቻይና ምርቶች በ20 በመቶ ቢቀንሱም፣ ቻይና ወደ ሌሎች የአለም ክፍሎች በመላክ አጣጥታዋለች። በተለይም ወደ አፍሪካ የሚላኩ ምርቶች በ26 በመቶ፣ ወደ ደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት በ13 በመቶ፣ እና ወደ አውሮፓ ህብረት በ8 በመቶ ጨምረዋል።
የኮምፒውተር ቺፖች፣ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች እና የኤሌክትሪክ መኪናዎች ሽያጭ መጨመርም ለዚህ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ተገልጿል፡፡
የቻይና የንግድ ትርፍ በአሁኑ ወቅት ከአለም አቀፍ ጠቅላላ ምርት (Global GDP) አንጻር ሲታይ እጅግ ከፍተኛው ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህም ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ጋር ያለውን የንግድ ውጥረት ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል ተገምቷል።
#ጋዜጣ ፕላስ

ኢትዮጵያ ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከኒውክሌር ቴክኖሎጂ ኃይል ማመንጨት ትጀምራለች
ኢትዮጵያ ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን በመገንባት የኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አብዱረዛቅ ዑመር ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለመገንባት ከ10 እስከ 15 ዓመታት የሚፈጅ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ አሁን ባለው የቅድመ ዝግጅት ፍጥነት ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ለመግባት አቅዳ እየሠራች ነው።
ለዚህም የኒውክሌር ልማት ሥራውን በኃላፊነት መወጣት የሚችል ተቋም ተቋቁሞ አስፈላጊ መሠረተ ልማቶችን የመገንባትና ከጥንቃቄና ደኅንነት አኳያ የሚከናወኑ ተግባራት እየተሠሩ መሆኑን አብዱረዛቅ ዑመር አስረድተዋል።
የኒውክሌር ልማት ፕሮግራሙ የኃይል አቅርቦትን ከአየር ንብረት ጋር በተጣጣመ መልኩ አስተማማኝ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።
ቴክኖሎጂው በጤና፣ በኢንዱስትሪና በግብርና ዘርፎች ምርታማነትን ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸው፤ ኒውክሌር ኃይልን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለልማት ለማዋል ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር መጀመሩን ተናግረዋል።
ይህ አስተማማኝ የኃይል ምንጭ ሀገሪቱ ለምታደርገው ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል።
Via ጋዜጣ ፕላስ

አፈርን ከሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ጥናት ተጠናቀቀ‼️
ከትንሽ ሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ታምራት ሙሉ (ኢ/ር) ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተጠናው ይህ ጥናት ትኩረት ያደረገው በሐረሪ፣ በድሬዳዋ እና በጅግጅጋ አካባቢዎች የሚገኘውን አፈር ለቤት ግንባታ በሚውል መልኩ ማዘጋጀት ላይ ነው።
ቴክኖሎጂው የተለመደውን ብሎኬት ከመጠቀም ይልቅ፣ በአካባቢው የሚገኘውን አፈር ከትንሽ ሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ነው ብለዋል።
በእነዚህ አካባቢዎች ለሚኖሩ ከ6 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች የቤት ግንባታ ችግርን የሚቀርፍ መፍትሔ ይዞ መቅረቡን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ግንባታዎች ሙሉ በሙሉ በሲሚንቶ ላይ ብቻ የተንጠለጠሉ እንዳይሆኑ በማድረግ የግንባታ ወጪን በእጅጉ እንደሚቀንስም ተገልጿል።
ጥናቱ ሁሉንም የኢንጂነሪንግ መስፈርቶች አሟልቶ በቤተ-ሙከራ የተረጋገጠ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት "ለአካባቢያዊ ችግር አካባቢያዊ መፍትሔ" በሚል ስትራቴጂ ለመጨረሻ ማረጋገጫ ለውይይት ቀርቧል።
seledadotio

