21 days ago
በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ለሀገራቸው 162 የኦሎምፒክ ደረጃ የጁዶ ማሰልጠኛ ምንጣፎችን አበረከቱ
#ethiopia | በጀርመን በርሊን ነዋሪ የሆኑት የዲያስፖራ አባል ዶክተር ጸጋዬ ደግነህ ከዓለም አቀፉ የጁዶ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር 162 የኦሎምፒክ ደረጃ ያላቸው የጁዶ ማሰልጠኛ ምንጣፎችን ለኢትዮጵያ በስጦታ አበርክተዋል።
ይህ የተደረገው ድጋፍ የማሰልጠኛ ምንጣፎቹን ዋጋ፣ የማጓጓዣና የዴሙሬጅ ወጪዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 30 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንደሚገመት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል።
አምባሳደር ፍጹም ባስተላለፉት መልዕክት፣ በጀርመን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲና የዲያስፖራ አገልግሎቱ የስጦታ ሂደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
የስጦታ ማስረከቢያና የምረቃ ሥነ ስርዓቱ በአዲስ አበባ በሚገኘው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የተካሄደ ሲሆን፣ ከዲያስፖራ አገልግሎቱ የተወከሉ ዳይሬክተር በቦታው ተገኝተዋል።
ይህ ዓይነቱ ድጋፍ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት ከእናት ሀገራቸው ጋር ያላቸውን ቁርኝት የሚያጠናክርና ለሀገራዊ ልማት የሚያበረክቱትን የጎላ ሚና የሚያሳይ መሆኑን አምባሳደሩ ጠቁመዋል።
ስፖርት ጤናማና ጠንካራ ማኅበረሰብ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለው የገለጹት አምባሳደር ፍጹም፣ እንደ ጁዶ ያሉ የማርሻል አርት ስፖርቶች በሕፃናትና ወጣቶች ዘንድ ሥነ ምግባርን፣ ድፍረትን፣ ጽናትን፣ ኃላፊነትንና መከባበርን ለማስረጽ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ከ18 ዓመታት በፊት ዘመናዊ የጁዶ ስፖርትን ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት ዶክተር ጸጋዬ ደግነህ፣ በስፖርቱ የዕውቀት ሽግግር ከመስጠታቸው ባሻገር በሕዝብ ዲፕሎማሲ፣ በሥራ ባህል፣ በፕሮጀክት አመራርና በዲጂታል አስተሳሰብ ዘርፎች ሀገራቸውን ሲደግፉ መቆየታቸው ተገልጻል።
ዶክተር ጸጋዬ በጀርመን በሚገኘው የሜርሴዲስ ቤንዝ ኩባንያ የሙሉ ጊዜ ሠራተኛ ሲሆኑ፣ በዓለም አቀፉ የጁዶ ፌዴሬሽን ሥር የሚገኘው የጁዶፎር ፒስ ኮሚሽነርና ዋና ተናጋሪ ናቸው።
በተጨማሪም ዶክተር ጸጋዬ በጀርመን ፕሬዚዳንት የሚሰጠውን የከበረ የክሮስ ኦፍ ሜሪት ሽልማት የተቀበሉ ሲሆን፣ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ለሀገራቸው ለሚያደርጉት ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ቁርጠኝነት ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበውላቸዋል።
#ethiopia #judo #diaspora #ijf #addisababa #adwamuseum #ኢትዮጵያ #ጁዶ #ዲያስፖራ #ስፖርት #አድዋሙዚየም #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments