14 days ago
መስከረም እና ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) መስከረም በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ መጀመሪያ ወር ብቻ አይደለም፤ የሀገሪቱ ተፈጥሯዊ መታደስ፣ የህዝቦች አንድነት እና የመንፈሳዊ ተስፋ ታላቅ ምልክት እንጂ።
የዓመቱ አስቸጋሪ እና ዝናባማው የክረምት ወቅት አብቅቶ፣ ምድር በለመለመ መስክ የምታጌጥበት ይህ ወር ለኢትዮጵያውያን ልዩ ስሜት ይፈጥራል።
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በጋራ የሚታደሙባቸው ታላላቅ ሀገራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት የሚበዙበት ወር ነው - መስከረም፡፡
አርሶ አደሮች የክረምቱን ድካም አልፈው የልፋታቸውን ውጤት የሚያዩበት እና በምርት የሚንበሸበሹትን የመኸር ወቅት በተስፋ የሚጠባበቁበት ወር ነው።
ልክ እንደ ተፈጥሮው ኡደት ሁሉ፣ የኢትዮጵያ የትምህርት ዓመት የሚጀምረው በመስከረም ወር ነው። በመስከረም ተማሪዎች የትምህርት መሳሪያዎቻቸውን አሟልተው፣ በአዲስ የደንብ ልብስ ደምቀው የናፈቁ ጓደኞቻቸውን የሚያገኙበትና አዲስ የትምህርት ምዕራፍ የሚተልሙበት ነው፡፡
መስከረም ሁሌም ቢሆን ከጭጋግ በኋላ ብርሃን፣ ከችግር በኋላ ሲሳይ እንደሚመጣ ለኢትዮጵያውያን በተግባር የሚያስተምር የዘመን መባቻ ነው።
በኢትዮጵያ ምድር መስከረም በተለያዩ የአደባባይ በዓላት የሚታጀብ ወር ነው፡፡
መስከረም 16 ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል መገኘትን የሚዘክረው የደመራ ማብራት ስነ-ስርዓት በደመቀ ሁኔታ ይከበራል። ይህ በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰስ የዓለም ቅርስ ሆኖ ተመዝግቧል።
በኦሮሞ ባህል የመስከረም ወር ማብቂያ ላይ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል፣ የክረምቱን ጨለማ እና ጎርፍ በማለፍ ለብርሃን እና ለምለም ወቅት ላደረሰ ፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት ታላቅ ህዝባዊ እና ባህላዊ በዓል ነው።
መስከረም ሲጠባ፣ አደይ ሲፈነዳ፣
እንኳን ሰው ዘመዱን፣ ይጠይቃል ባዳ፡፡
የተባለለት መስከረም የኢትዮጵያን የብዝሃነት ስብጥር በጉልህ የሚያሳይ መስኮት ነው። ከእንቁጣጣሽ፣ የመስቀል በዓል እና ከኢሬቻ በዓል ባሻገር፤ እንደ ያሆዴ፣ ማሽቃሮ ፤ ዮ ማስቃላ ያሉ በርካታ የብሔር ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ እና የምስጋና በዓላት በአንድነት የሚፈኩበት ወቅት ነው።
እነዚህ ሁሉ በዓላት የተጣላ የሚታረቅበትን፣ የራቀ የሚቀራረብበትን፣ ይቅርታን እና ለፈጣሪ የሚቀርብን ምስጋናን የሚያሰረጹ በዓላት ናቸው።
ስለ ውቡ መስከረም የተለያዩ ገጣሚያን ብዕራቸውን አንስተው ከትበዋል፡፡
ደራሲና ባለቅኔ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን መስከረም የዚች ሀገር ታሪክና ተፈጥሮ ተጋብተው የሚያበሩበት የዕንቁጣጣሽ አክሊል ነው።” ብለውታል። ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያሙሌ) ደስ ይላል መስከረም
በሚል ግጥሙ፡-
ደስ ይላል መስከረም ! ! !
እንደቢራ ቢሮ አበባ ለአበባ ዐደይ እንቡር እንቡር
በፍቅር ለመክረም -
ደስ ይላል መስከረም ! ! !
ሲል ተቀኝቷል፡፡
በአጠቃላይ መስከረም ወር ኢትዮጵያ እውነተኛ የተፈጥሮ ውበቷን እና ድምቀቷን ለዓለም የምታሳይበት የህይወት፣ የሰላም እና የብሩህ ተስፋ ማህተም ነው፡፡
በትዕግስት ግዛቸው

18 days ago
ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!
-የግዮን እንግዳ አምዳችን :-
‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ ነው›› ክቡር ገና
‹‹የኢትዮጵያ ትልቁ ሀብት ሕዝቧ ነው››
ዶ/ር ንጉሡ ለገሠ
"ልዩነታችንን እነደ ጠላትነት ሳይሆን አብሮ ለመስራት የሚያስችል ዕድል አድርገን ማየት አለብን"
አለባቸውደሳለኝ
‹‹ሚዲያ እንደ ምግብና ኦክስጅን የሕይወት አካል ነው››ኤልያስ አወቀ
‹‹ግዮን›› ጥሪዋን ታቀርባለች!
የኢትዮጵያ ቱሪዝምና እና ያሳለፍነው የኢትዮጵያውያን ዓመት ሄኖክ ስዩም
የግዮን መጽሔት የ2018 ዓ.ም እንግዶች
የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት፡-ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊ፤ ትውፊታዊ እና ሳይንሳዊ አንድምታው!! ዲ/ን ተረፈ ወርቁ
በ፳፻፲፰ ዓ.ም ያጣናቸው ታላላቅ ሰብዕናዎች!
ሙዚቃ እና ዘመን ሠሎሞን ለማ ገመቹ
የእንቁጣጣሽ ትዝታ
በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር
የኢትዮ ቴሌኮም :- ከተሞክሮ መላቅ እስከ አህጉራዊ ዲጂታል መሪነት
በእርጋታ መፍጠን ይቻላል
ከዕዝራ እጅጉ
ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ እነዚህንና ሌሎች መጣጥፎችን ይዛ ገበያ ላይ ትገኛለች።

19 days ago
የመስከረም ጸጋዎች፡ ከበዓላት ድምቀት እስከ ቱሪዝም ትሩፋት
(የዕለቱ መልዕክት)
********************
የመስከረም ወር በኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ፣ የክረምት መውጫና የምድር በአደይ አበባ በነፃነት ማጌጫ ብቻ ሳይሆን የአገራችን የቱሪዝም ዘርፍ ዋነኛ ሞተር የሚነሳበት ወሳኝ ወቅት ነው።
ይህ ወር እንደ እንቁጣጣሽ ካለው ብሔራዊ የአንድነትና የተስፋ በዓል ጀምሮ በዩኔስኮ በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የመስቀል ደመራ በዓል እንዲሁም የክረምት ጨለማ አልፎ ወደ ብርሃን መሸጋገር የሚበሰርበት የኦሮሞ ሕዝብ የምስጋና በዓል የሆነውን ኢሬቻን በሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ አርሰዲ በድምቀት የምናስተናግድበት ልዩ ወር ነው።
ከእነዚህም ባሻገር እንደ ጊፋታ፣ ዮሆ እና ሌሎችም የብሔር ብሔረሰቦች ደማቅ የዘመን መለወጫ በዓላት የሚከበሩበት በመሆኑ፣ መስከረም ወር የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ቱሪስቶች እንዲሁም ዳያስፖራው በብዛት ወደ ኢትዮጵያ የሚጎርፉበት የቱሪዝም ማዕከል ነው።
ከበዓላቱ ድምቀት በተጨማሪ የክረምቱ ከባድ ዝናብ አክትሞ ወንዞችና ፏፏቴዎች ሞልተው የሚፈሱበት ማራኪ የተፈጥሮ አየር ንብረት ኢትዮጵያን ለሥነ-ምህዳር ቱሪዝም ልዩ ተመራጭ ያደርጋታል።
ይህን የተፈጥሮ፣ የታሪክና የባህል ፀጋ ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለመቀየር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተተገበሩት ስር ነቀል መዋቅራዊና ተቋማዊ ለውጦች አስደናቂ ፍሬ እያፈሩ ይገኛሉ።
ለረጅም ዓመታት ሳይሻሻል የቆየው የቱሪዝም ፖሊሲ በአዲስ መልክ መዋቀሩ እንዲሁም የኮንፈረንስ ቱሪዝም ስትራቴጂዎችና የኢ-ቪዛ ዲጂታል አሠራሮች መዘርጋታቸው የውጭ ቱሪስቶችን ፍሰት ከወትሮው በተለየ እጅግ ከፍተኛ ደረጃ አድርሶታል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ እንደ “ገበታ ለሸገር”፣ “ገበታ ለሀገር” እና “ገበታ ለትውልድ” ባሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የተገነቡት አዳዲስ ፓርኮች፣ የኢኮ ሪዞርቶች፣ ሎጆችና ታሪካዊ ስፍራዎች ማራኪ የቱሪስት መዳረሻዎች በመሆን ሀገራዊ አቅማችንን አጎልብተውታል።
በአዲስ አበባ ከተማ የተተገበረው የኮሪደር ልማትም የዋና ከተማዋን ውበትና ምቾት በመጨመር የቱሪስት መስህብነቷን ይበልጥ አጉልቶታል።
እነዚህ የተቀናጁ ጥረቶች የሀገራችንን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከማሳደግ ባለፈ፣ በሆቴል፣ በመጓጓዣና በአስጎብኚነት ዘርፍ ለበርካታ ዜጎች አዳዲስና ዘላቂ የሥራ ዕድሎችን ፈጥረዋል።
የዘርፉ መነቃቃት ኢትዮጵያ በዓለም ቱሪዝም ድርጅት (UNWTO) ልዩ ዕውቅናና ሽልማት እንድታገኝ ያደረገ ሲሆን፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨማሪ ቅርሶችን በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት መዝገብ ላይ በማስመዝገብ የዓለም ክብረ-ወሰን እንድትጨብጥም አስችሏታል።
አሁን ላይ የመደመር መንግሥት የውጭ ቱሪስት ፍሰቱን ይበልጥ ለማሳደግ ግዙፍ ብሔራዊ ራዕይ ሰንቆ እየሠራ ይገኛል። ይህን ዕቅድ ከዳር ለማድረስ አዳዲስ የኢኮ-ቱሪዝም መዳረሻዎችን ማስፋፋት፣ ቅርሶችን በሳይንሳዊ መንገድ መጠገን፣ የመዳረሻዎችን መሠረተ ልማት ማሟላት እንዲሁም ዘመናዊ የዲጂታል ቴክኖሎጂንና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም አገልግሎቱን ይበልጥ ማዘመን ቀዳሚ ስትራቴጂ ሆኖ ይቀጥላል።
በመሆኑም የቱሪዝም ወር የሆነውን መስከረምን በብቃት በመጠቀም፣ ሀገራችን የጀመረችውን የተስፋ ጉዞ ወደ ላቀ የኢኮኖሚና የገፅታ ግንባታ ስኬት ለማሸጋገር ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

