2 days ago
«ቤተክርስቲያናችንን አስከፍቱልን» — የድጋፍ ጥሪ
በቢሾፍቱ ወረዳ ቤተክህነት ሥር የሚገኘው የአቡ ገርቢ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ከተመሠረተ በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ቤተክርስቲያን መሆኗ ተገልጿል።
በአካባቢው በተካሄደ ልማት ምክንያት በዚያ ይኖሩ የነበሩ ምእመናን ከአካባቢው በመነሳታቸው ቤተክርስቲያኗ የነበራትን ገቢ እንዳጣች ተገልጿል። በዚህም ሳቢያ ካህናቱ ተበትነው፣ የአምልኮ አገልግሎቱም ተቋርጦ ቤተክርስቲያኗ መዘጋቷን የድጋፍ ጥሪው ያስረዳል።
በቦታው የሚገኙት አባት በሐዘን እንዲህ ይላሉ፦
««ይህን ቤተክርስቲያን ከአባቶቼ በአደራ ተረክቤዋለሁ። ዛሬ ግን ምእመናን በማጣቴ ምክንያት ተዘግታብኛለች፤ ካህኑም ትቶኝ ሄዷል። ብቻዬን ምን ላድርግ? በዓለም ያላችሁ የእመቤታችን የድንግል ማርያምና የቅዱስ እግዚአብሔር አብ ወዳጆች፣ እባካችሁ ድረሱልን፤ ቤተክርስቲያናችን እንዳትዘጋ እርዱን።»»
የድጋፍ ጥሪ
በኢትዮጵያም ሆነ በውጭ አገር የምትኖሩ የቤተክርስቲያኗ ልጆች፣ በአቅማችሁ መጠን ድጋፍ በማድረግ የእጣን፣ የጧፍ፣ የዘቢብ፣ የመገበሪያ እና የካህናት አልባሳት እንዲሟሉ በመርዳት የቤተክርስቲያኗን አገልግሎት እንደገና ለማስጀመር ድጋፋችሁን እንጠይቃለን።
የድጋፍ አካውንት
የአቡ ገርቢ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን
1000781062058
ስልክ፦
+251-901-613814
ድጋፍ ካደረጉ በኋላ የክርስትና ስምዎን በዚህ ስልክ ቁጥር እንዲልኩ ተጠይቋል፤ አባቶችም በጸሎት እንደሚያስቧችሁ ተገልጿል።
«የእያንዳንዱ ሰው ትንሽ አስተዋጽኦ ለቤተ እግዚአብሔር ትልቅ ተስፋ ሊሆን ይችላል።»
#አቡገርቢ #ቅዱስእግዚአብሔርአብ #ቤተክርስቲያን #የድጋፍጥሪ #ኢትዮጵያ #በጎነት #ድጋፍ
Comments