1 month ago
ለ17 ዓመታት የተጓተተው፣
መገጭ የመስኖ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት ለመስጠት ተቃረበ ተብሏል
#ethiopia | በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ዙሪያ የሚገነባው የመገጭ የመስኖ ግድብ ግንባታ 94 በመቶ መድረሱን የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ገልጿል።
ይህ ግድብ በአጠቃላይ 33 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን ከ9.4 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የዋና ግድብ ሙሌት ውስጥ 8.25 ሚሊዮኑ መጠናቀቁንና ቀሪው 1.15 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የውሃ ሙሌት በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተመልክቷል።
በ2.4 ቢሊየን ብር ወጪ በ2001 ዓ.ም የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት በተለያዩ ምክንያቶች ሳቢያ ላለፉት 17 ዓመታት ተጓትቶ ቆይቷል።
በአሁኑ ወቅት የግድቡ ትርፍ ውሃ ማስወጫ፣ የመስኖ ውሃ መቆጣጠሪያ ሲቪል ሥራ፣ የመስኖ ውሃ ማስወጫ መጠንና ሃይል መቆጣጠሪያ እንዲሁም ለጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚሆን ውሃ ማስወጫ ቱቦ እና መቆጣጠሪያ ገጠማ ሥራዎች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸው ተረጋግጧል።
#መገጭግድብ #መስኖ #ጎንደር #ልማት #የመስኖእናቆላማአካባቢሚኒስቴር #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments