29 days ago
የአርቲስትና ታጋይ እልፍነሽ ቀኖ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ
#ethiopia | የአንጋፋዋ አርቲስትና ታጋይ እልፍነሽ ቀኖ ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት በአምቦ ከተማ ተፈጸመ።
በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የቤተሰብ አባላቷ፣ ወዳጅ ዘመዶቿ፣ አርቲስቶች፣ አድናቂዎቿ እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
እልፍነሽ ቀኖ በአፋን ኦሮሞ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ፈር ቀዳጅ ከነበሩ አንጋፋ አርቲስቶች መካከል አንዷ ስትሆን፣ በርካታ የማይረሱ የሙዚቃ ሥራዎችን ለትውልድ አበርክታለች።
በወጣትነቷ ወደ ጥበብ ዓለም በመቀላቀል የኦሮሞን ባህልና ኪነ-ጥበብ ለማሳደግ የሰራችው እልፍነሽ፣ እስከ መጨረሻው የሕይወቷ ዘመን ድረስ ከመድረክ ድምፇን ሳታርቅ ለአድናቂዎቿ የማይረሱ ሥራዎችን አበርክታለች።
በምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ነቀምቴ ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው ታሪካዊቷ ሲቡ ጉቶ የተወለደችው እልፍነሽ ቀኖ፣ በሙዚቃዎቿ ያሳየችው ቁርጠኝነትና የዓላማ ጽናት በብዙዎች ዘንድ የጀግንነትና የጽናት ምሳሌ እንድትሆን አድርጓታል።
በተለይም በ1969 ዓ.ም. ወደ ትግል በመቀላቀል፣ ጥበብን እንደ የመብትና የነፃነት ድምፅ በመጠቀም የተጫወተችው ሚና በኦሮሞ ሥነ-ጽሑፍና ኪነ-ጥበብ ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ ያለው ነው።
እልፍነሽ ቀኖ ጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። ከእሷ በኋላ የተረፈው የሙዚቃ ሥራዋ፣ የጥበብ አስተዋፅኦዋና የትውልድ ቅርስ ግን በማስታወሻነት ይቀጥላል።
አርቲስትና ታጋይ እልፍነሽ ቀኖ የሁለት ሴት ልጆችና የአንድ ወንድ ልጅ እናት ነበረች።
ነፍሷ በሰላም ትረፍ።
ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿ፣ ለአድናቂዎቿና ለመላው የጥበብ ቤተሰብ መጽናናትን እንመኛለን።
#እልፍነሽቀኖ #elfneshkeno #oromomusic #oromoart #ethiopia #የኦሮሞጥበብ #የኢትዮጵያጥበብ #ጌጡተመስገን

Comments