25 days ago
(ዘ-ሐበሻ ሕይወት| የአምናዋ ሚስ ወርልድ አፍሪካ ሐሤት ደረጀ የአዲስ ዓመት መልዕክቷ እንዲህ ይነበባል፦ "በራሳችን የዘመን ቀመር አዲስ ምዕራፍን ዳግም መጀመር ልዩ የሆነ የውበት ስሜት አለው። አዲሱን ዓመት በደስታ ስንቀበል፣ ለምንወዳት ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለኝ ትልቅ ምኞት፤ ሰላም፣ እውነተኛ ፈውስ እና በአንድነት የምንፈነድቅባቸው በርካታ ምክንያቶች እንዲበዙላት ነው።
"አዲሱ 2019 ዓ.ም ሩህሩህ ቀናትን፣ ለወጣቶቻችን ሰፊ ዕድሎችን፣ እንዲሁም እያንዳንዱን ቤት የሚያንኳኳ ብሩህ ተስፋን ይዞልን ይምጣ።
ይህንን መልእክቴን ለምታነቡት ደግሞ፤ ለሰዎች የምታካፍሉት ጣፋጭ የምሥራች፣ አብረዋችሁ ደስታችሁን የሚያከብሩ ቅን ሰዎች፣ እንዲሁም ለረጅም ጊዜ ስታልሙት የነበረውን ህልም እውን ለማድረግ የሚያስችል ወኔና ድፍረት ይስጣችሁ። ቆም ብላችሁ፣ "አምላኬ ሆይ... ለዚህች ቀን እኮ ነበር ስጸልይ የነበረው" ብላችሁ በደስታ የምታመሰግኑባቸው ልዩ አጋጣሚዎች በዓመቱ ውስጥ ይብዙላችሁ።
ከብዙ ፍቅር ጋር፣ መልካም የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት!
መልካም አዲስ ዓመት! 🤍🌼 እንቁጣጣሽ!

መልካም አዲስ ዓመት።
በጎጆ የህሙማን ማረፊያ የበጎ ፍቃደኝነት ጉብኝት እንደቀጠለ ነው...
እንደተለመደው የአዲስ ዓመት የዘመን መለወጫን (የእንቁጣጣሽ) በዓልን በማስመልከት የዘወትር የማረፊያው ቤተሰብ ቤሩት(መሠረት) እና ቤተሰቦቿ የሙስሊም እና የክርስቲያን በጎችን በመግዛት በህሙማኑ ማረፊያ በመገኝት በዓሉን በማዘጋጀት፣ አቶ ፍቃዱ ጣፋ እና ቤተሰቦቹ 240 እንቁላል ለበዓሉ በማበርከት እንዲሁም ትጉ እና ባለቤቷ ለመቶ ሰው የሚሆን የሙስሊም እና የክርስቲያን ምግብ,በማቅረብ፣ የቡና ሴሬሞኒምውን በማዘጋጀት ከህሙማኑ ጋር በዓሉን በዚህ ሁኔታ አሳልፈዋል።
ቤሩት(መሠረት)ን እና ቤተሰቦቿን፣ ትጉ እና ባለቤቷን እንዲሁም አቶ ፍቃዱ ጣፋ እና ቤተሰቦቹን እያመሰገንን መላው የማረፊያው ቤተሰብን መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላቹ እንላለን።
የማረፊያው ተጠቃሚ ህሙማንን እንዲሁም ሌሎችም ወገኖች በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ባለንበት እንኑር እንላለን።

የቀድሞ ንጉሥ የልጅ ልጅ የአዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መልዕክት
#ethiopia | የዘውድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ልዑል ኤርሚያስ ሣህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከ፳፻፲፰ ዘመነ ማርቆስ ወደ ፳፻፲፱ ዘመነ ሉቃስ እንኳን በሰላም አሸጋገራችሁ በማለት የመልካም ምኞት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ልዑሉ በመልእክታቸው እንደገለጹት አዲስ ዓመት ሲባስ ያለፈውን የስኬትና የመማሪያ ጊዜያት እያሰቡ ፈጣሪን ማመስገንና የሚመጣውን ዘመን ደግሞ በተስፋና በጸሎት መቀበል የቆየ ባህላችን መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም የእንቁጣጣሽ በዓል ከንግሥተ ሳባ ዘመን ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የሀገራችን ልዩ ባህልና የኢትዮጵያዊነት ኩራት መሆኑን ያሳሰቡት ልዑል ኤርሚያስ በአዲሱ ዓመት ሀገራችንንና ሕዝባችንን ከጦርነት፣ ከወገን መከፋፈልና ከስደት ይታደግ ዘንድ ሰላምና አንድነትን ፈጣሪ እንዲሰጠን ጸሎት ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
አክለውም በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰፈነው የኑሮ ውድነትና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ምክንያት በጉዳት ላይ የሚገኙ ወገኖችን በቻሉት መጠን መርዳትና በሐሳብም ሆነ በጸሎት መደገፍ የሁላችንም ሰብአዊ ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

Sponsored by
Surafel
25 days ago
🔥 ዓባይ ቲቪ ዘንድሮ ምን አዲስ ነገር ይዞ መጣ?! 🔥
ዓባይ ቲቪ እና ንግሥተ ሳባ?! ይሄ ምንድነው! 😮
“እንቁ ለጣትሽ!” እያለ — ዓባይ ቲቪ ዘንድሮ ከወትሮው ለየት ባለ፣ አስደናቂ ዝግጅት መጥቷል! ንግሥተ ሳባን አፈታሪክ እና ታሪክ አሻግሮ እስከ ዓባይ ቲቪ ስቱዲዮ እንዴት አመጣት?! 💍✨
የዘንድሮ እንቁጣጣሽ በዓባይ ቲቪ — ምን ዓይነት አቀራረብ ነው! 👏
ከኢትዮጵያ የአዲስ ዓመት በዓል ድምቀት ጋር ተጣጥሞ የቀረበው ይህ ፕሮግራም፣ የቴሌቪዥን መስኮታችሁን ልዩ ውበት እንደሚያላብሰው አንዳች ጥርጥር የለውም።
አዲሱን ዓመት በልዩ ድምቀት እና በተለየ እይታ ለመቀበል — ዓባይ ቲቪን ይከታተሉ!
የፕሮግራሙ ሊንክ ኮሜንት ላይ ተቀምጧል

ንግሥተ ሳባ በዓባይ ቲቪ?! 😮💍
ይሄ ምን ዓይነት አስደናቂና ለየት ያለ አቀራረብ ነው! 👏
ዓባይ ቲቪ በዘንድሮው እንቁጣጣሽ “እንቁ ለጣትሽ!” በሚል ድንቅ ሀሳብ የንግሥተ ሳባን ታሪካዊ ግርማ ሞገስ ከዛሬው ዘመን ጋር አገናኝቶ ይዞልን መጥቷል። 👑
ንግሥተ ሳባ በዚህ ዘመን መጥታ በዓባይ ቲቪ ልዩ አቀባበል ስትደረግላት ማየት—ታሪክ፣ ባህልና ዘመናዊ መዝናኛ ተዋህደው ድንቅ ትዕይንት ፈጥረዋል።
ዘንድሮ ዓባይ ቲቪ በእውነት ለየት ብሎ መጥቷል! 🔥📺
እናንተስ ይህን ድንቅ የእንቁጣጣሽ ዝግጅት ተከታትላችሁታል? ኮሜንት ላይ ባለው ሊንክ አይታችሁ አስተያየታችሁን ላይ አጋሩኝ! 👇💬

