2 days ago
«ቤተክርስቲያናችንን አስከፍቱልን» — የድጋፍ ጥሪ
በቢሾፍቱ ወረዳ ቤተክህነት ሥር የሚገኘው የአቡ ገርቢ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ከተመሠረተ በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ቤተክርስቲያን መሆኗ ተገልጿል።
በአካባቢው በተካሄደ ልማት ምክንያት በዚያ ይኖሩ የነበሩ ምእመናን ከአካባቢው በመነሳታቸው ቤተክርስቲያኗ የነበራትን ገቢ እንዳጣች ተገልጿል። በዚህም ሳቢያ ካህናቱ ተበትነው፣ የአምልኮ አገልግሎቱም ተቋርጦ ቤተክርስቲያኗ መዘጋቷን የድጋፍ ጥሪው ያስረዳል።
በቦታው የሚገኙት አባት በሐዘን እንዲህ ይላሉ፦
««ይህን ቤተክርስቲያን ከአባቶቼ በአደራ ተረክቤዋለሁ። ዛሬ ግን ምእመናን በማጣቴ ምክንያት ተዘግታብኛለች፤ ካህኑም ትቶኝ ሄዷል። ብቻዬን ምን ላድርግ? በዓለም ያላችሁ የእመቤታችን የድንግል ማርያምና የቅዱስ እግዚአብሔር አብ ወዳጆች፣ እባካችሁ ድረሱልን፤ ቤተክርስቲያናችን እንዳትዘጋ እርዱን።»»
የድጋፍ ጥሪ
በኢትዮጵያም ሆነ በውጭ አገር የምትኖሩ የቤተክርስቲያኗ ልጆች፣ በአቅማችሁ መጠን ድጋፍ በማድረግ የእጣን፣ የጧፍ፣ የዘቢብ፣ የመገበሪያ እና የካህናት አልባሳት እንዲሟሉ በመርዳት የቤተክርስቲያኗን አገልግሎት እንደገና ለማስጀመር ድጋፋችሁን እንጠይቃለን።
የድጋፍ አካውንት
የአቡ ገርቢ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን
1000781062058
ስልክ፦
+251-901-613814
ድጋፍ ካደረጉ በኋላ የክርስትና ስምዎን በዚህ ስልክ ቁጥር እንዲልኩ ተጠይቋል፤ አባቶችም በጸሎት እንደሚያስቧችሁ ተገልጿል።
«የእያንዳንዱ ሰው ትንሽ አስተዋጽኦ ለቤተ እግዚአብሔር ትልቅ ተስፋ ሊሆን ይችላል።»
#አቡገርቢ #ቅዱስእግዚአብሔርአብ #ቤተክርስቲያን #የድጋፍጥሪ #ኢትዮጵያ #በጎነት #ድጋፍ
5 months ago
ትኩረት ለገጠር ቤተክርስቲያን
የጎፎሬ ደብረ መንክራት በአታ ለማርያም አስቸኳይ የድጋፍ ጥሪ
በከምባታ ጠምባሮና ሀላባ ሀገረ ስብከት የሚገኘው የጎፎሬ ደብረ መንክራት በአታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የህንፃ ግንባታ አሁን ላይ በከፍተኛ የግብዓትና የገንዘብ እጥረት ምክንያት ፈተና ገጥሞታል።
የአካባቢው ምእመናን ግንባታው እንዳይቆም ድንጋዩን በአህያና በኮርቻ እየተሸከሙ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
ያጋጠሙ ዋና ዋና ችግሮች፦
የድንጋይ እጥረት
የግንባታው መሠረት እየተሠራ ቢሆንም፣ ድንጋዩን ለማውጣትና ለማጓጓዝ የገንዘብ እጥረት ገጥሟል።
የትራንስፖርት ችግር
የመንገድ ብልሽትና የነዳጅ እጥረት ድንጋዩን በመኪና ለማቅረብ አዳጋች አድርጎታል።
የባለሙያ ክፍያ
ለግንባታ ባለሙያዎች የሚከፈል የገንዘብ እጥረት ስራው እንዳይቋረጥ ስጋት ሆኗል።
የልገሳ ሂሳብ ቁጥሮች (የህንፃ አሰሪ ኮሚቴ)፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000624326281
አቢሲኒያ ባንክ፦ 240587815
አዋሽ ባንክ፦ 013201006748101
ዳሸን ባንክ፦ 5640919295011
📞 ለበለጠ መረጃና የሞራል ድጋፍ፦
0933055802 ወይም 0911414852 ደውለው "አለንላችሁ" በማለት ከጎናቸው መሆንዎን ይግለጹ።
ወገኖቼ ዛሬ በከተማው ዘመናዊ ህንፃዎች መሀል ሆነን ድል ስናከብር፣ በገጠር ያሉ ወገኖቻችን በአህያ ድንጋይ እየጫኑ ቤተ መቅደስ ለመሥራት የሚደክሙትን መዘንጋት የለብንም። የሰጡት ጥቂት ብር ለዚህች ቤተክርስቲያን ትልቅ ተስፋ ነው። በእመቤታችን ስም የቀረበውን ይህን ጥሪ ሰምተን ሁላችንም የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን እማጸናለሁ።
የሰጡት ጥቂት ብር፣ ለቤተክርስቲያኗ ትልቅ ተስፋ ነው!
#getu #goforebaatamariam #orthodoxethiopia #churchconstruction #charityappeal #ethiopia #helpruralchurch #ትኩረትለገጠርቤተክርስቲያን #የጎፎሬበአታለማርያም #ተዋህዶ #የድጋፍጥሪ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments