2 months ago
የወልቂጤ የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ጣቢያ ስርጭት ተቋረጠ
#ethiopia | በደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ስር የሚገኘው የወልቂጤ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች፣ ከመስከረም 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የነበረበት የደመወዝ ማሻሻያ አልተደረገልንም በሚል መጋቢት 16 ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ መምታታቸውን አስታወቁ።
ሠራተኞቹ በጻፉት ደብዳቤ፤ "ሌሎች አቻ ቅርንጫፎች ጥቅማጥቅሙ ተከብሮላቸው እኛ ጋር ግን ምላሽ የሚሰጥ አካል ጠፋ" ብለዋል።
በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ምክንያት ልጆቻቸውን ከትምህርት ቤት እስከማስወጣት መገደዳቸውንና ማህበራዊ ሕይወታቸው መቃወሱን በምሬት ገልጸዋል።
በአማርኛ፣ በቀቤንሲኛ፣ በየሚኛ፣ በጉራግኛና በማረቂኛ ቋንቋዎች የሚተላለፈው ስርጭት ጥያቄያቸው ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ተቋርጦ እንደሚቆይ ሠራተኞቹ በፊርማቸው አረጋግጠዋል።
#ኢትዮጵያ #ወልቂጤ #ደቡብ_ሬድዮና_ቴሌቪዥን #የደመወዝ_ማሻሻያ #የሠራተኞች_መብት #getu_temesgen #ዜና #gurage #wolkite

Comments