18 days ago
የተፈጥሮ ሕግ ለምን አይሻሻልም?
* ከተፈጥሮአዊ ህጋዊ እይታ አንጻር የህግ አወጣጣችንን ለመዳሰስ የቀረበ ጹሑፍ
መግቢያ #ethiopia | የተፈጥሮ ህግ (Natural Law) ከሰው ልጅ ታሪክ፣ ስልጣኔና ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ቀድሞ የነበረ፣ አጽናፈ-ዓለምና የሰው ልጅ ህልውና የሚመሩበት ዘላለማዊ ሰንሰለት ነው። የሰው ልጅ ማህበራዊ ኑሮውን ለመምራት ህጎችን ያወጣል፣ ይሽራል፣ ያሻሽላል። ነገር ግን የተፈጥሮ ህግ ጊዜ የማይሽረው፣ ቦታ የማይወስነውና በፍጹም የማይሻሻል ፍጹም እውነት ነው። ይህ ጽሑፍ የተፈጥሮ ህግ ለምን ሊሻሻል እንደማይችል፣ በሳይንስ፣ በሃይማኖትና በጥንታውያን ፈላስፋዎች እይታ መርምሮ፣ እኛ ሰዎች በህግ አወጣጥ ሂደታችን ውስጥ ምን መማር እንዳለብን በጥልቀት ያብራራል።
ዋና ዋና አንኳር ይዘቶች
1. ፍጹም ንጽህና፣ ፍጹም እውቀትና የህግ ምንጭ
በፍልስፍና እይታ ህግን ለመደንገግ ፍጹም ንጽህና (ከራስ ወዳድነትና ከጥቅም ግጭት የጸዳ እውነት) እና ፍጹም የበሰለ እውቀት ያስፈልጋል። ይህ ፍጹም ንጽህናና እውቀት ደግሞ የሁሉም ነገር ፈጣሪ የሆነው የአምላክ መገለጫ ነው። የተፈጥሮ ህግ ምንጩ ፍጹም የሆነው መለኮታዊ ጥበብ በመሆኑ መሻሻል አያስፈልገውም። እኛ ሰዎች ግን ማህበራዊ ህጎችን ስናወጣ ፍጹም ንጽህና (ከቡድንና ከግል ጥቅም የጸዳ) እና የበሰለ እውቀት (የማህበረሰቡን ስነ-ልቦና፣ ታሪክና የወደፊት እጣ ፈንታ ያገናዘበ) ሊኖረን እንደሚገባ የተፈጥሮ ህግ ያስተምረናል። ፍጹም እውቀት ሳይኖር የሚወጣ ህግ ሁልጊዜም ጎደሎና ተሻሻይ ነው።
2. የኮስሞስ ምስክርነት እና የተፈጥሮ ህግጋት መገለጫዎች
የተፈጥሮ ህግጋት የማይለወጡና የማይደክሙ መሆናቸውን በዙሪያችን ባለው ዓለም በተግባር እንረዳለን፡
• የፀሐይ ብርሃንና ኃይል፦ ፀሐይ በየቀኑ የምትሰጠው የብርሃንና የሙቀት ኃይል መቼም ቢሆን አያልቅም። ይህ ጽኑ ህግ ማሻሻያ አያስፈልገውም።
• ብርሃን፣ ጨለማና የፀሐይ ዙረት፦ መሬትና ፕላኔቶች በፀሐይ ዙሪያ የሚያደርጉት ስልታዊ ዙረት የቀንና የሌሊት (የብርሃንና የጨለማ) ኡደትን ይፈጥራል። ይህ የስነ ፈለክ ህግ ሳይዛነፍ ለዘመናት የጸና ነው።
• የህይወት ኡደት (መወለድ፣ መኖር፣ መሞት)፦ ማንኛውም እንስሳም ሆነ እጽዋት ይወለዳል፣ ይኖራል፣ ይሞታል። የእነሱ የእንትንፋስና የህልውና ህግ ማንም ሰው ሊሽረው የማይችል የተፈጥሮ ዑደት ነው።
3. የሳይንስ ህግጋት ጽኑነት (ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪና ባዮሎጂ)
በሳይንስ ዓለም ውስጥ የምናገኛቸው ህጎች የሰው ልጅ የደረሰባቸው የተፈጥሮ እውነታዎች እንጂ ሰዎች የፈጠሯቸው አይደሉም። ለዚህም ነው የማይሻሻሉት፡
• የፊዚክስ ህግ (የኃይል ጥረት ህግ)፦ በፊዚክስ ትልቅ ስፍራ ያለው ህግ "ኃይል (ኢነርጂ) አይፈጠርም፣ አይጠፋምም፤ ከአንድ ቅርጽ ወደ ሌላ ቅርጽ ይለወጣል እንጂ" (Energy is neither created nor destroyed, it can only be transformed from one form to another) ይላል። ይህ ህግ ከዘላለም እስከ ዘላለም የማይሻሻል የተፈጥሮ እውነት ነው።
• የኬሚስትሪና ባዮሎጂ ህግጋት፦ ውሃ ሁልጊዜ ከሁለት ሀይድሮጅንና ከአንድ ኦክስጅን (H₂O) ይፈጠራል። የሰው ልጅ ስነ-ህይወታዊ (Biological) መዋቅር፣ የደም ዝውውርና የሴሎች ኡደት በተመሳሳይ ጽኑ ህግ የሚመሩ ናቸው። እነዚህ የሳይንስ ህጎች የሰው ልጅ ህግጋት ምን ያህል ደካማና ተለዋዋጭ እንደሆኑ ትልቅ ማስረጃዎች ናቸው።
4. "አዳም አትብላ"፦ የመጀመሪያው ህግ፣ ሞት፣ ካሳ እና ህይወት
በትዕዛዝ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው ህግ ለአዳም የተቀመጠው "ይህን ዕፅ አትብላ፣ ሌላውን ግን ብላ" የሚለው መለኮታዊ ህግ ነበር። ይህ ክስተት የህግን መዋቅር ፍልስፍናዊ በሆነ መንገድ ያሳያል፡
• ህግ (Law)፦ ድንበርንና ክልከላን ያስቀምጣል። "አትብላ" መባሉ የህግ የበላይነትን ያሳያል።
• ሞት (Death)፦ ህግ ሲጣስ የሚመጣውን ፍጹም ቅጣትና ውጤት ያመለክታል። አዳም ህጉን በመጣሱ ምክንያት ሞት ወደ ዓለም ገባ።
• የሞት ካሳ (Compensation for Death)፦ ፍትህ መዛባትን አትፈቅድም። ለተፈጠረው ጥፋትና ሞት ተመጣጣኝ የሆነ የካሳ ወይም የቤዛነት ህግ አስገዳጅ ሆነ።
• ህይወት (Life)፦ ከካሳውና ከፍትህ መረጋገጥ በኋላ የሚመጣውን አዲስ ተስፋና ህይወትን ያሳያል። ይህ ዑደት ህግ የራሱ የሆነ የውጤትና የፍትህ ሚዛን ማስጠበቂያ ሰንሰለት እንዳለው ያስገነዝበናል።
5. የሰው ልጅ ህግጋት ተለዋዋጭነት (የምዕራባውያን አገራት ማሳያ)
ከተፈጥሮ ህግ በተቃራኒ፣ በሰዎች የሚወጣ ህግ ሁልጊዜም ተለዋዋጭ ነው። የሰዎች ህግ የመንግስታት ስልጣን በየጊዜው ሲቀያየር፣ የመሪዎች ወንበር ሲናወጥና እንደየአስፈላጊነቱ አብሮ ይለወጣል። ለአብነት ያህል የታላላቅ ምዕራባውያን አገራትን ህግ መመልከት ይቻላል፡
• የአሜሪካ ህግ (United States)፦ የአሜሪካ ህገ-መንግስት ከተረቀቀ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከ27 ጊዜ በላይ ማሻሻያ (Amendments) ተደርጎበታል። ይህም የሰዎች ህግ ፍጹም ባለመሆኑ በየጊዜው መታረም እንዳለበት ያሳያል።
• የካናዳ ህግ (Canada)፦ የካናዳ የህግ ስርዓትም እንደ ማህበረሰቡ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ፍላጎት በየጊዜው ማሻሻያዎችንና አዳዲስ አዋጆችን ያወጣል።
• የእንግሊዝ ህግ (United Kingdom)፦ እንግሊዝ ያልተጻፈ ህገ-መንግስት ያላት አገር ስትሆን፣ ህጎቿ እንደ ፓርላማውና እንደ ገዢው ፓርቲ ፍላጎት በየቀኑ ሊለወጡና ሊሻሻሉ ይችላሉ።
እኛ ሰዎች በህግ አወጣጥ ምን እንማር?
የሰው ልጅ ህግ አውጪዎች ከተፈጥሮ ህግ መማር ያለባቸው ዋናው ቁምነገር፡ ህግ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ወይም ለስልጣን ማራዘሚያ የሚሆን ሳይሆን፣ እንደ ተፈጥሮ ህግጋት ሁሉ ትውልድ ተሻጋሪ፣ ፍትሃዊ፣ ተገማችና ሚዛናዊ መሆን እንዳለበት ነው። ህግ ሲወጣ በጥልቅ እውቀትና ከግል ጥቅም በጸዳ ንጽህና መሆን አለበት። ከተፈጥሮ ህግ (ከሞራልና ከፍትሃዊነት) የራቀ ሰው ሰራሽ ህግ ህግ ሳይሆን የጭቆና መሳሪያ ነው።
ማጠቃለያ
የተፈጥሮ ህግ የማይሻሻለው አስቀድሞ ፍጹም፣ ፍትሃዊና ሚዛናዊ በሆነው መለኮታዊ እውቀትና ንጽህና ስለተሰራ ነው። የሰው ልጅ ህግ ግን የመንግስታት መቀመጥና መነሳት፣ የሰዎች ፍላጎት መቀያየር የሚወስነው ተለዋዋጭ ሂደት ነው። የህግ ባለሙያዎችም ሆኑ ማህበረሰቡ ህግን ሲያወጡና ሲተገብሩ፣ ከተፈጥሮ ህግጋት በስተጀርባ ያለውን ፍጹም ንጽህና፣ የበሰለ እውቀት፣ ተገማችነትና ፍትሃዊነት እንደ መርህ በመውሰድ፣ የሰዎች ህግም ለዘላቂ ትውልድና ለፍትህ መከበር የሚቆም እንዲሆን ማድረግ ይኖርባቸዋል።
ማጣቀሻዎች
• ቅዱስ መጽሐፍ (መጽሐፍ ቅዱስ)፦
o "ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም" (ማቴዎስ 24:35) — መለኮታዊና የተፈጥሮ ህግጋት የማይለወጡ መሆናቸውን ያሳያል።
o "በገነት ካለው ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ..." (ዘፍጥረት 2:16-17) — የመጀመሪያው ህግ፣ ክልከላ እና የሞት ውጤት ምሳሌ።
• ቅዱስ ቁርዓን፦
o "በአላህ የፍጥረት ህግ ላይ ምንም ለውጥ አታገኝም፤ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው" (ሱረቱ አል-ሩም 30:30) — ፍጥረት የተገነባበት የተፈጥሮና የመለኮት ህግ ጽኑና የማይቀየር መሆኑን ያስረዳል።
• የትላልቅ ሰዎች ፍልስፍና፦
o ሶክራትስ (Socrates)፦ ህግ ከጽንሰ-ሃሳባዊ ፍትህና ከሞራል እሴት መነጨት እንዳለበትና ፍጹም እውቀትን መፈለግ የህግ መሠረት መሆኑን አስተምሯል።
o ፕላቶ (Plato)፦ "ሪፐብሊክ" (The Republic) በተሰኘው መጽሐፉ ላይ አገሪቱን የሚመሩና ህግ የሚያወጡ ሰዎች ጥበብና የበሰለ እውቀት ያላቸው "ፈላስፋ ነገሥታት" (Philosopher Kings) መሆን እንዳለባቸውና ይህም የህግን ንጽህና እንደሚያስጠብቅ ገልጿል።
o አሪስጣጣሊስ (Aristotle)፦ የተፈጥሮ ፍትህ (Natural Justice) በሁሉም ቦታ እኩል ኃይል አለው፣ ሰዎች ስላጸደቁት ወይም ስላልተቀበሉት አይለወጥም በማለት የሰው ልጅ ህግ ከተፈጥሮ ህግ ጋር መጣጣም እንዳለበት ተከራክሯል።
https://www.facebook.com/s...
በፋንታሁን ደለለው (Fantahun Delelew)
ህግ አዋቂ (Lawyer)
ስልክ፦ 0929101037

1 month ago
የለውጡ ዘመን የትውልድና የሀገር አቅጣጫ የተወሰነበት የእመርታ መሰረት ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የለውጡ ዘመን የትውልድና የሀገር አቅጣጫ የተወሰነበት የእመርታ መሰረት ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርና ሚኒስቴር በተካሄደው የእመርታ ቀን አከባበር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዕለቱ ኢትዮጵያ ከፈተና ወደ ዕድል፣ ከጥገኝነት ራስን ወደ መቻል፣ ከተረጂነት ወደ አምራችነት እየተሸጋገረች ያለችበትን ታሪካዊ ምዕራፍ የምናበስርበት ነው ብለዋል።
ባለፉት ዓመታት በሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በመመራት የተካሄዱ ሪፎርሞች የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ መሰረት ማጠናከራቸውን ተናግረዋል።
በምግብ ሉዓላዊነት ዘርፍ አኩሪ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ በመስኖ ስንዴ፣ በሩዝ፣ በበቆሎና በሌሎች ሰብሎች ልማት የተገኙ ስኬቶች በብርታታችን ያጨድናቸው የትጋታችን አዝመራዎች ናቸው ብለዋል።
ፈጠራ እና ፍጥነት እሴቶቹ የሆኑት የመደመር መንግሥት የጀመራቸው የሌማት ትሩፋት ፍሬዎች፣ የክላስተር እርሻና የዘመናዊ ግብርና አሰራሮች ተግባራዊነት ኢትዮጵያ የራሷን ምግብ የማምረት አቅሟን አሳይተዋል ነው ያሉት፡፡
የምግብ ሉዓላዊነት ለእኛ የልማት ግብ ብቻ ሳይሆኑ፤ የነፃነታችን፣ የክብራችንና የፅናታችን ማረጋገጫ ደማቅ የትውልዳችን ማህተም ጭምር ናቸው በማለት አውስተዋል፡፡
በተጨማሪም በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን በቱሪዝምና በዲጂታል ዘርፎች የተሰራው የፖሊሲና የአመራር ለውጥ የኢትዮጵያን አዲስ አሻጋሪ ምዕራፍ መክፈታቸውን ጠቅሰዋል።
የመደመር መንግሥት በጀመራቸው ዘርፎች ሁሉ የታየው የዛሬው እመርታችን የትናንት ቁርጠኝነታችን ፍሬ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከፍታችንም የዛሬ ትጋት ውጤት እንደሚሆን አመልክተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የመደመርን ጎዳና በመተለም፤ እያመረተች፣ እየተለወጠችና እያንሠራራች ነው ብለዋል፡፡
ይህንን የእመርታ ቀን የስኬቶቻችን ማሳያ ብቻ ሳይሆን፤ ወደሚቀጥለው ከፍተኛ የዕድገት ማዕረግ ለመሸጋገር የጋራ ቃል ኪዳናችንን የምናድስበት ዕለት ልናደርገው ይገባል ብለዋል።
በለይኩን አለም

እኔ አምላክ አይደለሁም" — የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት የፎቶግራፋቸውን በቢሮዎች እንዳይሰቀል አዘዙ
ውሳኔው አወዛጋቢ ስሜቶችን ጭሯል የሴኔጋሉ የ44 ዓመት ወጣት ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፌይ (Bassirou Diomaye Faye) የመንግሥት ባለሥልጣናትና ሠራተኞች የእሳቸውን ምስል በቢሮዎቻቸው ውስጥ እንዳይሰቅሉ ማገዳቸው ተሰማ።
ፕሬዝዳንቱ ውሳኔአቸውን ሲያብራሩ፡ "ፎቶግራፌ በየቢሮዎቻችሁ ውስጥ እንዲሰቀል አልፈልግም። እኔ አምላክ ወይም የሚመለክ ምስል አይደለሁም፤ የሕዝብ አገልጋይ እንጂ። በምትካቸው ውሳኔዎችን በሚታስተላልፉበት ወቅት ሁሉ እንዲታዩአችሁ የልጆቻችሁን ፎቶዎች ስቀሉ" ብለዋል።
የፕሬዝዳንቱ እርምጃ መልካም አስተዳደርን በግልጽነትና በሥነ-ምግባር ላይ ለመመሥረት ያለመ መሆኑ ቢደነቅም፣ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ ግን ለየት ያሉ አስተያየቶችን አስተናግዷል።
በአንድ በኩል፣ ወጣቱ መሪ የፕሬዝዳንትነትን ወንበር ከግል ስብዕና አምልኮ (personal idolization) ነፃ በማድረግ ለአገልግሎት ትኩረት መስጠታቸው የሚደነቅ ነው ሲሉ አድናቆታቸውን የገለጹ አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ፣ የሀገር መሪ ፎቶግራፍ በሕዝባዊ ተቋማት ውስጥ መሰቀሉ ለአመራሩ የሚሰጥ ግላዊ አምልኮ ሳይሆን፣ የተቋሙንና የሀገሪቱን ልዑላዊነት እንዲሁም ክብር የሚያንፀባርቅ ባህላዊ አሠራር በመሆኑ ውሳኔው የፕሬዝዳንትነቱን ማዕረግ ግርማ ሞገስ እንዳይቀንሰው የሚሉ ሥጋቶች ተንፀባርቀዋል።
ይሁን እንጂ ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ባለሥልጣናት ከግል ገጽታ ግንባታ ይልቅ ለወደፊቱ ትውልድና ለልጆቻቸው መልካም ሀገር የማስረከብ ኃላፊነታቸውን እንዲያስታውሱ ያስተላልፉት መልእክት በብዙዎች ዘንድ አዲስ የፖለቲካ ባህል መነሻ ተደርጎ እየተወሰደ ይገኛል።

ጥሪ ለዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን
ይህ የድሃ ኢትዮጵያውያን ህዝብን ብር ያልመዘበረ ንፁህ እጅ ሊሸለም ይገባዋል
ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ጋር በተደረገው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አስቸጋሪ ድርድር ወቅት የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በፅናት የተሞገቱትንና የዲፕሎማሲያዊ ግምባር መሪ የነበሩትን የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ዛሬ በስደት ሀገር በተራ የመኪና ማቆሚያ ስራ ላይ ተሰማርተው ማየት በእጅጉ የሚያሳዝንና የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነው።
በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ በከፍተኛ የስልጣን ማዕረግ ላይ የነበሩ ሰዎች የህዝብን ሀብት ዘርፈው በውጭ ሀገር ባንኮች በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር አካብተው በቅንጡ ህይወት ሲኖሩ ማየት በተለመደበት በዚህ ዘመን፣ አቶ ገዱ በስልጣን ዘመናቸው እጃቸውን ከሙስና እና ከሀገር ሀብት ምዝበራ ያቀቡ ታማኝ መሪ መሆናቸውን ዛሬ በራሳቸው ላብና ጥረት ለመኖር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ህያው ምስክር ነው።
ስለሆነም በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት እና ሀገር ወደድ ወገኖች፣ ይህንን የታማኝነት እና የህሊና ንጽህና አርአያ የሆነ ታላቅ ሰው በሰው ሀገር በጉልበት ስራ እንዲንገላታ መተው የለብንም።
ሀገራቸውን በቆራጥነት ያገለገሉ እና የህዝብን አደራ ያልበሉ ንጹሃን መሪዎችን ማከበርና መደገፍ የታማኝነትን ዋጋ የሚያጎላ ከመሆኑም በላይ ለቀጣዩ ትውልድና ለሌሎች ባለሥልጣናት ትልቅ አስተምህሮ የሚሰጥ ነው።
እኒህ ክቡር ሰው ያላቸውን ከፍተኛ የዲፕሎማሲና የአመራር ልምድ ተጠቅመው የሚገባቸውን የክብር ቦታ እንዲያገኙ፣ ባሉበት ሀገር የግል ቢዝነሳቸውን ማስጀመር የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ በማድረግ እና ተገቢውን የሞራልና ቁሳዊ ድጋፍ በመስጠት ከጎናቸው እንድንቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን።

2 months ago
የአፋልጉኝ ተማጽኖ
#ethiopia | አሊያ ቢፍቱ ቃሌ ትባላለች። ላለፉት 9 ዓመታት ኑሮዋን ለማሸነፍ በሱዳን ካርቱም የቆየች እህታችን፣ በሱዳን ባለው ጦርነት ምክንያት ተፈናቅላ የተለያዩ ጉዳቶች ደርሰውባታል።
በመተማ የሚገኘው IOM ከለላ አድርጎላት ቆይቷል። ባጋጠማት የአዕምሮ ህመም ምክንያት ህክምናዋን ለማስተናገድ ምቹ ሁኔታ ስላልነበር፣ ተቋሙ ከማዕከላችን ጋር ባለው መልካም ግንኙነት ጎንደር ወደሚገኘው “ካለን ብናካፍል” እንድትመጣ ተደርጓል።
ከመጣችበት ጊዜ ጀምሮ በተደረገላት አስፈላጊ ህክምናና እንክብካቤ፣ አሁን ላይ ነገሮችን በማስታወስ መናገር ችላለች።
በዚህም መሠረት ትውልድና እድገቷ በኦሮሚያ ክልል፣ ገደብ አሳሳ ከተማ መሆኑን ገልጻለች።
የቤተሰቦቿ ስም፦
እናቷ፡ ወ/ሮ መዲና ሀሱ ደለቁ
ወንድሞቿ፦
• የሱፍ ቢፍቱ
• አህመድ ቢፍቱ
• ሀጂ ቢፍቱ
• መሀመድ አዎል ቢፍቱ
እህቶቿ፦
• ሙኩ ቢፍቱ
• አሚና ቢፍቱ
• ሲምባ ቢፍቱ
ቤተሰቦቿ ያለችበትን እንዲያውቁ እና እሷም ከናፈቀቻቸው ቤተሰቦቿ ጋር እንድትገናኝ፣ ይህ መልዕክት ለሚመለከተው ሁሉ እንዲደርስ ጥሪ እናቀርባለን።
ለበለጠ መረጃ፦
09 18 82 82 00
09 41 02 03 04
ካለን ብናካፍል የህፃናት፣ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህመም መረጃ ማዕከል
እባክዎ ለቤተሰቦቿ እንዲደርስ Share ያድርጉ!

Sponsored by
Surafel
2 months ago
ክብ ታሪኮች /በቡናዬ እስኪሰክን/
* ገጣሚ ታገል ሰይፉ የቤተ-ማሪያም ተሾመ ቡናዬ እስኪሰክን መፅሐፍ የህይወትና የታሪክ አዙሪቶችን የዳሰሰበት መንገድ
#ethiopia | ይህ እንደሃያሲ መፅሐፉ እንዴት እንደተፃፈ ለመፈተሽ የቀረበ ትንተና አይደለም፡፡ እኔ እንዴት እንዳነበብኩት ለመግለፅ እንጂ…
እንደ እኔ ንባብ ከሆነ የደራሲ ቤተ-ማሪያም ተሾመ “ቡናዬ እስኪሰክን” እንደኦሎምፒክ አርማ በብዙ ህብረ ቀለማዊ ክብ ቀለበቶች የተሞላ መፅሐፍ ነው፡፡
መፅሐፉ በአእምሮ ውስጥ እንደጅረት የሚፈስን ሃሳብ ተከትሎ የሚጓዝ ዓይነት ነው፡፡ በሰው አእምሮ ውስጥ እንደጅረት የሚፈሱት ሃሳቦችና ስሜቶች ከጅረቱ በተቃራኒ ከሚጓዙት ድርጊቶችና ንግግሮች ጋር ትይዩነት አላቸው፡፡ ብዙ ጊዜ እነዚህን የተቃረኑ ቁርኝቶች ጮክ ብለን አናወራቸውም፡፡ በአእምሯችን ሸለቆ ውስጥ ተቀብረው ይፈሳሉ እንጂ…
በዚህ መፅሐፍ ግን በፍሰታቸው ውስጥ የራሳቸውን ክብ እየፈጠሩ ያልፋሉ እንጂ ቀጥ ብለው አይጓዙም፡፡ በአጭሩ ይህ መፅሐፍ የብዙ ክብ ታሪኮች ስብስብ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ክቦቹ ከህይወታችንና ከታሪካችን የተቀዱ ናቸው፡፡
ክብ በሆነ መንገድ ላይ ስንጓዝ የትም አንደርስም፡፡ ከማያቋርጠው ድግግሞሽ የተነሳ ዞረን ዞረን እዛው ነን፡፡ ደራሲው በቡናዬ እስኪሰክን መፅሐፉ ቀጥ ብሎ ወደ ሆነ ግብ የሚያመራ ታሪክ አያሳየንም፡፡ ከዋናው ገፀ ባህሪይ ስሜት እና ፍላጎት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው ታሪኮች የራሳቸውን ክብ እየሰሩ ይጠናቀቃሉ፡፡
ለምሳሌ ሚስቱ ጠዋት ያሳየችውን የተሸመደደ ጠባይ ማታም ትደግመዋለች፡፡ በማለዳው የቡና ስኒ የተጀመረው ታሪክ ዞሮ ዞሮ እዚያው ሲኒ ላይ ያከትማል፡፡ በታሪኩ መጀመሪያ አካባቢ የአደጋ ማስጠንቀቂያ የደረሰው ሰውዬ መጨረሻ ላይ አደጋውን ያስተናግዳል፡፡ በአስመራው ባሬስታ ላይ የደረሰው ነገርም በለሚ ኩራው ባሬስታ ላይ ይደገማል፡፡ የጀብሎዎቹና የሊስትሮዎቹ ምሬትና አመፅም በሀገሪቱ ግዙፍ የታሪክ አዙሪት ተውጦ ይቀራል፡፡ የአታክልቲ መጨረሻም እንዲሁ፡፡
መፅሐፉ በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥም ዞሮ ዞሮ ያው የሆነውን የመበላላት አዙሪት ያነሳል፡፡ በኮሎኔል መንግስቱና በእነተፈሪ ባንቴ መካከል የተፈጠረውን… በህወአት አመራሮች የእርስ በእርስ ግጭት የተደገመውንና በቅንጅት መሪዎች የተሰለሰውን የመበላላት አዙሪት ይታዘባል፡፡
የዋናው ባለታሪክ አለም አቀፍ ግንዛቤዎች ጭምር ዞሮ ዞሮ እዛው በሆነ የታሪክ አዙሪት የተዋጡ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ማ ቤከርን ያነሳል፡፡ ቦኒየሞች የዘፈኑላት ማ ቤከር በዘመኗና በመንደሯ የበረታው ግፍና ወንጀል አስመርሯት ከአራት ልጆቿ ጋር አመፅ ማስነሳቷን ይነግረናል፡፡ ድል አድራጊው የማ ቤከርና የልጆቿ ስኬታማ አመፅ የሚጠናቀቀው ግን ያንኑ ግፍና ወንጀል በመድገም ነው፡፡
የስኒውን ምልኪ ጨምሮ በቡናዬ እስኪሰክን ደጋግመን የምናገኛቸው እንደ ውርርድ፣ እጣ ፋንታና የአርባ ቀን እድል ዓይነት ቃላት ራሳቸው የክብነት ባህሪይ አላቸው፡፡ ንግርት ሁሌም የሚነግርህ የፈለግከውን ያክል ብትፍጨረጨር ከተፃፈልህ እጣ ፋንታ እንደማታመልጥ ነው፡፡
የሰው ልጅ የሚሆነውን ነገር ለምን እንደሚሆን የሚረዳበት አእምሮ እና ተጨባጭ ምክንያት ሲያጣ የምልኪ ፣ የጥንቆላና የአርባ ቀን እድል ሰለባ ይሆናል፡፡ በማይቆጣጠረው የህይወት አዙሪት ውስጥም ይወድቃል፡፡
በዚህና በሌሎች ምክንያቶች የተፈጠረው የሃሳብና የታሪክ አዙሪት መፅሐፉን አሰልቺ አለማድረጉ ይልቁንም ጣእሙን እንዳሳመረ እስከመጨረሻው የመዝለቁ ነገር የፅሁፌ ዋና ጉዳይ ነው፡፡ ይህን የማነሳው አለምክንያት አይደለም፡፡
ብዙ ጊዜ በኢትዮጵያ ስነ-ፅሁፍ ፈር ቀዳጅ የተባሉ አንዳንድ የስነ-ፅሑፍ ሙከራዎች አንባቢን የማታከት ባህሪይ ይታይባቸዋል፡፡ አንዱን ሲይዙት ብዙ ያመልጣቸዋል፡፡ በእኔ እምነት የተሟላ ፈር ቀዳጅ ስራ ነጠላ መልክም ትርጉምም የለውም፡፡ ቢያንስ አምሰት ተጨማሪ ሙላቶች አሉት፡፡ ስድስተኛውም እጅግ ይመረጣል እላለሁ፡፡
-የመጀመሪያው የቋንቋ ውበት ነው፡፡ ቋንቋው ካላማረህ ጀምረህ አትጨርሰውም፡፡ በዚህ መፅሐፍ ዋናው ባለታሪክ ህይወትን አሟጦ ሲኖር አይታይም፡፡ ኑሮን በቀጥታ የመጋፈጥ ድፍረት ይጎለዋል፡፡ በአብዛኛው የታሪኩ ክፍል ሲሸሽ እንጂ ሲያሳድድ አናየውም፡፡ ሌላው ቀርቶ የተላኩለትን ሁለት አጓጊ ደብዳቤዎች እንኳ አንብቦ የመጨረስ ድፍረት የለውም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ዋና ገፀ-ባህሪይ ይዞ ማራኪ ታሪክ መፍጠር ይከብዳል፡፡ ያም ሆኖ የደራሲው ቋንቋ ቀላል እና ውብ ስለሆነ ሳይሰለቸን እንዲያውም ደስ እያለን እናነበዋለን፡፡
-ሁለተኛው የሃሳብ ጉልበት ነው፡፡ በሃሳብ ጥልቀት የዳበሩ መፅሐፎችን ስናሰላስላቸው እንከርማለን እንጂ አንብበን አንጨርሳቸውም፡፡ “እግሮችህ የአንተ ናቸው፡፡ ወዳሻው የሚራመድበት ግን ሌላ ነው” የምትለው የመፅሐፉ ደማቅ አረፍተ ነገር ተነባ የምታልቀው መቼ ነው?
-ሶስተኛው የትውልድና የዘመን ነፀብራቅነት ነው፡፡ አፈወርቅ ገብረ እየሱስ የባሪያ አሳዳሪውን ዘመን… ሃዲስ አለማየሁና ዳኛቸው ወርቁ የፊውዳሉን… በአሉና ብርሃኑ ዘሪሁን የአብዮቱን ዘመን ከነሙሉ ጠረኑና ለዛው እንደፃፉልን ሁሉ ቤተ-ማሪያምም የኮሪደር ዘመኗን አዲስ አበባ ፊልም በሚመስል ትእይንት ያሳየናል፡፡
-አራተኛው ከውስጥ የመነጨ ልዩነት ነው፡፡ ለየት ለማለት ብሎ ከእውነታውም ከችሎታውም ከማንነቱም ከስሜቱም የራቀ ደራሲ ህያው እስትንፋስ ያለው የጥበብ ስራ ሊያቀርብልን መቻሉን እጠራጠራለሁ፡፡ እንዲያውም በእኔ እምነት መለየት የሚባለው ነገር ፈልገህ የምታገኘው ሳይሆን ተለይተህ የምትገኝበት ወይም የምትፈጠርበት ዓለም ነው፡፡ ቤተ-ማሪያም ተሾመ በጠያይም መላእክትም ሆነ በዚህኛው መፅሐፉ ተለይቶ የተፈጠረ ወዛም ደራሲ እንጂ ለመለየት የተፍጨረጨረ ችኮ ብእረኛ ሆኖ አላገኘሁትም፡፡
-አምስተኛው ውስጡ የሰፋ ስስነት ነው፡፡ ራስህ ካልተቆነጠጥክ በቀር ህመም የማይሰማህ ከሆነ አንተ ዳያሪ ፀሃፊ እንጂ የተዋጣለት ደራሲ የመሆን እድልህ ጠባብ ነው፡፡ ለትልቅነት የታጨ ደራሲ በቤቱ ብቻ ሳይሆን በጎረቤቱ… በሰፈሩ ብቻ ሳይሆን በሀገሩ የመጣ ቁንጥጫ ያመዋል፡፡ ከዚያም አልፎ የሰው ልጅ ውጋት ይቀስፈዋል፡፡ ከእኛ ዘመን እና ሀገር የራቁ ታላላቅ ደራሲያን በሌላ ቋንቋ ፅፈው ስሜታቸውን የሚያጋቡብን ከዚህ የተነሳ ነው፡፡ ቤተ-ማሪያም ተሾመ በሰፈሩም በሃገሩም የሚሆነው ነገር የሚሆነውን የሚያሳጣው ዓይነተ ደራሲ መሆኑን ከስራዎቹ መረዳት ችያለሁ፡፡
በዚህ ዓይነት ደረጃ ከመሰጡኝ የሀገራችን ደራሲያን ግን የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ስነ-ፅሁፍ ታሪክ ፈር ቀዳጅ ሆኖ ያገኘሁት ከፍቅር እስከ መቃብር በኋላ ያነበብኩትን የዳኛቸው ወርቁን አደፍርስን ነው፡፡ በአጭር ልብ-ወለድ ዘርፍም ከስብሃት ገብረእግዚአብሔር በኋላ ያነበብኳቸው የአዳም ረታ አጫጭር ልብ -ወለዶች በእኔ እይታ የኢትዮጵያ ስነ-ፅሁፍ ፈር ቀዳጅ ስራዎች ናቸው፡፡ በተለይ አለንጋና ምስር ውስጥ ያሉት…
ከእነዚህ ሁለት ታላላቅ ደራሲያን ስራዎች በኋላ በተሟላ ሁናቴ ፈር ቀዳድ ሆኖ ያገኘሁት የቤተ-ማሪያም ተሾመን ቡናዬ እስኪሰክን ነው፡፡
ቤተ-ማሪያም በዚህ መፅሐፉ ከተጠቀማቸው ቃላት በላይ ብዙ ፅፏል፡፡ በበኩሌ አንድን ስራ ምርጥ ስነ-ፅሁፍ ከምልባቸው ምክንያቶች ስድስተኛው በትንሽዬ መፅሐፍ ውስጥ ብዙ ሺህ ገፆች ሲያስነብበኝ ነው፡፡
ለጆርጅ ኦርዊል አኒማል ፋርም… ለሚካኤል ቡልጋከቭ ሳባቺዬ ሴርሴ… ለሄሚንጉዌይ ሽማግሌውና ባህሩ… ለቼሆቭ ዋርድ ነበር ሲክስ… ለቶልስቶይ የኢቫን ኤሊይች እረፍት… ለአልበርት ካሙ ባይተዋር… ከፍተኛ አድናቆት ያለኝ ከዚህ የተነሳ ነው፡፡
ቡናዬ እስኪሰክን ከላይ ከገለፅኳቸው መፅሐፎች ጋር የሚመጣጠን ልዩ እርካታ ፈጥሮብኛል፡፡ በእያንዳንዱ አዙሪት እያሽከረከረ እኛንም ዘመናችንንም ሀገራችንንም በጥልቀትና በድምቀት ያሳየ ስራ በመሆኑ…
በነገራችን መሀል በቤተ-ማሪያም ተሾመ ቡናዬ እስኪሰክን የክብ ታሪኮች ጅረት የመጨረሻ ገፅ ላይ ያሉት የመጨረሻዎቹ ሁለት መጠይቃዊ ቃላት ራሳቸው አዙሪቱ የፈጠረውን ተደጋጋሚ ክብ አሳስበውኛል፡፡
“… ተጀመረ? ወይስ ተፈፀመ? …” ይላሉ፡፡
ህይወትም ታሪክም ፖለቲካም ክብ ሲሆንብህ እንዲህ ትጠይቃለህ፡፡
ክቡ የት ጋ እንደሚጀምር አታውቅም፡፡ የት ጋ እንደሚጠናቀቅ ጭምር፡፡
#bunaeeskisekin #betemariamteshome #ethiopianliterature #amharicbooks #ethiopianwriters #bookreview #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago
“በጋና አክራ ከተማ የሚገኘውን ታሪካዊውን የክዋሜ ንክሩማህ መታሰቢያ ፓርክን ጎብኝተናል” - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
*********************
“በጋና አክራ ከተማ የሚገኘውን ታሪካዊውን የክዋሜ ንክሩማህ መታሰቢያ ፓርክን ጎብኝተናል፤ በሐውልታቸው ሥርም የአበባ ጉንጉን አኑረናል” ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ስፍራው የጋና የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት እና የፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ የዶክተር ክዋሜ ንክሩማህ እንዲሁም የባለቤታቸው የፋቲያ ንክሩማህ መካነ መቃብርና ታሪካዊ ሙዚየምን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል።
ጋናውያን ለአፍሪካ ነፃነትና አንድነት አቀንቃኙ መሪያቸው ግዙፍ ሐውልት መታሰቢያ መገንባታቸው የቀደሙትን ማክበር ለትውልድና ለሀገር ግንባታ ያለውን ሚና ያሳያል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባጋሩት መልዕክት።
ዶ/ር ክዋሜ ንክሩማህ ለጋና ነፃነት ብቻ ሳይሆን፣ ሙሉ አፍሪካ ከቅኝ ግዛት ነፃ እንድትወጣ የነበራቸው ራዕይ ዛሬም ድረስ ለትውልዱ ትልቅ የብርታት ምንጭ ነውም ብለዋል።
በተለይም ከኢትዮጵያ ጋር የነበራቸው ጥብቅ ወዳጅነት እና ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኑ አፍሪካ ኅብረት) መመስረት ያበረከቱት አስተዋጽኦ ሁልጊዜም በክብር የሚታወስ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

''የውቦች ንግስት''
በምህረት
#Ethiopia | ምህረት ደግፍ ትውልድና እድገቷ አዲስ አበባ ፤ በልዩ ስሙ ኮልፌ 18 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በሐምሌ 19 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፣ ሁለተኛ ደረጃን በየካቲት 23 ት/ቤት ፣ የመሰናዶ ትምህርቷን ደግሞ በአዲስ ከተማ መሰናዶ ተከታትላ ጨርሳለች።
ቀጥሎም በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት በመመረቅ ትምህርቷን ያጠናቀቀች ሲሆን ፤ በአሁኑ ወቅትም በዚሁ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እና ሥነ-ጽሑፍ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ ናት።
የጋዜጠኝነት ሞያን ከከፍታ የትምህርት ሥልጠና እና የማማከር ተቋም ያጠናቀቀች ሲሆን ፤ በፋክት ቼኪንግ እና ሌሎችም ተያያዥ ሥልጠናዎችን ከሌሎች የሃገር ውስጥ እና የውጪ ተቋማት በሰርተፊኬት ማግኘት ችላለች።
ከመደበኛው ትምህርት ባሻገር ሙሉ የልጅነት ሕይወቷ ያለፈው በደብረ ገሊላ አማኑኤል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ትምህርት ቤት ነው። አሁን ላለችበትም መሰረት የጣለችው ሰንበት ትምህርት ቤት በነበረችበት ወቅት ነው። በተለይም በሥነ-ጽሑፍ ረገድ ዝንባሌ ሊኖራት የቻለው ከልጅነት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤት እና በመደበኛ ት/ቤት በነበራት ተሳትፎ ነው። እንደ ግጥም ፣ መነባንብ ፣ ድራማ እና ሌሎችም ላይ የበዛ ተሳትፎ ታደርግ ነበር። ይህ ተሳትፎ አሁንም ድረስ ተከትሏት በመምጣት ለፍሬ እንደደረሰ ታምናለች።
በት/ቤት ፣ በወረዳ እና በክፍለ ከተማ ብሎም በከተማ አቀፍ በነበሩ የሥነ-ጸሑፍ ውድድሮች ፣ መድረኮች እና መሰል ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ የተለያዩ ሽልማቶችን እና የምስጋና ወረቀቶችን ማግኘት ችላለች። በመንፈሳዊም በኩል በተመሳሳይ ሁኔታ በነበሯት ተሳትፎዎች በርካታ ሽልማቶችን አግኝታለች። እስከዛሬ ድረስም በተለያዩ የሥነ-ጸሑፍ መድረኮች ሥራዎቿን እያቀረበች ትገኛለች።
ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንደተመረቀች በአጼ ፋሲል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለሁለት ዓመት ያህል በመምህርነት አገልግላለች። በሞያው በቆየችባቸው ጥቂት ዓመታት የተለያዩ የምስጋና እና የደረጃ ሽልማቶችን ማግኘት ችላለች።
ከዚያ በመቀጠል በተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ለአንድ ዓመት ያህል በፕሮግራም አዘጋጅነት የሠራች ሲሆን ፤ የራሷን መንፈሳዊ ፕሮግራሞች እና ሥራዎች በመሥራት ቆይታለች። በአሁኑ ወቅት በሐገሬ ቴሌቪዥን በከፍተኛ ሪፖርተርነት መደብ እየሠራች የምትገኝ ሲሆን ፤ ላለፈው አንድ ዓመት ያህል በዚሁ ጣቢያ የዜና ክፍል ባልደረባ በመሆን ቆይታለች።
ከልጅነት ጀምሮ የተከተላት የሥነ-ጽሑፍ ፍቅር አሁንም ድረስ ተከትሏት የመጣ ሲሆን ፤ የመጀመሪያ የሆነውንና ” የውቦች ንግሥት” ስትል የሰየመችውን መጽሐፏን ለአንባቢያን ለማድረስ ዝግጅቷን አጠናቃለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የሀብት ማሰባሰቢያ ንቅናቄ በይፋ ጀመረ!
#fastmereja :- የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና የሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ ተቋማዊ አቅማቸውን ለማሳደግና ዘላቂ የልማት ፕሮጀክቶችን ለመተግበር ያለመ ታሪካዊ የሀብት ማሰባሰቢያ ንቅናቄ በይፋ መጀመራቸውን አስታወቁ።
ንቅናቄው ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ኤሊያና ሆቴል በተካሄደ ደማቅ መርሐ ግብር የተበሰረ ሲሆን፣ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የገዳሙ ፍሬዎች፣ የሃይማኖት ማኅበራት ተወካዮች፣ ምዕመናንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ይህ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ንቅናቄ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ የገዳሙን ተማሪዎች፣ ወዳጆችና በጎ ፈቃደኞችን በአንድ ራዕይ በማሰባሰብ የገዳሙን የትምህርትና የማኅበራዊ አገልግሎት ሥራዎች ለማስፋፋት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህ ንቅናቄ አማካኝነት ተግባራዊ የሚደረጉ ዋና ዋና ፕሮጀክቶች ይፋ የተደረጉ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በዲፕሎማ ደረጃ ትምህርት እየሰጠ የሚገኘውን የመንፈሳዊ ሥራ አመራር ኮሌጅ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማሳደግ ዋነኛው መሆኑ ተጠቅሷል።
ከዚህ በተጨማሪም የካህናትና የሰባኪያን ሥልጠናን በኦሮምኛ፣ በሌሎች የአገር ውስጥ ቋንቋዎችና በእንግሊዝኛ መስጠት፣ ወላጅ ያጡ ሕፃናትን የመቀበል አቅምን ማሳደግ፣ እንዲሁም የአገልግሎትና የፋይናንስ ተቋሙን በዘላቂነት ለመደገፍ በአዲስ አበባ ከተማ ቋሚ የገቢ ምንጭ የሚሆን ዘመናዊ ሁለገብ ሕንፃ (Mixed-Use Building) መገንባት የሚሉት ይገኙበታል።
የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ባስቆጠረው አገልግሎቱ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ መንፈሳዊ ብቃትና አመራርን ያጣመሩ መሪዎችን በማፍራት የሚታወቅ አንጋፋ ማዕከል ነው።
ከተቋሙ የፈሩ ከ17 በላይ ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ከፍተኛ ኃላፊዎችና የወንጌል አገልግሎት መሪዎች በአሁኑ ወቅት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በብቃት በማገልገል ላይ እንደሚገኙ ተመላክቷል።
የገዳሙ ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ ተቋሙ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ መሪነት የተማረው ትውልድና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመጡ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ሲሆን፣ ይህ እንቅስቃሴ በቀጣይ ለማኅበረ ቅዱሳን መመሥረት መሠረት የጣለ እንደሆነም የተገለፀዉ።
ገዳሙ ይህንን ትውልድ ተሻጋሪና ዘላቂ በጎ ቅርስ ለማንጽ የተጀመረውን የልማት ፕሮጀክት በገንዘብ፣ በእውቀትና በሙያ ይደግፉ ዘንድ ለሁሉም የገዳሙ ፍሬዎች፣ ምዕመናን፣ ባለሀብቶችና የልማት አጋሮች የከበረ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን ይህ በተለያዩ መርሐ ግብሮች የተዋቀረው የሀብት ማሰባሰቢያ ንቅናቄ እስከ መጪው ታኅሣሥ 19 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

4 months ago
ሰላም….ደህና አመሻችሁ?
ወደፊት ሊመጡ የሚችሉ ክስተቶችን እንተንብይ፡፡ እድሎችን እና ፈተናዎችን እንደ ሀገር ቀድመን እንረዳ፤ ሀገር ለማዳንና ለመገንባት ዛሬ እንዘጋጅ፡፡
ይህ እሳቤ እንደ ማህበረሰብ ካለፈው ተምረን፣ የዛሬን ተጨባጭ ሁኔታ አገናዝበን፣ ዘላቂ የነገን ህይወት እንድንገነባ ያስችለናል፡፡
ሀገራችን በትውልድ ቅብብሎሽ እኛ ጋር ደርሳለች፡፡ አሁን እኛ አደራ ተሸካሚዎች ነን፡፡
ከትናንቱ ትውልድ ሀገር የሚያሻግሩና የሚያሰባስቡንን ትርክቶች እንውረስ፡፡
ለጊዜያዊ ጥቅም ሳይሆን፣ ለነገው ትውልድና ለዘላቄታው እናስብ፡፡
በየዘመናቱ ሀገር ለማሻገር ዘላቂ ተቋማትን የመገንባት ትልሞች ነበሩ፡፡ ነገር ግን በውጭ ጫና እና በውስጥ ችግሮች የተነሳ እየጎተቱን ጠንካራ ማህበራዊ እና ህጋዊ ሥርዓቶችን መዘርጋት ተስኖን እስከ ዛሬ የቤት ሥራ ሆኖብን እየታገልን እንገኛለን፡፡
ይህ ደግሞ በየጊዜው ለሚመጡ ፈተናዎች ጊዜያዊ መፍትሄ ላይ እንድናተኩር እና ቀልባችንን ሰብሰብ አድርገን ሀገረ መንግሥት ግንባታ ላይ እንዳናደርግ አድርጎናል፡፡
በሌላ መልኩ ድህነታችን ስለ ነገ ከማሰብ ይልቅ ለዕለት ጉሮሯችን ብቻ እንድንጨነቅ ሲያደርገን ቆይቷል፡፡ ይህ ደግሞ ተደጋጋሚ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን እያስተናገድን በየጊዜው አለመረጋጋት ውስጥ እንድንቆይ አስገድዶናል፡፡
እናማ አሁን ያ ጊዜ ሊያልፍ እና ልንነቃ ይገባናል!
ሀገራችንን መጠበቅ የእኛ የአሁኖቹ ትውልድ ድርሻ ነውና፡፡ አንድነታችንን፣ ሰላማችንን፣ ሉዓላዊነታችንን እና ደህንነታችንን የማስከበር ኃላፊነት አለብን፡፡ እነዚህን ማስከበር የፀጥታው አካል ስራ ብቻ ሳይሆን፣ የእኛ የዜጎች የእያንዳንዳችን የዕለት ተዕለት ተግባር እና ግዴታ መሆን አለበት፡፡ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተሳትፏችንን እንዳሳየነው ሁሉ፣ በሀገራችን ጉዳዮች በንቃት ስንሳተፍ ኢትዮጵያ ውስጣዊና ውጫዊ አደጋዎችን በቀላሉ መቋቋም ትችላለች።
ታዲያ እኛ እንደ ህዝብ ምን እናድርግ?
• ሀገራችንን እንጠብቅ!
ሀገር መጠበቅ የመንግሥት የሥራ ድርሻ ብቻ አይደለም፡፡ ለደህንነታችን ዘብ እንቁም፡፡ የአካባቢያችንን ሰላም በጋራ መጠበቅ እና አጠራጣሪ ድርጊቶችን ለህግ አስከባሪዎች በፍጥነት ማሳወቅ ይገባናል፡፡ ይህ የዜግነት ግዴታችንም ነው፡፡
• አንድነታችንን እናጠናክር!
ለከፋፋይ አስተሳሰቦች ጆሮ አንስጥ፡፡ ማህበራዊ ትስስራችንን የሚያላሉ የጥላቻ ንግግሮችን እና የህዝብ ለህዝብ ግጭቶችን መከላከል አለብን። አንዳችን ለሌላችን ጋሻ ነን፡፡ የተለየ አስተሳሰብ፣ ብሔር እና ሃይማኖት ሊኖረን ይችላል፡፡ ይህ ውበት እንጂ የሚያራርቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ በመከባበር ለመኖር፣ የሀገርን ሰላም የሚነሱ ዋልታ ረገጥ ትርክቶችን እንከላከል፤ ማህበራዊ አንድነታችንን እናረጋግጥ፡፡ ያኔ ጠላቶቻችንም መግቢያ ቀዳዳ ያጣሉ፤ እኛም ሰላም እንሆናለን፡፡
• ብልሹ አሰራሮችንና ሙስናን እንዋጋ!
በየመስካችን በታማኝነት እንሥራ! እኛም ህጋዊ አሰራሮችን ብቻ እንከተል፡፡ ግብራችንንም በታማኝነት እንክፈል፡፡ ህግን አክብረን እናስከብር፡፡
• በራሳችን ምርት እንኩራ!
የሀገር ውስጥ ምርቶችን በመጠቀም እና ኮንትሮባንድን በመከላከል የሀገር ኢኮኖሚን ከውድቀት እንጠብቅ።
• የህዝብ መሠረተ ልማቶችን ከውድመት እንከላከል፡፡
የልማት ተቋማትን እንንከባከብ፡፡ ዛሬ የእኛ ናቸው፣ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ነገ ደግሞ ለቀጣዩ ትውልድ ይሻገራሉ፡፡ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት እናቆይ፡፡
ኑ፤ ሀገር እንሥራ!

ምሕረት ደግፍ ትውልድና እድገቷ አዲስ አበባ ፤ በልዩ ስሙ ኮልፌ 18 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በሐምሌ 19 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፣ ሁለተኛ ደረጃን በየካቲት 23 ት/ቤት ፣ የመሰናዶ ትምህርቷን ደግሞ በአዲስ ከተማ መሰናዶ ተከታትላ ጨርሳለች። ቀጥሎም በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት በመመረቅ ትምህርቷን ያጠናቀቀች ሲሆን ፤ በአሁኑ ወቅትም በዚሁ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እና ሥነ-ጽሑፍ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ ናት።
የጋዜጠኝነት ሞያን ከከፍታ የትምህርት ሥልጠና እና የማማከር ተቋም ያጠናቀቀች ሲሆን ፤ በፋክት ቼኪንግ እና ሌሎችም ተያያዥ ሥልጠናዎችን ከሌሎች የሃገር ውስጥ እና የውጪ ተቋማት በሰርተፊኬት ማግኘት ችላለች።
ከመደበኛው ትምህርት ባሻገር ሙሉ የልጅነት ሕይወቷ ያለፈው በደብረ ገሊላ አማኑኤል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ትምህርት ቤት ነው። አሁን ላለችበትም መሰረት የጣለችው ሰንበት ትምህርት ቤት በነበረችበት ወቅት ነው። በተለይም በሥነ-ጽሑፍ ረገድ ዝንባሌ ሊኖራት የቻለው ከልጅነት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤት እና በመደበኛ ት/ቤት በነበራት ተሳትፎ ነው። እንደ ግጥም ፣ መነባንብ ፣ ድራማ እና ሌሎችም ላይ የበዛ ተሳትፎ ታደርግ ነበር። ይህ ተሳትፎ አሁንም ድረስ ተከትሏት በመምጣት ለፍሬ እንደደረሰ ታምናለች።
በት/ቤት ፣ በወረዳ እና በክፍለ ከተማ ብሎም በከተማ አቀፍ በነበሩ የሥነ-ጸሑፍ ውድድሮች ፣ መድረኮች እና መሰል ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ የተለያዩ ሽልማቶችን እና የምስጋና ወረቀቶችን ማግኘት ችላለች። በመንፈሳዊም በኩል በተመሳሳይ ሁኔታ በነበሯት ተሳትፎዎች በርካታ ሽልማቶችን አግኝታለች። እስከዛሬ ድረስም በተለያዩ የሥነ-ጸሑፍ መድረኮች ሥራዎቿን እያቀረበች ትገኛለች።
ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንደተመረቀች በአጼ ፋሲል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለሁለት ዓመት ያህል በመምህርነት አገልግላለች። በሞያው በቆየችባቸው ጥቂት ዓመታት የተለያዩ የምስጋና እና የደረጃ ሽልማቶችን ማግኘት ችላለች።
ከዚያ በመቀጠል በተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ለአንድ ዓመት ያህል በፕሮግራም አዘጋጅነት የሠራች ሲሆን ፤ የራሷን መንፈሳዊ ፕሮግራሞች እና ሥራዎች በመሥራት ቆይታለች። በአሁኑ ወቅት በሃገሬ ቴሌቪዥን በከፍተኛ ሪፖርተርነት መደብ እየሠራች የምትገኝ ሲሆን ፤ ላለፈው አንድ ዓመት ያህል በዚሁ ጣቢያ የዜና ክፍል ባልደረባ በመሆን ቆይታለች።
ከልጅነት ጀምሮ የተከተላት የሥነ-ጽሑፍ ፍቅር አሁንም ድረስ ተከትሏት የመጣ ሲሆን ፤ የመጀመሪያ የሆነውንና ” የውቦች ንግሥት” ስትል የሰየመችውን መጽሐፏን ለአንባቢያን ለማድረስ ዝግጅቷን አጠናቃለች።
Via: Addis Books

ጤና ልክ እንደ ሰላም በጣም አስፈላጊ ነገር ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጤና ልክ እንደ ሰላም በጣም አስፈላጊ ነገር ነው አሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነባው የላፍቶ ሆስፒታል በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በኢትዮጵያ የጤና ፖሊሲ ባለፉት 10 ዓመታት ስንጠቀምት የነበረው ፖሊሲ ቅድሚያ መከላከል ላይ ያተኮረ ነበር፡፡
በዚህም መከላከል እንደተጠበቀ ሆኖ ታመው ከመጡ ማከም የሚለው ሀሳብ ተካትቶበት ፖሊሲው መሻሻሉን አውስተዋል፡፡
ጤና ልክ እንደ ሰላም በጣም አስፈላጊ ነገር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ካላመመን አናውቀውም፤ ሲያመን ነው የምናውቀው ሲሉም አስረድተዋል፡፡
በሽታ ልክ እንደ ጦር ሰራዊት ውጊያ እንደሚፈልግ ጠቅሰው፥ ውጊያው ደግሞ ትጥቅ ይፈልጋል ትጥቁ ደግሞ ምግብ ነው ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች የመመገቢያ ማዕከል የተገነባው ሰዎች መብላት እንዲችሉና ማዕድ ማጋራት ልማድ አንዲሆን ነው ሲሉም አብራርተዋል፡፡
ተማሪዎች ቢያንስ በቀን ሁለቴ መብላት እንዲችሉ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው የሚቸገሩ ሰዎች ስላሉ ይህ ልምምድ መጠናከር አለበት ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ዜጎቿን መርዳትና መመገብ እስክትቸል ድረስ ዜጎች በትብብር ይህንን ችግር ማለፍ ይኖርባቸዋል ነው ያሉት፡፡
ይህንን እያደረግን ስንሄድ የተሟላ ጤንነት ያለው ትውልድና ማህበረሰብ ይፈጠራል ብለዋል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ

7 months ago
#ፍትህአወቅ የወንድወሰን (የሙያ ታሪክ)
በተወዳጅ ሚድያ (ዕዝራ እጅጉ )የተዘጋጀ
#ethiopia | ጋዜጠኝነት የሚድያ ሰው ፍትህአወቅ የወንድወሰን የምስራቅ አፍሪካ አርታዒያን ሶሳይቲ (EAES) ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመርጧል።
በምስራቅ አፍሪካ የሚዲያ ዘርፍ ላይ ኢትዮጵያ ያላትን ተሰሚነት የሚያጎላ አዲስ ምዕራፍ ተመዝግቧል። እ.ኤ.አ. የካቲት 28 ቀን 2026 በናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ሚዲያ ፌስቲቫል ማጠናቀቂያ ላይ፣ ፍትህአወቅ የወንድወሰን የሶሳይቲው ፕሬዝዳንት በመሆን በከፍተኛ ድምፅ ተመርጧል።
* ምክትል ፕሬዝዳንት፦ ወ/ሮ ዙቤይዳ ካኑ (ከኬንያ አርታዒያን ማህበር)
"ይህ ምርጫ ለኢትዮጵያ አርታዒያን ብቻ ሳይሆን፣ በቀጠናው ለሚገኙ ሁሉም የሙያ ባልደረቦች የጋራ እድገት ትልቅ ፋይዳ አለው።"
#ስለ ምስራቅ አፍሪካ አርታዒያን ሶሳይቲ (EAES)
የምስራቅ አፍሪካ አርታዒያን ሶሳይቲ (EAES) የአምስት ሀገራት የሚዲያ ማህበራት ጥምረት ሲሆን፣ አባላቱም ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ዩጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ናቸው። ሶሳይቲው በዋናነት በፕሬስ ነፃነት፣ በሙያ ስነ-ምግባር እና በጋራ ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሠራል።
ተወዳጅ ሚድያም የጋዜጠኞችን ታሪክ በዲጂታል ሚድያ እና በመፅሐፍ የሚሰንድ ሲሆን በዚህ መሠረት የፍትህ አወቅ ሙያዊ አስተዋፅኦ በተወዳጅ ሚድያ የመዝገበ አእምሮ ቦርድ የሚመጥ ሆኖ በመገኘቱ ታሪኩን ሰንደነዋል። ዕዝራ እጅጉ ታሪኩን እንደሚከተለው ያቀርበዋል።
፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨
አባቱ አቶ የወንድወሰን ክፍሌ ወደ ንባቡ ዓለም እንዲሳብ መሠረት ሆነውታል። እርሳቸው ጋዜጣና መፅሔት የማንበብ ልምዱ ስለነበራቸው ፍትህ ገና በታዳጊነት ህትመቶቹን እየተቀበለ ያነብ ነበር። ይህ ንባቡ ዛሬ ለያዘው ዕውቀት መነሻ ሆኖታል። ፍትህ በደንብ ማንበቡን የተረዱት አባቱ ፊልድ ደርሰው ሲመለሱ ምን አዲስ ክስተት አለ? ብለው የሚጠይቁት ፍትህን ነበር። እርሱም የቤት ውስጥ የዘጋቢነት ኃላፊነቱን እየተወጣ አለም እንዴት እንደሰነበተች ለአባቱ መረጃ ያቀርባል። አባትም በልጃቸው የመተንተን ፣ የማስረዳት አቅም እየተደሰቱ ጎሽ ልጄ ይሉት ነበር።
ታላቅ ወንድሙ ለአለም የወንድወሰን እንደሚናገረው ፍትህ በትምህርቱም እየበረታ ፣ አለምአቀፍ ዕውቀቱንም እንደያዘ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሊገባ ችሏል።
".....ፍትህ ከበፊት ጀምሮ ነገሮችን ሚዛን አስጠብቆ በማስኬድ ያምናል። የሚያነባቸው የፖለቲካል ኢኮኖሚ መፅሐፎች እገዛ ስለሚያደርጉለትም በአለም አቀፍ ጉዳይ ላይ ያለው መረዳት ከፍ ያለ ነው። ሲያወራም በቀላሉ የማሳመን ክህሎት አለው። ለእኔ 5ኛ ታናሼ ሲሆን ባለው የተለየ ዕውቀት አከብረዋለሁ።ከበፊትም ጀምሮ ለአመራር የሚሆን ሰብዕና እና አቅም እንዳለው እገነዘብ ነበር። አሁን በተግባር የማየውም ይህን የሊደርሺፕ ችሎታውን ነው። " በማለት ታላቅ ወንድሙ ምስክርነት ሰጥቷል።
ፍትህ ብዙም ሳያጠና ከሚገባቸው ጎበዝ ተማሪዎች አንዱ ነበር። ከክፍል አንደኛ ሲወጣ ተማሪዎች መቼ አጥንቶ ነው እያሉ ይገረሙበት ነበር። ፍትህ በፍልስፍና ፣ በፖለቲካ፣ በቀጠና ጉዳዮች ፣ በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ማንበብ ርካታ ይሰጣዋል። ዛሬም ቢሆን ፍትህ መፅሐፍት ከእጆቹ አይለዩም። በአገር ውስጥ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ለአንዳንድ ሚድያዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ትንታኔ ይሠጣል። ይህ እንግዲህ ከአለምአቀፍ ፖለቲካ ጋር ያለውን የቅርብ ትስስር የሚያሳየን ሲሆን እርሱም ይህን አቅሙን በየጊዜው እያዳበረ ሄዶ ዛሬ ላይ መድረስ ችሏል።
ፍትህ በአንድ ወቅት ሶማሌ ክልል ለዘገባ አቅንቶ በነበረው ውጥረት ጥይት ካረፈበት ሆቴል እንዳለፈ ይነገራል። ይህም ለሙያው የከፈለውን ዋጋ የሚያሳየን ነው።
ፍትህ በ1998 ዓ.ም ወደ ሚድያው አለም ሲቀላቀል የዜና ክፍል ኃላፊ የነበረችው ብርቱካን ሐረገወይን የፍትህአወቅን ችሎታ ታደንቅ ነበር። እንዲህ ትላለች"... ያኔ አብረውት ከተቀጠሩት መካከል የተሻለ መረዳት ነበረው። የሚፅፋቸው ዜናዎችም በሳል እንደነቀሩ አስታውሳለሁ። የሚሠራውን ዜና በሚገባ አውቆት ስለሆነ ሚዛናዊ እና በዕውቀት የተሞላ ዘገባ እናገኝ ነበር። የፖለቲካ ዘገባን በልዩ መልኩ ይገነዘብ ነበር። ደግሞም በፍጥነት ስለሚያደርስ ይደነቅ እንደነበር አስታውሳለሁ። ፎርማት በመቅረፅና እና በአመራር ቦታም ላይ ሁኖ የተቻለውን እንዳደረገ አውቃለሁ" ስትል ብርቱካን ከተወዳጅ ሚድያ ለተጠየቀችው ምላሽ ሰጥታለች።
#የሐረር ልጅ!
ታሪካዊቷ የሐረር ከተማ ካበቀለቻቸው የሚድያ ፈርጦች መካከል ይጠቀሳል። ፍትሕ ሐምሌ 23 1976 ተወለደ።ትውልድና እድገቱ በሐረር ከተማ የሆነው ፍትህአወቅ የወንድወሰን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በየሺህ እመቤት ት/ቤት፣ በልዑል ራስ መኮንን ት/ቤት እና ሐረር ኤስ ኦ ኤስ ት/ቤቶች ተከታትሏል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪውንም አግኝቷል።ሁለተኛ ዲግሪውን ያገኘው በ2007 ዓ.ም ነው።
#ጋዜጠኛው
ከተማሪነት አንስቶ በሚድያና ጥበብ ንቁ ተዋናይ የሆነው ፍትህአወቅ ሚያዝያ 1998 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ራድዮን በመቀላቀል የጋዜጠኝነት ሙያውን ጀመረ። ከኢትዮጵያ ራድዮ ዜና ፋይል አንጋፋ ጋዜጠኞች ጋር መስራቱ በአጭር ጊዜ በሙያው ከፍተኛ ብቃት እንዲላበስ እንደረዳው ይናገራል። በ2001 የኢትዮጵያ ራድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ውህደትን ተከትሎ በቴሌቪዥን ጋዜጠኝነትም ስማቸው ከሚጠቀሱ የ2000ዎቹ ጋዜጠኞች መካከል ሆነ።ከሪፖርተርነት እስከ ዋና አዘጋጅነት በቆየበት ኢቲቪ ለ12ዓመታት አገልግሏል።
ፍትህአወቅ የወንድወሰን በታላላቅ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የዲፕሎማሲ የዜና ዘገባዎቹ እና ትንታኔዎቹ የሚታወቅ ሲሆን በተለይም 'ሚድያ ዳሰሳ' እና 'ዲፕሎማሲያችን' ፕሮግራሞች ከተመልካች ቤት ደርሷል። የአፍሪካ መዲና ከሆነችው አዲስ አበባ በርካታ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤዎችን የዘገበ ሲሆን በተለያዩ የዓለም ሀገራት በመዘዋወር በርካታ ዓለም አቀፍ ዘገባዎችን አቅርቧል።
ከ2010 ዓ.ም አንስቶ ፍትህአወቅ የወንድወሰን ከባልደረቦቹ ጋር በመሆን የሚድያ ስራዎችን ማከናወኑን ቀጥሏል። በአሐዱ ራድዮ 94.3 'ቅዳሜ ገበያ' የሚሰኝ የቢዝነስና ኢኮኖሚ ሾው ዘወትር ሰኞ፣ ረቡዕ እና አርብ እያዘጋጀ ይገኛል።
ፍትህአወቅ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን አቅም ለማጎልበትና፣ ለመብታቸው ለመሟገት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ዓርታኢያን ማህበር መስራች አባል ሲሆን የማህበሩ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ በመሆን እያገለገለ ይገኛል። ከኢትዮጵያ ባሻገር በአፍሪካ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የአፍሪካ አርታኢያን ፌደሬሽን አባል ሲሆን የምስራቅ አፍሪካ አርታኢያን ሶሳይቲ የቦርድ አባል ነው። ጋዜጠኛ ፍትህአወቅ በ2026 በተደረገው ጉባኤ የምስራቅ አፍሪካ አርታኢያን ሶሳይቲ ፕሬዘዳንት ሆኖ በመመረጥ የምስራቅ አፍሪካ ጋዜጠኞችን የማገልገል ኃላፊነት ተቀብሏል።
አብዱል ሰመድ መሐመድ ከፍትህአወቅ ጋር ከ17 አመት በላይ ትውውቅ አለው። አብዱልሰመድ ፍትህን ሲገልፀው ለነገሮች ልዩ ትኩረት የሚሰጥ ጠንካራ ሰው ይለዋል።ሀሣቡንም አብራርቶ ሲገልፅ አብዱልሰመድ እንዲህ ይላል
"....ፍትህ ፖለቲካ ሳይንስ እንደማጥናቱ በአለም ፖለቲካ ላይ የመተንተን ልዩ ክህሎት አለው ። ኢቲቪ በሠራባቸው ጊዜያትም ዜና ክፍል ኃላፊ ሆኖ ይሠራ ነበር። በዚያን ወቅት የማስተባበር ችሎታው ገራሚ ነው።" በማለት አብዱልሰመድ ምስክርነት ሰጥቷል።
ፍትህ እንደተባለው ከስሩ ያሉትን ሪፖርተሮች አሰማርቶ ሁሉንም እንደ ችሎታቸው ይዞ በጥሩ አክብሮት ሲያሠራቸው እንደነበር ብዙዎች ይመሰክራሉ። አብዱልሰመድ ይህን ተባብሮ የመሥራት ችሎታውን ያደንቅለታል።
"... ፍትሕ አንድ ነገር ከጀመረ ሳያጠናቅቀው አይተኛም።አዳዲስ ፕሮግራሞች የማፍለቅ ሀሣቦችንም የማዳበር ችሎታን ታድሏል።በአሐዱ ሬድዮ የሚቀርበው ቅዳሜ ገበያ የሚለውን ስም ፍትህ እርሱ ነው ያወጣው። ፕሮግራሙም ላይ እንደ አዘጋጅ የራሱን ትልቅ አሻራ ማኖር ችሏል።ፍትህአወቅ የአርታኢያን ማህበር እንዲመሠረት ትልቅ ጥረት አድርጎ ልፋቱም ፍሬ አፍርቷል። በአርታኢያን ማህበር ላይ በውይይት መድረክ የሚነሱ ሀሣቦች ጥልቅ እንዲሆኑም የተቻለውን ጥረት አድርጓል። የምስራቅ አፍሪካ አርታኢያን ማህበር ፕሬዚዳንት ሆኖ በመመረጡም የተሰማኝን ደስታ መግለፅ እወዳለሁ" በማለት አብዱል ሰመድ ምስክርነቱን ለተወዳጅ ሚድያ ሰጥቷል።
#ነፃነት ፈለቀ ስለ ፍትህአወቅ
ነፃነት በኢቢሲ የዕቅድ ዲፓርትመንት ኃላፊ ስትሆን ስለ ፍትህ ይህን ምስክርነት ሰጥታለች።
እኔ ፍትህአወቅ የወንደወሰንን የማውቀው ኢትዮጵያ ሬዲዮ ዜና ክፍል በሪፖርተርነት ሲቀጠር ጀምሮ ነው፤ በወቅቱ የዘገባ ሥራዎቹ ጥንቅቅ ያሉ ስለነበር ትንሹ ኤዲተር ይባል ነበር። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዜናና ወቅታዊ ክፍል በነበረበት ወቅትም የዘገባ ሥራዎቹ በመረጃ የዳበሩና ጥልቀት ያላቸው ናቸው፤ በቀጥታ ዘገባ ሥራው ንግግሩ የጽሑፍ ያህል ፍሰት ያለውና የአድማጭ ተመልካቹን ቀልብ የመያዝ አቅም የነበረው ነው። ቴሌቪዥን ላይ በዜና ኤዲተርነት አሉ ከሚባሉ የይዘት ኤዲተሮች አንዱ ነው። በወቅታዊ ፕሮግራሞችም እንዲሁ። ፍትህ ዓለም አቀፍና ሀገራዊ የፖለቲካ አውዱን በሚገባ ተረድቶ ወደ ሚዲያ ይዘት የሚቀይርበት አቅም ሁሌም የሚያስደንቅ ነው። ሪፖርተሮችን የማዳመጥና የተረጋጋ ተግባቦቱ ለሌሎች አስተማሪ ነው።
ፍትህ የምስራቅ አፍሪካ የኤዲተሮች ማሕበር ፕሬዝዳንት ሆኖ መመረጡ አቅሙን ለአፍሪካውያን ወንድሞች የማጋራት ዕድል ስለሚፈጥርለት እንኳን ደስ ያለህ ማለት እፈልጋለሁ። ከዚህም በላይ ይገባሃል 🙏
#ፍሬው አበበ ስለ ፍትህአወቅ
ፍትህአወቅ የወንድወሰን የዛሬ 7 አመት ገደማ የኢትዮጵያ አርታኢያን ማኀበር ከመሰረቱ ጥቂት ጋዜጠኞች ግንባር ቀደሙ ነው። ማኀበር መመስረት ብቻም ሳይሆን ማኀበሩ በሁለት እግሩ እንዲቆም በአመራርነት የላቀ ሚናውን ተወጥቷል። በእሱና በባልደረቦቹ ጥረት በአሁን ሰአት ማኀበሩ ለአባላቱ መብትና ጥቅም መቆም የሚችልና በጎ ተጽእኖ ፈጣሪ ለመሆን ችሏል።
ፍትህአወቅ በአሁን ሰአትም የማኀበሩ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛል።
ፍሬው አበበ
የኢትዮጵያ አርታኢያን ማኀበር ቦርድ ሰብሳቢ

#ቃለየሱስ በቀለ - የአቪየሽን ወርቃማው ጋዜጠኛ
#ethiopia | ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
#በዚህ የስነዳ ሥራችን ውስጥ በቅፅ 3 ከተካተቱት 20 ዘርፎች ውስጥ የሥራ ዘርፎች ውስጥ ሚድያ አንዱ ነው። በአሁኑ የሚድያ ሰዎችም፣ የቴአትር ባለሙያዎች እየተሰነዱ ይገኛሉ። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
#ዛሬን ሰንደን የምናስነብባችሁ የሚድያ ባለሙያ የቃለየሱስ በቀለን የሙያ ታሪክ ነው። በሚድያው ሥራ ሩብ ክፍለ- ዘመን የዘለቀው ቃለየሱስ በአቬሽን እና ማዕድን ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመዘገብ ትልቅ አሻራ አኑሯል። በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ በአገራችን በአንድ ርዕስ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ወይም ተክኖ መዘገብ ባልተለመደበት ሁኔታ ቃለየሱስ ችሎ አሳይቷል። ከባለታሪኩ የተገኘውን መረጃ በማግኘት፣ የቅርብ ሰዎቹን በማነጋገር የሙያ ታሪኩ ተሰንዷል። ዕዝራ እጅጉ እና ታደሠ ማሞ አጠናክረውታል።
፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#ትውልድና ዕድገት
‹‹የትኛውም አውሮፕላን ወደ አየር አኮብኩቦ መነሳቱ የተለመደ የጉዞው አማራጭ ቢሆንም አውሮፕላኑ ካሰበበት ደርሶ ማረፉ ደግሞ የግድ መሆን ያለበት ተግባር ነው፡፡››የሚል የአቪየሽን አባባል አለ፡፡በዚህ አባባል ተንደርድረን ወደ ውስጥ እንዝለቅ፡፡ሁሉም ዘርፍ የየራሱ አነፍናፊ ጋዜጠኞች እንዳሉት ሁሉ ቃለየሱስ በቀለ የተባለ ህልመኛና ደፋር ጋዜጠኛ በአቪየሽኑ ዘርፍ በተለየ መንገድ የራሱን የብዕር አሻራ ማኖር መቻሉ የዚህ ፅሁፋችን መነሻ ነው፡፡
#ቃለየሱስ በቀለ የውልደቱም ሆነ የእድገቱ መነሻ የምስራቅ ሸዋ አዳማ (ናዝሬት) ከተማ ናት፡፡ሀምሌ 18/1967 ዓ.ም በአዳማ ሀይለ ማሪያም ማሞ ሆስፒታል ቃለየሱስ የተባለ ብላቴና ከተፋፋመ ምጥ ውስጥ ወቅቱ አብዮታዊ ለውጥ ኢትዮጵያን በሚንጥበት በዚያ ጊዜ የለውጥ አየሩን እየማጉ ድምፃቸውን በማሰማት ይቺን ምድር ከተቀላቀሉት ጨቅላዎች አንዱ ሆኖ ተመዝግቦ በስሙ የልደት ካርድ ወጣለት፡፡
#ይህ ሰው ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ያለውን የትምህርት ጉዞውን ያሳለፈው በናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት ነው፡፡ትምህርት ቤቱ ከቀለም ትምህርት በተጨማሪ ተማሪዎችን በግብረ ገብና በመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት አንፆ በማብቃት ረገድ የተዋጣለት እንደነበር ቃለየሱስና አብረውት የተማሩት ሁሉ የሚመሰክሩት ሀቅ ነው፡፡
#በ1986 ዓ.ም ውጤታማ ሆኖ የአዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅን ደጃፍ መርገጥ የቻለው ቃለየሱስ በኮሌጁ ሁለት ዓመታት በአካውንቲነግ ሙያ ተምሮ ቢያሳልፍም የሂሳብ ባለሙያ ሆኖ መቀጠሉ ስላልተዋጣልኝ ከልጅነቴ ጀምሮ አልመውና እፈልገው የነበረውን የጋዜጠኝነት ሙያ ለመቀላቀል መንከራተት የየዕለት ተግባሬ ሆነ ይላል፡፡ያኔምደፋር ብዕሩን ስሎ አሰሳውን የጀመረውና በእንግሊዝኛ ቋንቋ አርቲክሎችን እየዘጋጀ ለዴይሊ-ሞኒተር እና ዘ-ሪፖርተር ጋዜጦች ማቅረብ መጀመሩ የምኞት ጭላንጭሉን ወገግ አደረገለት፡፡
#ጋዜጠኝነት
እንደምኞትና ፍላጎቱም መንከራተቱ ፍሬ አፍርቶ ሳምንታዊ የቢዝነስ ጋዜጣ በሆነው ፎርቹን ጋዜጣ ላይ በሪፖርተርነት ተቀጥሮ ማገልገል ጀመረ፡፡ምኞትና ህልሙ መሬት እንዲረግጡ ቀዳሚውን ዕድል ያመቻቸለት የፎርቹን ጋዜጣ መስራችና ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው አቶ ታምራት ሀይለ ጊዮርጊስ በቃለየሱስ የህይወት ጉዞ ውስጥ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡የጋዜጠኝነት ሀ ሁን ከማስቆጠር ጀምሮ ከዚያም ባሻገር አንደ ዓለም ባንክ፣የአሜሪካ ኤምባሲና ብሪቲሽ ካውንስል ያሉ ተቋማት በሚያዘጋጁት የሚዲያ ስልጠናዎች ላይ ተሳታፊ እንድሆን ዕድሉን ከማመቻቸት አልፎ ጠንካራ የጋዜጠኝነት ሰብዕናን እንድላበስ ያደረገኝ ባለውለታዬ ታምራት ነው ይላል ቃለየሱስ፡፡
#ወትሮም ለጋዜጠኝነት ታላቅ ጉጉት የነበረው ቃለየሱስ ዜና እንዴት ይፃፋል፣የዜና ግብዓቶች እንዴት ይሰበሰባሉ፣የዜና አስተማማኝ ምንጮችን እንዴት ማዳበር ይቻላል፣ፊቸር አርቲክል እንዴት ይፃፋል የሚሉና ሌሎችም ስልጠናዎችን አግኝቶ በብዕሩ መጠንከር የቻለው በፎርቹን ጋዜጣ ቆይታው እንደሆነ ያስታውሳል፡፡መች ይሄ ብቻ ከሀገር ውጪም በዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት በኤር ባስ አማካኝነት ከበረራና የበረራ ደህንነት መረጃ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ስልጠናዎችን በስፋት በመውሰድ የማረጋገጫ ሰርቲፊኬቶችን ተቀብሏል፡፡
#ቃለየሱስ ባለውለታዎቼ ብዙ ናቸው ይላል፡፡የፎርቹን ጋዜጣ ኤዲተር የነበሩት መላኩ ደምሴና ይበቃል ጌታሁን በጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ኮትኩተው ለውጤት አብቅተውኛል ካለ በኋላ በአጠቃላይ የፎርቹን ኤዲተሮች እኔን ጠፍጥፈው ሠርተውኛል ብል ማጋነን አይሆንም በሚል ያለፈበትን የጋዜጠኝነት ህይወት በአጭሩ ገልፆታል፡፡
#ከፎርቹን የሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ ሪፖርተር ጋዜጣን በመቀላቀል ለ18 ዓመታት ከከፍተኛ ሪፖርተርነት እስከ ኤዲተርነት ያገለገለው ቃለየሱስ ከሪፖርተር ጋዜጣ መሥራች አቶ አማረ አረጋዊ ጋር መሥራት መታደል ነው ይላል፡፡ከአቶ አማረ ጋዜጠኝነትን ብቻ ሳይሆን የአገር ፍቅርና ብሔራዊ ጥቅምን (National Interest)፣ደግነትንና ለሠራተኞቹ ያለውን ፍቅርና አክብሮት እንዲሁም ለጋዜጠኞች የሙያ ነፃነት ሰጥቶ ሠርቶ የሚያሠራበትን መልካም ትምህርት ቀስሜያለሁ ብሏል፡፡በሪፖርተር ሳለሁም በርካታ የሙያ ማሻሻያዎችንና የአጭር ጊዜ ሥልጠናዎችን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገሮች አግኝቻለሁ በማለት ትናንቱን ያመሰግናል፡፡
#በዘ -ሪፖርተር እንግሊዝኛ ጋዜጣ የማቀርባቸው ዘገባዎቼ በአብዛኛው ቢዝነስ ተኮር ነበሩ የሚለው ቃለየሱስ በተለይ በአቪዬሽንና በማዕድን ዘርፎች ላይ አተኩር ስለነበር፤በእነዚህ ዙሪያ በሚሠሩ የውጭ መጽሔቶች ለእኛም ጻፍልን የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበውልኝ እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ ኤርላይን ፍሊት ማኔጅመንት፣ወርልድ ኤር ኒውስ፣ኤርላይን ኢኮኖሚክስ፣አፍሪካን ኤሮስፔስና ዓረቢያን ኤሮስፔስ፣አቪዬሽን ኢንተርናሽናል ኒውስ፣አፍሪካን ቢዝነስ እና አፍሪካን ማይኒንግ ጆርናል ለተባሉ መጽሔቶች በፍሪላንስነት ለረዥም ዓመታት ሠርቻለሁ ይላል፡፡
እ.ኤ.አ.በ2008 በእንግሊዝ አገር በሚካሄድ “Best Aerospace Journalist of the Year” ሽልማት ታጭቼና ለንደን ተጋብዤ ዋናውን ሽልማት ባላሸንፍም፣"How Safe Are African Airlines?" በሚል ርዕስ በኤርላይን ፍሊት መጽሔት ላይ ያሳተምኩት ጽሑፍ ከ500 ለውድድር ከቀረቡ ጽሑፎች አምስቱ ምርጥ ውስጥ ለመግባት በመቻሉ፣ሰርተፊኬት ተበርክቶልኛል ብሏል፡፡
#በ2007 ዓ.ም. በትግራይ ሽመልባ የኤርትራ ስደተኞች መጠለያ ካምፕ ጉብኝት በማድረግ፣ ስለኤርትራዊያን ስደተኞች አሳዛኝ ሕይወት "The Woes of Eritrean Refugees” በሚል ርዕስ በዘ- ሪፖርተር ጋዜጣ ያሳተምኩት ሰፊ ጽሑፍ ጄኔቭ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) ዋና መሥሪያ ቤት ተመርጦ፣ለረዥም ጊዜ በድረ ገጻቸው ላይ ለንባብ ተቀምጦ ነበር፡፡በሻሸመኔ መልካ ኦዳ ስለሚገኙ የራስ ተፈሪያን ማኅበረሰቦች በቦታው ተገኝቼ የሠራሁት "The Plight of Rastafarians in Ethiopia" ዘገባ ከራስ ተፈሪያን ማኅረሰብ ምሥጋናና ዕውቅና አስገኝቶልኛል ይላል፡፡
ቃለየሱስን አንባቢያን የሚያውቁት ስለኢትዮጵያ አየር መንገድና በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ስለሚካሄዱ የማዕድንና የነዳጅ ፍለጋዎች ተከታታይ በርካታ ዜናዎችን በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በመሥራቱ ነው፡፡ ከዚያ ባለፈም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች ጋር የመሥራት ዕድሉን አግኝቷል፡፡
#የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ለሥራ ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡበት ወቅትም እነሱን በማገዝ የተለያዩ ሥራዎችን ከውኗል፡፡ከእነዚህም መካከል “CNN, Aljazeera, SKY News, The Economics, National Geographic, Los Angeles Times, News Week, New York Times, Christian Science Monitor, Chicago Tribune…” እና ሌሎችም ከተሳተፈባቸው ውስጥ ይገኙበታል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2019 አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን በተመለከተ ሲኤንኤን (CNN) በሠራቸው ዘገባዎች ላይ በረዳት ፕሮዲዩሰርነት የሠራ ሲሆን፣በወቅቱ ላበረከተው አስተዋጽኦ ከሲኤንኤን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ምሥጋና ተችሮታል፡፡በዘገባዎቹ ላይም ሙሉ ስሙን በማስፈር ተገቢውን ዕውቅና ሰጥተውታል፡፡የአሜሪካው አልጄዚራ ኢንግሊሽ ቡድን ስለአውሮፕላን አደጋው ዶክመንተሪ ለማዘጋጀት አደጋው ከደረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመጣበት ወቅትም፣አብሮ የአገር ውስጥ ፕሮዲዩሰር (Local Producer) ሆኖ ሠርቷል፡፡
መቼ ይሄ ብቻ ቃለየሱስ የ”Fault Lines” ፕሮግራም አዘጋጅ ከሆነው ጆሽ ረሺንግ (Josh Rushing) እና ፕሮዲዩሰሯ ካቢታ ቺኩሩ ጋር የሠሩት ዶክመንተሪ የተለያዩ አህጉሮችን የሸፈነ ሲሆን፣ለኤሚ አዋርድ ዕጩ ሆኖ ቀርቦም ነበር፡፡
#ከ18 ዓመታት አገልግሎት በኃላ እ.ኤ.አ. በ2020 ሪፖርተር ጋዜጣን ተሰናብቶ ኦሪጅንስ ሚዲያን በማቌቋምና ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ የአየር ሰዓት በመውሰድ፣‹‹ኢትዮ የንግድና የኢንቨስትመንት መድረክ››የተሰኘ ፕሮግራም በሳምንት ለሁለት ቀናት እያዘጋጀ ለሦስት ዓመታት ያህል አቅርቧል፡፡ኦሪጅንስ የሚል የጉዞ (Travel Magazine) ለማሳተም እየንቀሳቀሰ የነበረ ቢሆንም፣በኮቪድ ወረርሽኝና በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ለፍሬ ሊበቃለት እንዳልቻለ በቁጭት ያስታውሳል፡፡
#ገጠመኞቹ
#ቃለየሱስ በጋዜጠኝነት ሙያ የገጠሙኝ ፈተናዎች ብዙ ናቸው ይላል፡፡ሙያው ራሱ የሚያስደስት ነገር እንዳለው ሁሉ ብዙ የሚያስጨንቁና የሚከብዱ ነገሮችም አሉት።ጋዜጠኛው ከህሊናው ጋር ተሟግቶና ሚዛኑን ጠብቆ የሚሰራው ነገር አንዱ ሲሆን።ዘገባን ወቅት ጠብቆ መስራትም የራሱ ፈተና አለው። ሚዛናዊነቱ ሳይጓደልም እንኳን ስለአንድ ነገር ሲፃፍ ወይም ሲዘገብ በዜናው ምከንያት የሚጠቀሙ ወገኖች ሊኖሩ ይችላሉ።
ወዲህ ደግሞ ጉዳቱም የዛን ያህል ነው።አንድ ሚዲያ በሚሰራው ዘገባ ባለስልጣንም ሆነ ካምፖኒ ሊሆን ይችላል የነበረውን አቅም ሊያጣ ይችላል።ይህ የሚዲያ ባህሪ ነው።ፈተናዎቹ የበዙ ቢሆኑም ጋዜጠኛው ሲፅፍ ሚዛናዊነት የተለበሰ መሆን አለበት ባይ ነው ቃለየሱስ።
#ቃለየሱስ ረጅም ዓመት የሠራው ህትመት ሚዲያ ላይ ነው።በአንድ ወቅት ከቺጋጎ ትሪቡን ጋዜጠኛ ጋር ወደ ትግራይ በማቅናት በኢትዮ ኤርትራ ስላለው ሁኔታ ለመዘገብ አመሩ፡፡ሽሬ አካባቢ ሽመልባ የሚባል የኤርትራ ስደተኞች ያሉበትን ስፍራ ጎብኝተውና አነጋግረዋቸው ወደ ሽራሮ ሄዱ፡፡የጦርነቱ ከተማ ወደነበረችው ባድመ ሄደውም ነዋሪዎችን፣አርሶ አደሮችና የከተማውን አስተዳደር ቃኝተውና ቃለመጠይቅ አድርገው ወደ ኤርትራ ድንበር ተጠጉ፡፡
#የኤርትራን መሬት ከወንዝ ባሻገር እያዩና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ሲያስጎበኟቸው የተቀበሩ ፈንጂዎች ስለነበሩ በተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሀይል አማካኝነት የፈንጂ ማስወገድ ስራው እየተሰራ ስለነበር የምንረግጠውን መንገድ ጠቆሙን ካለ በኋላ ቀይ ቀይ የተደረገባቸውን ድንጋዮች አሳይተውን ለእግር ፉካ የምትሆን ድንጋይ አሳዩን።ቀይ ምልክት የተደረገባቸውን ድንጋዮች ትተን ሌላ ከረገጥን ልንሞት እንደምንችል ነገሩን።በፈንጂ መሀከል በጭንቅና በዝግታ ያሳለፍንውን ምንጊዜም አልረሳውም ይላል ቃለየሱስ።
ሌላ ጊዜ ደግሞ በአቬየሽን፣በነዳጅ እና ማዕድን ፍለጋ ስራዎች ዙሪያ ለመዘገብ ወደ ሱማሌ ክልል ይሄዳል፡፡ከኦጋዴን ነፃ አውጪ ጋር የነበሩ ውጊያዎች ስለነበሩ አንድ ጊዜ አቦሌ ከሚባል በደቡብ ምዕራብ በሚገኝ ኩባንያ የነዳጅ ስራ ፍለጋ በሚያደረግ ካምፕ ላይ ታጣቂዎቹ ጥቃት ሰንዝረው 9 ቻይናውያን እና ወደ 65 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ህይወት ያልፋል።
ያንን ለመዘገብ ወደ አካባቢው የሄደው ቃለየሱስ ከቺጋጎ ትሪቡን ጋዜጠኛው ፖልስ አሎቤ ጋር ያለ እንቅልፍ ረጅም ቀናት በማሳለፋቸው በሀሩራማው ኦጋዴን ውስጥ ለረጅም ሰአታት ራሱን ስቶ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ በህክምና የነቃበትን ጊዜም ያስታውሳል።ቃለየሱስ ገጠመኞቹ የትየለሌ ናቸው፡፡በችሎት ዘገባ እንዲሁም ጋምቤላ ለዘገባ ሄዶ ያጋጠሙትንም ሁሌ እያስታወሰ ይገረምባቸዋል፡፡ በተለያዩ የአቪዬሽን ስብሰባዎችና እንዲሁም በአውሮፕላን አምራች ካምፓኒዎች በአካል እየተገኘም የሚያማልሉ ዘገባዎችን አስነብቧል፡፡
#ስለ ቃለየሱስ የታላላቅ ሰዎች ምስክርነቶች
"ቃለ ኢየሱስ በቀለ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በትጋት ከሠሩ ባለሙያዎች አንዱ ነው።" ይላል የሪፖርተር ጋዜጣ መስራች አማረ አረጋዊ። ምስክርነቱንም በመቀጠል፦
"... ቃለ ኢየሱስ በአቬሽን እና በማዕድን ዘገባዎች ላይ ያተኩር እንጁ የተሰጠውን ደስ ብሎት የሚሠራ ጋዜጠኛ ነው። የጋዜጠኝነት የሥነ ምግባር ደንብን አውቆ የሚተገብር ባለሙያ ነው። ፕሮፌሽናሊዝም እንዲሰፍን የሚታገል ጠንቃቃ ባለሙያ መሆኑን መመስከር እወዳለሁ።" በማለት ገልጿል
፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#የአቶ ግርማ ዋቄ ምስክርነት
#ቃለ ኢየሱስ በቀለን ረጅም ጊዜ አውቀዋለሁ። ለአቬሽን የተለየ ፍቅር አለው። አለምአቀፍ ኮንፈረንሶች ላይ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋል። ከዚያም በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ፅሁፍ ያቀርባል።ብስለቱ ይደንቃል። ከሌሎች የስሚ ስሚ ሰምቶ ሳይሆን አንድን ጉዳይ ከስር ከመሠረቱ አውቆ የመዘገብ ችሎታውን አደንቅለታለሁ። ስለ አፍሪካ አየር መንገድ ፣ ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በወጉ ተረድቶ ስለሚፅፍም ፅሑፉ ተነባቢ ለመሆን ችሏል። ኢትዮጵያ ውስጥ አቬሽን ጋዜጠኝነት በጥልቀት ሲሠሪ የማውቀው እርሱን ነው።ሌሎችም አሉ። እርሱ ግን ከፍ አድርጎ በልህቀት የሚሠራ በመሆኑ ይለያል።
ገና አየር መንገድ ሲመጣ መረጃ ለማግኘት ፍላጎት ያሳያል። ዕውነትን ለማግኘት ይጎለጉላል። አፍሪካም ውስጥ ፈጠን ብሎ አቬሽን ጋዜጠኝነት ላይ የገባ በመሆኑ ይህም ግንባር ቀደም ያደርገዋል። ቃለኢየሱስ ካለበት ካናዳ ሆኖ የአቬሽን ጋዜጠኝነትን ሙያ እንዲያሳድግ ምክሬን እለግሰዋለሁ።
አቶ ግርማ ዋቄ
የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
‹‹እኔ ቃለየሱስ በቀለን የማውቀው ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ፎርቹን ጋዜጣ አብረን ስንሠራ ጀምሮ ነው›› የሚለው የሪፖርተር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው መላኩ ደምሴ ነው፡፡‹‹ከዚያም በኌላ ለ18 ዓመታት አብረን በሪፖርተር ጋዜጣ ሠርተናል፡፡ከጀማሪ ሪፖርተርነት አንስቶ እስከ አርታኢነት በዘለቀው የሥራ ጉዞው በሚገባ አውቀዋለሁ፡፡በተለይ በአቪዬሽንና በማዕድናት ዘርፍ እጅግ በጣም በርካታ ዘገባዎችን የሠራ ሲሆን፣በሁሉም ሥራዎቹ አንጀት አርስ የሚባል ጋዜጠኛ ነው፡፡ጋዜጠኝነትን ከልቡ ከማፍቀሩ የተነሳ አብረው ለሚሠሩ ጋዜጠኞች ጭምር የሙያውን ፍቅር የማጋባት ችሎታ ያለው ነው፡፡ቃለየሱስ ዘገባዎችን ሲሠራ የሁሉንም ባለጉዳዮች ደምፅ ከማካተት በተጨማሪ፣አንባቢያን ለርዕሰ ጉዳዩ ቅርበት እንዲፈጥሩ የሚያስችል ስሜትን የተካነ ነው፡፡
‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአቪዬሽን ዘገባ በግንባር ቀደምነትነት የሚጠቀስ ጋዜጠኛ ማነው ቢባል በመጀመሪያው ረድፍ ላይ የሚገኘው ቃለየሱስ ነው፡፡በዓለም ላይ አሉ የሚባሉ አውሮፕላን አምራች ኩባንያዎችን፣አየር መንገዶችን፣በአቪዬሽን ዘርፍ ውስጥ የተሰማሩ የሥራ ኃላፊዎችንና ባለሙያዎችን ሳይቀር በተለያዩ አገሮች በማግኘት በሪፖርቶቹ ውስጥ ድምፃቸውን ከማካተቱም በላይ በቃለ ምልልስ ጭምር ለአንባቢያን ተደራሽ በማድረግም ወደር የለውም፡፡የአውሮፕላን አደጋዎች ሲያጋጥሙም ሆነ የተለዩ ክስተቶች ሲኖሩ ከሚሠራቸው ዘገባዎች በተጨማሪ፣በተለያዩ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለማብራሪያ የሚፈለገው ቃለየሱስ ነው፡፡በውጭ ለሚዘጋጁና ቁጥራቸው ቀላል ለማይባል የአቪዬሽን መጽሔቶች በርካታ ዘገባዎችን በመሥራትም ታዋቂ ነው፡፡
‹‹በማዕድናት ዘርፍም ከካሉብ ነዳጅ የጀመረው የጋዜጠኝነት ህይወቱ በተለያዩ ክልሎች የሚደረጉ የነዳጅ፣የወርቅ፣የብረት፣የፖታሽ፣የታንታለም፣የኦፓልና ሌሎች የከበሩ ማዕድናት ፍለጋ ሥራዎችን በስፋት የዳሰሰ ነው፡፡በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታዎች፣በጂኦ ተርማል ፕሮጀክቶች፣ በፀሐይና በንፋስ ኃይል ማመንጫዎች፣በሲሚንቶና በሌሎች የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችም ሰፋፊ ዘገባዎችን በማበርከት ስመጥር ሆኖ ዘልቌል፡፡በፖለቲካው መስክ ደግሞ በተለያዩ አገራዊ ምርጫዎች ከአዲስ አበባ ውጪ በክልሎች ተሰማርቶ አመርቂ ሪፖርቶችን በማቅረብ ችሎታውን ማስመስከር የቻለ ነው፡፡ከሪፖርተር በገዛ ፈቃዱ ከተሰናበተ በኃላም በኤፍኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ የአየር ሰዓት ወስዶ ያቀርባቸው የነበሩ የቢዝነስ ፕሮግራሞቹ፣የቃለየሱስን ችሎታ ከጋዜጣ አንባቢያን ወደ ሬዲዮ አድማጮች በማዝለቅ ረገድ ትልቅ ግምት የሚሰጣቸው ነበሩ፡፡
‹‹ቃለየሱስ ግልጽ፣ ቅን፣ ሰብዓዊነትን የሚያስቀድም፣ኃላፊነት የሚሰማው፣ በአስገራሚ ትውስታው የረሳናቸውን ጉዳዮች የማስታወስ ችሎታ ያለው፣በቀልድም ሆነ በቁምነገር የሚታወቅ፣ ከማንኛውም ሰው ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር ምንጊዜም ዝግጁ የሆነ፣በተለይ በሪፖርተር የሥራ ባልደረቦቹ ዘንድ በእጅጉ ተወዳጅና ምሥጉን ጋዜጠኛ ነው፡፡በተጨማሪም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በሚሰጣቸው ሰፊና ጥልቅ ትንተናዎቹ የሚታወቅ ሲሆን፣ብዙዎችም በዚህ መጠን ለነገሮች ትኩረት ሰጥቶ የማስረዳት ብቃቱን በአድናቆት የሚመሰክሩለት ነው፡፡እኔም ከሁለት አሠርት ዓመታት በላይ አብሬው ስለሠራሁ ችሎታውን በዚህ መጠን ስገልጽ በከፍተኛ ስሜት ሲሆን፣ይህንን ከመሰለ ብርቱና ታታሪ ጋዜጠኛ ጋር የመሥራት ዕድል በማግኘቴ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ›› በማለት መላኩ ምስክርነቱን አጠቃሏል፡፡
ካፒቴን ሰሎሞን ግዛው ስለ ቃለየሱስ በሰጡት ምሥክርነት ‹‹እኔ እሱን ለአየር መንገዱ ልዩ እንደ ሆነ ሰው አየዋለሁ።በጣም ትሁት፣አዳማጭ የሆነ ሰው ነው።ከየት እንዳመጣው ባላውቅም ልዩ የሆነ የኢንግሊዘኛ ፀሀፊ ነበር።በሁለት ምክንያት የሱን ፅሁፍ አነብ ነበር፡፡አንዱ በፅሁፉ ለመደሰትና እንደ ግጥም ስለምወደው ነው።ሌላው ከእውቀቱ ወይም አንብቦም ይሁን ባላውቅም የፅሁፎቹ ይዘት በሚያውቀው ነገር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ነው።በዚህም በጣም አበረታታዋለሁ።
‹‹ከተዋወቅን 15 ዓመታት ሆኖናል።በውጪ ህትመቶች ላይ የሚያወጣቸው ስራዎች ቃለየሱስ ብሎ ስሙ ይገለፅ ይሆናል እንጂ ማንም ነጭ የሚፅፈው አይነት ፅሁፍ ነው።የፅሁፉ ይዘትና አያያዝ ደረጃውን የጠበቀ ነው።የሚፅፍባቸው መፅሄቶች ደረጃቸውን የጠበቁና ትላልቅ ናቸው።ነገር ግን ደረጃቸውን ጠብቀዋል የሚባሉትም አንዳንዴ ትርኪምርኪ ሲፅፉም ይታያል።ግን የሱ ፅሁፍ በጣም የሚያኮራ ነው።ሌላው ዜግነቱን የሚወድ ሰው ነው።ተጨባጭ በሆነ መልኩ ለኢትዮጵያ አየርመንገድ በቦታው ካሉት ህዝብ ግንኙነቶች እሱ ብዙ የሰራ ይመስለኛል።እውቅናና ሽልማት ሊሰጠው በርታ ሊባል የሚገባው ልጅ ነው።ወገቡን ይዞ ነበር ለአየር መንገዱ ይሰራ የነበረው።አሁንም ቢሆን ባለበት ሆኖ ለአየርመንገዱ ነገሮችን መስመር የሚያሲዝ ሰው ነው››ብለዋል፡፡
፨፨፨፨፨፨፨
የቀድሞ የሲቪል አቬሽን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ወሰንየለህ ሁነኛው በበኩላቸው ‹‹ከተዋወቅን ከ7 ዓመት በላይ ይሆነናል።እኔ ከማቃቸው የሚዲያ ሰዎች በጋዜጠኝነት የሱን ያህል ብዙም አቬሽን ዘርፉ ላይ ገብቶ እያንዳንዱን ነገር አይቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሁን የግል ኦፕሬተሮቹም ጋር እንደሱ የሚፅፍ አላየሁም።እሱ ነው የተሻለ ጠይቆ አንብቦ ተረድቶ አስተዋጽዖ ለማድረግ የሚጥረው።በዛ ወቅት ቃለ እየሱስ ጥሩ ዘጋቢ ነበር።ብዙ መፅሄቶች ላይ ይሳተፋል አንዳንድ አለም አቀፍ ስብሰባዎች ላይ ይሄዳል። በኢትዮጵያ አየርመንገድና በሲቪል አቬየሽን ላይ የተለየ እውቀት ያለው ነው።ምክንያቱም በየእለቱ ስለሚከታተል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አቬየሽን ኢንዱስትሪ በደንብ ያውቀው ነበርና ነው።
‹‹አቬየሽን ኢንዱስትሪው በእነዚህ መፅሄቶች በብዙ መንገድ ይጠቀማል።ህብረተሰቡ አቬየሽኑም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራሱን ከማስተዋወቁ በላይ ምን ላይ እንዳለ እና በተለየ አካል እንዲሰራለት ትክክለኛነቱን ይረጋገጣል።እንዲሁም ምን ያህል የግል ኦፕሬተሮች ምን ያህል በኢኮኖሚው ይሳተፋሉ የሚለውንም ለህብረተሰቡም ለመንግስትም መረጃ ይሰጣል።ስራዎቹ ለብዙ ነገሮች የመረጃ ምንጮች ሆነው ያገለግላሉ ።
‹‹ቃለእየሱስ በዚያ ወቅት የሚያደርገው የኢትዮጵያን አቬየሽን ኢንዱስትሪ ከሌላው እያነፃፀረ በሚያውቀው ልክ ለህብረተሰቡ ሙሉ መረጃ ይሰጣል።ለግል ኦፕሬተሮችም ለኢትዮጵያ አየር መንገድም ግብዐት የሚሆኑ ብዙ ነገሮችን ያደርጋል።በተዘዋዋሪም ያስተዋውቃል።እውነተኛ መረጃ ሲያቀርብ ሰው ስለ አቬየሽን ኢንዱስትሪ ያለውን እውቀት ያዳብራል።አብዛኛው ሰው ስለ ግል ኦፕሬተር አያውቅም አውሮፕላን አላቸው ወይ ? ብሎ የሚጠይቅም ብዙ ሰው ነው።በዚህ ጉዳይ ላይ በብዛት የሚሰራው ቃለእየሱስ ነበር››ብለዋል፡፡
‹‹በኢትዮጵያ የጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ የቃለየሱስ አስተዋፅኦ ትልቅ ነው።››ብለው ምስክርነታቸውን መስጠት የጀመሩት አቶ ተወልደ ገብረማርያም የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው፡፡‹‹ቃለየሱስና እኔ ለረጅም ጊዜ እንተዋወቃለን በ«Reporter» ጋዜጣ ሲሰራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዜናዎችንና እድገቶችን ይዘግብ ነበር።በቀጣይ የአቪዬሽን ዘርፍ ላይ ጥልቅ ፍላጎት አሳየ፤እኛም ከIATA ጋር እንዲገናኝ አደረግነው፣በተለይም በየዓመቱ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚካሄዱ የIATA አመታዊ አጠቃላይ ጉባኤዎች (AGM) ላይ የፕሬስ ኮንፈረንሶች ላይ ይሳተፍ ነበር።
‹‹በአፍሪካ አየር እና አቪየሽን (African Aerospace and Aviation) መጽሔት እና በሌሎች ከአቪየሽን ጋር የተያያዙ መጽሔቶች ላይ ጽሁፎችን ይጽፍ ነበር።በአጋርነትም ብዙ ፕሮጀክቶችን አከናውነናል። እኔም የኢትዮጵያ ቱሪዝም ቦርድ ሊቀመንበር በነበርኩበት ሰዓት፣የራሱን የጉዞና ቱሪዝም መጽሔት እንዲጀምር ወይም እንዲያስብበት ሀሣብ አቀርብለት ነበር፤እርሱም ይህን ሀሳብ በአዎንታ ይመልከተው ነበር።
‹‹በአጠቃላይ፣ ይህ ዘርፍ እስከዛሬም በቂ የሚዲያ ሽፋንና የማስተዋወቂያ መድረክ ስላልነበረው፣ ቃለየሱስ ይህን ክፍተት ልብ ብሎ በማጤን በኢትዮጵያ የጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ ልማት ላይ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል።በእኔ አመለካከት፣ያበረከተው አስተዋፅኦ አስደናቂ ነው፣ለሥራውም እውቅናና ምስጋና ሊቀርብለት ይገባል››ብለዋል፡፡
ሲጠቃለል ከ15 አመት በላይ በአለም አቀፍ የአቪየሽን ስብሰባዎችን በአሜሪካ፣አውሮፓ፣አፍሪካ፣ መካከሉኛው ምስራቅ እና ኤሽያ ተሳትፌያለሁ 36 ሃገሮችንም የማየት እድል ገጥሞኛል የሚለው የአቪየሺን ባለወርቃማ ብዕሩ ቃለየሱስ በቀለ እ.ኤ.አ.ከ2023 መጨረሻ ጀምሮ ኑሮውን በካናዳ ያደረገ ሲሆን፤ለአፍሪካ ኤሮስፔስና አቪየሽን ኢንተርናሽናል ኒውስ በፍሪላንስነት በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

8 months ago
በዶ/ር አብዲበሺር ሰኢድ የተጻፈው "ፍካሬ ትኩረት" የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ተመረቀ
#ethiopia | በዲጂታል ዘመን የሰው ልጅ ትኩረትና ማንነት ላይ የሚያጠነጥነው የዶክተር አብዲበሺር ሰኢድ "ፍካሬ ትኩረት " የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ባሳለፍነው ቅዳሜ በብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ አንጋፋው አርቲስት ሥዩም ተፈራ፣ የኢትዮጵያ ሠዓሊያን እና ቀራፂያን ማኅበር ፕሬዚዳንት አርቲስት አክሊሉ መንግሥቱን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ምሁራንና የጥበብ አፍቃሪያን ተገኝተዋል።
"ፍካሬ ትኩረት" የዲጂታል ዘመን ልማት፣ማንነት፣ እና ኃያልነት መበየኛ መጽሐፍ በአሁኑ ዘመን እንደ ትልቅ የገቢ ምንጭ የሚቆጠር ሀብት መሆኑን መጽሐፉ ከዓለም አቀፍ እውነታ ጋር እያመሳከረ ይተነትናል።
መጽሐፉ በዲጂታል መሣሪያዎችና በማኅበራዊ ትስስር ገጾች አማካኝነት የሚሰረቀውን የሰው ልጅ አእምሯዊ ንቃት እንዴት መመለስ እንደሚቻል የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ያመላክታል።
✅ በዲጂታል ዘመን ውስጥ የማንነትን ጥያቄ በጥልቀት የሚዳስስ
✅ ለሀገራዊ ልማት አዳዲስ አቀራረቦችን የሚያቀርብ
✅ በትምህርት፣ በምርምር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት ያለውን ልምድ የሚያንጸባርቅ
✅ ለወጣቱ ትውልድ መሪ ሐሳብና ተግባራዊ መንገድ የሚያበረታታ መሆኑን ሒሳዊ ዳሰሳ ያቀረቡ ምሁራን እና ተወያዮች ገልጸዋል።
ዶ/ር አብዲበሺር ሰኢድ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ እና ጂኦግራፊ ትምህርት፤ የመጀመረያ ድግሪ የማስተርስ ድግሪ፤ በቱሪዝም እና ልማት ጥናት ከታላቁና አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የፍልስፍና ዶክትሬት ዲግሪ ከአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
በተጨማሪም ፣ ከሕንዱ ሀገር አቀፍ የኢንተርፔነርሺፕ ልማት ተቋም የድሕረ-ማስተርስ የዓለም አቀፍ የኢንተርፕሬነር የአሰልጣኞች ስልጠና አግኝተዋል።
በተጨማሪም ከኬኒያው ሞይ ዩኒቨርሲቲ በድሕረ ማስተርስ የቱሪዝም አስተዳደር ስልጠና ፣ ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የድሕረ ምረቃ ዲፕሎማ በከፍተኛ ትምህርት የማስተማር ሥነ ዘዴ ስልጠናዎችን የወሰዱ ሲሆን ፣
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የልማት ጥናት ረዳት ፕሮፌሰር ፣የቱሪዝም፣ የእንተርፕሬነርሺፕ እና የድኅነት ቅነሳ ተመራማሪ ፣በዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊና ሰብዓዊ ልማት ጥናቶች ኃላፊ ፣በታላቁ የአል-ነጃሺ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት የቅርስና ቱሪዝም አመራር ጥናቶችን ሠርቷል።
በቱሪዝም፣ በኢንተርፕሬነርሺፕ፣ በምጣኔ ሀብት ዘርፎች የተለያዩ ጥናቶችን በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ያሳተመ
በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሕንድ እና ሌሎች ሀገሮች ውስጥ የጥናት ምርምሮችንና የስልጠና ፕሮግራሞችን ያቀረበ ነው።
ከዚህ ቀደም ሲል የሴቶችን ትውልድ የማነጽ ሚና የሚዳስሰውንና በሦስት ቋንቋዎች(በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ) የታተመውን "Architects of The Ummah" የተሰኘ መጽሐፍ ከጓደኞቹ ጋር ለንባብ አብቅቷል።
በ7 ምዕራፎች ተቀንብቦ በ107 ገጾች የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ፣ በአሁኑ ወቅት በ320 ብር ለገበያ ቀርቧል። መጽሐፉ በተለይ በቴክኖሎጂ ተጽዕኖ ውስጥ ለሚገኘው ወጣት ትውልድና ለምሁራን ትልቅ ግንዛቤን እንደሚሰጥ በምረቃው መርሐግብር ላይ ተገልጿል።
ከረመዳን ጾም በኃላ በሀረር የመጽሐፍ ምረቃና የፊርማ ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል።
#ethiopia #fikretukret #digitalage #identity #newbook #focus #mentalawareness #drabdibeshir #literature #addisababa #booklaunch #attentioneconomy

9 months ago
ነፃነት ወርቅነህ እምሩ( 1974-2018)
ማስታወሻ፦ሐምሌ ወር ላይ 2017 ነፃነት ለተወዳጅ ሚድያ ደወለ፦
"....እዝራ። ታሪካችን እኮ መሰነድ አለበት።እኔም መረጃ እልካለሁ።" በማለት ነበር ነፃነት የስነዳ ሥራው አዎንታዊ እሳቤውን የገለፀው። እኛም መረጃ ማሰባሰብ ጀምረን ነበር። ነፂ ግን"... ደርሶኛል። አየዋለሁ እዝራችን ነበር የስንብት መልዕክቱ።
ዛሬ ጥር 8 2018 ዓ.ም የሰማነው ክፉ ዜና ግን ለመስማት ይከብዳል። ነፂ ነፍስህ በሰላም ትረፍ። እንደወደድከው ታሪክህን ሰንደናል።
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
ከእነዚህ ውስጥ የሚድያ ሰዎችና የቴአትር ባለሙያዎች ይገኙበታል። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ 50 በላይ የፊልምና የቴአትር ባለሙያዎች ፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን አመራሮች እና የሚድያ ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
በዚህ ፅሑፍ የሙያ ታሪኩ የሚሰነድለት ጠንካራ ባለሙያ ነፃነት ወርቅነህ ነው። ዕዝራ እጅጉ እና ሣራ አህመድ ታሪኩን አጠናክረውታል።
#ትውልድና ልጅነት
የኪነ ጥበብ ባለሙያ ነፃነት ወርቅነህ እምሩ የካቲት 10 1974 ዓ.ም ከአባቱ ከአቶ ወርቅነህ እምሩ እና ከእናቱ ከወይዘሮ ምናለሸዋ ይፍሩ በአዲስ አበባ ከተማ በፖሊስ ሆስፒታል ተወለደ።ለቤተሰቡ አራተኛ ልጅ ሲሆን ሶስት ወንድሞች እና አንድ እህት በነበረው ቤተሰብ ውስጥ በኡራኤል ሰፈር እንዳደገ ይነገራል።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በአስፋው ወሰን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማረ ሲሆን እስከ 7ኛ ክፍል ባለው የልጅነት እና የትምህርት ቤት ቆይታው ለኪነጥበብ የተለየ ፍቅር አልነበረውም። የ8ኛ ክፍል ተማሪ እያለ "የጉሊቷ እናቴ የሚል ቲያትር ላይ የሴት ገፀ-ባህሪይ ይዞ መተወኑ ይነገራል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ምሥራቅ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል።
#ወደኪነ -ጥበብ አለም የገባበት አጋጣሚ
የ16 አመት ልጅ ሳለ ከኡራኤል መርካቶ ድረስ በእግሩ እየተመላለሰ ዩኒቲ የቴአትር ክበብን እንደተቀላቀለ ቲያትር መስራት መጀመሩ ይነገራል። የዩኒቲ ክለብ መፍረስ ቀጣዩ የነፃነት መዳረሻ የሩሲያ ባህል ማዕከል ወይም ፑሽኪን አዳራሽ እንዲሆን አደረገው። በፑሽኪን ቆይታውም በግጥሞች በወጎች መሀል የሚተላለፉ የተመልካችን ቀልብ የሚይዙ የ30 ደቂቃ ድራማዎችን ሠርቷል።በፑሽኪን ቆይታው ፍሬሸ ማን የሚለውን ድርሰቱን በ40 ደቂቃ የሚያልቅ ድራማ አድርጎ ሠርቶት ነበር።በኃላም ቲያትሩን አሻሽሎ ከአዳነች ወ/ገብርኤል ጋር መስራቱ አይዘነጋመሰ። ነፃነት በአንድ በኩል ፍሬሽ ማንን ፑሽኪን እያሳየ" የመጨረሻ ሀጢያት" የሚል በቀበሌ አዳራሽ ውስጥ የተሰራ ቲያትርም አሳይቷል።
በፑሽኪን በነበረው ቆይታ ላይ አብረውት ከሰሩት ተዋናዮች መሀከል ኢሳያስ አስራት ስለነፃነት የትወና አቅም ይህን ብሏል።
"እኔ ስለ ነጺ እመሰክራለሁ።የሚሠራውን ገና ሲወጥነው ያውቀዋል።
ፑሽኪን (የሩሲያ ባህል ማዕከል) በነበርንበት ወቅት እኔም እርሱም ተውኔት እንጽፋለን፣እናዘጋጃለን፣እንተውናለን።ፉክክር ነበር በመሀላችን።
ነፂ ግን ይለያል። አድምቶ መሥራት እና በዚያው መጠንከር እና ግቡን መምታት ያውቅበታል" በማለት መስክሯል።
ነዋሪነቱን በካናዳ ያደረገው ገዛኸኝ መኮንን ሲናገር ፦ "...ለመጀመሪያ ጊዜ በፑሽኪን ማዕከል መድረክ በግጥም መሀል በሚያቀርባቸው አጫጭር ተውኔቶች ላይ ነበር extraordinary የሆነ ችሎታ እንዳለው ያስመሰከረው።
እኔ እና ወዳጄ ሚሊዮን አየለ በጋራ ጽፈን ባዘጋጀነው ፌስታል የተሰኘች የ 5 ደቂቃ ድራማ ላይ ካስት ስናደረገው ከሙናዬ መንበሩ ጋር እንዴት በልዩ ሁኔታ እንደተጫወተው አሁንም አይረሳኝም።
ከዚያ በኋላ በጣም በርካታ ፊልሞች ላይ በመተወን አቅሙን አሳይቷል " በማለት ምስክርነት ሰጥቷል።
#የነፃነት ኪነ ጥበባዊ አበርክቶዎች
በቲያትር ዘርፍ
ነፃነት ወርቅነህ "በይቅርታ ምሽት በማዘጋጃ ቲያትር ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በቲያትር ቤት ደረጃ የሰራው ሥራ ሲሆን በመቀጠልም በብሔራዊ ቲያትር "ካብ ለካብ" የሚባል ቲያትር ላይ "የትወና ብቃቱን አሳይቷል። የዳዊት እንዚራ፤ፍሬሽ ማን፤የጓሮ ጌታ ፤የብሩክታዊት ስጦታ የተባሉ ቲያትሮች የሰራ ሲሆን ፍሬሽ ማን የራሱ ድርሰት እና በህዝብ ዘንድም ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘበት ስራው ነው።
#በቴሌቪዥን ድራማ እና በሬዲዮ ድራማ
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ በነበረው ስንቅ ፕሮግራም ላይ ባለቤትነቱ የአለልኝ መኳንንት እና የጥላሁን ዘውገ ፕሮግራም ላይ በድርሰት ፤ በአዘጋጅነት ፤ በዳይሬክተርነት እንዲሁም በተዋናይነት ሠርቷል። ጥላሁን ዘውገ ስለ ነፃነት ሲመሰክር ነፃነት ከትወና ባሻገር የማዘጋጀት ችሎታም ስለነበረው ድራማዎችን እንዲያዘጋጅ ዕድል እንሰጠው ነበር ብሏል።
በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳር ቴሌቪዥን በሚተላለፈው "መስኮት በተሰኘ የአምስት ደቂቃ ድራማዎች ላይ በበርካታ ድርሰቶች ላይ የነፃነትን አሻራ ማግኘት ይቻላል።
በሬዲዮ ድራማዎች ላይ በድርሰት በኢትዮጵያ ሬዲዮ እንዲሁም በfm 97.1 ተሳትፏል።
#የፊልሙ አለም
የመጀመሪያ ፊልሙ "የማይደረስበት" የሚለው ሲሆን ኪሳራ ላይ የጣለው ፊልም ሲሆን ከዛ በኃላ FBI1,2,3፤ የአንቺው ሌባ 1,2፤ Mr x ፤ባለቀለም ህልሞች፤ስለማይዘነጋ ውለታ፤ዕድል 20 የተሰኙ ፊልሞችን የሠራ ሲሆን የFBI 1,2,3 ፊልም ደራሲ እሱ ሲሆን፤በባለቀለም ህልሞች ላይ በዳይሬክቲንግ እንዲሁም በMr X ፊልም ላይ በድርሰት ተሳትፏል።በህዝብ ዘንድ በባለቀለም ህልሞች ፤ በአንቺው ሌባ እንዲሁም በFBI ፊልሞችየተለየ አድናቆት እና ተወዳጅነት ሊያገኝ ችሏል።
#ሌሎች ሥራዎች
ነፃነት ደራሲ ፤ተዋናይ ፤ዳይሬክተር ብቻ አልነበረም። ጎበዝ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢም ጭምር እንጂ በተለይ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚተላለፈው የቤተሰብ ጨዋታ በየፕሮግራሙ አዳዲስ ቃና እየጨመረ ለዓመታት ፕሮግራሙ በህዝብ ልብ ውስጥ እንደተወደደ እንዲሁም ሳይሰለች እንዲታይ አስችሎታል።
ከቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነቱ በተጨማሪ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን እንዲሁም መድረኮች መልዕክታቸውን ሳያጡ በሳቅ እንዲታጀቡ አድርጎ ማቅረብም ላይም የሚደርስበት የለም። በአጠቃላይ ነፃነት የዘርፈ ብዙ ሙያ ባለቤት ነበር ማለት ያስችላል።
#ልዩ ሰብዕና
ነፃነት ወርቅነህ ሌሎች ሲደሰቱ ከማንም በላይ ይደሰታል። በበርካታ ችግሮች ቢያልፍም ሳቅ ከምንም በላይ መድኃኒት ነው በሚለው አስተሳሰቡ ለዓመታት ዘልቋል። አብረውት ለሚሠሩ የኪነ -ጥበብ ባለሙያዎች ልዩ ክብር ያለው ነፃነት ለሰዎች በመድረስ የሚያምን በሰዎች የደስታና የሀዘን ጊዜም ቀድሞ የሚገኝ መሆኑን የቅርቦቹ ይመሰክራሉ።
#የትዳር ህይወት
ነፃነት ወርቅነህ፣ ከንፁህ ዘር በላይ ጋር ትዳር የመሠረተ ሲሆን የሦስት ልጆች አባት ነው። ልጆቹም የ18፤15 እና የ9 አመት ዕድሜ ሲኖራቸው የመጀመሪያ ልጁ ኦራገን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ነፃ የትምህርት ዕድል አግኝቶ እየተማረ እንደሆነ፤ሁለተኛ ልጁ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መከታተል እንደጀመረች እንዲሁም የመጨረሻዋ ለፒያኖ ፍቅር እንዳለት ከወራት በፊት ገልፆ ነበር።
ነፃነት ወርቅነህ አርብ ጥር 8 2018 44 አመቱን ሊይዝ 30 ቀናት ሲቀረው ከዚህ አለም ድካም አርፏል።

8ኛው 'የባለ ራዕይ ሴት' የዕዉቅና መርሀ-ግብር ተካሄደ!
#fastmereja : ሴቶች ከቤተሰብ ምሥረታ እስከ ማህበረሰብ ግንባታ ድረስ ላበረከቱት አዎንታዊ አስተዋጽኦ እና ሚና ዕውቅና በመስጠት በሌሎች ሴቶች ዘንድ መነቃቃትን የመፍጠር ዓላማ አንግቦ “ባለ ራዕይ ሴት" በሚል መሪ-ቃል የዕውቅና እና ሽልማት ስነስርዓት ተከናዉኗል።
ዘንድሮ ለ8ተኛ ጊዜ በተካሄደው መርሀ-ግብር ራዕያቸውን ተገንዝበው፣ ለትውልድና ለሀገር የላቀና የሚታይ አስተዋጾ ያበረከቱ ተምሳሌት ሴቶችን ነዉ በዛሬዉ እለት የተሸለሙት።
የዘንድሮው 'ዕንቁ ሴት ንቁ ሴት' መርሀ ግብር መሪ ቃል ባለ ራዕይ ሴት የሚል ሲሆን መሪ ቃሉ ወደፊት አዳዲስ ራዕይ የሰነቁ ወጣቶችንም የማነቃቃት ዓላማ እንዳለው ተገልጿል።
በዚህ ታላቅ የዕውቅና አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ላይ፣ አዝናኝ መሰናዶዎች የቀረበ ሲሆን ዶክተር ወዳጄነህ ማህረነ እና ዶክተር ሮዳስ ታደሠ አስተማሪ አበረታች መልዕክቶችን አጋርተዋል።
የዕንቁ ኢቬንትስ ሀሳብ አመንጪና ባለራዕይ የሸጋ ትውልድ መሥራችና የከፍተኛ ተቋም መምህር አቶ ሳሙኤል ገረመው ይህን የዕውቅና አሰጣጥ የሚከታተል የዝግጅት ቦርድ ተዋቅሮ ኃላፊነቱን ሲወጣ መቆየቱን ገልፆ ለዘንድሮ መከበር ያለባቸውን 1ዐ ሴቶች እንደሸለመ ገልጿል።
የዕንቁ ሴት የበላይ ጠባቂ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ሲሆኑ ሰፊ ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎችም በዕንቁ ሴት የሽልማት ዝግጅት ላይ ልዩ ተሳትፎ አድርገዋል።
በዛሬዉ እለት የእዉቅና እና ሽልማት የተበረከተላቸዉ ዕንቁ ሴቶች:-
📌 ዶ/ር ትዕግስት በጤና ዘርፍ
📌 አበበች አፈወርቅ የህይወት ዘመን ሽልማት
📌 ሀናን ማህሙድ ከበጎ አድራጎት ማህበር
📌 በሻቱ ቶለማርያም ከሚዲያና ጋዜጠኝነት
📌 አርቲስት መሠረት መብራቴ በኪነ ጥበብ
📌 ዲዛይነር ሔዋን ቀለመ ወርቅ ከሥራ ፈጠራ
📌 ሣምራዊት መሐመድ ከወጣት ባለራዕይ
📌 ልዕልት አንድሮሜዳ ከኢትዮጵያ
📌 ገነት ገ/ሥላሴ ከልመና ወደ ሽመና
📌 ዶክተር ሀመልማል መንግሥቱ

8ኛው 'የዕንቁ ሴት ንቁ ሴት' ሽልማት የፊታችን ቅዳሜ ይደረጋል
ዕዝራ እጅጉ (ተወዳጅ ሚድያ)
#ethiopia | የጠራ ራዕያቸውን ተገንዝበው፣ ለትውልድና ለሀገር የላቀና የሚታይ አስተዋጾ ያበረከቱ ተምሳሌት ሴቶች የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 25 2018 ዓ.ም በሳፋየር አዲስ ሆቴል ዕውቅና ይሰጣቸዋል።
የዕንቁ ኢቬንትስ ሀሳብ አመንጪና ባለራዕይ የሸጋ ትውልድ መሥራችና የከፍተኛ ተቋም መምህር አቶ ሳሙኤል ገረመው ለተወዳጅ ሚድያ እንዳስረዳው ሌሎችን ለሥራ የማነሳሳት አቅም ያላቸው ጠንካራ ሴቶች ዕንቁ ሴቶችን ማክበራችንን ቀጥለንበታል ብሏል።
አቶ ሳሙኤል እንዳስረዳው፣ ይህን የዕውቅና አሰጣጥ የሚከታተል የዝግጅት ቦርድ ተዋቅሮ ኃላፊነቱን ሲወጣ መቆየቱን ገልፆ ለዘንድሮ መከበር ያለባቸውን 10 ሴቶች አሳውቋል ብሏል።
የዘንድሮው 'ዕንቁ ሴት ንቁ ሴት' መርሀ ግብር መሪ ቃል ባለ ራዕይ ሴት የሚል ሲሆን መሪ ቃሉ ወደፊት አዳዲስ ራዕይ የሰነቁ ወጣቶችንም የማነቃቃት ዓላማ እንዳለው ታውቋል። ይህ መርሀ- ግብር የገና በዓል ሰሞን መደረጉ ለመሰናዶው ልዩ ድምቀት እንደሚሰጠው ይነገራል።
በዚህ ታላቅ የዕውቅና አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ላይ፣ አዝናኝ መሰናዶዎች የሚኖሩ ሲሆን ዶክተር ወዳጄነህ ማህረነ እና ዶክተር ሮዳስ ታደሠ አስተማሪ ዝግጅት ያቀርባሉ።
የዕንቁ ሴት የበላይ ጠባቂ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ሲሆኑ ሰፊ ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎችም በዕንቁ ሴት የሽልማት ዝግጅት ላይ ልዩ ተሳትፎ አድርገዋል።በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ኪነ ጥበብ ቢሮ ይህን በጎ አገራዊ እንቅስቃሴ ሲያግዝ እና ልዩ ትብብር ሲያደርግ መቆየቱንም መሥራቹ አቶ ሳሙኤል ይናገራል።
አጠቃላይ የዕንቁ ሴቶች ሽልማት የቅዳሜውን ጨምሮ ለ45 ሴቶች ዕውቅና የሰጠ ሲሆን ይህን ተግባሩንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።
የዚህን መርሀ ግብር የሚድያ ዘገባ ሥራና የዕጩዎች የግለ ታሪክ ክትትል የሚያደርገው ተወዳጅ ሚድያ (ዕዝራ እጅጉ ) ሲሆን በመርሀ ግብሩም ላይ ታላላቅ እንግዶች እንደሚታደሙ ይጠበቃል።
በዚህ ሽልማት ዕውቅና የሚያገኙት፦
1.ዶ/ር ትዕግስት በጤና ዘርፍ
2. አበበች አፈወርቅ የህይወት ዘመን ሽልማት
3. ሀናን ማህሙድ ከበጎ አድራጎት ማህበር
4. በሻቱ ቶለማርያም ከሚዲያና ጋዜጠኝነት
5. አርቲስት መሠረት መብራቴ በኪነ ጥበብ
6ኛ ዲዛይነር ሔዋን ቀለመ ወርቅ ከሥራ ፈጠራ
7 ሣምራዊት መሐመድ ከወጣት ባለራዕይ
8 ልዕልት አንድሮሜዳ ከኢትዮጵያ
9 ገነት ገ/ሥላሴ ከልመና ወደ ሽመና ናቸው።
10ኛ ዶክተር ሀመልማል መንግሥቱ