☎️+971527866251
የዳንዩብ ግሩፕ መስራችና ሊቀመንበር፣ ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ቀዳሚ የሪል እስቴት አልሚዎች አንዱ የሆነውን ዳንዩብን የሚመሩት አቶ ሪዝዋን ሳጃን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለደንበኞችና ለአጋሮች የአዲስ ዓመት ሰላምታቸውን አቅርበዋል።
አዲሱ ዓመት ሰላም፣ ጤና፣ ደስታ፣ ብልጽግና እና ስኬት ይዞላችሁ ይምጣ። 🙏✨
እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት አደረሳችሁ! 🎉
— Brook Real Estate 🏙️🏡
#brookrealestate #danube #rizwansajan #መልካምአዲስዓመት #እንቁጣጣሽ #ኢትዮጵያ #ዱባይ #ሪልእስቴት #ethiopiannewyear
26 days ago
ከጎረቤት አልፎ ወደ ሀገር የዘለቀው የኢትዮጵያውያን የማጋራትና የደግነት እሴት
**************
መስከረም ሲጠባና አደይ አበባ የኮረብታዎችን ማዕረግ ለብሶ ሲያብብ፣ ህፃናት በውብ ባህላዊ አልባሳታቸው አምረው "አበባ አየሽ ወይ፣ ለምለም" እያሉ በየደጃፉ በእንቁጣጣሽ ዝማሬ አዲሱን መንፈስ ያበስራሉ።
አባወራዎች የሸማኔውን ጋቢ ተጎናጽፈው፣ እናቶች በባህል ቀሚስ ተውበው፣ መላው ቤተሰብ ማዕድ በጋራ ታድመው በዓሉን በደስታ ያደምቁታል።
አዲስ ዓመት በሀገራችን የዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን፤ ዘመድ ከዘመድ የሚጠያየቅበት፣ ያለው ለሌለው እጁን ዘርግቶ የሚያካፍልበት እና የደግነት እሴታችን የሚንጸባረቅበት ታላቅ ማኅበራዊ ሁነት ነው።
በኢትዮጵያውያን ባህል "ለብቻ መብላት" ነውር ተደርጎ ይታያል። ይህ የደግነት እሴት በተለይ በበዓላት ወቅት ከቤት አልፎ ወደ እምነት ተቋማትና የሕዝብ አደባባዮች ዘልቆ ይስተዋላል።
በየቤተእምነቱ ደጅ እና በየአደባባዩ አቅም የሌላቸውና ጧሪ አልባ ወገኖች እንዲሁም መንገደኞች በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ማዕድ ይላክላቸዋል።
በአሁኑ ወቅት ደግሞ ይህ ማዕድ በማጋራት አብሮ የመደሰት እሴት ከቤተሰብ፣ ከጎረቤትና ከአካባቢ አልፎ ወደ ሀገር ደረጃ በመሻገሩ ፍቅርን እና መተማመንን በማጠናከር ላይ ይገኛል።
አዲሱ ዓመት የማካፈል ደግነታችን፣ የገበታ አብሮነታችንና ትስስራችን ተጠናክሮ ሀገራዊ መግባባት የሰፈነበት እንዲሆን እንመኛለን።
መልካም አዲስ ዓመት!
በልዩ እሸቱ
#ethiopia #newyear #ethiopiannewyear #sharing #ebc

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የዩክሬይን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ‹‹መልካም እንቁጣጣሽ›› የሚል መልእክት አስተላለፈ፡፡ ዩክሬይን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኤክስ ገፁ ‹‹ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ለእንቁጣጣሽ በአል እንኳን አደረሳችሁ እንላለን፡፡ በአሉም ለአገራችሁ ሰላምን፣ ብልፅግናንና አዳዲስ ስኬቶችን የሚያመጣ ይሁንላችሁ›› ብሏል፡፡ ጨምሮም ‹‹ዩክሬይን ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ወዳጅነት ትልቅ ዋጋ የምትሰጥ ከመሆኑም በላይ በሁለቱ አገራት መካከል የትብብር ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከር ትሻለች›› በማለት ገልጿል፡፡
26 days ago
አንቺን ከቶ አለማሰብ እንዴት ይቻላል ዛሬ 11 ዓመት ሆነሽ በዚህ ከሰዓት በመስከረም በእንቁጣጣሽ አንቺን ማጣት ህመም ነው ሁልጊዜም ውለታሽን አልረሳሁም ሰብልዬ እናቴ እወድሻለሁ ነፍስሽን ከፃድቃን ሰማዕታት ጎን ያሳርፍልኝ።
ሰብለ ተፈራ መስከረም 1/2008 ዓ.ም በመኪና አደጋ ያጣንበት ቀን ነው እኔም በዚህ ሁሉ ዓመታት በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን በመሄድ አስባታለሁ ነፍሰ ይማር 🙏
ቴዲ ባጫ
መስከረም 01/2019 ዓ.ም
ሰብለ ተፈራ መስከረም 1/2008 ዓ.ም በመኪና አደጋ ያጣንበት ቀን ነው እኔም በዚህ ሁሉ ዓመታት በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን በመሄድ አስባታለሁ ነፍሰ ይማር 🙏
ቴዲ ባጫ
መስከረም 01/2019 ዓ.ም
Sponsored by
Surafel
26 days ago
የ2018 የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ተቆረጠ፡ 20 ሚሊዮን ብሩን ያሸነፈው ዕጣ ቁጥር ታወቀ!
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የ2018 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ ልዩ ሎተሪ ዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ምሽት ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሕዝብ ፊት በድምቀት ማካሄዱን አሳውቋል።
በዚሁ መሠረት ከፍተኛውን የ20 ሚሊዮን ብር አንደኛ ዕጣ ያሸነፈው 2302203 የሆነው የዕጣ ቁጥር ነው።
ዋና ዋና የዕጣ ቁጥሮች እና የሚያስገኙት የገንዘብ መጠን፦
1ኛ ዕጣ (20,000,000 ብር)፦ ዕጣ ቁጥር 2302203
2ኛ ዕጣ (10,000,000 ብር)፦ ዕጣ ቁጥር 1057413
3ኛ ዕጣ (5,000,000 ብር)፦ ዕጣ ቁጥር 0829516
4ኛ ዕጣ (2,000,000 ብር)፦ ዕጣ ቁጥር 2161591
Seledadotio

27 days ago
አዲስ ዓመት፤ የብሩህ ተስፋና የተፈጥሮ መታደስ ብስራት
***********
የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የክረምቱን ጭጋግ ገፎ፣ የአዲስ ተስፋ ብርሃን ይዞ ብቅ ይላል። በዓሉ ከቀናት በፊት ከሚጀምረው የዋዜማ ድባቡ አንስቶ በበርካቶች ዘንድ እጅግ የተወደደና የሚጠበቅ ነው።
አገርኛ ዜማዎች፣ የእንቁጣጣሽን ጣጣ ለመሙላት የሚሯሯጡ ወላጆች፣ "አበባዮሽ" እያሉ የሚጨፍሩ ልጆችና የመኖሪያ ቤቶችን ስዕል ይዘው የሚዞሩ ህፃናት የበዓሉን መቃረብ ያበስራሉ። በየመንገዱ ዳር የሚከመረው ችቦና ቄጤማ፣ የሰፈር አብሮ አደጎች እንቅስቃሴ፣ የገበያው ግርግርና የአደይ አበባው መዓዛ ለነፍስ ልዩ ደስታን ይሰጣሉ።
የዋዜማው አመሻሽ ደግሞ የበለጠ ይሞቃል። እናቶችና ልጆች የሐበሻ ቀሚሳቸውን ይለብሳሉ፤ ፈንዲሻው ይፈካል፤ የታመሰ ሱፍ ከገብስ ቆሎ ጋር ቀርቦ ይበላል፣ ቄጤማ በተጎዘጎዘበት ቤት ውስጥ በዕጣን ጭስ የታጀበ ቡና ይፈላል።
ይህ በዓል አዲስ ተስፋ የሚሰነቅበት ወቅት ነው። ሰዎች ያለፉትን ህልሞች ገምግመው፣ አዳዲስ አቅጣጫዎችን በቁርጠኝነት ለመተግበር ለራሳቸው ቃል የሚገቡበት ልዩ አጋጣሚ ነው። መስከረም 1 ቀን ሲጠባ አገሪቱ ከክረምቱ ድብት ወጥታ ወደ ብርሃን ተሸጋግራለች። ዝናቡ ጎድሎ ደመናው ይፈታል፤ ሰማዩ ጠርቶ ወንዞች ይረጋሉ፤ ምድሪቱም በአዴይ አበባ ታብባለች። ይህ የተፈጥሮ መታደስ ከሰው ልጅ ውስጣዊ ደስታ ጋር ተዋህዶ መላ አገሪቱን ያደምቃል።
ከዚህም በተጨማሪ አዲስ ዓመት የእርቅ፣ የፍቅርና የማህበራዊ ትስስር መታደሻ ነው። ሰዎች ያለፈውን ዓመት ቂምና ቁርሾ አውልቀው በመጣል፣ አዲሱን ዘመን በይቅርታ ይጀምራሉ። ከሩቅና ከቅርብ ያሉ ቤተሰቦች፣ ዘመድ አዝማድና ጎረቤቶች በአንድ ላይ ይሰበሰባሉ። የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት ይለዋወጣሉ፤ አረጋውያንና ወላጆችም መርቀው ወጣቶችን ያበረታሉ።
ባህላዊና ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶችም ለበዓሉ ሌላ ድምቀት ያበስራሉ። በዋዜማው የችቦ ማብራት ስርዓት ይከናወናል፤ በዕለቱ ደግሞ ህፃናት የደስታ ዜማዎችን በመጫወትና በለመለመ ሳር ያጌጡ ምስሎችን በመስጠት በየቤቱ በረከት ያድላሉ። በሃይማኖታዊ ተቋማት የሚካሄደው የቅዳሴ፣ የጸሎትና የምስጋና ስነ-ስርዓት ደግሞ የበዓሉን መንፈሳዊ ጥልቀት ያጎላዋል።
የምግብና የቁሳቁስ ዝግጅቱም የበዓሉ ዋና አካል ነው። ከቀናት በፊት ጀምሮ ገበያው በበግ፣ በዶሮ፣ በቅቤና በቅመማ ቅመም ግዢ ይደራል። በዕለቱ በየቤቱ የዶሮ ወጥ፣ የጠጅና የጠላ፣ እንዲሁም የምስጋና እርድ ተዘጋጅቶ በጋራ ይበላል፤ ይጠጣል። ቤቶች በለመለመ ሳር፣ በዕጣን ጭስና በአደይ አበባ ተሸልመው ልዩ የመዓዛና የሞቅታ ድባብ ይፈጥራሉ።
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የተፈጥሮ መታደስ፣ የማህበራዊ ፍቅር፣ የባህልና የሃይማኖታዊ እሴቶች ውህደት የሚታይበት ታላቅ በዓል ነው። ያለፈውን ዓመት አጠናቆ በአዲስ እቅድ፣ ተስፋና መንፈስ ወደፊት ለመራመድ የሚያስችል የአእምሮና የመንፈስ መታደሻ ወቅት በመሆኑ በኢትዮጵያውያን ዘንድ የላቀ ቦታ ይሰጠዋል።
በመሐመድ ፊጣሞ

