7 months ago
"ጽዮናዊነት ለሰብአዊነት ስጋት ነው" — የፓኪስታን መከላከያ ሚኒስትር
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ውጥረት በታላላቅ የእስያ ኃይሎች ዘንድ ከፍተኛ ስጋትን መፍጠሩን ቀጥሏል። የፓኪስታን መከላከያ ሚኒስትር ካዋጃ አሲፍ በሰጡት መግለጫ፣ የጽዮናውያን ርዕዮተ ዓለም ለአለም አቀፍ አለመረጋጋት እና ለሰብአዊነት ቀጥተኛ ስጋት መሆኑን በጽኑ አስታውቀዋል።
የፓኪስታን ስጋት እና ማስጠንቀቂያ
መከላከያ ሚኒስትሩ በኢራን ላይ እየተካሄደ ያለው ግጭት "ተገዶ የተጫነ" መሆኑን በመጥቀስ፣ ጦርነቱ ቀጣይነት ካለው የፓኪስታንን ደህንነት አደጋ ላይ እንደሚጥል አስገንዝበዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም፦
* እስራኤል በፍልስጤም ምድር ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ ለደረሰው ጥፋት ሁሉ የጽዮናውያን ርዕዮተ ዓለም ተጠያቂ እንደሆነ።
* ፓኪስታን ያላትን የኒውክሌር አቅም እንደ ማንኛውም የውጭ ስጋት መከላከያ "ጋሻ" እንደምትጠቀምበት በድጋሚ አረጋግጠዋል።
የቤጂንግ ዲፕሎማሲያዊ ጥሪ
በሌላ በኩል፣ ቻይና በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ ውጥረቱ በንግግር እንዲፈታ ግፊት እያደረገች ትገኛለች። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የምትፈጽመው ጥቃት የአለም አቀፍ ግንኙነት መርሆችን የሚጥስ መሆኑን ተችተዋል።
ቤጂንግ ኢራን የኒውክሌር ኃይልን ለሰላማዊ ዓላማ የመጠቀም ህጋዊ መብት እንዳላት በማመን፣ ጉዳዩ ወደ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ የድርድር ጠረጴዛ መመለስ እንዳለበት ጥሪዋን አቅርባለች።
ማጠቃለያ፦ የፓኪስታን ጠንካራ ወቀሳ እና የቻይና የዲፕሎማሲ ጥሪ፣ በቀጣናው ያለው ሁኔታ ከቀጥታ ጦርነት ባለፈ ወደ ሰፊ የርዕዮተ ዓለም እና የኃይል አሰላለፍ ፍልሚያ እየተቀየረ መሆኑን ያሳያል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #bisratfm #ፓኪስታን #ኢራን #ቻይና #ጽዮናዊነት #የአለም_ዜና #ጂኦፖለቲካ

1 year ago
የሁለቱ ኮርያዎች የ ሞንታርቦ ጦርነት ማክተሙ ተሰማ !
ታላቋን የኮርያ ምድር ከሁለት ከከፈለዉ እ.ኤ.አ. ከ1950-53 የኮሪያ ጦርነት በኋላ በዛቻና በፕሮፓጋንዳ ታጅበዉ በቴክኒካዊ ጦርነት ውስጥ የቆዩት ሁለቱ ኮሪያዎች ውጥረቱን ለማርገብ እየሰሩ መሆኑ ተነገረ ።
ፒዮንግያንግ ከሳምንት በፊት ከሰሜን ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል በሚል ለረጀም አመታት በድንበር አካባቢ ተገጥመዉ የነበሩ የፕሮፓጋንዳ ስፓከሮችን ማንሳቷን ተከትሎ ሲኦልም ተመሳሳይ እርምጃ በመዉሰድ ድምጽ ማጉያዎቿን ከድንበር አካባቢ እያነሳች እንደሚገኝ ዘጋርዲያን ዘግቧል ።
ወግ አጥባቂው ዩን ሱክ ዮልን በመተካት ፕሬዝዳንት ሊ ጄ ሚዩንግ በሰኔ ወር ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል መቀራረብና ሰላማዊ አካሄድ እየታየባቸው ይገኛል ። ያለዉ ዘገባው
የደቡብ ኮሪያ ጦር ባገኘሁት መረጃ መሰረት ሰሜን ኮሪያ በደቡብ ላይ ያነጣጠሩ አንዳንድ የፕሮፓጋንዳ ድምጽ ማጉያዎችን በድንበር አካባቢ አንዳንድ ክፍሎች እያፈረሰች ሲሆን ደቡብ ኮሪያም ውጥረቱን ለማርገብ ተመሳሳይ እርምጃ እየወሰደች ነዉ ። ብሏል
ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ ያወጣዉ የደቡብ ኮሪያ የጋራ መኮንኖች ሰሜን ኮሪያውያን ተናጋሪዎችን እያነሱ ያሉባቸውን ቦታዎች ይፋ ያላደረጉ ሲሆን የማፍረስ ሂደቱ በሁሉም ወገን በድንበር አካባቢዎች እየተካሄደ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
" በደቡብ ኮሪያ ላይ ለፕሮፓጋንዳ ተገጥመዉ የነበሩ ድምጽ ማጉያዎችን ከቅዳሜ ማለዳ ጀምሮ በግንባር ቀደምት አካባቢዎች የተወሰኑት ተነስተዋል " ሲል ወታደራዊው ቅዳሜ ለጋዜጠኞች በላከው መግለጫ ተናግሯል።
ከሳምንት በፊት ደቡብ ኮሪያ የገጠመቻቸዉና ከ20 ኪሎ ሜትር በላይ (12.4 ማይል) ወደ ሰሜን ኮሪያ እንደሚጓዝ የሚነገርላቸውን የአለም ዜና እና ስለዲሞክራሲያዊ እና የካፒታሊስት ማህበረሰብ መረጃ ከኬ-ፖፕ ሙዚቃ ጋር በማቀናጀት የምትለቅበትን ስፒከር ያነሳች ሲሆን ከቅዳሜ ጀምሮ ደግሞ ምላሽ ለመስጠት በሚል የሰሜን ኮሪያም በኩል የሚያናድዱ እንስሳትን እና የጎንጎችን ጩኸት ጨምሮ የሚያናድድ ድምጾችን ወደ ደቡባዊው ስታስላላልፍበት የቆየችውን ማንሳቷ ነዉ የተነገረው ።
የደቡብ ኮሪያ የቀድሞ ወግ አጥባቂ መንግስትና የሰሜን ኮርያ ሁለንታዊ መሪ ኪም ጆንግ-ኡ እርስ በእርስ በቆሻሻ የተሞሉ ፊኛዎችን የድምጽ ፕሮፓጋንዳዎች እርስ በእርስ ትንኮሳዎች የቆዩ ሲሆን ፕሬዝዳንት ሊ ከፒዮንግያንግ ከመጡ በኋላ ግን ግንኙነት ለማሻሻል እየሞከሩ ይገኛል ።
ሊ ከሰሜን ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል ተጨማሪ እርምጃዎችን ወስደዋል ፣የሲቪክ ቡድኖች ሰሜንን የሚተቹ በራሪ ወረቀቶችን እንዲያቆሙ እና በሚቀጥሉት ሳምንታት ከዩኤስ ጋር ይደረግ የነበረዉን" የኡልቺ የነፃነት ጋሻ "የተሰኘ ዓመታዊ የጋራ ወታደራዊ ልምምዶችን አስቁመዋል።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

Comments