ኒኮላስ ማዱሮ ከባለቤታቸው ጋር በኒውዮርክ ፍርድ ቤት ቀረቡ
የቀድሞው የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እና ባለቤታቸው ሴሊያ ፍሎሬስ በሽብርተኝነትና በአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ተከሰው በኒውዮርክ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተገለጸ።
ቢቢሲ እንደዘገበው፤ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እና ባለቤታቸው የቀረበባቸው ክስ ከሽብርተኝነት ተግባራት እና ከዓለም አቀፍ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ጋር የተያያዘ ነው።
ይህ የአሜሪካ የሕግ ርምጃ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ያስከተለ ሲሆን፤ በተለይም የስፔን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሜሪካ መንግሥት በቬንዙዌላ መሪዎች ላይ የወሰደውን ርምጃ አጥብቀው ኮንነዋል።
በሌላ በኩል ሩሲያና ቻይና የተወሰደውን ርምጃ በመቃወም ኒኮላስ ማዱሮ እና ባለቤታቸው ሴሊያ ፍሎሬስ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል።
ጉዳዩ በላቲን አሜሪካ ፖለቲካ እና በአሜሪካ የውጭ ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ የፍርድ ሂደቱ በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ዘንድ በትኩረት ክትትል እየተደረገበት ይገኛል።

ቱርክ ከ125 በላይ የሽብር ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዋለች
የጸጥታ ኃይሎች በመላ ሀገሪቱ ባደረጉት የተቀናጀ አሰሳ ከ125 በላይ የአይ.ኤስ.አይ.ኤስ (ISIS) ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የቱርክ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የቱርክ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ዬርሊካያ እንደገለጹት፤ ዋና ከተማዋ አንካራን ጨምሮ በ25 ግዛቶች ውስጥ የተቀናጀ የፍተሻና የቁጥጥር ስራ ተከናውኗል።
ርምጃው በያሎቫ ከተማ በፖሊስና በታጣቂዎች መካከል በተከሰተ የተኩስ ልውውጥ የሦስት ፖሊሶችና የስድስት ታጣቂዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ የተወሰደ ነው።
ዘመቻው በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ የተከናወነ ሦስተኛው መጠነ ሰፊ ፍተሻ ሲሆን፤ በሀገሪቱ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የአልጄዚራ ዘገባ እንደሚያመለክተው ቱርክ በሽብር ቡድኖች ላይ የምታደርገውን ክትትል አጠናክራ ቀጥላለች።

“ግብፅ በታንዛኒያ የገነባችው ግድብ የትብብር ማሳያ ሳይሆን የመከፋፈያ ዘዴ ነው”
- ፈቅ አህመድ ነጋሽ
ግብፅ በታንዛኒያ የገነባችው ግድብ የትብብር ማሳያ ሳይሆን የናይል ተፋሰስ ሀገራትን የመከፋፈያ ዘዴ መሆኑን የቀድሞ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ቡድን አባልና የውኃ ሀብት ተመራማሪ ፈቅ አህመድ ነጋሽ ገለጹ።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የታንዛኒያው ጁሌየስ ኔሬሬ የኃይል ማመንጫ ግድብን የናይል ተፋሰስ ሀገራት የትብብር ምሳሌ አድርገው ማንሳታቸውን ተከትሎ ተመራማሪው ለጋዜጣ_ፕላስ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ግብፅ ግድቡን የገነባችው እንደማንኛውም ኮንትራክተር ሥራውን ወስዳ እንጂ በነጻ ወይም በትብብር እንዳልሆነ ፈቅ አህመድ ነጋሽ አብራርተዋል።
ግብፅ ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ኃይል እንዳትሸጥ እንቅፋት ለመሆን እየተንቀሳቀሰች መሆኑንና ለዚህም ለጅቡቲ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ እየገነባች መሆኗን በምሳሌነት ጠቅሰዋል።
እንደ ተመራማሪው ገለጻ፤ ግብፅ የታላላቅ ሐይቆች አካባቢ ሀገራት የሚያካሂዱት ልማት ግድቦቻቸው አነስተኛ በመሆናቸው ተጽዕኖ አያደርስብኝም የሚል እምነት ቢኖራትም፣ በምሥራቅ ናይል ላይ ግን አንዲት ጠብታ ውኃ ጥቅም ላይ እንዳይውል ትቃወማለች።
በቅርቡ በናይል የትብብር መድረክ ላይ የታላላቅ ሐይቆችን የልማት ዕቅድ አጽድቃ የምሥራቅ ናይልን ግን አልቀበልም ማለቷን ተመራማሪው አስታውሰዋል።
ግብፅ የምታደርገው እንቅስቃሴ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራትን ድጋፍ ለማግኘት ያለመ ቢሆንም፤ ውኃውን በተመለከተ ያላት ተቀባይነት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን ተመራማሪው ፈቅ አህመድ ነጋሽ አክለው ገልጸዋል።

Comments