10 months ago
ሊከተሉት የሚገባ ሰው!
ሠዓሊና ቀራፂ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን
(ሂላሪያ ተስፋዬ እና ዕዝራ እጅጉ ተወዳጅ ሚድያ)
#ፕሮፌሰር በቀለመኮንን ለተወዳጅ ሚድያ የቅርብ ወዳጅና ቤተሰብ ነው። የምንሠራውን የስነዳ ፕሮጀክት በሙሉ ልብና መንፈስ የሚደግፍ ቀና ምሁር ነው። ታናሾቹን ለማገዝ በቀዳሚነት የሚሰለፍ ኩራት ያልፈጠረበት ታላቅ ወንድም እንደማለት ነው። ከ4 ዓመት አስቀድም "መዝገበ አእምሮ" ቅጽ አንድ ሲዘጋጅ ከጀርባ እና ከጎን ሆኖ ሲረዳን ነበር። የኃይሉ ልመንህን ታሪክ ፕሮፌሰር በቀለ አስታውሶ ታሪኩን ባይነግረን ኖሮ ኃይሉ ልመንህን አናገኘውም። ፕሮፌሰር በቀለ ሌሎችም ስሙን ከአክብሮት ጋር የሚያነሱት የሥነጥበብ ሰው ነው።
#ተወዳጅ ሚድያ እስከዛሬ የ432 ባለሙያዎችን ታሪክ በመፅሐፍ፣ በዲጂታል ሚድያ እና በድምፅ ሲሰንድ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንንም እንዲካተት አድርጓል። እስከዛሬ በሚዲያ እና ኪነ-ጥበብ ዘርፍ የሠሩትን በምንችለው አቅም ታሪካቸው ዘመን እንዲሻገር ያደረግን ሲሆን የስነዳ ተግባሩም ተጠናክሮ ቀጥሏል። በቀጣይ እያዘጋጀነው ባለነው ዕትም ከ20 ዘርፎች የተውጣጡ ታላላቆችን በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን ። ከእነዚህ ታላላቆች ውስጥ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን አንዱ ነው። የሕይወት ታሪኩንም ብዙ ካልታዩ የልጅነት ምስሎቹ ጋር አንድ ላይ በማድረግ ታሪኩን አጋርቶናል። ዕዝራ እጅጉ እና ሂላሪያ ተስፋዬም ታሪኩን እንደሚከተለው ሰንደውታል።በነገራችን ላይ በዚህ የሕይወት ታሪክ መጣጥፍ ውስጥ ተባባሪ ፕሮፌሰር ቴዎድርስ ገብሬ "በቀለን በብሔራዊ ትእምርት ፍለጋ ውስጥ" ብሎ የጻፈው ረዘም ያለ ምሁራዊ ትንተና አቅርበናል። የፕሮፌሰር በቀለ መምህር ወርቁ ጎሹ የሰጡትንም ምስክርነት አካተናል። መልካም ንባብ።
#የሰባተኛ ክፍል ተማሪ እያለ የስዕል ዝንባሌውን እንዲከተል እንዲሁም የስዕል ትምህርትን እንዲማር ያመለከቱትን መምህሩን በአንደበቱ ቃላት ይስላቸዋል። እኚህ መምህሩን፥ “ሊከተሉት የሚገባ ሰው” ሲል ይገልጻቸዋል። ምንአልባት ከበርካታ ዓመታት በኋላ እርሱ ራሱም እንዲያ ያለ ‘ሊከተሉት የሚገባ’ የጥበብ ሰው ሊሆን እንደሚችል አልገመተ ይሆናል።
#ፍላጎቱ ከእኩዮቹ የተለየ፣ ‘ተርታ’ ለሆነ ነገር መሻት የሌለው፣ በለጋ እድሜው ሳይቀር ነገሮችን እንደሆኑ ማየትና መሥራትን የማይመርጥ፣ አዲስ ነገር መፍጠርን አልያም የነበረውን በአዲስ መልክ መቃኘት ይቀናው የነበረ ተማሪ ነው። ስሙን ሳይቀር በስዕል ይጽፍ እንደነበር ይናገራል። በስጋው ላይ ያሠለጠናት ነፍሱ፥ ሰዓሊ የመሆን ግቡን ለማሳካት ይችል ዘንድ ‘የሰው ልጅ መሠረታዊ ነገሮችን’ አሻግሮ እንዲያይ ጉልበት ሰጥታዋለች። ይህ ጉልበትና ጽናት ነው፣ አሁን በሥነ ጥበብ ዘርፍ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሙሉ ፕሮፌሰር የወለደው፥ ሠዓሊና ቀራፂ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን።
#ትውልድና እድገቱ ደብረዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማ ነው። ጥር 6 1956 ዓ.ም። ትምህርትን አሃዱ ያለው በቆሎ ትምህርት አቡጊዳ ብሎ ፊደል ቆጥሮ፣ ዳዊት ደግሞ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን አፄ ልብነ-ድንግል ወናግሰገድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ እንዲሁም ኹለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በዚያው ደብረዘይት ልዕልት ተናኘወርቅ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል። የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተናውን የወሰደው ደግሞ በአዲስ አበባ ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው።
ከልጅነት እድሜው ጀምሮ የተገዛው ለስዕል ጥበብ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ ለጥበብ ነበር። አዲስ ነገርን አልያም የነበረው በተሻለ መንገድ ሆኖ ማየትን ይመርጣል። በጥበብ ለሚሠራ ነገር ሁሉ ልዩ ፍቅር አለው። አሁን በአዋቂነትና በርቱዕ አንደበቱ ውበት እንደሚገዛው፥ ሰው የማይሠራውን መሥራት አልያም የተሠራውን ነገር ባልተሠራበት መንገድ መሥራት እንደሚወድድ ይናገራል። ይህን ቃሉን በልጅነት እድሜው ሲገልጥ ደግሞ፣ ስሙን ሳይቀር በስዕል ይጽፍ ነበር።
#የተካነበት፣ የሠለጠነበትና የታወቀበት የስዕል እና የቅርጻ ቅርጽ ጥበብ ይሁን እንጂ፥ ለጽሑፍ ጥበብ እና ውበትም ስሱ ነው። በልጅነትና ወጣትነት እድሜው በደብረዘይት ኪነት ውስጥ ቴአትር፣ ግጥም እንዲሁም መፈክር ጭምር በመጻፍ ይታወቃል። እንደውም ለተማሪዎች፣ ለሰፈሩ ወጣቶች የጻፋቸው የፍቅር ብሎም ልዩ ልዩ ደብዳቤዎችና ግጥሞች ጋር በተያያዘ በተለያየ አጋጣሚ የሚያነሳቸው ገጠመኞቹ ጥቂት አይደሉም። የእጅ ጽሑፉን ብቻ ሳይሆን የሚጽፋቸው ጽሑፎችና ግጥሞች ይዘት ጭምር ነበር ብዙዎችን የሚስበው።
#በኋላ 12ኛ ክፍል ፈተናን ከመውሰዱ አስቀድሞ፥ የስዕል ትምህርትን ለመማርና መምህሩ የዘራበትን ዘር ለማፍራት ዝንባሌውን ተከትሎ በዘመኑ አዲስ አበባ የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት (አሁን አለ ሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት) አቀና። ትምህርት ቤቱን ለመቀላቀል ደጅ ጥናትና ምልልስ እንዲሁም ተማጽኖ አስፈልጎታል። በኋላም ተሳክቶለት ተማሪ ለመሆን በሚጠበቀው ፈተና አንድ ሺህ ከሚጠጉ ተወዳዳሪዎች መካከል ከ14 አላፊ ተማሪዎች አንዱ መሆን ቻለ።በ1971።
#በአንድ ወቅት በአራዳ ኤፍኤም አዲስ አራዳ የራድዮ ፕሮግራም ላይ ባደረገው ቆይታ፣ የዚያን የአምስት ዓመት የትምህርት ዘመን ሲያነሳ፥ በትምህርት ቤቱ የነበረው የ5 ዓመት ቆይታ ቀላል እንዳልነበር ያስታውሳል። ሌሊት ማረፊያ የሚያጣባቸው ቀናት ብዙ ናቸው። ምንም እንኳ ለአምስት ዓመታት እያንዳንዱ ቀን የአንድ ዓመት ያህል ከባድ የነበር ቢሆንም፥ እርሱ ግን ‘ቀኑን ጎበዝ መሆን ነበር የሚፈልገው’። እናም ቀኑን ጎብዞ ከባዱን ጊዜ በብልሃትና በጽናት ተወጣው። ትምህርቱን አጠናቅቆም በማዕረግ ተመረቀና እዚያው የተማረበት ትምህርት ቤት መምህር ሆኖ ተቀጠረ።
በተማረበት ትምህርት ቤት በወጣት መምህርነት ለአራት ዓመታት አገልግሏል። ከዚያ በኋላ፥ ወደ ሩሲያ ለከፍተኛ ትምህርት ተላከና ሞስኮ ከተመ። ‘ግራጫ’ ይለዋል፣ የሩስያን ፀሐይ አልባ ቀዝቃዛና ደመናማ የጨላለመ የዘመኑን ድባብ። በዙሪያው ውበትን ማሰስ የለመደ ዐይኑ በሞስኮ ያንን ሊያገኝ አልቻለም። እንዲያም ሆኖ የደከመለት ትምህርቱን ለመፈጸም ጽናትን በመምረጥ፥ ከስድስት ዓመት የሞስኮ ቆይታ በኋላ የከፍተኛ የሥነጥበብ ትምህርቱን በሚገባ አጠናቅቆ ወደ እናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ተመለሰ።
ከሩስያ መልስ አስቀድሞ በመምህርነት ያገለግልበት በነበረው ሥነ -ጥበብ ትምህርት ቤት የማስተማር እድል አገኘ። በዚያም በመጀመሪያ በሥነ ጥበብ ታሪክ ከዚያም በንድፍ ጥናት መምህር ሆኖ ቆይቷል። በመምህርነት ብቻም አይደለ፥ በጊዜው ‘አርት ስኩል’ ይባል የነበረውን ይህን ትምህርት ቤት፣ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋምነት ለማሳደግ ከ1990ዎቹ ጀምሮ ለዓመታት በዘለቀውና በተደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ ከፊት ሆነው ሲያስተባብሩ ከነበሩት መካከል ሆኗል። በመጨረሻም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ በተሰጠ የጥናት ውሳኔ ሥነ ጥበብ ትምህርት ቤቱ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተዛውሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሲሆን ትልቁን ድርሻ ከተወጡት ጥቂት ግለሰቦች መካከል ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ተጠቃሽ ነው።
ትምህርት ቤቱ የዩኒቨርሲቲው አንድ አካል ክፍል ከሆነ በኋላ የመጀመሪያው ዳይሬክተር በመሆን ሠርቷል። በዚያም ወቅት የትምህርት ቤቱን ነባር ስርዓት የከፍተኛ ትምህርት ስርአት ቅርፅ ለማስያዝ በብርቱ ለፍቷል፣ አሳክቷልም። በ2009 ዓ.ም ገደማ የሥነጥበባት ኮሌጅ ሲመሠረት በድጋሚ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ሆኖ ከማገልገሉ ባሻገር፥ ትምህርት ቤቱ መጠሪያው ወደ አለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት የተቀየረው የኮሌጁ ዲን ሆኖ ባገለገለበት ዘመን ነበር። ከዚያም ባሻገር አዲስና ተጨማሪ የፊልም ትምህርት ክፍል እንዲቋቋም ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ትምህርት ክፍሉ እውን እንዲሆን አስችሏል። ከዚህም ባሻገር በማስተማርና በማማከር በርካታ ተማሪዎችን ያፈራ ብርቱ ባለሙያ ነው።
#ፕሮፌሰር በቀለ በብሉይ ወይም ክላሲክ አካዳሚ ትምህርቱን ጠንቅቆ የተማረ ይሁን እንጂ በዘመነኛ የሥነ ጥበብ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ከሚጠቀሱ ባለሙያዎች አንዱ ነው። አዳዲስ ሙከራዎችና አሰሳዎችን በድፍረት ግን በኃላፊነት በማከናወን ሁሌም ፈር ቀዳጅና አዲስ መንገድ የሚያሳይ ከልቡ የፈጠራ ሰው ስለመሆኑም ብዙዎች ይመሰክራሉ፥ ከዚያም በላይ ሥራዎቹ ምስክሮቹ ናቸው።
#ፕሮፌሰር በቀለ የመጀመሪያ የሥዕል ኤግዚቢሽኑን ያቀረበው ከሀገር ውጭ ፊንላንድ፥ ‘ኮ’ፕዮ’ የሚባል ዩኒቨርሲቲ (Kuopio - በአሁኑ ምሥራቅ ፊንላንድ ዩኒቨርሲቲ) ነበር። ይህም በሞስኮ የሥነጥበባት የመጨረሻ ዓመት ተማሪ እያለ ሲሆን፣ ለዕይታ ያቀረባቸው ሥራዎቹም የተለያዩ አስቀድሞ በትምህርት ቤት ቆይታው ያዘጋጃቸው ናቸው።
ከዚያ በኋላ ለቁጥር በርካታ፣ ለዓይነት ብዙ፣ ለዐይን ውብና አስደማሚ የሆኑ ሥራዎችን ያለማቋረጠ ለበርካታ ዓመታት ሲያቀርብ ቆይቷል። ከስዕል ኤግዚቢሽን እስከ አደባባይ ሐውልቶችና ዓለም አቀፍ መድረኮች፥ በቀለ መኮንን የሚለው ስም እንግዳ ሆኖ አያውቅም።
#በ1996 ዓ.ም ያቀረበው ‘እንቆቅልሽ’ የተሰኘ የ‘ኢንስታሌሽን ጥበብ’ ትርዒቱ ዘይቤያዊ (Methaphorical) ትርጉም የያዘና አሁንም ድረስ አነጋጋሪ ሆኖ የቆየ ሥራ አንዱ ተጠቃሽ ነው። በ2000 ዓ.ም ‘እድልና ምርጫ’ የሚል ‘ክሪቲካል’ ትርዒቱን አቅርቦ ተመልካቹን አስደምሟል። በ2010 ዓ.ም ‘ባሩድና ብርጉድ’ ሲል የሰየመው አነጋጋሪና አወያይ ኤግዚቢሽኑ፥ ተመልካቹ ስለ ሥነጥበብ ያለውን አመለካከት ደጋግሞ እንዲፈትሽ ያስገደደ ነበር።
በ2016 ዓ.ም በኢትዮጵያውያን የሕይወት ዘይቤ ላይ ትልቅ ጥያቄ አንስቶ ያወያየውንና እስከ አሁንም የሚያወያየውን “ግሉተን ፍሪ-ደም” ወይም ‘ጤፍና ነፃነት’ የተሰኘውን ልዩ ትርዒት አቅርቦ የሥነ ጥበብ ተመልካቾችን ማስደነቁና ማነጋገሩን ቀጠለበት።
ከ25 ዓመታት በላይ እነዚህን የፈጠራ ሥራዎቹን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር በተለያዩ መድረኮች ሲያሳይ ቆይቷል። በአፍሪካ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ፣ በተለያዩ ሙዚየሞች ሥራዎቹን አቅርቧል፣ ሐሳብና ዕይታውን አስደምጧል። ሀገሩን አልፎም አኅጉሩን አፍሪካን በዓለም መድረክ በዘርፉ በኩራት እንዲቆሙም ምክንያት ሆኗል።
#በቅርብ ማለትም ባለፈው 2017 ዓ.ም፥ በኢጣሊያ ቱሪን ከተማ ሮያል ፓላስ ሙዚየም ተጋብዞ ‘ዘ ስሞኪንግ ቴብል’ ወይም ‘የሚጤሰው ጠረጴዛ’ የተሰኘ ፀረ ቅኝ ግዛት ይዘት ያለው ዘመነኛ የሥነ ጥበብ ሥራ በመፍጠር ለዕይታ አቅርቧል። ይህም ከፍተኛ እድናቆትን ያስገኘለት ብሎም ሐሳቡን ያስደመጠበት አውድ መሆን ችሏል።
#መሥራት እንጂ ይህን ሠራሁ ብሎ መናገርን የማያዘወትረው ፕሮፌሰር በቀለ፣ እንዲህ ካሉ አውደ ርዕዮች ባሻገር በቀራጺነቱ የተጠበበባቸው ሥራዎችም እጅግ በርካታ ናቸው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሠራቸውን በማማከር የተሳተፈባቸውን ብቻ ለመጥቀስ፥ በሙሉ ነሃስ የተሠራው የቀዳማይ ኃይለሥላሴ ኪነ ሀውልትን ጨምሮ፥ አብርኆት የሕዝብ ቤተመጻሕፍት ደጃፍ የሚገኘው ኪነ ሀውልት (ከነሐስ ቀልጦ የተሠራው ሕፃን)፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ያሠራው ሕንጻ ጋር የሚገኘው የባንኩን ዓላማና ርዕይ የሚያሳየው ግዙፍ ኪነ ሀውልት (ሀብት ካለ በሰማይ መንገድ አለ) እጅግ ጥቂቶቹ ናቸው።
ታድያ ለእነዚህና ለበርካታ ሥራዎቹ ሽልማቶችና እውቅናዎች ተበርክተዉለታል። ከእነዚያም መካከል በ1990 ዓ.ም የቺካጎ አርቲስቶች ዓለም አቀፍ ሽልማትን ያሸነፈ ብቸኛው አፍሪካዊ የስነ ጥበብ ባለሙያ መሆን ችሏል። እ.ኤ.አ. በ2006 በአሜሪካ ኒው-ዮርክ ውስጥ የIIE ፕሮግራም የሆነውን የ’Scholar Rescue Fund’ ሲቀበል የመጀመሪያው የሥነ ጥበብ ሰው ነበር። በዚያው ዓመት በባልቲሞር ሜሪላንድ ውስጥ በተጋባዥ ሠዓሊነት በበሜሪላንድ የአርት ኮሌጅ (MICA-Maryland institute college of Art) ለስምንት ወራት ቆይታ አድርጓል።
#ፕሮፌሰር በቀለ የኢትዮጵያ ሚሌኒየም ዓርማ ነዳፊ ሲሆን በመላ ሀገሪቱ በርካታ ኪነ ሀውልቶችን ነድፏል፣ አቅዷል፣ አማክሯል፣ መርቷል፣ ሠርቷል። በርካታ የመጻሕፍት ሽፋኖችንና የውስጥ ምስሎችን አዘጋጅቷል። በሀገር እና በዓለም አቀፍ የሥነጥበብ እና የሥነ ሕንፃ የውድድር መድረኮች ላይ በከፍተኛ ዳኝነት አገልግሏል። ከስነጥበቡ ማኅበረሰብ ውስጥ ደግሞ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ መደበኛ አባል ነው።
#ከዚህም በላይ ከእለት እለት የማስተማር ተግባሩ ጎን ለጎን በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት ፕሮጀክት ስር ነባሩ የአፍሪካ አዳራሽና የሥነ ጥበብ ሥራዎቹ እድሳት ውስጥ ባለሞያ፣ አማካሪና ተቆጣጣሪ በመሆን የተሳካ ሙያዊ ተልዕኮ ፈፅሟል። በአሁኑ ወቅትም በአለ ሥነጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ፕሮፌሰር ሲሆን፣ የዘመናዊ ሥነጥበብ ሙዚየም ገብረ ክርስቶስ ማዕከልንም በመምራት ላይ ይገኛል።
#ኅዳር 4 ቀን 2018 ዓ.ም የአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ የአክብሮትና የምስጋና ፕሮግራም አድርገዉለታል። ተማሪዎቹ ያንን ያደረጉት ፕሮፌሰር በቀለ በጀርመን ሀገር ፍራንክፈርት ከተማ ከሚገኝው የሥነጥበብ ዩንቨርሲቲ ጋር ከዓመታት በፊት የተጀመረውን የኹለትዮሽ ግንኙነት ዳር በማድረስ ላደረገው ታላቅ ተግባር እና የትምህርት ቤቱን ዳግም ትንሳኤ ለማሳካት ድልድይ በመሆኑ በማመስገን ነው።
አሁን ታድያ ይህና ያልተነገረ እጅግ በርካታ፣ ውብና አስደናቂ፣ ገና ያልተተነተነና ዐይን የሚሻ ሥራን የሠራ ሰው ነው፥ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ የሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት የመጀመርያው ሙሉ ፕሮፌሰር ማዕረግ የተሰጠው።
#ምንአሉ ?
ይህንን ዜና በደስታ በማኅበራዊ ገጾቻቸው ካጋሪት መካከል ጋዜጠኛ #ቴዎድሮስተክለአረጋይ እንዲህ አለ፥
“አንዳንድ ጊዜ ማዕረግም፣ ሹመትም፣ ሽልማትም በተለያዩ ምክንያትና አጋጣሚዎች ያልተገባ ሰው እጅ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። ይህ ይበልጡን በሀገራችን፣ በዓለምም ላይ ታይቷል። ለፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ዓይነቱ ደግሞ እንዲህ ግጥም ያለ ፣ በልኩ የተሰፋ ይሆናል። የበቄ ፕሮፌሰርነት በሥነ ጥበብ ዘርፍ የተሰጠ የመጀመሪያው ቢሆንም የሰውየው የበቀለ ብቻ አይደለም። የመጭው ትውልድ ሁሉ ነው። የሥነ ጥበብነት ብቻ ሳይሆን የመቻል ፕሮፌሰርነት ነው። ከእንግዲህ ለአንድ ጥበበኛ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መሰጠት እንደሚችል ማሳያው፣ ማመላከቻው፣ ዳገቱ፣ ምልክቱ ነው፥ በቀለ መኮንን። ያሉትና የመጭዎቹ የሥነጥበብ ልሂቃን ተስፋና ብርታት ነው። እንደሚቻል ማሳያውም፣ ማረጋገጫውም ሆኗል። ይህ ለሥነጥበቡ ብቻም ሳይሆን ለሙዚቃውም ፣ ለትያትሩም ነው።”
የሙያ አጋሩንናበአለ የሥነ ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ዲን #ሠዓሊአገኘሁአዳነ በበኩሉ፥ “የቤት ሰው፣ መምህር፣ ባልደረባ፣ የሞያ አባት… ከፍ ሲል፣ ሲከብር፣ ድካሙ ፍሬ ሲያፈራ ወዘተ. ልብ ይሞላል። በቀለ መኮንን ንጉሡ ባለግዙፍ ሰብዕና፣ ከሰው ፊት የሚያቀረቡት፣ የሚያኮራ፣ ጥንቅቅ ያለ ሙያተኛ፣ በጥረቱ ከጉልበተኞች ቅሚያና ንጥቂያ፣ ከሰሜነኛው ንፍቀ ክበብ (global north) በር ጠባቂነት በጥበብ ሾልኮ በርካታ ዓለማቀፍ መድረኮችን የተጋራ፣ ረብ ያለው ተግባር እየፈጸመ ያለ ሰው የሚሠራበት ተቋም አዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቶታል። የአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት የመጀመርያው ሙሉ ፕሮፌሰርሽፕ ማዕረግ መሆኑ ነው።” ሲል አያይዞ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክቱን እስተላልፏል። #ደራሲእንዳለጌታከበደ (ፒኤችዲ) “አሁን የሆንከውን ለመሆን፣ አንተው ራስህ የጻፍከውን ግጥም ኖሮ መገኘትን ይጠይቃል።” ሲል መግቢያ አኑሮ ባጋራውና ራሱ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን በጻፈው ‘ቼ በለው’ በተሰኘው ግጥም እናብቃ፥
ቼ በለው!
ሕይወት ጎዳናው ገጹ ሲለወጥ
በጭነት ታክቶ ጀርባው ሲመለጥ
የእንቅፋት አጽሙ ቋጥኙ ሲገጥ
ሸክም ዘንቦበት ትቢያው ሲላቆጥ
ሲሆን ድጥ በድጥ
ሾህ ጭቃ ቅይጥ
ልብህ አይደንግጥ።
በምኞት ቅዥት በስጋት ርዶ
አይፍረስ ግንቡ ወኔህ ተንዶ
ከቆመው ቆመህ ከንፈር ከመምጠጥ
በተስፋ ፈረስ በልጓም ሸምጥጥ።
አያረጅ የለም አይለዋወጥ
ነገን ተማምነህ በመጓዝ ቁረጥ…
ከሩቅ አልመህ ቅርብ አትርመጥመጥ
ሰግተህ ከምትቆም ስትጋልብ ፍረጥ።
#መምህሩጋሽወርቁ ስለ ፕሮፌሰር በቀለ
መምህር ወርቁ ጎሹ የፕሮፌሰር በቀለ መኮንን አስተማሪ ሲሆኑ የ85 ዓመት ሰውም ናቸው። በቀለ ከወጣትነቱ አንስቶ ህልሙን ለማሳካት ታላቅ ጥረት የሚያደርግ ተማሪዬ ነው ሲሉ በኩራት ምስክርነት ይሰጣሉ። መምህር ወርቁ ጎሹ ቀራጺ በቀለ ከሰዎች ጋር የመግባባት ክህሎትን የታደለ የሚወደውን ሙያ እየሠራ ያለ ብቃት ያለው የሥነ ጥበብ ባለሙያ ነው ሲሉ ይገልጹታል።
ጋሽ ወርቁ 30 ዓመታት አስተምረዋል። በቀለን ሲገልጹት የሚደነቅና የሚከበር ይሉታል። በራሳቸው ጥረት ካደጉት ተርታ ይመድቡታል።
ጋሽ ወርቁ ወደ ኃላ መለስ ብለው የፕሮፌሰር በቀለን የትምህርት አቀባበል ሲያጤኑ የቀን የሌት ጥረት የሚያደርግና የልፋቱን ያገኘ በሚል ያስረዳሉ። ተሰጥዖም የሚታይ ነው ይላሉ።
ዛሬ ፕሮፌሰር መሆኑ ለአገር ትልቅ ኩራት መሆኑንም ነግረውናል።
" የበቀለ ፕሮፌሰር መሆን ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለአገር ኩራት ነው። እኔ እንደ አስተማሪው ይህን የምሥራች ስሰማ ደስታዬ ያይላል።እንኳን ደስ ያለህ ልለውም እወዳለሁ። "ሲሉ ለተወዳጅ ሚድያ ምስክርነት ሰጥተዋል።
በቀለ መኮንን፤
በብሔራዊ ትእምርት ፍለጋ ውስጥ
#በተባባሪፕሮፌሰርቴዎድሮስገብሬ
I
ከብረት እስከ ጨርቅ በደረሱ ትይዩ ተቃራኒዎች መካከል ሲያመላልሰን የከረመው በቀለ መኮንን፣ ጥቁር ጤፍ ፈጭቶ--ጥቁር ጤፍ አቡክቶ “በጋገራቸው” ኪነቶች አማካይነት ሊፈትነን “ጤፍና ነጻነት” የሚል ርእስ በሰጠው አዲስ ትርኢት ተገልጧል፡፡ “ጤፍ” እና “ነጻነት”? ጤፍ ገቢር ነው፡፡ ነጻነት ደግሞ ኀልዮ፡፡ ጤፍ ይሰፈራል፤ ይፈጫል፤ ይቦካል፤ ይጋገራል፡፡ ነጻነት ግን በኅሊና ይነደፋል፡፡ ጤፍ እና ነጻነት በነገረ ፍጥረታቸው አይገናኙም፡፡ 'እናስ በምን ተጠየቅ ተዛምደው በአንድ ርእስ ውስጥ በ“እና” ተዳሩ?' የሚል ጠያቂ ከመጣ ምላሹን የሚያገኘው ከትርኢቱ ዐውድ ይሆናል፡፡
በቀለ በትርኢት መግለጫዎቹ በገሀድ እንደሚጠቁመን በአዳዲስ ሥራዎቹ ውስጥ ረቂቁ “ነጻነት” በግዙፉ ጋሻ ውስጥ አድሮ ተጨባጭ ሆኗል፡፡ በእርግጥ ጋሻ የሚመስሉ “እብጠቶች” በበቀለ ዕይታዊ መድበለ ቃላት ውስጥ የሰርክ ጉዳዮች ናቸው፡፡ በቀደሙት ትርኢቶች ውስጥ ጋሻዎች አንድም ቅርጽ ከቅርጽ ተጋጭተው ለሚፈጥሩት “ግብታዊ” ፍቺ ሲባል ይመላለሳሉ፤ አንድም ደግሞ የማረሻን የገነነ ወንዴነት ማስከኛ ሆነው በሚዛን ጠባቂነት (as a feminine energy) ይመጣሉ፡፡ በ“ጤፍና ነጻነት” ነጻነት በጋሻ ውስጥ በማደሩ፣ ጋሻ ከቀደመ ግብሩ የተለየ አዲስና ቋሚ ሚናና ግብር ይዟል ማለት እንችላለን፡፡ አዲስ ግብር ለመያዙ ምስክሩ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ በትርኢቱ ውስጥ የሚገጥሙን ጋሻዎች በሙሉ በጤፍ ዱቄት የተገነቡ (የተለሰኑ) ናቸው፡፡ የጋሻዎቹ በጤፍ ዱቄት መገንባት አንድም፣ በትእምርቶቹ መካከል የባሕርይ መጋራት እንዲፈጠር፤ አንድም በኪነቱ ውስጥ ጥንድ ምናብ--ድርብ አስተማስሎ (double representation) እንዲከሰት ዕድል ሰጥቷል፡፡ የጉዳዮች በአንድ ወደተሸረቡ መንታ ትእምርትነት ማደግ ተመልካች ሐሳቡን የሚያሰላበትን፣ ትችቱን የሚያፍታታበትን ምቹ የመፈከሪያ ዐውድ እንዲያገኝ አስችሎታል፡፡
ጋሻ የነጻነት እና የአርበኝነት ማኅደር ነው፡፡ (ይህ ዓይነቱ የጋሻ ፍቺ በተገኘበት ባህል ውስጥ ጭምር ይታወቃል፡፡) ቆየት አድርጌ በስፋት እንደማሳየው ጤፍ በፈንታው የ“ኢትዮጵያ” እና “የኢትዮጵያዊነት” ብሔራዊ ትእምርት ነው፡፡ በዚህ ዐውድ የብሔራዊ ትእምርት ፋይዳ አንድም፣ በነጻነት፣ በአገር እና በብሔራዊ ምንትነት መካከል ያለውን ረቂት ተራክቦና ውስብስብ ተጻምሮ ተጨባጭ ማድረግ ነው፡፡ አንድም ደግሞ ተራክቦውን--ተጻምሮውን ጠብቆ ለማኖር ዜጎች በአርበኝነት መንፈስ የሚከፍሉትን የላብና የደም መስዋዕትነት ማመልከት ነው ማለት እንችላለን፡፡ (በ“Gluten-free-dom II” እንጀራ የጠመጠመ ጋሻ በአናታቸው የደፉ፣ በትኩስ የአመድ ደለል ላይ/ውስጥ የቆሙ ሰባት እናቶች እንዲህ ላለው አንድምታ አስረጂዎች ይሆኑናል፡፡)
II
ብሔራዊ ትእምርቶች የብሔራዊ ምንትነት ግላጼዎች (identity expressions) ናቸው፡፡ የምንትነቱ ሥሪት (identity construction) በተረኮቹና በትእምርቶቹ ጥራትና ጥንካሬ ላይ ይወሰናል፡፡ ግላጼዎቹ እና ሥሪቱ የሚተጋገዙ ብቻ ሳይሆን የሚተካኩ ጉዳዮች ጭምር ናቸው፡፡ ያንዱ መድከም ሌላውን ያጎድላል፡፡ ያንዱ መዛል ሌላውን ያፈርሳል፡፡ የብሔራዊ ትእምርት ቀረጻ ብሔራዊ-ጥበባዊ ተልእኮ ነው፡፡ የአንድ ሕዝብ ብሔራዊ ምንትነት በአንጻራዊነት ለዘመናት ጸንቶ ይዘልቅ ዘንድ ተረኮች (ቃላዊ፣ ዕይታዊ፣ ትውናዊ፣ ወዘተ. ተረኮች) እና ትእምርቶች በጥንቃቄ መመረጥና መቀናበር፣ በየጊዜው እየተመረመሩ መታረምና መከለስ ይኖርባቸዋል፡፡ ብሔራዊ ምንትነት በዐቢይነት የውክልና ጉዳይ ነው፡፡ በአንድ አገር ውስጥ እያሉ እንደሌሉ የተቆጠሩ ወገኖች፣ ቸል የተባሉ ሰብአዊ ዕሤቶች፤ አቅም ባገኙ፣ የኃይል ሚዛን በለወጡ ጊዜ በነባር ተረኮች እና ትእምርቶች የተሸመነውን ብሔራዊ ምንትነት እስከ መሻር፣ አፍርሶ እንደ አዲስ እስከመሥራት የሚያደርስ ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ ይህ ሲከሰት የአገር ግንባታ ሂደት ይስተጓጎላል፤ ማኅበራዊ ውጥረት ይነግሣል፡፡ (የዛሬዋ ኢትዮጵያ ለዚህ ዓይነቱ እውነታ አብነታችን ናት፡፡) በመሆኑም ብሔራዊ ትእምርት ቢያንስ ቢያንስ ረጅም የታሪክ ዘመንን፣ ሰፊ መልክአ ምድርን እና ገሀድ የወጡ የማኅበረሰብ ክፍሎችን እና ዕሤቶችን ሊያካልል ይገባል፡፡ ብሔራዊ ትእምርት ከውክልናው ፈርጀ ብዙነት ባሻገር በኪነት ከፍታው እና በኀልዮ ጥራቱም ተለይቶ መታወቅ አለበት፡፡ ጥቅል በሆነ አነጋገር፣ ብሔራዊ ትእምርት ጥልቅ በሆነ ጊዜ ውስጥ፣ ጽኑእ በሆነ መሠረት ላይ የሚታነጽ በነባርና በአዳዲስ ዕሤቶች ትብብር የሚሸመን ዐውራ ምስል ነው፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ላለ ኅብረ ባህላዊ አገር ብሔራዊ ትእምርት በትግግዝ የሚፈጸም ብሔራዊ--ኪናዊ ተልእኮ ነው፡፡ ብሔራዊ ትእምርት እርስ በርስ ሊናበቡና ሊከታተሉ በሚችሉ በግለሰብ፣ በቡድን፣ በትውልድ በሚፈጠሩ ገባር ምናቦች ትግግዝ በዘመናት ሂደት ምልዓት ላይ የሚደርስ ዐውራ ትእምርት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ኪናዊ ትግግዝ--የምናብ ተናባቢነትና የምስል ተከታታይነት--በተጨባጭ ለማሳየት “ጤፍና ነጻነት”ን በሁለት መንገዶች ማንጸር እንችላለን፡፡ ቀዳሚው መንገድ ይህንን ትርኢት ከበቀለ መኮንን ነባር ትርኢቶች ጋራ እያመሳከሩ መፈከር ሲሆን፤ ተከታዩ ደግሞ በየትኛውም የኪነት ዘርፍ ካሉ ዘመነኞቹ ጋራ--ለምሳሌ ከአዳም ረታ ጋራ--እያናበቡ ማስተሳሰር ነው፡፡ የበቀለ መኮንንን ዕይታዊ ጥበብ ከአዳም ረታ ቃላዊ ኪነት አናብቦ በብሔራዊ ትእምርትነት ለማስላት በቂ ምክንያቶች አሉ፡፡ ለዛሬው ትርኢት የነፍስ ያህል የሆነውን ዐውራ መባያ[1]--ጤፍን በበቀለ የአከያየን ልማድ ውስጥ ከገነነው፣ ከማረሻ ጋራ አስተሳስሮ ለማሰብም እንዲሁ፡፡ ከምክንያቶቹ ውስጥ መሠረታዊዎቹ፡- አንደኛ፣ የዐውድ ተዛማጅነት፤ ሁለተኛ፣ የኀልዮ (የጭብጥ) ተከታታይነት፤ ሦስተኛ፣ የቅኝት ወይንም (የርእዮተ ዓለም) ተወራራሽነት፤ አራተኛ፣ የጊዜ ጥልቀት (የነገረ ፍጥረት ብሉይነት)፤ አምስተኛ፣ ሥነ ልሳናዊ ተዛማችነት ናቸው፡፡
“ማረሻ” የግብርና ማምረቻ መሣሪያ፣ “ጤፍ” ደግሞ የግብርና ምርት በመሆናቸው በተፈጥሮ የቅደም-ተከተል ዝምድና አላቸው፡፡ (ተፈጥሯዊው ቅደም ተከተል በጉዳዮቹ መካከል አለ ያልነውን የጭብጥ ተከታታይነት እና የትእምርት ተጋጋዥነት ተጨባጭ ያደርግልናል፡፡) የማምረቻ መሣሪያው (ማረሻ)፣ የአምራቹ (ገበሬ) እና የምርቱ (ጤፍ) ተፈጥሯዊ የተራክቦ ዐውድ ገጠር ነው፡፡ ጤፍ እና ማረሻ ከ85 ከመቶ በላይ ኢትዮጵያዊ ይኖርበታል የሚባለውን፤ ዳሩ ግን በአገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ተገቢ ሥፍራ የተነፈገውን ወገን በቀጥታ ይመለከታሉ፡፡ ከያኒው ለተገፉ፣ ሥፍራ ለተነፈጉ ብሔራዊ ጉዳዮች ማድላቱ የትእምርቶቹን ምርጫ ተገቢነት ከማረጋገጡ ባሻገር ቅኝቱን ርእዮተ ዓለማዊ ያደርገዋል፤ (“history from below” እንደሚባለው)፡፡ ገጠርን አትኩሮ፣ ነባር የግብርና መሣሪያንና ጥንታዊ ምርትን (ማረሻንና ጤፍን) ከዚያው ዐውድ መልምሎ በምናብ ማጥለቁ፣ በምስል ማበልጸጉ እና በኀልዮ ማራቀቁ ብዙኃኑን የሚወክል፣ ዘመናትን የሚዋጅ ጽኑእ ብሔራዊ ትእምርት ለመቅረጽ ዕድል የሚሰጥ ይመስለኛል፡፡
የጤፍ ነገረ ኪን እና ፖለቲካም (the poetics and politics of teff) በቅኝት ከዚህ የሚለይ አይመስለኝም፡፡ ጤፍ በመጠን በአነስተኛነቱ “ዝነኛ” ነው፡፡ ለምሳሌ፣ አንድ የስንዴ ቅንጣት በአማካይ ከአንድ መቶ ሃምሳ የጤፍ ቅንጣቶች ጋራ እኩል እንደሆነ ይገመታል፡፡ ይህ ደግሞ “ከትውልድ ሥፍራው” አልፎ በዓለም ካሉ የእኽል ዝርያዎች በሙሉ በመጠን ትንሹ ያደርገዋል፡፡ በደስታ ተክለ ወልድ መዝገበ ቃላት ይህ የእኽል ዘር በተከታዩ መንገድ ተበይኖ እንመለከታለን፤ “ጤፍ፤ የታናሽ እኽል ስም፤ የሣር ዐይነት ሙርዬ የሚመስል፡፡ (ተረት)፤ ሳይቸግር ጤፍ ብድር” (19962፡ 675)፡፡[2] በዓለም ምግብ ድርጅት ገጽ ላይ ሰፍሮ እንደምናነበው፣ ጤፍ ከኢትዮጵያ ውጪ ባሉ አገራት፣ ለምሳሌ በደቡብ አፍሪካ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከከብቶች ቀለብነት ባለፈ የአፈር መሸርሸርንና የውሃ ብክነትን ለመቀነስ ታስቦ የሚለማ “ተራ ሣር” ነበር፡፡[3] ተወዳጅ ነው በሚባልባት እናት አገሩም ቢሆን በመጠን ማነሱን ታክከው የሚቀርቡ ንጽጽሮች አጓጉልነት አላጣቸውም፡፡ ለአብነት፣ “ከመጤፍ አልቆጠረኝም” እና “ሰው ጤፉ” የሚሉ አገላለጾች በደረጃ ማነስን በገሀድ ያውጃሉ፡፡
ጤፍ በጄኔቲካዊ አወቃቀሩ እጅግ የተወሳሰበ፣ በጾታ ቅንብሩ የተደባለቀ (ፈናፍንት)፣ በምግብ ይዘቱ የበለጸገ የእኽል ዓይነት እንደሆነ የአዝርእት ባለሙያዎች ያስረዳሉ (ሰይፉ 1997)[4]፡፡ ሰይፉ ከተማ በመስኩ ላይ የተካሄዱ ምርምሮችን በከለሱበት ጽሑፋቸው እንደሚያስረዱን፣ የጤፍን የትውልድ ቦታ በእርግጠኝነት መናገር ቢከብድም፣ ጄኔቲካዊ ብዝኃነቱን በማጤን ኢትዮጵያ እናት ምድሩ ልትሆን እንደምትችል መገመት አስቸጋሪ አይሆንም፤ “[T]he genetic diversity for teff exists nowhere in the world except in Ethiopia, indicates that tef originated and was domesticated in Ethiopia” (12)፡፡ ጤፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ጥንታዊ ከሚባሉ ጥቂት የእኽል ዘሮች መካከል አንዱ ነው፡፡ በዚህ የእኽል ዘር ላይ ከተካሄዱ ምርምሮች መካከል ብዙዎቹ፣ Nicolai Vavilovን (1951)[5] መሠረት በማድረግ፣ ቅድመ ክርስቶስ ከ4000–1000 በኢትዮጵያ ውስጥ እንደበቀለና ተስፋፍቶ እንደለመደ ይገምታሉ፡፡ እንደ ጤፉ ሁሉ፣ “ኢትዮጵያዊው” ማረሻ፣ ከዕድሜው ጥንትነት ባለፈ ልደትና ዕድገቱም እዚሁ መሆኑን የሚያመላክቱ ምርምሮች አሉ፤ ለምሳሌ፣ Hubert Cochet ኢትዮጵያውያን ገበሬዎች በማረሻ ለ2000 ዓመታት እንዳረሱ ይጠቁማል (2011፡ 31)፡፡[6]
በኢትዮጵያ ውስጥ ከሦስት ሺህ በላይ ዘመናትን ያስቆጠረው፣ ከአገሪቱ ሕዝብ መካከል 70 ከመቶው በእንጀራ መልክ ይመገበዋል ተብሎ የሚገመተው ጤፍ (ታደሠ 2017፡ 50) በሦስቱ ዐበይት የሥነ ልሳን ቡድኖች ተቀራራቢ ስያሜም አለው፡፡ በአማርኛ “ጤፍ”፣ በኦሮምኛ “tafi” በትግሪኛ “ጣፍ”፡፡ በቀለም ስርጭትም ረገድ ወተት ከመሰለ ነጭ (ማኛ) አንስቶ እስከ ጥቁር ድረስ የሚዘልቁ አራትና አምስት ቀለማትን ያቅፋል (አዳም በሁሉም ቀለሞች የሚጫወት ሲሆን የበቀለ ምርጫ ጥቁሩ ነው)፡፡ እንዲህ ያለው የባሕርይ ውስብስብነት፣ የጾታ መንታነት፣ ኅብረ ቀለማዊነት ጤፍን--በአዳም ረታ ጥበበ ቃላት እና በበቀለ ዕይታዊ ጥበብ--ውስጥ ለብሔራዊ ትእምርትነት የተመቸ መባያ አድርጎታል፡፡ “ማረሻ” በበኩሉ ኢትዮጵያውያን የወል ምንትነታቸውን ከሚቀርጹባቸው ብሉይ ዕሤቶች መካከል አንደኛው ነው፡፡ የወልነቱን በዐበይቱ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ውስጥ ባለው የስያሜ ተወራራሽነት መረዳቱ አያሰቸግርም (የአማርኛው “ማረሻ”-- በግእዝ “ማሕረስ”፣ በኦሮምኛ “maarashaa”፣ በትግርኛ “ማሕረሻ” የሚሉ አቻዎች አሉት)፡፡ ብሉይ ነው ስል አንድም፣ የዘፍጥረቱን ጥንታዊነት፤ አንድም፣ የጊዜ ጥልቀቱን ታክኮ የሚመሠረተውን ባህል ጽኑእነት ማመልከቴ ነው፡፡ በተፈጥሮው ቀጥ ያለው፣ የተሳለውና የሾለው ማረሻ፣ በበቀለ ትርኢቶች ውስጥ በከያኒው ፈቃድ፣ ፍላጎትና እጅ መዋቅሩ ተናግቶ፣ “ተፈጥሮው” ተዛብቶ ልክ እንደ ጤፍ ወደ ፈናፍንትነት ተቀይሯል፡፡ የበቀለ ማረሻዎች መዋቅር መናጋት የአድሏዊው የተባዕትነት ሥርዓት ፈርሶ በአዲስ ተምኔታዊ ሥርዓት የመተካቱ አምሳያ ነው፡፡ ከዚህ ሥርዓት ውስጥ ነው እንግዲህ ከያኒው አዳዲስና ነባር ዕሤቶች ተዳርተው የሚሰናኙበትን ብሔራዊ ትእምርት ለመፍጠር የሚታገለው፡፡[7]
ጤፍ እና ማረሻ ኢትዮጵያውያን ጥልቅ ከሆነ ጊዜ፣ የጋራ ታሪካቸውን፣ ርእዮታቸውንና ንጽረታቸውን የሚጠልቁባቸው፤ ሩቅ ከሚባል ትናንት የወል ልቡናቸውንና ምንትነታቸውን የሚያደሩባቸው “ቁሳዊ” ዕሤቶች ናቸው፡፡ ቤኔዲክት አንደርሰን፣ “It is the magic of nationalism to turn chance into destiny” (1983፡ 12)[8] እንዳለው ዕጣ ፈንታቸው ጭምር ተጠላልፎ የተሰናኘባቸው የወል ዕሤቶች፡፡ ማን ከዕጣው ማምለጥ ይቻለዋል? እንደሚታወቀው እንዲህ ያለ ዕሤት በጥልቅ ጊዜ እና በጽኑእ መሠረት ላይ የሚቆም አገር ለማነጽ ምቹ ዕድል ይፈጥራል፡፡ በእርግጥ አንድ ማኅበር በጽናት ይቆም ዘንድ ዕጣውን ከቋጠረበት ሩቅ ትናንት በተጨማሪ፣ በገነነ “የሕዝብ ማኅበራዊ ልቡና” ነገውን የሚዋጅበት የጋራ ስኬት እንደሚያስፈልገው አሌ አይባልም፡፡ ለዚህ ዓይነቱ ስኬት ጤፍ እንግዳ አይመስለኝም፡፡ ትናንት፣ ጤፍን ለሰው ልጅ ምግብነት በማዋል ረገድ ኢትዮጵያ ከዓለም ብቸኛ አገር ነበረች፡፡ ዛሬ፣ በተለይ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ በሚኖሩ፣ እንጀራን መለያቸው ባደረጉ በ“ነባሬ ባዕድ”[9] (diaspora) ኢትዮጵያውያን በሚተዳደሩ ምግብ ቤቶች አማካይነት ዝናን ያተረፈው ይህ የእኽል ዘር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሯል፡፡ በጣዕሙ፣ በምግብ ይዘቱና ለጤና ባለው ጠቀሜታ ከተመጋቢው እኩል በሥነ ምግብ ተመራማሪዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው ጤፍ በትልልቆቹ የዓለም የመገናኛ ብዙኋን ሳይቀር (ለምሳሌ፣ በBBC, VoA, The Washington Post, The Guardian, The New York Times, ወዘተ.) “the next ‘super grain’ of the World” የሚል መወድስ ወርዶለታል፡፡ ይህንን ዝና ተከትሎ ሊመጣ የሚችለው ማኅበራዊ ከፍታ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ--(as a national branding) ብሔራዊ ክብርና ኩራትን የመፍጠር አቅም አለው፡፡ የጤፍ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው አንድም በመከባበር ላይ የተመሠረተ አንድነትን ለመፍጠር የሚያግዝ፤ አንድም በጎሣ፣ በሃይማኖት እና በቋንቋ ምክንያቶች የተፈረቀቀውን ብሔራዊ ልቡና (the national psyche) ለማከም የሚያስችል ዕድል እመስጠቱ ላይ ነው፡፡[10]
III
ትኩረታችንን ወደ ዛሬው ትርኢት እንመልስ፡፡ “ጤፍና ነጻነት”፡፡ ጤፍ የ“ኢትዮጵያ” እና “የኢትዮጵያዊነት” ብሔራዊ ትእምርት፤ ጋሻ በበኩሉ የነጻነት እና የአርበኝነት ማኅደር መሆኑን በመግቢያዬ አመልክቻለሁ፡፡ እንዲህ ያለው የጋሻ ትርጉም ህልው በሆነበት ባህል ውስጥ ጭምር ታውቆ የሚሠራበት ነው፡፡ በትርኢቱ ውስጥ ከቀረቡት ሥራዎች ብዙዎቹ ከጤፍ እና ከጋሻ ተራክቦ የተገኙ ናቸው፡፡ ይህ ማለት ግን ሁለቱ ጉዳዮች በሁሉም ትዕይንቶች ውስጥ እኩል ሥፍራ አላቸው ማለት አይደለም፤ በፍጹም፡፡ ጤፍ በሚናው ይልቃል፡፡ የጭብጥ ክትትል ከመፍጠር፣ የመተርጎሚያ ዐውድ ከመተለም ባለፍ ዝርው ህልውናም አለው፡፡ ጤፍ በቤት ውስጥ ቁስነት ተከስቷል፤ የግድግዳ ምርጊት ሆኖ ተገልጧል፤ ወዘተ፡፡ ጤፍ ታሪክ ነው፤ ምጣኔ ሀብት ነው፤ ፖለቲካ ነው፤ ርእዮተ ዓለም ነው፡፡ በጤፍ የሰው አካል ተገንብቷል፤ የሰው ገጽ ተነድፏል፡፡ ገጻተ ሰብኡ ከጤፍ መልኩንም ይዘቱንም ወርሰዋልና ወደ ጤፍነት ተለወጡ ማለትም እንችላለን፡፡ ከተጨባጭ ሁነቶችና ህልውናዎች ባለፈ ጤፍ ለልእለ አካላዊ ክስተቶች ማድሪያነት ውሎም እንመለከታለን፡፡ ለምሳሌ፣ “ጓዳና ግርግዳ” የሚል ርእስ በተሰጠው፣ በቀጫጭን ዘንጎችና በጥቁር ጤፍ ትግግዝ በተቀናበረ ግድግዳ ላይ (በጤፍ ቡኮ የተመረገ፣ ጋሻ ያዘለ ግድግዳ) ከያኒው ይሁነኝ ብሎ በተዋቸው ሽንትር ሽንቁሮች ውስጥ አሳልፈን የምናየው “የቤተ ክርስቲያን” ጨርቅ ልእለ ፍጥረት ህላዌ ከልደትና ሞት ጋራ የታተመበት ነው፡፡ በመሆኑም ጤፍ በትርኢቱ ውስጥ የነገረ ሰብእን ዕጣ የምናሰላበትን ስብርባሪ አፍታ ጭምር ይሰጠናል ማለት ነው፡፡
በትርኢቱ ውስጥ በጤፍ ከተገነቡ ምስሎች መካከል ገጸ ሰብእ[11] የተነደፈው በሁለት ተከታታይ ትዕይንቶች ውስጥ ብቻ ነው፤ በ“Gluten-free-dom I” እና በ“Gluten-free-dom II”፡፡ እነዚህ ትዕይንቶች “ተከታታይ” ብለን ብቻ የምናልፋቸው አይመስሉኝም፡፡ ይልቁንም እጅግ በተወሳሰበ ትእምርታዊነትና በተራቀቀ ዘይቤ የተከየኑ፣ ለፈርጀ ብዙ ንጽጽርና ትርጓሜ የተመቹ ወደረኛ ቅርጾች ናቸው፡፡ ኋለኛውን መነሻ እናድርግ፡፡ ጀርባ ለጀርባ እንጂ ፊት ለፊት የማይተያዩ፣ ትከሻ ለትከሻ ገጥመው ክብ የሰሩ የሰባት ነፍሰ ጡሮች ትዕይንት ነው፡፡ በዚህ ትዕይንት ውስጥ ሴቶቹ ክብነቱን ጠብቆ በጠባቡ በሚዞራቸው ቡላ ቀለም ያለው የአመድ ደለል ላይ ቆመዋል፡፡ ደለሉን ተከትሎ በክቡ የሰፈነው ነጭ አመድ ከሸማ የተሠራ ምንጣፍ፣ በዙሪያው የተኮለኮለው የከሰል ሰልፈኛ ደግሞ ጥቁር ጥለት ይመስላሉ፡፡ በሆዳቸው ፍሬ የያዙ ሰባት ሴቶች የተደራረቡ እጆቻቸውን ሐፍረታቸው ላይ ጣል እንዳደረጉ፣ እንጀራ የለበሰ ጋሻ አናታቸው ላይ እንደደፉ፣ በአክብሮት ይሁን በፍርሐት አልያም በሐፍረት አቀርቅረዋል፡፡
ሁለተኛው ትዕይንት የአንድ ሰው “ገድል” ነው፡፡ ይህንን ገድል እኔ “ገልና ገልቱ” ብዬ እጠራዋለሁ፡፡ (“ገል” የጋን ስባሪ፤ “ገልቱ” ያልሠለጠነ፣ በድንቁርና የተደፈነ፡፡) ዙሪያውን በተሰባበሩ ሸክላዎች የተከበበ፣ ከምድር ከፍ ብሎ የታነጸ፣ ባለ ስድስት ማዕዘን ቅርጽ ያለው ጡብ ገዝፎ ይታያል፡፡ ሙቀት ፍለጋ እጆቹን ወደ ፊት የዘረጋው ሰው እጡቡ አናት ላይ ባፍጢሙ እደፋው የአባቶቹ ጋሻ ላይ “ተመቻችቶ” ተቀምጦ “የደቀቁ የሸክላ ገሎችን በተመስጦ ይሞቃል”፡፡ ሁለቱ ትይዕንቶች የመከታተል ብቻ ሳይሆን እርስ በእርስ የመተረጓጎም ባሕርይም አላቸው፡፡ ይህንን ለማጤን እላይ በገለጻዎቹ ውስጥ የሰፈሩትን ወደረኛ ድርጊቶችና ሁነቶች ማነጻጸሩ ብቻ በቂ ይመስለኛል፡፡
ሴቶቹ በገዛ ፈቃዳቸው ፋታ ለማይሰጥ፣ ድካም ለበረታበት፣ ህመም ላለበት ኃላፊነት ራሳቸውን የሞሸሩ ይመስላሉ፡፡ አንድም የቁጥራቸው ሰባትነት የኃላፊነቱን ክብደት ያጸናል፡፡ ሰባት ቁጥር በትውፊት፣ በሃይማኖት፣ በኪነት፣ ወዘተ. ውስጥ ምልዐትን፣ ፍጹምነትን ለማመልከት ተመላልሶ የሚመጣ ነባር መባያ ነው፡፡ ፍጹምነቱና ሙሉነቱ የበረከትም የቅጣትም ሊሆን ቢችልም፡፡ አንድም ሴቶቹ የቆሙበት የአመድ ደለልም ሆነ አካላቸው ተገጣጥሞ የፈጠረው የቅርጽ ክብነት እላይ በቁጥር ጸና ያልነውን በድካምና በህመም የተሞላ ኃላፊነት ፍጹም ያደርገዋል፡፡ በክብነት ውስጥ መውጫ ቀዳዳ ይጠፋል፤ መነሻና መድረሻ ይታጣል፡፡ ለእረፍት የሚሆን ጥጋት አይሰጥም፡፡ በቀለ በምስሉ መግለጫ ላይ በገሀድ እንደሚጠቁመን ሰባቱ ሴቶች በዝርው ሰባቱን ቀናት ይወክላሉ፡፡ በዚህም ሰንበት ተገድፏል፤ የለመድነው የጊዜ መስፈሪያ ተሽሯል፡፡ ቀናቱ በሴቶቹ ድርጊት ተቃኝተው “ጊዜ” ከሰው ጋራ የሚለያይበት መስመር ደብዝዟል፡፡ መነሻ፣ ማጋመሻ፣ መዳረሻ የሚባሉ አንድም፣ የድርጊትና የሁነትና መሥፈሪያዎች፤ አንድም የጊዜ ዋቢዎች ሳስተዋል፡፡
እላይ በእንጥልጥል ወደተውነው ጉዳይ እንመለስ፤ “ገሎችን መሞቅ” ምን ማለት ነው? ከከያኒው ምስክርነት ባሻገር የወጣቱ የእጅ አዘረጋግ ሁኔታ በሙቀቱና በአካሉ መካከል በፈጠረው ሚዛን ሙቀትና ምቾት መኖራቸውን እንረዳለን፡፡ ግን እሳቱ ወዴት ነው? የሙቀቱ ምንጭስ ምንድ ነው? ለእነዚህ ጥያቄዎች በአንድምታ የምንገልጠው እውነታ ካልሆነ በቀር፤ በቀጥታ የምናገኘው መልስ ያለ አይመስለኝም፡፡ በባለ ስድስቱ ማዕዘን ጡብ ዙሪያ በሰፊው የፈሰሱት የገል ስብርባሪዎች በኢትዮጵያውን የቆየ ታሪክ ውስጥ ቋሚ ሥፍራ ያላቸው፣ በሸክላ የተሠሩ አገረ ሰብአዊ ዕደ ጥበባት ናቸው፤ በየዓይነቱ --የጀበና፣ የምጣድ፣ የድስት፣ የጋን፣ የጣባ፣ የዕጣን ማጨሻ፣ ወዘተ. ስብርባሪዎች፡፡ ስብርባሪዎቹን በቅርበት ላጤነ ሰው ዕደ ጥበባቱ በእርጅና ምክንያት ከሰርክ ግብራቸው የተገለሉ አይመስሉም፡፡ ይልቁንም ከነወዛቸው ከነጉልበታቸው ያሉ፣ ከግብራቸው በግድ ተነቅለው የደቀቁ ነው የሚመስሉት፡፡ በሌላ ቋንቋ ሙቀቱ የሚመነጨው ከገሎቹ ትኩስነት ነው፡፡ ትኩስነት፤ አንድም፣ ከእሳት ምድጃ የሰበሰቡትን ሙቀት ይዞ ማቆየት ነው፡፡ ገልቱው ዕደ ጥበባቱን ከተሰየሙበት ምድጃ ላይ ነቅሎ --ቡናና ወጡን ደፍቶ፣ ዳቦና እንጀራውን ገልብጦ--ጀበናውን፣ ድስቱን፣ ገበር ምጣዱን፣ ምጣዱን አንክቶ፣ እንካቹን ሜዳ ላይ ዘርቶ ትኩስነታቸውን እየሞቀ ነው፡፡ አንድም በዘይቤ ተራ እንናገርና ትኩስነት አፍላነት ነው፡፡ የአገልግሎት ዘመን አለመጋመስ፡፡ ከብርታትና ጥንካሬ ጋራ መሆን፡፡ ጠላውን ደፍቶ፣ እርጎውን ገልብጦ፣ ወዘተ. ያደቀቃቸው የሸክላ ውጤቶች፡፡
በዚሁ ተጠየቅ ከተጓዝን የሴቶቹን አቋቋም በመመርመር በሰባት ቁጥር እና በክብ ቅርጽ ትግግዝ ጸና ያልነውን ህመም በተጨባጭ መመልከት እንችላለን፡፡ የሴቶቹ ፋታ የለሽነት ድርጊቶቹንና ሁነቶቹን በሙሉ ወደማያቋርጥ ሂደትነት ለውጧቸዋል፡፡ ይህንን ለማጤን--በተለመደው አገላለጽ--እንጀራ የጠመጠመ ጋሻ ከሰፈነበት የራስ ጸጉራቸው፣ በአመድ ደለል እስከተደበቀው የእግር ጥፍራቸው ድረስ መመልከቱ በቂ ነው፡፡ አመዱ እና እንጀራው ትይዩ ናቸው፤ አንዱ ምርት ሌላው ግርድ፡፡ ከአናት እንጀራው በተመረተ ቁጥር ከስር አዲስ አመድ ይወድቃል፡፡ አዲስ አመድ --ትኩሣቱን ያልጨረሰ አመድ፤ ረመጥ፡፡ ይህ ማለት ሴቶቹ ረመጥ ላይ ቆመዋል እንደማለት ነው፡፡
ቀደም አድርጌ ለማሳየት እንደሞከርኩት ሴቶቹ እንዲህ ያለውን በድካምና በህመም የተሞላ ኃላፊነት በፈቃዳቸው መርጠው ተቀብለዋል፡፡ በማሕፀኗ ሽል የያዘችን እናት በረመጥ እስከመድበን የሚያደርስ መስዋዕትነት ምን የሚሉት ኃላፊነት፣ እንዴት ያለ ዓላማና ተልእኮ ነው? የራስን ሰብእና የሚያደቅቅ፣ ህልውናን የሚያመነምን፣ ሕይወትን የሚያሰልል ተግባር ውስጥ በፈቃድ መሳተፍ ራስን ለከፋ ጉዳት ማጨት ይመስላል፡፡ የፈቃድ ጉዳት (self-destruction)፣ ከፍ ሲልም የፈቃድ ሞት ከዳግም ልደት ጋር የሚዛመዱበት እንዲህ ያለው አቀራረብ ሚታዊ አመሳሰል ነው፡፡ ይህን ዓይነቱን አመሳሰል በሚቶሎጂ ውስጥ በብሉየ መዋዕልና[12] ደንብ ከተቀረጹ ምስሎች (archetypal imageries) ጋራ አቆራኝተን መመልከት እንችላለን፡፡ በሆዳቸው ፍሬ የያዙ ሴቶች ትከሻ ለትከሻ ገጥመው ክብ መሥራታቸው፣ በሠሩት ክበብ ውስጥ ረመጥ ላይ መቆማቸው፣ በአመድ ደለል መያዛቸው፣ እንጀራ “ማብቀላቸው” በአንድ ግዜ ኦሮቡረስን (በክብነት) እና ፊኒክስን (በረመጥነት-አመድነት) አቃልጠን እንድናስብ ያደርገናል፡፡ ራሷን አቃጥላ ከትቢያዋ ላይ ነፍስ የምትዘራው ፊኒክስ (Phoenix) እና በክብ ቅርጽ ከጅራቱ አንስቶ ሙሉ አካሉን በልቶ በአዲስ ህልውና የሚከሰተው አሮቡሮስ (Ouroborus) “ሁለንተናዊ” ሊባሉ የሚችሉ የህመምና ድኅነት፣ የሞትና ልደት ትእምርቶች ናቸው፡፡ ባዶ እግራቸውን ረመጥ ላይ የቆሙ ሰባት እናቶች በቸልታ የተጎዳውን ነባር ምንትነት፤ በሆዷቸው የያዟቸው ሰባት ፍሬዎች ደግሞ እንደ አዲስ ይወለድ ዘንድ የሚጠበቀውን ርእይና ርእዮት ይወክላሉ፡፡ ከዚህ ትዕይንት ዓላማዎች መካከል አንዱና ምናልባትም ቀዳሚው ለዘመናት ለኖረው፣ ዳሩ ግን ቸል ለተባለው የእናቶች ህመምና ድካም--የላቀ ብሔራዊ ተግባር--ዕውቅና መስጠት ነው፡፡ ይህ ዕውቅና ልዕለ ሰብአዊ እና ልዕለ ታሪካዊ እንጂ ተርታና ሰርካዊ አይደለም፡፡ በሌላ ቋንቋ፣ ከያኒው ከፍ ባለ የአከያየን ስልትና ርእዮት እናቶችን ጥልቅ ጊዜ ውስጥ በመትከል ወደ ሚታዊ ተጋዳሊነት ቀይሯቸዋል፡፡ በምላሹም ከዚያው ጥልቀት ውስጥ በጽናት የሚቆም ብሔራዊ ትእምርት እና ብሔራዊ ምንትነት ለማስገር ሞክሯል፡፡
አንድም እናቶች ካለመኖር ህጽን መኖርን አስገኝተዋልና ለዚያም ኪናዊ ውዳሴ እንደ ማውረድ ሊቆጠር ይችላል፡፡ በአንዳንዶች ግምት “ጤፍ” የሚለው መጠሪያ “ጠፋ” ከሚለው ቃል የተገኘ ነው፤ ጠፋ፣ መኖር አቆመ፣ ህልውናው አበቃ እንደማለት፡፡ በሌላ ቋንቋ የዚህ የእህል ዘር የመጠን አነስተኛነት ከመኖር ይልቅ ላለመኖር ይቀርባል እንደማለትም ነው፡፡ የ“ጤፍ” የፍቺ ነቅኡ “ጠፋ” የሚለው ግስ ከሆነ፣ አንድም፣ ጤፍ የምንለው፣ በጣት የምንቆነጥረው ደቃቅ ነገር በተጨባጭ አለመኖርን ያስተማስላል (the representation of absence, the visibility of invisibilty) እንደማለት ነው፡፡ አንድም ዐውራውን የብሔራዊ ሚቶች መሻት--የመነሻዎች ሁሉ መነሻ የመሆንን፣ ከምንምነት ነቅእ የመፍለቅን መሻት--ይጠልፍልናል፡፡ ጤፍ አለመኖርን ከወከለ ከጤፍ የምንጠልቀው “ኢትዮጵያዊነት” ከእመ አበ አልቦ እንደተገኘ (creation ex nihilo, that is, creation from nothing) ይቆጠራል፡፡ በዘይቤ ተራ እንነጋገርና የኢትዮጵያ ገበሬ “አለመኖርን” ይዘራል፡፡ እናቶች ደግሞ ከአለመኖር ማሕጸን “እንጀራን” የመሰለ ግዙፍ ኑባሬ ያዋልዳሉ እንደማለት ነው፡፡ ከጤፍ አብራክ እንጀራ የመክፈሉን ጉዳይ፣ እናቶቹ በሆዳቸው ከያዙት ጽንስ መወለድ ጋራ አቆራኝቶ ማየት ይቻላል፤ ያ ጽንስ አንድም በነባርና በአዳዲስ እሴቶች ትብብር ይሸመናል ያልነው “ኢትዮጵያዊነት” (pan-Ethiopianism) ነው፡፡ የእንጀራው አናት ወጥቶ በጋሻ ቅርጽ መስፈኑ ደግሞ የልደቱ መፈጸም ማረጋገጫ ትእምርት ነው፡፡ ጋሻ የአርበኝነትና የነጻነት ትእምርት፤ ጤፍ ደግሞ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ማደርያ ነው ካልን፣ በጋሻ መልክ የተከሰተው እንጀራ የዚህ ማረጋገጫ ሰንደቁ (the symbol of national imaginary) ይሆናል፡፡ አንድም በጋሻ ቅርጽ አናታቸውን የከበበው እንጀራ በሰማዕትነት እንዳገኙት የብርሃን አክሊል (halo or nimbus) ሊቆጠር ይችላል፡፡ እንዲህ ያለው ሐቲት ለኪነቱ በ“በብሉየ መዋዕልና” ደንብ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን አጥልቆ የሚተክልበትን ረቂቅ ዐውድ ይሰጠዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን አንጀራን መመገብ የጀመሩበትን ጊዜ የሚያመለክት እርግጠኛ መረጃ የለም፡፡ ነገር ግን የእንጀራን መነሻ የሚጠቁሙ፣ ዘመኑን እስከ ቅድመ ክርስቶስ እስከ 100 ዓ.ዓ.
የሚያደርሱ የቃል ተረኮች እንዳሉ ስትዋርትና አስናቀ ይናገራሉ (1962: 127)[13]፡፡ በእነዚህ ተረኮች ወስጥ እንጀራ ኢትዮጵያውያን በተቸገሩ ወቅት ከልእለ ፍጥረት ህላዌ የተሰጠ በረከት ተደርጎ ነው የሚቀርበው፡፡ (በበቀለ ኪነት ውስጥ ያንን ሚና ወደ ሚታዊ ህልውናነት የተሸጋገሩት እናቶች ወስደውታል):: ቀደም አድርገን የጠቀስነው የታደሠ ጥናት እንደሚያመላክተን (2017፣ 50) ከኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ 70 ከመቶ ያህሉ ጤፍን በእንጀራ መልክ ተመጋቢ ነው፡፡ ይህ ቁጥር የጤፍ እንጀራን ለብሔራዊ ምግብነት የሚያበቃው ይመስለኛል፡፡
ጋኖቹን[14] አንክቶ፣ ባፍጢሙ እደፋው ጋሻ ላይ ተቀምጦ ስብርባሪ ገሎች እየሞቀ በምቾት የሚመሰጠው ገልቱ በፈንታው ፍቺው የዚህ ተቃራኒ ነው የሚመስለው፡፡ በእኔ አረዳድ ትዕይንቱ የዘመናችን ክፉ አባዜ--አገር ለዘመናት ጸንታ የኖረችባቸውን የዕሤት ሥርዓቶች፣ የጋራ ታሪኮች፣ የወል ልቡናዎች የመቀናቀን አባዜ--በስላቅ የተነደፈበት ነው፡፡ ስላቁ የቤቱን ማገር እየመዘዘ በሚያነድድ፣ መሠረቱን እየቆረቆረ ቤቱን ራሱ ላይ በሚንድ ገልቱ ላይ ቢያርፍም፣ አገራዊ አደጋው የምር እና ቅርብ መሆኑን ትላልቅ ጋኖችን በማውደም አሳይቷል፡፡ አገር ጸናባቸው ያልናቸው ረቂቅ ዕሤቶች ወጣቱን በከበቡት ስብርባሪ ገሎች ገዝፈው ይታያሉ፡፡ “ጋን” ከአገረ ሰብእ ጥበብነቱ ባሻገር አገር አጽንተው ያቆዩትን ረቂቅ ዕሤቶች ለመወከል የሚያበቃ ሥነ ልሳናዊ እና ሥነ ፍቻዊ ባሕርይ አለው፡፡ በተለይም ቃሉ “ጋኖች” ተብሎ በብዙ ቁጥር ሲጠራ የፍቺው ስፋት ከማጀት እስከ አደባባይ ይዘልቃል፤ “ጋኖች፤ ትልልቆች ሰዎች ዋኖች ጨዎች ጎምቱዎች አባቶች ዐዛውንቶች፡፡ (ተረት)፤ ጋኖች ዐለቁና ምንቸቶች ጋን ኾኑ” (ደስታ ተክለ ወልድ፣ 280)፡፡ አንድም፣ ከማጀት እስከ ቤተ መንግሥት የተዘረጋ ፍቺ አለው፤ ከጠላ መጥመቂያ፣ ከጠጅ መጣያ ቁስነት እስከ ንጉሥ መጠሪያት የሚደርስ ፍቺ፤ የጃን ሆይ አቻ ሆኖ፣ “ጋን ሆይ ፤-ገናና ሆይ፤--ጃን ሆይ፡፡” (280) እያስባለ፡፡
እስካሁን ለማሳየት እንደሞከርኩት Gluten-free-dom “I” እና “II” በተወሳሰቡ ትእምርቶች እና በተራቀቁ እይታዊ ሜታፈሮች የተከየኑ ድንቅ ምስሎች ናቸው፡፡ በምስሎቹ መካከል የሚካሄደው ንጽጽር ከዚህም አልፎ ልሄድ ይችላል፡፡ እኛ ይህን በይደር ዘግተን ለመጣጥፉ እንደ ማሳረጊያ ወደሚያገለግሉ አንድ ሁለት ነጥቦች እንለፍ፡፡
IV
በትርኢቱ ውስጥ ከቀረቡት ሥራዎች ብዙዎቹ --ከፀሐይ እና ጎጆ (ከባህል እና ተፈጥሮ ) መስተጋብር ከተቀሰቀሱ የሰርክ ደፋ ቀናዎች (“አሁንና ቅድም” I፣ II፣ III)፣ የዘወትር ስሜቶች (“አዙረኝ አዛዙረኝ”) አንስቶ፤ ረቂቆቹ የወል ዕሤቶች፣ የጋራ ልቡናዎች እስከተከተቡባቸው ምስሎች (“ጓዳና ግድግዳ”፣ Gluten-free-dom “I” እና “II”) ድረስ ከጤፍ እና ከጋሻ ትእምርታዊ ተራክቦ የተገኙ ናቸው፡፡ እርግጥ ነው እንዲህ ካለው የትርኢት ጠቅላይ ፈለግ የሚሸሹ ጥቂት ሥራዎች አይጠፉም፡፡ ለዚህ ደግሞ፣ “የገደል ማሚቶ”፣ “ቆሜ ተቀምጬ” እና “አዲስ ጠላ በሰባራ አንኮላ” አብነት ይሆናሉ፡፡ “የገደል ማሚቶ” ለኀልዮ እምብዛም ያልተጨነቀ፣ ምናልባትም የሄደ ድምጽ ተመልሶ የሚመጣበት የቅርጾች ጨዋታ ነው፡፡ በ“አዲስ ጠላ በሰባራ አንኮላ” ውስጥ የጤፍና የጋሻን የተናጠልም ይሁን የወል ህልውና በገሀድ ፈልገን ስለማናገኝ ሥራው ከትርኢቱ አጠቃላይ መንፈስ ያፈነገጠ ይመስላል፡፡ ይሔ ግምት ግን ኪነቱን ከቀሪዎቹ ሥራዎች ጋራ አናብበን መተርጎም ስንጀምር በቀላሉ የሚፈርስ ነው፡፡ እንዲህ፣ እንደ “ጤፍና ነጻነት” ባለ አንድ ወጥ ርእስ በተሰጠው ከፍ ያለ ትርኢት ውስጥ ሥፍራ ያገኙ፣ በተቀራራቢ የጊዜ ክበብ ውስጥ የተከየኑ ሥራዎች በአመዛኙ ተነጥሎ ከሚከናወን ዝግ ምልከታ ይልቅ ለአጎራባች (co-textual) እና ለዐውዳዊ (contextual) ምርምር ይጋብዛሉ፡፡ ይህንን አጠቃላይ የነገረ ፍካሬ መርህ ከግምት ካስገባን፣ ከያኒው በምስሉ መግለጫ ላይ ባቀረበው ፍቺ ብቻ ረግተን የምንቆም አይመስለኝም፡፡ ይልቁንም በአንድምታ ተጨማሪ ትርጉም ለማከል እንጋበዛለን፡፡ በእኔ እምነት በትርኢቱ ውስጥ በአካል ጭምር የተጎራበቱት Gluten-free-dom “I” እና “አዲስ ጠላ በሰባራ አንኮላ” ከጤፍ እና ጋሻ መጉደል ባሻገር በገሎቻቸው ተሳስበው በመንፈስ ይሰምራሉ፤ በጭብጥ ይከታተላሉ፡፡ በትርጓሜም እንደሚከተለው ይተጋገዛሉ፡፡
በጥንታዊው የሒሳብ ማሰላሰያ፣ በአባከስ አምሳያ የተበጀው በአራት ማዕዘን የብረት ፍሬም የታጠረ ምስል፣ ብረቱ ላይ ሻጥ ሻጥ ተደርገው አግድም የተዘረጉ ወልጋዳ የእንጨት ዘንጎች፣ በዘንጎቹ ላይ የሚንሸራሸሩ በቅርጽ

11 months ago
"የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች"በአሮጌ ሸክም የጎበጠው ወጣት ትውልድ ፖለቲካዊ ፍዘት
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ ግል ሀሳብ)
#ethiopia | በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ስለ ትውልድና ኃላፊነት ሲነሳ የ1960ዎቹ ትውልድ (የእኛ ወላጆች ትውልድ) የፈጠረው ሥብራት ዋነኛ መነጋገሪያ ነው። ያ ትውልድ በለውጥ ጥማትና በፖለቲካዊ ጽንፈኝነትና አብዩታዊነት መሬቱን ሸንሽኖ፣ለሀገር ብዙ ውድመትና ያልተፈቱ የፖለቲካ ቀውሶችን አውርሶ ሄዷል።(ዘመናዊ ትምህርትን ሊቀስም ባህር ማዶ ተልኮ ዳንስ እና የሲጋራ አጫጫስ ቂንጠኛ አያያዝ ተምሮ መጣ፤ የጃፓኑ ሰው ቴክኖሎጅ ኮረጆ፣ ሀገሩን አቀና ከተረጅነት ወደ አምራችነት አሸጋረ-ጃፖን እንደምን ሠለጠነች በክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል፣የጃፓን መንገድ የተሰኙ መፃህፍት በአንጋፋው ዲፕሎማት አሰፋ ማመጫ አርጋው የተፃፉ ሁለቱን በጊዜ ንፅፅር ለተመለከተ የእኛ እና የእነሱን እድገት ማየት ይቻላል ።)የእኔው ሰው ደግሞ በአንፃሩ በዘመኑ የግብረ-ገብነት ትምህርት( የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ የተማረ የተመራመረ ከጥቂት የአፍሪካ ሀገሮች በነፃነቱ፥ በስብዓናው እና የተሻለ እድል በአገሩ የተፈጠረለት እንደነበር የታሪክ ቅጅዎች ያስረዳሉ ።እናንተ፣እኔ "የዛሬ አበባዎች፤ የነገ ፍሬዎች" ተብላችሁ በቴሌቪዥን የተመከራችሁት እና ዛሬ 37 ዓመት ያስቆጠራችሁት ትውልድ፣ የዚህ ታሪካዊ ሸክም ቀጥተኛ ቀንበር ተሸካሚ ሆናችኋል።የትናንቱ ሸክም እና የዛሬው ፍዘት እናንተ የተወለዳችሁበት እና ያደጋችሁበት ዘመን "የነገ ፍሬዎች"ለሚለው ተስፋ የተገባ አይደለም። በልጅነት የመከራችሁ ትውልድ ለሀገር የሚበጀውን ሰላማዊ የፖለቲካ ባሕል ከማስረፅ ይልቅ የፖለቲካ ሥብራትን እና የጥላቻ ፖለቲካን አትርፎ አልፏል።
"ሁሉንም ነገር እኔ ካልባረኩት" የሚል አባዜ የያዘ የአለቆች ፖለቲካ (Elite Politics) አናፂ ሆኗል። እኛም የነሱን ነዶ ሀሳብ ሰምተን በድሮ ቀረ የተንሸዋረረ እሳቤ ቁመን ቀርተናል አሁንም የእኔ ዘመን " ...ድሮ ቀረ መሃንዲስ፣ድሮ ቀረ መሪ፣ ድሮ ቀረ ሀኪም ፣ ድሮ ቀረ ጋዜጠኛ ፣ ድሮ ቀረ መምህር ፣ ድሮ ቀረ የባንክ ባለሙያ፣ ድሮ ቀረ ሙዚቀኛ ፣ድሮ ቀረ ዳኛ መዝገብ አገላብጦ ግራ ቀኙን ተመልክቶ የሚወስን፣...እረ ...ድሮ ቀረ ፖለቲከኛ ሲሉት አምኖ ተቀብሎ ዝም ጭጭ ብሏል። አሁንም አልነቃም የድሮ ናፋቂ ነው ግን እድሜው የእኔ ዘመን 37 ነው ። ይህ አባዜ ዛሬም ድረስ በአመራር ቦታ ላይ ተንጠልጥሎ በመገኘት፣ የእኔ ትውልድ የሚገባውን ቦታ እንዳያገኝ እና አዲስ አስተሳሰብ እንዳያመጣ እንቅፋት ሆኗል።
የፖለቲካ ፍዘት መንስኤዎች የእኔ ዘመን ሰው ( My Generation )ለሀገር የሚገባውን ያህል ለመስራት እድል እና ጊዜ አሁን ተሰጥቶታል፤ ራስን መውቀስ ተገቢ ቢሆንም፣ከጀርባ ያሉት መሰረታዊ ችግሮች አይቶ ከወጀብ እና ከሌሎች ነዶ ሀሳቦች እራሱን መጠበቅ እና ማረቅ አለበት ። የአሮጌው ትውልድ ሸክም የ60ዎቹን ትውልድ ያልተፈቱ የፖለቲካ ቁስሎች (ብሔርተኝነት፣ ማንነት፣ የመሬት ባለቤትነት፣ አክራሪነት (በትናንት መቸከል) ሁኖ መገኘቱ ፤ እነዚህ ጉዳዮች አሁንም ድረስ የትውልዱን አቅም(Potential )ወጥረው ይዘውታል።
የዚህ አባዜ ፖለቲካዊ ባህል ዕድሜው የገፋውና ከሥልጣን የማይለየው የፖለቲካ ልሂቅ በወጣቱ ላይ የመተማመን እጦት መኖሩ አዲሱ የለውጥ አመራር እና የመደመር እሳቤን እና የፖለቲካ ስክነትን በመካድ አሁንም በጥርጣሬ እንዳመለከተው( የሰሞኑ የቀይ ባህር እና የኢትዮጵያ የወደብ አቅርቦት እና የብሔራዊ ጥቅም አጀንዳ ሲነሳ ፥ከዚህ በፊት በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲነዙ የነበሩ አሉባልታዎችን ማስታወስ በቂ ነው) እና የውዥንብር ሀሳብ በሁሉም ዘርፎች መኖሩ የእኔ የመደመር ዘመን ትውልድ እድል ማጣት (The Blocked Path)፡ ወጣቱ ትውልድ በሃሳብ፣ በአስተሳሰብ እና በዕውቀት ተዘጋጅቶ ቢመጣም፣ የሥልጣን መንገዱ በቆዩ ፖለቲከኞች በመዘጋቱ ምክንያት የመሰራት እድሉን አጥቷል።
ከፖለቲካ ማፈግፈግ (Political Apathy) በፖለቲካው ዓለም ውስጥ የሚታዩት የመረረ ልምምዶች፣ግጭቶች እና ጽንፈኝነት ወጣቶችን "ፖለቲካ ሸክም ነው፤ ያስጠይቃል" ብለው እንዲርቁና ኃይልና ጊዜያቸውን ወደ ግል ጉዳይ፣ ቢዝነስ ወይም ወደ ውጪ ሀገር ጉዞ ብቻ እንዲያደርጉ አድርጓል።እንደ እኔ ላሉ በለውጥ እና በመደመር ፅንሰ ሀሳብ የሚያምኑ እና ለሀገር ግንባታ ትንሽ አስተዋጽኦ ለማድረግ የሚሞክሩ የተቋም ግንባታ ሂደት ጅምር ላይ በመሆኑ ቱማታው ሌላ ነው ።መፍትሔው ከጎበጡበት ቀጥ ማለት ነው ።የእኔ ትውልድ "በጎበጠበት" ሁኔታ መቀጠል የለበትም፤ ፖለቲካዊ ፍዘትን (Apathy) ወደ ፖለቲካዊ ተሳትፎ መቀየር የግድ ነው።(Politically Active Person )ይገባዋል ። ሸክሙን መፍታት የ60ዎቹ ትውልድ የፈጠረውን የፖለቲካ ሥብራት መፍታት የሚችለው ይህ ወጣት ትውልድ ብቻ ነው። የትናንቱን ታሪክ ወደ ኋላ መተው ሳይሆን፣ ከዛሬው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚያገናኝ አዲስ የጋራ ራዕይ መፍጠር ያስፈልጋል።
አዲስ የፖለቲካ ባሕል መገንባት ከጥላቻ ፖለቲካ፣ ከማን አለብኝነት እና "እኔ ካልባረኩት አይሆንም" ከሚለው አባዜ በመውጣት ወጣቱ ትውልድ ለውይይት፣ ለመደራደር እና ለሥርዓት ተገዢነት የሚመች የፖለቲካ ባሕል መፍጠር አለበት።
ኃላፊነት በመውሰድ ዕድሜያቸው 37 ዓመት እና ከዚያ በታችም የሆናቸው ግለሰቦች ዛሬ መካከለኛ አመራሮች (Middle-Level Leadership) አካል በመሆን እና የሀገርን ኢኮኖሚና ማህበራዊ ህይወት የመምራት አቅም አላቸው። ፖለቲካውን ሙሉ በሙሉ በትናንት ትውልድ ትቶ በ"ፍዘት" ውስጥ መቆየት ሳይሆን፣ሥርዓት ባለው መንገድ መብትን መጠየቅና ኃላፊነት መውሰድ ይገባል።
"የዛሬ አበባዎች" የሚለው ተስፋ እውን የሚሆነው፣ በአሮጌው ትውልድ የፖለቲካ ሸክም ጎብጦ ከመቅረት ይልቅ፣ ወጣቱ ትውልድ የትከሻውን ሸክም አራግፎ "የዛሬ ፍሬዎች" ለመሆን ሲነሳ ብቻ ነው። አሁን ላይ በእኔ ዘመን ሀገርን የሚድስ(The Era of Ethiopia's Renewal)፣ትጉህ እና ለትውልድ ለውጥ የሚተጋ መሪ ( የእኔ ዘመን ነፀብራቅ ) ግስጋሴ ላይ ነው ። እኔም ከዘመኑ የፍዝ ፖለቲካ ነጠብጣብ ዕጩ ፈልቅቄ ወጥቻለሁ፤ከእንግዲህ በኃላ ለሀገሪቱ ይጠቅማል የምላቸውን ሀሳቦች ፣በተከታታይ አካፍላለሁ ። ( የክቡር የኢ.ፊ.ዲ.ሪ.ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሀገራዊ የመደመር መንግሥት ተልዕኮዎች እና የሀገር ግንባታ እሳቤዎች በመደገፍ በጊዜ እንቀድማለን ። የህልማችን ሀገርን በማገልገል በእውነት እንኖራለን !!

