12 days ago
ተስፋዬ ገሠሠ
ጎምቱ የጥበብ ባለሟል
የሕይወት ታሪክ
ደራሲ፦ ደረጀ ትዕዛዙ
የአዘጋጁ መልዕክት
#ethiopia | የሰው ልጅ ሲፈጠር በምክንያት ነው። እግዚአብሔር አዶልፍ ሂትለርን እና ሞሶሎኒን በአንድ በኩል፤ ማሃትመ ጋንዲ እና አልበርት አንስታይን በሌላ ቋት ሲፈጥር፤ ሕይወትን ፅንሰ ሀሳብ ለመስጠት፤ ለሰዎች ወጥ የሆነ የአኗኗር ዘይቤ እንዳይኖር ፈልጎ ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ ይቻላል።
እነዚህ በአንድ ወቅት በተግባራቸው ዓለም ያገናኛቸው ሰዎች፤ ማንነታቸው ቢፈተሽ ማህበራዊ እርከናቸው፤ ስብዕናቸው የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን። ባሕሪያቸው ከተወለዱበት፤ ከያዙትና አብረው ከኖሩት ማህበረሰብ ሊቀዳ እንደሚችል ሁሉ፤ ከየራሳቸውም የዚያ ሥራቸው ነፀብራቅ እንደሆነ ይታመናል። መልካምነትና መጥፎነት ዘወር ብሎ ምንጩ ከዚያው ነው። የሆነው ሆኖ፤ ቅንና አስተዋይ ልቦና መታደል ግን መልካም መታደል ነው። ሁሉም በሚፈፅሙት ተግባር ምድራዊም ሆነ በሰማይ የሚጠየቁበት ወይም የሚመሰገኑበት ነገር እንዳለ ሁሉ፤ እነሱም በየራሳቸው የተደሰቱበት ወይም ተፀፅተው ያለፉባቸው ጊዜያት ስለመኖራቸው አይጠረጠርም።
የሰው ልጅ በማንነቱ፤ በቀለሙ እና በተግባሩ ዥንጉርጉር ነው። እያንዳንዱ ግለሰብ በኖረበት ዘመናት ሁሉ በተግባሩ ለዚች ዓለም ይነስም ይበዛም ስለማንነቱ የሚያስቀምጠው አሻራ አለው። መታወቂያው እንደየ ተግባሩ ቢለያይም ሁሉም ታሪክ አለው። የግለሰቦች ታሪክ የሀገር ታሪክ አካል የሚሆንበትም አገባብ አለ። ይህ የሚሆነው ደግሞ ታሪክ ከቃል ትሬት ወደ ጽሑፍ ተለውጦ ሲመዘገብ፤ በአግባቡ ሲሰነድ፤ ሲያያዝ፤ ከዚያም አልፎ ለቀጣዩ ትውልድ ሲተላለፍ ነው። "የግለሰቦች ታሪክ ስብስብ የሀገር ታሪክ ይሆናል" የሚለውም ከዚሁ ጋር ነው።
ከዚህ ሀሳብ በመነሳት ይህ መጽሐፍ ምን ይዟል? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም።፤ ዋናው ነገር ገልጦ ማነበብ ነው። መጽሐፉ የዕድላቸው እና የሥራቸው ስለ አጋጣሚያቸው ጎምቱ የጥበብ ባለሟል ተባለው ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ የሕይወት ታሪክና ሥራዎችን ይተርካል:: ተስፋዬ ማን ነው? በኖሩባቸው ዓመታት ምን ሠሩ፤ አሻራቸው በሀገር ታሪክ ውስጥ ምን ፋይዳ አለው? የሚሉና ሌሎችንም ተያያዥ ጉዳዮችን ይጠይቃል፤ ይመልሳል፤ ይተነትናል።
ተስፋዬ በአንድ ሙያና ሥራ ብቻ የተወሰነ አይደለም:: የሕይወቱን ከሥራው ጋር እያነፃፀርኩ ማቅረቤም ለዚሁ ነው። ይህ ደግሞ ታሪኩ ሲነበብ ሰልችቶት እንዳይፈጠር ይረዳል የሚል እምነት አለኝ።
አብዛኛው የመጽሐፉ ክፍል ሲዘጋጅ ባለ ታሪኩ በሕይወት ስለነበረ ለመረጃ መብዛትና ተአማኒነት በአጅጉ ጠቅሞኛል። ከዚህ ቀደም ስለ ባለ ታሪኩ የተጻፉና የተነገሩ አጠራጣሪ ታሪኮችንና መረጃዎችን በቃለ መጠይቅ ለማጣራት ዕድሉን ፈጥሮልኛል።
ተስፋዬ በባህሪው "እንዲህ አደረግሁ፤ እንዲህ ፈጠርሁ..." እያለ ማንነቱን የመጎረድም ሆነ የመጎዳት ሰው አይደለም። ድንቅ ድንቅ ተግባሮቹ፤ መናገር የማይፈልጋቸው በጎ ሥራዎቹ ብዙ ናቸው። ስለዚህም በአመዛኙ በደራሲያን ደረጃ የተቀመጡ፤ በማስረጃዎችና በእውነቶች ተረጋግጠው እንዲወጡ ለማድረግ ጥሬአለሁ።
የጥበብ ሰው "አንቱ" አይባልም ከሚል ሀሳብ በመነሳት በአብዛኛው የመጽሐፉ ክፍል "አንተ"ን ብጠቀምም፤ አልፎ አልፎ እንደጽሑፉ አገባብና እንደየሁኔታው አጠራር "ጋሽ ተስፋዬ"፤ "ተጋባዥ ፕሮፌሰር ተስፋዬ" እና "አንቱ"ን ተጠቅሜበታለሁ። በዚህም የባለታሪኩን የመጫወቻም ሆነ የማህበራዊ ክብር የጎደልሁ ሁኚ እንደማይታሰብኝ አተማመናለሁ። እሱም ይህ እንዲሆን ፍቃዱን ሰጥቶኛል። አልፎ አልፎ ሌሎች የጥበብ ሰዎችንም በዚህ መልኩ መጥራቴ አልቀረም።
አልፎ አልፎ በታሪክ አፅንኦት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን እና በቃለ መጠይቅ ያገኛኋቸውን ሀሳቦች እንዳሉ አስቀምጣቸዋለሁ። በዚህም ወዳጆቹን፤ የሥነ ጥበብ ተማሪዎቹን፤ ቅርበት ያላቸው ቤተሰቦቹን እና ዘመዶቹን ጭምር አነጋግሬ የእውነተኝነት ቃላቸውን እንደ አግባቡ አሰፍሬአለሁ። አንዳንድ በሕይወት የሌሉና እኔ በአካል ያላገኘኋቸው ጥቂት ወዳጆቹ፤ በተለያዩ ወቅቶችና መድረኮች ስለ ተስፋዬ የሰጡትን የምስክርነት ቃል ስብስቤ አድርጌ አቅርቤአለሁ። ሥራዎቹን፤ በተለያዩ ጊዜያት ስለ እሱ የተጻፉና የተነገሩ ጉዳዮችን ፈትሻለሁ። የግል ማስታወሻና የተወሰኑ የዕለት ማስታወሻዎቹን /Daily diary/ ጭምር በርብሬአለሁ። ለዚህ ይጠቅማል፤ ይበጃል ያልኩትን ቁም-ነገር፤ ፍሬ-ነገር፤ ይሆናል ልክነቱን ነቅሼ በማውጣት በአስፈላጊው ቦታ አስፍሬአለሁ። ይህ ነው የዚህ መጽሐፍ ሂደት።
ይህ መጽሐፍ፤ የሕይወት ታሪክ (Biography) አጻጻፍ መርሁን የተከተለ እንዲሆን አድርጌአለሁ። ጋሽ ተስፋዬ የዚችኛውን ዓለም የጥበብ አውራ ኖሮ በ84 ዓመት ዕድሜው ወደማይቀረው ሄዷል። ከዚችኛዋ ዓለም በአካል ሞት ቢለይም ሥራውና ማንነቱ ግን እንዲህ ሲወሳ እና ሲዘከር ይኖራል።
መልካም ንባብ
***
የመጽሐፉ የጀርባ
“ግልጽነትን የሚያደፋፍርህ እውነት ነው። ሐሰት ውስጥህ ካለ ለመናገር ትሸማቀቃለህ። እርግጥ የፖለቲካ ሰዎች ይህንን ሊያደርጉት ይችላሉ፤ የፖለቲካ ሰው ግን ዲፕሎማት ነው። የሚናገረው የት፤ መቼ፤ እንዴት፤ ለማን፤ የሚሉትን አጢኖ፤ መትሮ ነው።
እኔ የፖለቲካ ሰው አይደለሁም፤ ተፈጥሮዬ አልፈቀደም። ስለዚህ ፊት ለፊት እናገራለሁ። መስዋዕትነት መክፈል አለብኝ፤ ይሁኑ! ይክፈል፤ እውነትን የያዘ ሁሉ ግን አሸናፊ ነው። በነጻ ህሊና ይኖራል።”
“ከፖለቲካዊ ሹመቱ በሕዝብ የታመነበት ሽልማት ይበልጥብኛል። ያስተማርኳቸው የጥበብ ልጆቼ በመድረክ፤ በፊልም፤ በሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ተሰማርተው ማየት ደስታ ይሰማኛል። ፍሬ አለኝ፤፤ ትልቁ ሽልማቴ እነሱ ናቸው።”
***
የአዘጋጁ ቀደሙት ሥራዎች፦
ደራሲ ደረጀ ትዕዛዙ
ጳውሎስ ኞኞ ከ1926-1984 (የሕይወት ታሪክ)
ሳተናው (የአጫጭር ልብወለዶችና የግጥሞች ስብስብ)
#የሕይወትታሪክ #ተስፋዬገሠሠ #መጽሐፍ #ኪነጥበብ #ደራሲደረጀትዕዛዙ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments