8 months ago
🩸 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መንፈሳዊ ጉዞ፡ ዐቢይ ጾም ከሰማያት መውረድ እስከ ቀራንዮ ደም
👉ከአንድ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ለፊደል ፖስት የተላከ
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ፣ ዐቢይ ጾም ዝም ብሎ የምግብ ለውጥ የሚደረግበት ወቅት አይደለም። ይህ ጾም የሰው ልጅ በኃጢአት ምክንያት ከፈጣሪው ተለይቶ በነበረበት የጨለማ ዘመን፣ አምላክ የሰውን ልጅ ፍለጋ ያደረገውን የፍቅር ጉዞ የምናስብበት የታሪክ መዝገብ ነው።
ከገነት የተሰደደውን አዳም እንባ ለማበስ፣ የአለማት ጌታ ዙፋኑን ትቶ በምድር የተንከራተተበት፣ የተራበበትና በመጨረሻም ደሙን ያፈሰሰበት ምስጢር በዚህ ጾም ውስጥ ተቀብሯል።
፩. ዘወረደ፡ ፍቅር አምላክን ከዙፋኑ አወረደው
ጉዞው የሚጀምረው "ዘወረደ" በሚለው ሳምንት ነው። ትርጉሙ "የወረደ" ማለት ነው። የሰማይና የምድር ጌታ፣ መላእክት በፊቱ የሚንቀጠቀጡለት አምላክ፣ አዳምን ፍለጋ ወደ ምድር ወረደ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ይህንን ሲገልጽ፣ አምላክ ክብሩን እንደ መጋረጃ ገፎ፣ ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሶ መምጣቱን ይነግረናል። የነፍሳችንን ስደት ሊያቆም እርሱ ስደተኛ ሆነ። አምላክ ለእኔ ሲል ተራ ሰው ሆኖ በበረት ተኛ!
፪. ቅድስት፡ የነፍስ መታጠቢያ
ሁለተኛው ሳምንት "ቅድስት" ነው። ጌታችን በገዳመ ቆሮንቶስ 40 ቀንና 40 ሌሊት የጾመውን ጾም እናስባለን። ዲያብሎስ በረቂቅ ተንኮሉ ቀረበው። አዳምን በምግብ ጥቂት ፍሬ ጥሎት ነበር፤ ጌታችን ግን በታላቅ ጾም ድል አደረገው። ጌታችን ስለ እኛ ተራበ፤ ስለ እኛ ተጠማ። እኛ ግን ዛሬም በሥጋ ፍላጎት ተሸንፈን ለፈጣሪያችን ጀርባችንን ሰጥተናል። ይህ ሳምንት "ጌታ ሆይ እንደ ቸርነትህ ማረኝ" ብለን የምንጮኽበት የቅድስና ወቅት ነው።
፫. ምኵራብ፡ የፈረሰውን መቅደስ አዳሽ
በሦስተኛው ሳምንት ጌታችን ወደ ምኵራብ (መቅደስ) ገባ። ቤቱ የንግድ ቦታ ሆኖ አገኘው። እየገፈተረ አስወጣቸው "ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል" ብሎ አስወጣቸው። ዛሬም ጌታችን ወደ እኛ ልብ መቅደስ ሲመጣ፣ ልባችን በቂም፣ በበቀልና በስግብግብነት ተሞልቶ ያገኘዋል። በመገፍተር ሳይሆን በፍቅሩ ሊገሥጸን ይሻል።
፬. መጻጒዕ፡ የብቸኞች መጠጊያ
ለ38 ዓመታት በአልጋ ላይ ተኝቶ "የሚረዳኝ ሰው የለኝም" እያለ ሲያለቅስ የነበረውን መጻጒዕን እናስባለን። ዓለም ሁሉ ስትረሳው፣ አምላክ ግን አልረሳውም። ዛሬም በሕመም የምትማቅቁ፣ በብቸኝነት የምትቆስሉ ነፍሳት ሆይ—አምላካችሁ አልረሳችሁም። "አልጋህን ተሸክመህ ሂድ" የሚለው ቃል ዛሬም ለደከመች ነፍሳችን ተስፋ ነው።
፭. ደብረ ዘይት፡ የተስፋ ብርሃን
የጾሙ እኩሌታ ላይ ስንደርስ ስለ ዳግም ምጽአቱ እናስባለን። ጌታችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ዓለም እንደምታልፍና እርሱ በክብር እንደሚመጣ ነገረን። ይህ ሳምንት የአዳምን ልጆች ናፍቆት ይጭራል። አማኞች በመልካም ሥራ እንዲጸኑና ልባቸውን እንዲያዘጋጁ የሚያሳስብ የንቃት ወቅት ነው።
፮. ገብር ኄር፦ ታማኝ አገልጋይ በመሆን በመክሊት (በጸጋ) ስለ ማትረፍ የሚማርበት።
፯. ኒቆዲሞስ፦ ስለ ዳግም ልደት (ጥምቀት) እና ስለ እውነት ፈላጊነት የሚነገርበት።
፰. ሆሣዕና፦ ጌታችን በታላቅ ምስጋና ወደ ኢየሩሳሌም የገባበትና የሕማማት መጀመሪያ።
🕯️ ሰሙነ ሕማማት፡ የአምላክ ስቃይ ጥልቀት
ከሆሣዕና ማግስት ጀምሮ የምንገባበት ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ይባላል። እዚህ ጋር ነው እንባ የሚፈሰው። እዚህ ጋር ነው የአምላክ ፍቅር ጥግ የሚታየው። ይህ ሳምንት "ሳምንተ ተገሥጾ" ይባላል።
ሰኞ (አንጽሖተ መቅደስ)
ጌታችን ከቢታንያ ሲመጣ ተራበ። ፍሬ የሌላትን በለስ ረገማት። በለስ የአዳም ምሳሌ ናት—በቅጠል (በተስፋ) የተሸፈነች ግን ፍሬ (ምግባር) የሌላት። "ከዛሬ ጀምሮ ለዘላለም ፍሬ አይገኝብሽ" ሲላት፣ እኛም በሕይወታችን ፍሬ እንዳይጠፋብን እያለቀስን እንድንጸልይ ያስተምረናል። በዚያው ዕለት በመቅደስ ይሸጡ የነበሩትን ገልብጧል።
ማክሰኞ (የጥያቄ ቀን)
ጌታችን በመቅደስ ሲያስተምር የአይሁድ ካህናትና ጻፎች መጡ። "እነዚህን በምን ሥልጣን ታደርጋለህ?" ብለው ጠየቁት። ሊያጠምዱት ፈለጉ። ጌታችን ግን በጥበቡ መለሰላቸው። ስለ ዓለም ፍጻሜም በሰፊው አስተማረ። ይህ ቀን "የጥያቄ ቀን" ይባላል፤ እኛም በሕሊናችን ብዙ ጥያቄዎችን ይዘን ወደ ጌታ የምንቀርብበት ቀን ነው።
ረቡዕ (የምክር ቀን / ምክረ አይሁድ)
ይህ ቀን እጅግ የሚያሳዝን ነው። ይሁዳ ጌታውን ለመሸጥ ከአይሁድ ጋር የተማከረበት ቀን ነው። "ምን ትሰጡኛላችሁ? እኔ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ" አለ። ለሦስት ዓመታት አብሮት የበላ፣ ተአምራቱን ያየ ደቀ መዝሙር፣ ጌታውን በሰላሳ ብር ሸጠው። ጌታችን ግን ይህን ሁሉ እያወቀ ይሁዳን ይወደው ነበር። "ይሁዳ ሆይ በመሳም አሳልፈህ ትሰጠኛለህን?" የሚለው ድምፅ ዛሬም የከዳነውን ጌታ ስናስብ ልብ ይሰብራል።
ጸሎተ ሐሙስ (የምስጢር ሐሙስ)
ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ። የዓለማት ንጉሥ ሆኖ ሳለ፣ የባሪያውን እግር ሲያጥብ እስቲ በዓይነ ሕሊናችሁ ተመልከቱት። ከዚያም "ይህ ሥጋዬ ነው... ይህ ደሜ ነው" ብሎ ምስጢረ ቁርባንን ሰጠን። በዚያች ሌሊት ወደ ጌቴሴማኒ ሄዶ ጸለየ። ጭንቀቱ በረታ፤ "ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ አዘነች" አለ። ላቡ እንደ ደም ጠብታ ወደ ምድር ፈሰሰ። ጌታችን ስለ እኛ ፍዳ ተጨነቀ።
🩸 ስቅለተ ዓርብ፡ የቀራንዮው ታላቅ ስቃይ
ይህ ቀን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እጅግ አስለቃሹ ቀን ነው። ፈጣሪ በፍጥረቱ እጅ የተገረፈበት ቀን!
ፍርዱ፦ ጌታን በፍርድ አደባባይ አቆሙት። ፊቱን ተተፋበት—ያ መላእክት ሊያዩት የሚመኙትን ቅዱስ ፊት! በጅራፍ ተገረፈ። ጅራፉ አጥንት ድረስ የሚሰነጥቅ ነበር። ሰውነቱ እንደ ታረሰ መሬት ተተለተለ። ደሙ እንደ ጎርፍ ፈሰሰ።
የእሾህ አክሊል፦ የእሾህ አክሊል ሰርተው በራሱ ላይ ደፉበት። በዘንግ መቱት፤ እሾሁ ወደ አእምሮው ሰረጸ።
መንገደ ቀራንዮ፦ ያንን ከባድ መስቀል ተሸክሞ ወደ ቀራንዮ እንዲወጣ ተገደደ። ደክሞት ሲወድቅ በጅራፍ ይገረፋል፤ ሲነሣ ይገፋታል። በመንገድ ላይ እናቱ ድንግል ማርያም አየችው። ልጇ ሲሰቃይ፣ ልብሷ በደሙ ሲጨማለቅ ስታይ "ልጄ ሆይ ምን አደረጉህ?" እያለች አለቀሰች። ያ የእናትና የልጅ መገናኘት ዓለትን የሚያቀልጥ ነበር።
ስቅለቱ፦ በቀራንዮ መስቀል ላይ ዘረጉት። እጆቹንና እግሮቹን በትላልቅ ሚስማሮች ወጉት። መዶሻው ሲመታ ድምፁ በሰማይና በምድር ተሰማ። በመስቀል ላይ ሆኖ ሳለ "ተጠማሁ" አለ። የውኃ ምንጭ የሆነው አምላክ፣ ስለ እኛ ሲል ተጠማ። "አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" ብሎ ለገዳዮቹ ጸለየ።
በመጨረሻም "ተፈጸመ" ብሎ ነፍሱን ሰጠ። ያኔ ፀሐይ ጨለመች፣ ጨረቃ ደም መሰለች፣ ምድር በታላቅ ድንጋጤ ተናወጠች። የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀደደ። ፈጣሪ ለፍጥረቱ ሲል ሞተ!
🎐 ቀዳም ስዑር እና ትንሣኤ
ቅዳሜ ጌታ በመቃብር ዋለ። መቃብሩ ታተመ። ነገር ግን ሞት ሊይዘው አልቻለም። እሁድ መንፈቅ ሌሊት፣ መቃብሩን ከፍቶ ተነሣ! ሞትን ድል አደረገው! አዳምን ከሲኦል አውጥቶ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው። የዐቢይ ጾም ለቅሶ በደስታ፣ በረከቱ በትንሣኤ ብርሃን ተተካ።
ማጠቃለያ፦
ይህ የ55 ቀናት ጉዞ፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች የአምላክን ፍቅር የሚረዱበት ነው። ይህ ታሪክ ዛሬም በልባችን ውስጥ ሊነገር ይገባል።
አምላካችን እግዚአብሔር ጾሙን የበረከትና የፈውስ ያድርግልን። ትንሣኤውን ለማየት ያብቃን።

እንኳን ለአብይ ጾም አደረሳችሁ🙏
ጣራዉ በሳር ግድግዳው በላስቲክ የተሸፈነው ቤተክርስቲያን‼️
+++++++++++++++++++++++++++++++++++
👇👇👇
ዘወረደ - ከሰማየ ሰማያት የወረደው
የሰው ልጅ ፍቅር አገብሮት ከሰማየ ሰማያት የወረደውን ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደውን፣ ከዓለም በፊት ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የነበረ ዘመን የማይቆጠርለት እግዚአብሔር ወልድ፣ በኋላም በዘመነ ስጋዌ ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ሊያድነን መውረዱን ለመዘከር የአቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት “ዘወረደ” ይባላል። ጌታችን አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት በገዳመ ቆሮንቶስ ጾመ ከማለት አስቀድሞ ሰው ሆኖ መገለጡን ማስረዳት ይቀድማልና “ዘወረደ - ከሰማየ ሰማያት የወረደው” ብንልም እርሱ ግን በሁሉ ምሉዕ ነው፡፡ አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ነው። ምልዓቱን ሳይለቅ በሰው አካል ተወስኖ ታይቷልና፡፡
በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን የአንጎቫ ጌቴሴማኒ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ደባርቅ ወረዳ ሰጊ ቀበሌ ይገኛል። ነገር ግን ቤተክርስቲያኑ በፎቶው እንደሚታየዉ በገንዘብ ችግር ላዩ በሳር ግድግዳዉ በላስቲክ የተሸፈነ ነዉና በመላዉ አለም ያላችሁ ወገኖቻችን ጾሙን የምንችለዉን በማገዝ ቤተክርስቲያናችንን እንስራ በማለት አባቶች ጥሪ አቅርበዋልና የበረከቱ ተሳታፊ ሁኑ።
ድጋፍ ለማድረግ የገዳሙ አካዉንት
👇👇👇
ንግድ ባንክ- 1000727191597
አቢሲኒያ ባንክ- 241335836
ስልክ- 0918259827 / 0918055897 ወይም 0957827972
ለብዙዎች እንዲዳረስ እባካችሁ ሼር አድርጉት‼️

ይህም ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ የሚታወስበት፣ የሚነገርበት ነው፡፡ አምላካችን ሰው ከሆነ በኋላ መጣ፤ ሔደ፤ ወረደ፤ ዐረገ የሚሉ ቃላት ይስማሙታል፡፡ ስለዚህ “ወረደ” እግዚአብሔር ሰው ሆኖ መገለጡን፤ “ዐረገ” ደግሞ የሰውነቱን ሥራ ፈጽሞ ማረጉን ያሳያል፡፡ ዐረገ ስንልም መለኮት የተዋሀደው ስጋ የማዳኑን ስራ ፈጽሞ ዐረገ ማለታችን ነው እንጂ ሲወርድ ሰማይን ለቆ ነበርና ወደ ቀደመ ቦታው ተመለሰ እያልን አይደለም፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ በዓለሙ ሁሉ ምሉዕ ነውና፡፡
ዘወረደ አምላክ ወረደ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፣ በፍጹም ተዋሕዶ ሰው ሆነ ማለታችን ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ. 5÷10 “ጠላቶቹ ሳለን እግዚአብሔር በልጁ ሞት ታረቀን” እንዳለ ማጥፋት ሲችል፣ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ አዳነን፡፡ በዚህም ትህትናን ፍቅርን አስተማረን፡፡
ገዳማውያን ይህን የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ዘወትር እያሰቡ ያመሰግኑታል፡፡ ይልቁንም ዓለምን ትተው የወጡት የስጋ ፈቃድ ምድራዊው ኑሮ ከምስጋና፣ ከጸሎትና ከስግደት እንዳያዘናጋቸው ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ለመስጠት ነውና ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና ከበረከታቸው እንሳተፋለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

እንኳን ለ2018 ዓ.ም የዐቢይ ጾም (ሁዳዴ) በሰላም አደረሳችሁ!
"ዘወረደ እምላእሉ፤ አይሁድ ሰቀሉ፤
እግዚአ ኩሉ ዘየሐዩ በቃሉ" — ቅዱስ ያሬድ
ትርጉም፦
ከላይ የወረደውን፣ በቃሉ ድውያንን የሚፈውሰውን የሁሉ ጌታ አይሁድ ሰቀሉት።
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት "ዘወረደ" ይባላል። ይህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ካለው ፍቅር የተነሳ ከሰማይ ሰማያት መውረዱን የምናስብበት ሳምንት ነው። ጾሙ የሰላም፣ የፍቅርና የበረከት ይሁንልን።
መንፈሳዊ ግጥሙንና ዜማውን በምስል የታጀበውን ይህንን ሊንክ በመጫን ይከታተሉ፦
👉 https://youtu.be/oZm360Cb_...
መልካም የጾም ጊዜ!
#ዐቢይጾም #ሁዳዴ #ቅዱስያሬድ #ዘወረደ #ኦርቶዶክስ #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Sponsored by
Surafel
Comments