እንቁጣጣሽ ሎተሪ ዛሬ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በእድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል፡፡
1 month ago
የእንቁጣጣሽ ባዛር በለንደን ፊንስበሪ ፓርክ
Habesha Gifts እና Gleamstone Events በጋራ በመተባበር ያዘጋጁት የእንቁጣጣሽ ባዛር በለንደን ፊንስበሪ ፓርክ ተካሂዷል።
ዝግጅቱን Teamer Properties በTitle Sponsor ደረጃ ሲደግፍ፣ Emmal Money Transfer ደግሞ በGold Level Sponsor ደረጃ ዝግጅቱን ደግፏል።
በዘንድሮው ባዛር 31 የተለያዩ የቢዝነስ ድርጅቶች ተሳትፈው፣ ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን ለጎብኚዎች አቅርበዋል።
ከዚህ ቀደም Habesha Gifts ያዘጋጃቸው ኤክስፖዎች በIndoor ሲካሄዱ የቆዩ ሲሆን፣ ዘንድሮ ግን ከGleamstone Events ጋር በመተባበር ዝግጅቱን ወደ Outdoor በማውጣት በፊንስበሪ ፓርክ አዘጋጅተውታል።
እንደዚህ ያሉ ዝግጅቶች በተለይ ከቤተሰብና ከወዳጆቻቸው ርቀው በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመትን ደስታ በጋራ እንዲያጣጥሙ፣ እንዲገናኙ፣ ባህላቸውን እንዲያከብሩ እና የሀገር ቤት ስሜትን እንዲጋሩ ልዩ አጋጣሚ ይፈጥራሉ።
ባዛሩ የእንቁጣጣሽን በዓል ከማክበር ባለፈ፣ የዳያስፖራ ማህበረሰብን ያቀራረበ፣ አነስተኛና ታዳጊ ቢዝነሶችን ያስተዋወቀ እና ባህልን፣ ቢዝነስንና ማህበረሰባዊ ትስስርን በአንድ መድረክ ያገናኘ ዝግጅት ሆኖ ተጠናቋል።

የልጅነታችን በመስከረም
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገር የዛሬ ብቻ ሳትሆን የትናንት የጋራ ትዝታ ውጤት ናት። በዜጎች ልብ ውስጥ የተጻፈ፣ የሚታወስና የሚናፈቅ ትናንት፣ በጋራ ሀገር ግንባታ ውስጥ ወሳኝ ግብዓት ነው።
አንድ ህዝብ የጋራ ትዝታ ሲኖረው፣ ከቋንቋ፣ ከሃይማኖት ወይም ከጂኦግራፊያዊ አካባቢ ልዩነት በላይ የሚያስተሳስረው የልብ ትስስር ይፈጠራል። ምክንያቱም የልጅነት ትዝታ ማንነትን ከፖለቲካ በላይ የሚያገናኝ፣ በስሜት ላይ የተመሠረተ ትስስር ስለሆነ ነው።
መስከረም አዲስ ነው፤ ልጅነታችንን ከሚያስናፍቁን ወቅቶች ሁሉ ቀዳሚ። መስከረም የአዲስ ቀን መምጣት፣ የአዲስ ወር መጥባት ምልክት ነው።
ለአዲስ ዓመት አዲስ ልብስ ተገዝቶልን እስክንለብሰው ድረስ የነበረን ጉጉት፣ ትምህርት ቤት ተከፍቶ ጓደኞቻችንን እስክናገኝ ያለን ናፍቆት፣ አዲስ ደብተር፣ አዲስ ክፍል፣ አዲስ መንፈስ… አዲስነት የሚታወጅበት ወር ነው መስከረም።
እስኪ ዛሬ ልጅነታችንን በትዝታ እንጋራ። በጋራ ያለፍንበትን፣ በህብረት የተሻገርነውን ያን ዘመን አብረን እንተዝተው…
መስከረም ሲመጣ የአስኳላ በሮች ይከፈታሉ። የትምህርት ቤቶቻችን ሜዳዎች በክረምት ዝናብ ለምልመው ሳር ሞልቷቸዋል፤ ያደገ፣ ልምላሜ የተላበሰ ሳር ይሆናሉ።
ያንን ሳር አጠላልፈን የምንቋጥረው፣ ተጠልፎ የሚወድቀውን ጓደኛችንን እያየን የምንስቀው ሳቅ ትዝ አላችሁ? ያቺ ስትስቅ ዓይኗ የምትጨፍነው ጓደኛችን የት ይሆን ያለችው?
ደወል ሲደወል ተሰልፈን ወደ ክፍል የምንገባበት ስርዓት፣ በአዲስ መምህር ስም ስንጠራ የልብ ትርታችን የሚጨምርበት ቅጽበት፣ አዲስ ጓደኛ ለማፍራት ያለን ስስት… እነዚህ ሁሉ በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ተቀርጸው የቀሩ ህያው ትዝታዎቻችን ናቸው።
መስከረም ሜዳውን በአደይ አበባና በቄጤማ ይሞላዋል። ከሳሩና ከአደይ አበባው ቀጥፈን ደብተራችንን የምናስውበው፣ በቢጫና በአረንጓዴ ቀለም ደብተራችንን የምናሸበርቅበት ትዝታ አልረሳችሁትም አይደል?
ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው እየዞርን «እንቁጣጣሽ» እያልን አደይ አበባ የምናበረክትበት፣ በምላሹ ገንዘብም ይሁን ጣፋጭ ነገር የምንቀበልበት ልማድ፣ «አበባየሆሽ» የሚለውን ዘፈን መንደር ለመንደር እየዞርን የምንዘፍንበት ማለዳ፣ ያ ሁሉ ትዝታ ዛሬም በልባችን ውስጥ ትኩስ ሆኖ ይኖራል።
አዲስ ዓመት ሲመጣ ቤታችን በዶሮ ወጥ ጠረን ይሞላል፤ እናቶቻችን ገና በሌሊቱ ተነስተው ሲያበስሉ የሚወጣው ጭስና መዓዛ ከእንቅልፋችን የሚቀሰቅሰን ደውል ነበር።
አዲስ ልብስ ለብሰን፣ በደስታ ተውበን ከቤተሰብ ጋር የምንነሳበት ጠዋት፣ አያቶቻችንን እጅ የምንነሳበት፣ በረከት የምናገኝበት ስርዓት፣ ጎረቤት ለጎረቤት እየተጠራሩ በጋራ የምንቀርብበት ማዕድ… እነዚህ ሁሉ የመስከረም ትዝታዎቻችን ናቸው።
ልጆች በአዲስ ልብሳችን ቄንጥ ተሞልተው ወደ ጎረቤት ቤት ስንሮጥ፣ «እንኳን አደረሳችሁ» የሚለው የሰላምታ ቃል ከሁሉም አፍ ሲደመጥ፣ መላው ሰፈር በአንድ የደስታ ስሜት ተውጦ የአዲስ አመት አዋጅ ይሆናል።
በመስከረም ዋናተኛ የምንሆነውስ ትዝ አላችሁ? ከትምህርት ቤት መልስ ሰፈራችን ያለ ወንዝ እንወርድና እንዋኛለን። ዋኝተን ስንጨርስ ለምን ነበር ነጭ አመዳሞች የምንሆነው? አመዳምነታችንን ለማጥፋት የምናደርገው ትግልስ?
ወራጅ ውሃ ውስጥ ተንቦራጭቀን ልብሳችን እየረጠበ ወላጆቻችን ቢያውቁብን በሚል ፍርሃት፣ ልብሳችንን በፀሐይ አድርቀን ወደ ቤት ስንገባ ንፁህ መስለን ለመታየት ያደረግነው ጥረት፣ ውሎ አድሮ ግን ተደርሶበት የምንቆነጠጠው ቁንጥጫ!
ሁሉም ስናስበው ፈገግ የሚያሰኘን ትዝታ ነው። ወንዝ ዳር ኳስ የምንጫወትበት፣ የጭቃ ሸርተቴያችን፣ ትንንሽ ጀልባ ከወረቀት ሰርተን በውሃ ላይ የምናንሳፍፍበት ልጅነት፣ የብዙዎቻችን ትዝታ ነው።
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የመስከረምን ጠረን ሲያሸት የአደይ አበባን ቀለም ሲያይ፣ ተመሳሳይ የልጅነት ናፍቆት ውስጡ ይላወሳል።
ይህ የጋራ ስሜት ነው ብሔራዊ ማንነትን ከመሬትና ከድንበር በላይ አጥብቆ የሚያስተሳስረው።
በአፈወርቅ እያዩ

ዳዊት ፅጌ ለአድናቂዎቹ ትልቅ ምስራች አብስሯል
#ethiopia | ዳዊት ፅጌ “የኔ ዜማ” የተሰኘውን የመጀመሪያ አልበሙን ለሙዚቃ አፍቃሪዎች ካበረከተ ከረጅም ዓመታት በኋላ፣ ሁለተኛ አልበሙን ለማቅረብ መዘጋጀቱን አስታውቋል።
“የኔ ዜማ” በወቅቱ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኘ ሲሆን፣ የዳዊት ፅጌን ልዩ የድምፅ ቀለምና የዜማ አቀራረብ ዘይቤ በጉልህ ያሳየ ሥራ ነበር።
በአራዳ ሙቭመንት በተዘጋጀው የዘመን መለወጫ — እንቁጣጣሽ ታላቅ ኮንሰርት ላይ ዳዊት ፅጌ በመድረክ በመቅረብ ተወዳጅ ሥራዎቹን ካቀረበ በኋላ፣ ሁለተኛ አልበሙን ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቁን ይፋ አድርጓል።
ድምፃዊው አልበሙ በ2019 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ተጠናቆ ለህዝብ እንደሚቀርብ መግለጹ የሙዚቃ አፍቃሪዎችን በጉጉት እንዲጠብቁት አድርጓል።
ከመጀመሪያው አልበም በኋላ የቆየው የስድስት ዓመታት ጊዜ በአድናቂዎቹ ዘንድ ትልቅ የሙዚቃ ጥማት ፈጥሯል። አሁን ግን የዳዊት ፅጌ ሁለተኛ አልበም መምጣት የብዙዎችን ጉጉት እንደገና ቀስቅሷል።
እስከዳር ይኩን አምላክ! 🙏
#ዳዊትፅጌ #የኔዜማ #አዲስአልበም #እንቁጣጣሽ #አራዳሙቭመንት #ethiopianmusic #dawittsige

ጳጉሜ - የጊዜ ድልድይ፣ የትዝታና የተስፋ መገናኛ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሮጌው ዓመት መጨረሻና በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ መካከል ቆማ፣ ያለፈውን በትዝታ እያሰናበተች የሚመጣውን በተስፋ የምትቀበል አንዲት ልዩ ወር አለች፣ እርሷም ኢትዮጵያዊቷ ጳጉሜ ናት።
ጳጉሜ ቀናቷ አምስት ወይም ስድስት ብቻ ቢሆኑም የምትሸከመው ጥልቅ ትርጉም ግን ከቀናት ቁጥር ይረዝማል።
እሷ ያለፈውን ዘመን በአንድ ገጽ ላይ አጠናቃ ለአዲሱ ብሩህ ምዕራፍ መንገድ የምትከፍት፣ የትናንትና የነገ መገናኛ ድልድይ ናት። ወደ ኋላ ለመቅረት ሳይሆን ለጥቂት ጊዜ ቆሞ ይበልጥ ለመፍጠን እና ነገን አርቆ ለማየት የሚደረግ ውብ የመንፈስ ጉዞ ማሳያ ናት፣ ጳጉሜ፡፡
በኢትዮጵያዊያን ህሊና ውስጥ ይህች አጭር ወር የታሪክ ማጠፊያና የይቅርታ ወር ናት። ያለፈውን ዓመት ድካም፣ ጭንቅና ቅሬታ አራግፋ እና አጽድታ፣ በአዲስ መንፈስ ለአዲሱ ዘመን ንጹህ ልብና አዲስ መንፈስ ታዘጋጃለች።
በጳጉሜ ሰዎች ከተጣሉት ጋር የሚታረቁበት፣ የፈጣሪን ምህረት በጸሎት የሚያስቡበት ቅዱስ ጊዜ በመሆኑ በማህበረሰባችን ዘንድ ልዩ የክብር ስፍራ አላት።
ይህ የመታደስ መንፈስ በተግባርም ይገለጣል። ጳጉሜ ሲመጣ ህፃናት፣ ወጣቶችና አዋቂዎች ጎህ ሳይቀድ ተነስተው ወደ ወንዝ ያመራሉ። በወሩ የሚዘንበው ዝናብና የሚፈሰው ውሃ ፈውስና በረከት አለው ተብሎ ስለሚታመን፣ ያለፈው ዓመት ደካማነትና ህመም በሙሉ ታጥቦ ይሄዳል ተብሎ ይታመናል።
በየቤቱም አዲስ አመትን ለመቀበል የሚደረገው ጉድጉድም በነዚህ ቀናት ነው የሚካሄደው፡፡
እናቶች የቤታቸውን ውበት እያደሱ ለአዲሱ ዓመት የእንቁጣጣሽ በዓል ሲሰናዱ፣ ህፃናት በየደጃፉ በቅኔና በጨዋታ ድምፃቸው መንደሩን ያደምቁታል። ይህም ልዩ የመታደስ የሽግግር መንፈስ እና የበዓል ድባብ ያላብሳል፡፡
ጎረቤት ከጎረቤቱ ጋር የሚጠያየቅበት፣ አረጋውያን የሚጎበኙበትና ያለው ከሌለው ጋር ተካፍሎ የሚበላበት ይህ ወቅት የኢትዮጵያዊነትን የመደጋገፍና የፍቅር እሴት በጉልህ ያሳያል።
በዚህም ጳጉሜ አንድ ትልቅ እውነት ታስተምረናለች፡፡ ይህም የአንድ ነገር መጨረሻ የሕይወት መጨረሻ ሳይሆን የአዲስ ጅምር መነሻ ሊሆን እንደሚችል ነው ።
ያለፈውን አስተውለን፣ ከስህተታችን ተምረን፣ ወደ አዲሱ ዓመት በተስፋ እንድንሻገር ጳጉሜ የተስፋ ድልድይ ሆና ታገለግላለች።
በአመለወርቅ ደምሰው

የመስከረሙ ኮከብ - ጥላሁን ገሰሰ
ጥላሁን ገሰሰ፣ የኢትዮጵያ ሙዚቃ አውራ፣ ዝንት ዓለም የማይደበዝዝ ኮከብ ነው። የተወለደው በመስከረም ወር በአስራ ሰባተኛው ቀን 1933 ዓ.ም ነው።
ጥላሁን ገሰሰ አብዝቶ የዘፈነለት ወር መስከረም ነው። ከመስከረም ወር መግባት ጋር ጥላሁን በናፍቆት ይጠበቃል።
ክረምቱ ሲገባ እነጥላሁን ይደበቃሉ። በድብቅ አዲስ ዜማ፣ አዲስ ጥበብ ያጠናሉ። ድምፃቸው ጎልቶ አይሰማም። መስከረም ሲጠባ ልክ ከተደበቁበት ይወጣሉ፡፡ እንደመስቀል ወፍ በተስረቅራቂ ድምፅ በተስፋ መዝሙራቸው ተስፋና ንጋትን እያወጁ በመድረኩ ይነግሱበታል።
“እንቁጣጣሽ የእኛ እንቁጣጣሽ
ደስ ይበለን እንኳን ደህና መጣሽ”
ጥላሁንና መስከረም ጥብቅ ነው ቁርኝታቸው።
ልደቱ ከአዲስ ዓመት መምጣት ጋር የተሳሰረ በመሆኑ፣ አድናቂዎቹ ጥላሁንን ከመስከረም ወር ተነጥሎ ሊታሰብ የማይችል ክስተት አድርገው ይመለከቱታል። ድምፁ የብርሃን ብስራት፣ የተስፋ ምልክት ሆኖ ዘመናትን ተሻግሯል።
ገና የክረምት ደመና እየተገፈፈ፣ የበልግ ልምላሜ ምድሪቱን ባማረ ልብስ ሲያስጌጣት፣ አድናቂዎቹ ልባቸው በጉጉት ይመታል። "ዘንድሮ ጥላሁን ምን ይል ይሆን?" የሚል ናፍቆት ደጋግሞ ይጎበኛቸዋል። ይህ ከዚያ ትውልድ ብቻ ሳይሆን ከዚህኛው ትውልድም ጋር የተሳሰረ ትዝታ ነው።
“አንዱ ዘመን አልፎ አንደኛው ሲተካ
ወፎች ሲዘምሩ ፏፏቴው ሲያውካካ
አተኩረው ሲያዩት በስሜት ተውጠው
ተራሮች በሙሉ በአደይ አበባ አጊጠው
"እንቁጣጣሽ"፣ "አስራ ሦስት ወር ፀጋ" እና ሌሎች ዘመን ተሻጋሪ ስራዎቹ የተፈጠሩት ለአዲስ ዓመት ብቻ ሳይሆን፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተስፋ ቃል ኪዳን ሆነው ነው።
እነዚያ ግጥሞችና ዜማዎች፣ ያለፈውን ችግር ወደ ኋላ ትተን ወደፊት እንድንራመድ የሚያበረታቱ፣ የብርሃን ጎህ አብሳሪዎች ናቸው። እያንዳንዱ ቃል በጥበብ የተሸመነ ተስፋ፣ እያንዳንዱ ዜማ ለልብ የሚነገር የፍቅር ደብዳቤ ይመስላል።
ጥላሁን በዚህ የተስፋ ጉዞ ብቻውን አልነበረም። ከክቡር ዘበኛ ባንድ ጓዶቹ ብዙነሽ በቀለ፣ መሃሙድ አህመድ፣ ተዘራ ኃይለሚካኤልና ሌሎችም ደማቅ ክዋክብት ጋር በመሆን፣ የሙዚቃ ሰማዩን በደመቀ ብርሃን አጥለቅልቀውታል። እነዚህ ታላላቅ ድምጻውያን በአንድነት ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ ንጋትን፣ አዲስ ተስፋን፣ አዲስ ህይወትን ዘርተዋል።
የአዲስ አመት ዕለት በሚቀርበው የሙዚቃ ድግስ እነገዛኽኝ ደስታ ንጋትን ያውጃሉ። ክዋክብቱ በመድረኩ ይገማሸሩበታል። የነግርማ ሃድጉና ሳህሌ ደጋጎ ድርሰቶች ለበዓሉ ድምቀትም ህይወትም ይሆኑለታል።
ዛሬም ድረስ፣ መስከረም ሲጠባ፣ የጥላሁን ድምጽ ከየቤቱ ሲሰማ፣ በየመገናኛ ብዙኀኑ ሲከፈት ልባችን በትዝታ ይሞላል፤ ያ ትዝታ ወደ ኋላ የሚጎትት ሳይሆን፣ ወደፊት የሚገፋ፣ የተስፋ ችቦ የሚያቀጣጥል ኃይል አለው። የጥላሁን ገሰሰ ድምጽ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሻገረ፣ በየአዲስ ዓመቱ አዲስ ብርሃን ሆኖ ይመላለሳል።
እርሱ የመስከረም ኮከብ ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ ተስፋ ዘላለማዊ ምልክት ነው።
በእንቁጣጣሽ ዘፈኑ እንዲህ ይመርቃል።
“አሮጌ ዓመት አልፎ አዲሱን ይዛችሁ
የሰላም የደስታ ዘመን አርጎላችሁ
ተባይን ከምድር ላይ በጥበቡ አጥፍቶ
እግዜር ይጠብቀን ጤንነትን ሰጥቶ!”

እንቁጣጣሽ፤ አዲስ ሰው የምንሆንበት ጥሪ
በዓለም ላይ ብዙ ሕዝቦች አዲስ ዓመትን ያከብራሉ። ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው ተፈጥሮ ራሷ በዓሉን የምታውጅላቸው።
ኢትዮጵያ ከእነዚያ ጥቂት ሀገራት መካከል አንዷ ናት።
መስከረም ሲገባ የሚቀየረው የቀን መቁጠሪያ ብቻ አይደለም፤ ሰማዩ ይጠራል፣ ምድሩ ያብባል፣ ወንዞች ይረጋጋሉ፣ አደይ አበባ ምድርን በወርቃማ ቀለም ትሸፍናለች። ተፈጥሮ እንደምትነግረን አንድ መልዕክት አለ፦ "ከረጅም ክረምት በኋላም ማበብ ይቻላል።"
ምናልባት የእንቁጣጣሽ ትልቁ ምስጢር ይሄ ነው።
በዓሉ በአዲስ ልብስ፣ በማዕድ፣ በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቶች ብቻ አይለካም።
ዛፎች ያረጁ ቅጠሎቻቸውን እንደሚጥሉት ሁሉ፣ እኛስ የቆዩ ቂሞቻችንን ጥለናል? ሰማይ ከደመና እንደሚጸዳው ሁሉ፣ ልባችንን ከጥላቻ አጽድተናል? አደይ አበባ ከዝናብ በኋላ እንደምታብበው ሁሉ፣ እኛስ ከፈተናችን በኋላ በተስፋ እንደገና አብበናል?
እንቁጣጣሽ እንዲህ የሚል ጥያቄም አላት!
"ዓመቱ ስንት ቀን አለፈ?" ሳይሆን፣ "በእነዚያ ቀናት አንተ/ች ምን አደረክበት/ሽበት?"
የሰው ዘመን በዓመታት ብቻ አይለካም፤ በእሴቶች ይለካል። የተኖረ ጊዜ በቁጥር ብቻ አይቆጠርም፤ በተዉት አሻራም ጭምር እንጂ።
ለዚህም ነው እንቁጣጣሽ የተስፋ በዓል ከመሆኗ በፊት የኃላፊነት በዓል የምትሆነው።
እውነተኛው አዲስ ዓመት የሚጀምረው አዲስ ልብስ ስንለብስ አይደለም፤ አዲስ አስተሳሰብ ስንለብስ ነው። ቤታችንን ብቻ ስናጸዳ አይደለም፤ ልባችንን ከጥላቻ፣ ከቅሬታ፣ ከተስፋ መቁረጥ ስናጸዳ ነው።
ምናልባት በዚህ መስከረም የምንለው "መልካም አዲስ ዓመት" ብቻ መሆን የለበትም።
"መልካም አዲስ ልብ፣ መልካም አዲስ አስተሳሰብ፣ መልካም አዲስ ኢትዮጵያ" ማለትም ይገባናል።
ምክንያቱም አገር የምትታደሰው ቀን ሲቀየር ብቻ አይደለም፤ ሰዎች ሲታደሱም እንጂ።
እናም የእንቁጣጣሽ ትልቁ ስጦታ አዲስ ዓመት ሳይሆን፣ አዲስ ሰው የመሆን ዕድል ነው።

የክብር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አህመድ ለታሪክ የተሰኘ የመጨረሻ አዲስ አልበሙን ለአድማጮች ሊያቀርብ ነው
#ethiopia | ለስድስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የማይተካ ሚና የተጫወተው የክብር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አህመድ፣ ለትውልድ የሚሻገር አዲስ የሙዚቃ አሻራ ለማስቀመጥ ያዘጋጀውን ለታሪክ የተሰኘ 26ኛ አልበሙን አስመልክቶ በሸራተን አዲስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
አልበሙ ለታሪክ የሚል ስያሜ የተሰጠው የቀደሙትን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ቅርሶች፣ ውበትና ወግ ሳይለቁ ለአዲሱ ትውልድ ለማስረከብ ታስቦ ነው።
ሥራው የአርቲስቱን ልዩ የመድረክና የድምፅ ስልት መሠረት ያደረገ ሲሆን፣ ዘመናዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችና ባህላዊ ቅኝቶች በተዋጣለት መልኩ ተዋህደውበታል።
በፍቅር፣ በሀገር፣ በህይወት ፍልስፍናና ማህበራዊ እሴቶች ላይ ያተኮሩ አዳዲስና በትዝታ የተቃኙ ዜማዎችንም አካትቷል።
በዚህ አልበም ዝግጅት ላይ አንጋፋና ወጣት የዜማና ግጥም ደራሲያን እንዲሁም የሙዚቃ አቀናባሪዎች በጋራ ተሳትፈዋል።
አርቲስቱ አልበሙ የኪነ ጥበብ ህይወቱ የመጨረሻ ሥራ መሆኑን ገልጾ፣ አዲሱ የሙዚቃ ትውልድ የሀገርን ባህልና ቅኝት ሳይለቅ ዘመናዊነትን እንዲቀላቅል ጥሪ አቅርቧል።
አልበሙ በስፖቲፋይ፣ አፕል ሙዚክ፣ യൂቱብ እና በሌሎች ዲጂታል መድረኮች ለህዝብ የሚሰራጭ ሲሆን፣ በይፋ ከመልቀቁ በፊት በእንቁጣጣሽ ዋዜማ አንድ ነጠላ ዜማ፣ ሙሉ አልበሙ ደግሞ በመስከረም አጋማሽ ለአድማጮች ይደርሳል።
ይህንን ሥራ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚያሰራጨው የሙዚቃ ኩባንያ ጋር በአጋርነት የሚያስተባብረው ይሳቃል ኢንተርቴይመንት ነው።
ይሳቃል ኢንተርቴይመንት የሀገራችን አንጋፋ ባለሙያዎች እንዲዘከሩ ከማድረግ ባለፈ፣ የሀገርን ባህልና ታሪክ በዓለም አቀፍ መድረኮች በማስተዋወቅና ደረጃቸውን የጠበቁ የሙዚቃ ድግሶችንና ኮንሰርቶችን በማዘጋጀት ይታወቃል።
#mahmoudahmed #ethiopianmusic #letarik #yisakalentertainment #ethiopianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የክብር ዶክተር አርቲስት ማህሙድ አህመድ "ለታሪክ" የተሰኘ የመጨረሻ አልበሙን ሊለቅ ነው
#fastmereja I ለስድስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የማይተካ አስተዋጽኦ ያበረከተው የክብር ዶክተር አርቲስት ማህሙድ አህመድ "ለታሪክ" የተሰኘውን 26ኛ እና የመጨረሻ አልበሙን ለአድማጮች ሊያደርስ መሆኑን ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አበሰረ።
ይህ አልበም የቀደሙትን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ቅርሶች፣ ለዛና ወግ ሳይለቁ ለአዲሱ ትውልድ ለማስረከብ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የአርቲስቱን ልዩ የመድረክና የድምፅ ስልት መሠረት ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል። በስራው ላይ ዘመናዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች እና ባህላዊ የቅኝት ድምፆች በተዋጣለት መልኩ የተዋሃዱበት ሲሆን፣ የፍቅር፣ የሀገር፣ የህይወት ፍልስፍና እና ማህበራዊ እሴቶችን የሚያንፀባርቁ አዳዲስና በትዝታ የተቃኙ ስራዎች ተካተውበታል።
በአልበሙ ዝግጅት ላይ አንጋፋ እና ወጣት የዜማና ግጥም ደራሲያን እንዲሁም የሙዚቃ አቀናባሪዎች በጋራ የተሳተፉ ሲሆን፣ አርቲስቱ ይህ አልበም የኪነ-ጥበብ ህይወቱ የመጨረሻ ስራ መሆኑን በመግለፅ አዲሱ የሙዚቃ ትውልድ የሀገርን ባህል፣ ቅኝት እና ማንነት ሳይለቅ ዘመናዊነትን እንዲቀላቅል ጥሪ አቅርቧል።
አልበሙን በዓለም አቀፍ ደረጃ የማሰራጨቱንና የማስተዋወቁን ስራ ይሳቃል ኢንተርቴይመንት ከሌሎች የሙዚቃ ኩባንያዎች ጋር በመተባበር የሚያከናውነው ሲሆን፣ በSpotify, Apple Music እና YouTube ጨምሮ በሁሉም ዲጂታል መድረኮች ለህዝብ ይደርሳል። በእንቁጣጣሽ ዋዜማ አንድ ነጠላ ዜማ የሚለቀቅ ሲሆን ሙሉ አልበሙ ደግሞ በመስከረም አጋማሽ ለአድማጮች ክፍት ይደረጋል።

11 months ago
ኑ !!! ጌትነትን እንየው ።
( ታላቁን የኪነ-ጥበብ ሰው እናመስግነው )
#ethiopia | ጸሐፊ ተውኔቱ ፣ ገጣሚው ፣ አዘጋጁ ፣ ተዋናዩ ፣ በሁሉ ተወዳጁ ጌትነት እንየው 68 መስቀል ተኩሷል ፤ 68 ክረምትና 68 በጋ አይቷል ፤ 68 እንቁጣጣሽ ፣ 68 ፋሲካ አክብሯል ። ከዚህ ውስጥ ደግሞ 43 ዓመት በጥበብ ላይ ነግሷል ። 43 ዓመት " ጌትነት ! ጌትነት ! " ተብሏል ። ሁሉ ወዳጁ ሁለገብ የኪነጥበብ ሰው ዘንድሮ 68ኛ ዓመት ልደቱ ነው ። ሁሉም ቀንና ሰዓት ከሌላው ቢለይም የዘንድሮው የታላቁ የኪነጥበብ ሰው የልደት በዓል ግን ከ67ቱ በተለየ ሁኔታ በምስጋና ሊከበር ነው ።
በተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ ፣ በአርቲስቱ የቅርብ ቤተሰቦች እና ወዳጆች በጋራ የተዘጋጀውን 68ኛ ዓመት የልደት በዓልና የ43 ዓመት የሙያ አገልግሎት ምክንያት በማድረግ የፊታችን ሰኞ ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሠዓት ላይ አርቲስቱን የማመስገን ልዩ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ተዘጋጅቷል።
እርስዎም በዕለቱ ተገኝተው ለተወዳጁ አርቲስት ያለዎትን አክብሮት እና ፍቅር እንዲገልጹ የክብር እንግዳችን ነዎት ።
በእለቱ የሚከናወኑ ፕሮግራሞች:-
1.ከቀኑ 11:00 ሠዓት ጀምሮ በርካታ የኪነ-ጥበብ ሰዎች በተገኙበት በፌደራል ፖሊስ ማርቺንግ ባንድ በመታጀብ ለዕለቱ የክብር እንግዶች ( ለእርስዎ ) እና ለታላቁ የጥበብ ሰው ጌትነት እንየው ልዩ የአቀባበል ሥነ-ስርዓት ይካሄዳል።
2.ታዋቂ ድምጻዊያን የሚሳተፉበት ልዩ የሙዚቃ ዝግጅት ይካሄዳል።
3.በአርቲስቱ ስም የተዘጋጀ ተውኔት ይቀርባል።
4.አርቲስት ጌትነት እንየው በድርሰት፣ በዝግጅት፣በትወና የተሳተፈባቸው ስራዎች በፎቶግራፍ መልክ ይቀርባሉ።
5.የተለያዩ የሙያ አጋሮቹ በሀገር ውስጥም በውጪም ያሉ ባለሙያዎች መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።
6.የተለያዩ ሰርፕራይዝ ፕሮግራሞች ይኖራሉ።
( የዚህ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ ተፈራ ወርቁ፣ የአርቲስቱ የቅርብ ወዳጀች እና ቤተሰቦቹ በጋራ በመሆን ነው። )
Via ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ
#share በማድረግ ለጌትነት እንየው ያለዎትን አጋርነት ያሳዩ ።

12 months ago
ለሎተሪ አሸናፊዎች ሽልማት ተበረከተ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሎሽንስ ጋር በመሆን የእንቁጣጣሽ ሎተሪ አሸናፊዎችን በታላቅ ስነ-ስርዓት ሸለመ፡፡
የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የአሁኑ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ለ65 ዓመታት ያህል ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የደስታ እንዲሁም የለውጥና የዕድል ምንጭ ሆኖ አገልግሏል::
የሽልማት መጠኑን በ50 ሺህ ብር አሀዱ ብሎ ጀምሮ ዛሬ ላይ ሽልማቱን በሚሊዮን አሳድጎ በርካቶችን በሽልማት ያንበሸበሸ ትልቅ ተቋም ነው፡፡
አሁን ላይ ይህ ተቋም ከዘመኑ ጋር እኩል በመራመድ በቴክኖሎጂው እየታገዘ ሎተሪን በወረቀት ብቻ ሳይሆን በዲጂታል አማራጭበማቅረብ ደንበኞቹ በየትኛውም ቦታ ሆነው በቀላሉ ዕድላቸውን እንዲሞክሩ አስችሏል፡፡
ዕድል ከቴክኖሎጂ ጋር መተሳሰርን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን ጋር በመተባበር ባሳለፍነው ዓመት አራት የሎተሪ ዘመቻን በዲጂታል በመሽጥ በስኬት አጠናቋል፡፡ ይህ የዲጂታል ሽያጭ ደማቅ የሆኑ የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዐቶችን እና የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት የሳቡ የሽልማት መርሃግብሮችን በማከናወን ግልፅነትና ታአማኒነትን ከማስፈን ባሻገር የኦንላይን ደንበኞች አባላት ቁጥር ወደ አንድ ሚሊዮን እንዲደርስ አስችሏል፡፡
ለሁለት ወራት ያህል በዲጂታል እና በወረቀት ሲሸጥ የቆየው የ"እንቁጣጣሽ ሎተሪ" የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት በስኬት ከተከናወነ በኋላ ዛሬ ለዕድለኞች የሚከተሉት ሽልማቶች ተሰጥተዋል፦
የገንዘብ ሽልማቶች በዲጂታል እና በወረቀት ለገዙ ፦ 👉 20 ሚሊዮን ብር ወይዘሮ ጌጤነሽ ብሩ
👉 10 ሚሊዮን ብር ወጣት አለሙ አማረ
👉 2.5 ሚሊዮን ብር አቶ በረከት ቢሆነኝ
👉 2.5 ሚሊዮን ብር አቶ በረከት ቢሆነኝ
👉 2.5 ሚሊዮን ብር አቶ ሀይሉ ተረዳ
👉 250ሺ ብር አቶ አስማረ መኮንን
እንቁጣጣሽ ሎተሪን በዲጂታል ለቆረጡ ብቻ ልዩ የቦነስ ሽልማት
👉 አቶ አስማረ ዱፋ የBYD ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ
👉 አቶ ኦልያድ ደሜ የኤሌክትሪክ ባጃጅ ለዕድለኞች ተሸልመዋል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በቀጣይ በ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ በ100 ብር ከ125 ሚሊዮን ብር በላይ ለሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን በየሳምንቱ ቅዳሜ አንድ ሚሊዮን ብር የቦነስ ሽልማት መዘጋጀቱን ተገልጿል።
በተጨማሪም ዕለታዊ ሎተሪ በ5 ብር እስከ 25,000 ብር በየቀኑ ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን ልዩ ዕድል ሎተሪ በ100 እስከ 10 ሚሊዮን ብር የሚያሸልም ሲሆን ዕጣው ህዳር 1 እንደሚወጣ ተገልጿል።
ሁሉንም በቴሌብር እና በ ethiolottery.et ላይ ያገኙታል!
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አዳዲስ የዕድል አማራጮችን ለህብረተሰቡ ማቅረብ እንደሚቀጥል በመግለፀ አሸናፊዎቹን በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሎተሪ አገልግሎት በዛሬዉ እለት ባለእድለኞችን ሸለመ
#fastmereja I የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሎሽንስ ጋር በመሆን የእንቁጣጣሽ ሎተሪ አሸናፊዎችን በታላቅ ስነ-ስርዓት በዛሬዉ እለት ሸለመ።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የአሁኑ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ለ65 ዓመታት ያህል ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የደስታ እንዲሁም የለውጥና የዕድል ምንጭ ሆኖ አገልግሏል ሲሉ ገልፀዋል::
የሽልማት መጠኑን በ50 ሺህ ብር አሀዱ ብሎ ጀምሮ ዛሬ ላይ ሽልማቱን በሚሊዮን አሳድጎ በርካቶችን በሽልማት ያንበሸበሸ ትልቅ ተቋም መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን ጋር በመተባበር ባሳለፉት ዓመት አራት የሎተሪ ዘመቻን በዲጂታል በመሸጥ በስኬት አጠናቋል።
ለሁለት ወራት ያህል በዲጂታል እና በወረቀት ሲሽጥ የቆየው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ታላላቅ የገንዘብ ሽልማቶች በዲጂታል እና በወረቀት ለገዙ 20 ሚሊዮን ብር፣ 10 ሚሊዮን ብር፣ 5 ሚሊዮን ብር፣ 2 ሚሊዮን ብር እና በርካታ የገንዘብ ሽልማቶች ለባለዕድለኛ ተበርክቷል።
እንቁጣጣሽ ሎተሪን በዲጂታል ለቆረጡ ብቻ ልዩ የቦነስ ሽልማት፡- የBYD ተሽከርካሪ እና የኤሌክትሪክ ባጃጅ ለዕድለኞች ሽልማታቸዉን ተረክበዋል።
አሁን ላይ ይህ ተቋም ከዘመኑ ጋርእኩል በመራመድ በቴክኖሎጂው እየታገዘ ሎተሪን በወረቀት ብቻ ሳይሆን በዲጂታል አማራጭ በማቅረብ ደንበኞቹ በየትኛውም ቦታ ሆነው በቀላሉ ዕድላቸውን እንዲሞክሩ አስችሏል ተብሏል።

1 year ago
እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2018 በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏
#ዕንቍ ዕጣ ወጣሽልኝ
የጥበብ ቤት፣ በክርስቶስ ደም የተመሰረተች፣ በሐዋርያት ትምህርት የጸናችው ቅድስት ቤተክርስቲያን ምጡቅ የሆነውን የዘመን ቀመር ፈጥራ ለዓለም አስረክባለች፡፡ የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት በዓለማችን ልዩና ጥንታዊ ከሚባሉት ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ መስከረም 1 የአዲስ ዘመን ብስራት የብሩህ ተስፋ መጀመሪያ ነው፡፡ እለቱ እንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ፣ ርዕሰ ዐውደ ዓመት ተብሎ ይጠራል፡፡ እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ መነሻው ኖኅና ልጆቹ ከጥፋት ውሃ በኋላ ሰማዩ በደመና በመክበዱ የጥፋት ውሃ እንደገና ይዘንም ይሆን እያሉ ሲደነግጡ ከርመው በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ሙሉ የፀሓይ ብርሃን ስላዩ፣ ምድር በአበባ አሸብርቃ ስለ ተገለጠችና በዚህም የእግዚአብሔርን ቸርነት የቃል ኪዳኑን መጽናት ስለ ተረዱ ይህንን በዓል ቀድሞ ከአባቶቻቸው እንደ ወረሱት ያው ጥንተ ብርሃን ጥንተ ዓመት ጥንተ ዕለት አድርገው አክብረውታል።
ሲያከብሩትም እንግጫ ነቅለው፣ አበባ ጐንጕነው መጀመሪያ መሥዋዕት ይሠውበት ከነበረው ቦታ ሄደው ለእግዚአብሔር ገጸ በረከት ካቀረቡ በኋላ እርስ በርስም የአበባ ስጦታ በመለዋወጥ ነበር። ሲያከብሩትም ዕንቍጣጣሽ በሚል ቃል እውነተኛ መልካም ምኞታቸውን ይገላለጡበት ነበር። በሌላ በኩል ዕንቍጣጣሽ ማለት ተንቈጠቈጠ፣ አንቈጠቈጠ ከሚለው ቃል የተወሰደ ምድር በአበባ አጌጠች፣ ሰማይም በከዋክብት አሸበረቀ፣ ሰማይን በከዋክብት ያስጌጠ አምላክ ምድርንም በአበቦች አጎናጸፋት ለማለት የተሰጠ ቃል ነው፡፡ ሁለተኛም ጥንታዊያን አባቶቻችን ኢትዮጵያን በሙሉ ሀብት ተረክበዋት ነበርና “ዕንቍ ዕጣ ወጣሽልኝ” ሲሉ ወደ አገራቸው ሲገቡ ለአገራቸው መታሰቢያ አድርገው የተጠቀሙበት ቃል ነው ይባላል።
በመሠረቱ ግን ያ የጥፋት ውሃ ቆሞ ምድር ጸንታ፣ አበባ ቋጥራ፣ ፍሬ ለመስጠት ተዘጋጅታ መገኘቷን የሚያበሥር ቃል ነው። በግእዝ ቋንቋ መርከብ መስቀር ይባላል። የኖኅ መርከብ እንደ ዕብራውያን አቈጣጠር ሰባተኛ በሆነው በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ በአራራት ተራራ አናት ላይ ዐርፋለች። ከዘመን ብዛት በኋላ «ቀ» ወደ «ከ» ተለውጦ መስከረም ተባለ እንጂ መስቀርም ምድር አገኘች፣ ወይም መርከቧ ምድር ነካች ለማለት የተሰጠ የወሩ ስያሜ ነው። ዐውደ ዓመት መባሉም፣ ዐውድ ማለት በግእዙ ቋንቋ ዙሪያ፥ ክብ የሆነ ነገር ማለት ነው። የዓመት ጠቅላላ ቀኖች መሠረታውያን ቀኖች የሚባሉት ሦስት መቶ ስድሳ አራት ቀኖች ናቸው። እነዚህም በኀምሳ ሁለት ሱባዔ ተከፍለው ለእያንዳንዱ ቀን በዓመት ውስጥ ለሰባቱ ዕለታት ኀምሳ ሁለት ኀምሳ ሁለት ቀን ይደርሳቸዋል።
ከነዚህ ቀኖች የተሳሳበ የሴኮንድ፣ የደቂቃ፣ የሰዓት ዕላፊ ተጠራቅሞ 365ኛዋን የዘመን ማገጣጠሚያ ቀን ያስገኛል። ስለዚህም ዕለቲቱ ዙሪያ፣ ክብ መግጠሚያ ወደ ዐዲሱ ዘመን መጀመሪያ የምንተላለፍባት ናት ማለት ነው። ዕለት አዕዋዲት፣ ዕለተ ምርያ የመዘዋወሪያ ቀን ወይም የመጨረሻ ቀን ተብላ ትጠራለች። በአራት ዓመት ደግሞ ከዚህች መሳሳብ የምትገኝ አንዲት ቀን ትመጣለች። ሦስት መቶ ስድሳ ስድስተኛ። ይህቺ ቀን ዕለተ ሰግር ትባላለች። መረማመጃ ማለት ነው። አንድ ቀን ታስተላልፋለችና። እንግዲህ እነዚህን ሁለቱን ቀኖች ተከትሎ የሚመጣው ቀን የዘመን መጀመሪያ፥ የዘመን ክብ መነሻና መድረሻ ተብሎ ርእሰ ዐውደ ዓመት ተብሎ በግእዙ ይጠራል። እነዚህ ቀኖች በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ተጠቃለው አንድ ጊዜ የሚገኙ ናቸው።
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

እናት ባንክ ለፍቅር የህጻናትና እናቶች በጎ አድራጎት ድርጅት የገንዘብ ስጦታ አበረከተ
#fastmereja I አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ እናት ባንክ ዛሬ ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም ለፍቅር የህጻናትና እናቶች በጎ አድራጎት ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
እንቁጣጣሽን ከፍቅር የህጻናትና እናቶች በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር ያከበሩት እናት ባንክ ከህብረተሰቡ ጋር አብሮ በዓልን በማሳለፍ የመረዳዳትና እሴትን ማጎልበት ዓላማ እንዳደረገ ተገልጿል።
እናት ባንክ ከባንክ አገልግሎት በተጨማሪ ባንኩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡
በተጨማሪም ለአዲስ አመት በዓል መዋያ ለእናቶች የገንዘብ ስጦታ ተደርጓል።
#ማህበራዊ

የ2024 ቢዋይዲ ሴጉል መኪና እና የባጃጅ ሽልማት ይፋ ተደረገ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን ጋር በመተባበር የዲጂታል ሎተሪ ሽያጭን ለማበረታታት ከነሐሴ 15 ቀን እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2017 ድረስ ለገዙ ደንበኞች የ2024 ቢዋይዲ ሴጉል መኪና እና የባጃጅ ሽልማት እድለኛ የሆኑት በዕጣ ተለዩ።
በዚህም መሠረት
1ኛ እጣ የማኘ ቁጥር 7477716 የእድለኛው ቁጥር 30006063 ሲሆን ቢዋይዲ ሴጉል የኤሌክትሪክ መኪና አሸናፊ ሲሆን ፤
2ኛ እጣ የማኘ ቁጥር 7267109 የእድለኛው ቁጥር 2482333 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ባጃጅ
በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እድል ማውጫ በዛሬው እለት ወጥቷል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከዚህ በፊት እንደተለመደው ብዙ ሰዎችን ሚሊየነሮች እንዳደረገ እና አሁን ደግሞ በዲጂታል ሽግግር ሂደት ተጨማሪ እድሎች መፈጠራቸው በእጣ አወጣጥ መርሐግብሩ ላይ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የእጣ አወጣጥ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ያለም ተስፋንጋት፥ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር እኩል በመራመድ ደንበኞቹን በየትኛውም ስፍራና በማናቸውም ጊዜ ሆነው የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ http://xn--ethiolottery-xt... እና በቴሌብር፣ በሲቢኢ ብር እና በሌሎች አማራጮች ሎተሪን በዲጂታል መንገድ የሚገዙበት ልዩ አሰራር አመቻችተናል ብለዋል።
የብሔራዊ ሎተሪ አገልግሎት በዲጂታል መድረኩ
በአሁኑ ጊዜ፣ ዋናው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ በገበያ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ዋንኛው ሽልማት 20 ሚሊየን ብር ነው። ቀጥሎም 10 እና 5 ሚሊየን ብር እንዲሁም ሌሎች ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል። የዚህ ሎተሪ ዕጣ ጳጉሜ 5 ላይ የሚወጣ ሲሆን፣ በወረቀትም ሆነ በዲጂታል መንገድ ትኬቱ ገቢያ ላይ ይገኛል።
የአዲሱ የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዕጣ ጳጉሜ 5 ቀን እንደሚወጣ የተገለጸ ሲሆን፣ ደንበኞች በወረቀትም ሆነ በዲጂታል መልክ ሎተሪውን በመግዛት ለሀገር ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

Comments