12 months ago
“የመድረኳ ንግሥት” ሙሉዓለም ታደሠ የሥራ ታሪኳን ለተወዳጅ ሚድያ ሰጠች
ሙሉዓለም ታደሠ
#ethiopia | ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን፣ መዝገበ-አእምሮ (የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች፣ በመጽሐፍ፣ በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል። ባለፉት 4 ዓመታት ከ5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መጽሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
ቅፅ 3 መዝገበ አእምሮ ከ20 በላይ ዘርፎች ይኖሩታል። በኪነጥበብና ትወና ዘርፍ ባለፉት 35 ዓመታት አሻራ ካኖሩት እና ታሪካቸውን ከምንሰንድላቸው መካካል አርቲስት ሙሉዓለም ታደሠ ትጠቀሳለች። ሙሉዓለም በመድረክ ቴአትርና በፊልም አቅሟን ያስመሰከረች፣ በማስታወቂያ ሥራና በመድረክ መሪነት ያገለገለች ባለሙያ ናት። የሬድዮ ድራማዎች እና ትረካዎች ላይ ሠርታለች። በዳይሬክተርነትም ችሎታዋን ያስመሰከረች ናት።ሙሉዓለም ተወዳጅ ሚድያ የሚሠራቸውን የህይወት ታሪክ ስነዳ ሥራዎችን የምታከብርና በሥራውም የምታምን ሲሆን የእርሷም የሕይወት ታሪክ እንዲሰነድ ፈቃዷን ሰጥታናለች። ይህን ታሪክ ስናሰናዳ ትልቁን ትብብር ያደረገልንን ወዳጃችንን ሚካኤል ታምሬን ማመስገን እንወዳለን። የሙሉዓለምን የሕይወት ታሪክ ዕዝራ እጅጉ እና ሂላሪያ ተስፋዬ እንደሚከተለው ሰንደውታል።
ትውልድና እድገቷ ሐረር ነው። በዚያው በሐረር ያሳደጓት ደግሞ መነኩሴዋ የእናቷ አክስት ናቸው፥ ሙሉዓለም ታደሠ። በልጅነቷና በአዳጊ እድሜዋ፣ የተሰጣትን የጥበብ ጸጋ ለይታ ያወቀች አይመስልም። እንዲያም ሆኖ ግን በተማረችባቸው ትምህርት ቤቶች በሥነጽሑፍ፣ ስፖርት፣ ቴአትር፣ ሙዚቃና በመሳሰሉት ሁሉ ተሳታፊ ናት።
ሙሉዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በአቡነ እንድርያስ እንዲሁም ኹለተኛ ደረጃ (9 እስከ 12) ትምህርቷን መተሓራ ስኳር ፋብሪካ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማረች። በዚህ መካከል ነው፣ እንደዋዛ ወዲያ ወዲህ የምትልበትና እረፍት የነሳችው የተለያየ የጥበብ ሥራ ተሳትፎዋ አብቦ፣ በድፍን ሀገር ደምቃ የምትታይ ኮከብ ለመሆን ጉዞዋ የጀመረው።
መጽሐፍ ማንበብና ፊልም ማየት አብዝታ ትወድድ የነበረችው ሙሉዓለም፣ ትዳር የመሠረተችው ገና በልጅነት ነበር፣ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሳለች። ታድያ የጥበብ ፍቅሯንና በትምህርት ቤት አጥር ተከልሎ የነበረ ለእርሷ ያልታያትን ኪናዊ ችሎታዋን የትዳር አጋሯ አስተውሎት ኖሯል።
እናም አንድ ጊዜ እንዲህ ሆነ፣ እርሷ ወደ አዲስ አበባ ባቀናች ወቅት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበብ መምህራን መተሓራ ተገኙ፥ የአጭር ጊዜ የቴአትር ሥልጠና ሊሰጡ። ምንም እንኳ ሙሉዓለም በሰዓቱ አዲስ አበባ የነበረች ቢሆንም፣ ባለቤቷ ግን ስሟን ከሠልጣኞች ዝርዝር እንዲካተት አስመዘገበ። ሙሉዓለም ከሄደችበት ስትመለስ፥ የቴአትር ሥልጠና ተቀበላት። እናም የቴአትር ትምህርት ጋር በመተሓራ ስኳር ፋብሪካ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተዋወቀች።
በሰዓቱ የቴአትር ሥልጠናውን ይሰጣቸው የነበረው መምህራቸው የቴአተር አዘጋጅና ጸሐፊ አስፋው አጽማት ነበር። ይህም ሥልጠና ታድያ በ1983 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ሲጠናቀቅ፣ እርሷን ጨምሮ ተስፋዬ ገብረሃና፣ ቴዎድሮስ ተስፋዬ እና ሰሎሞን ሙላት አንድ ላይ ለቴአትር ሙያተኛነት ተቀጠሩ።
ለሥራ ቅጥር የመጀመሪያ መድረክ ላይ የፈተናት ጌታቸው አብዲ ነበር። እናም ከቅጥር በፊት፣ እንደ ማሟሻ የመጀመሪያ ትወናዋን ከአንጋፋው የቴአትር ባለሞያ ዓለሙ ገብረአብ ጋር "ጭላንጭል" የተሰኘ ቴአትር ላይ ተወነች። ይህ ቴአትር የደረጀ በቀለ (የሕያው ፍቅር መጽሐፍ ተርጓሚ) ነበር።
ሙሉዓለም በዚህ ቴአትር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መድረክ ላይ የወጣችበትን ያንን ጊዜ መለስ ብላ ስታስታውስ፣ “ቴአትሩ አጭር ቢሆንም፣ አዳራሹ ሙሉ ነበር። ሙዚቃ በድምጽ ማጉያ ከቀረበ በኋላ ነው እኛ ቴአትር ለማቅረብ የገባነው፣ ያለ ድምጽ ማጉያ። ሙዚቃ ለለመደ ጆሮ ቀጥሎ ቴአትር ሲገባ ቀላል አልነበረም።” ስትል ትገልጸዋለች።
ከቅጥሩ መጠናቀቅ በኋላ ‘ውጫሌ 17’ የተሰኘው የታምራት ገበየሁ ቴአትር ላይ፣ ከሌሎች በሰዓቱ ከቴአትር ቤቱ ሥራ ከጀመሩ ተዋናዮች ጋር አጃቢ በመሆን ሠርታለች። ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ነው እንግዲህ፣ 20 ዓመታትን የዘለቀው የብሔራዊ ቴአትር ቆይታዋ አንድ ብሎ የጀመረው።
በ1984 ዓ.ም በሹመት ብሔራዊ ቴአትርን የተቀላቀለው ጸሐፌ ተውኔት ማንያዘዋል እንደሻው፣ ሙሉዓለምን ለመጀመሪያ ጊዜ በዚያ ወቅት መድረክ ላይ ልምምድ ስታደርግ እንዳያት ያስታውሳል። የተሰጣትን ገጸ- ባህርይ በሰውነት፣ በድምጽ እና በጭንቅላቷም የምትተረጉም፣ በእንግሊዝኛው ‘One of a kind’ የምትባል የሴት ተዋናያት ቁንጮ ናት ይላታል።
ከዚያ በኋላ ሙሉዓለም በትልልቅና ቢያንስ ሁለትና ሦስት ዓመት መድረክ ላይ በሚቆዩ ቴአትሮች ደመቀች፣ የቴአትሮቹም ድምቀት ሆነች። “በኋላ በ1985 ዓ.ም የሠራሁት ከሕዝብ ጋር ያስተዋወቀኝ ‘የሌሊት እርግቦች’ የሚለው፣ ተፈሪ ዓለሙ የተረጎመውና ጌትነት እንየው ያዘጋጀው ሥራ ነው። ከዚያ በዓመቱ ‘የጫጉላ ሽርሽር’ የሚል የተፈሪ ዓለሙን ትርጉም ይዘን ኩራባቸው ደነቀ፣ ተፈሪ ዓለሙ፣ ጀማነሽ ሰሎሞን እና እኔ ሆነን አሜሪካ ሄድን።” ብላለች።
የትወና ሙያ ችሎታና ብቃቷን ከዚያ በላይ ማስመስከር አልተጠበቀባትም። ቀጥላ በሃይማኖት ዓለሙ በተዘጋጀው ‘ዋዜማ’ የተሰኘ ቴአትር ላይ ሠራች። ‘ያለአቻ ጋብቻ’ ተከተለ፥ ቀጥሎ ደግሞ ‘ሐምሌት’ መጣ።
ማንያዘዋል እንደሻው‘ዋዜማ’ የተሰኘው ቴአትር ላይ ሙሉዓለምን እንዲህ ያስታውሳታል፥ “አስቂኝ/ኮሜዲ ዘውግ ያለው ቴአትር ነው። ከአንጋፋና ትላልቅ የቴአትር ባለሞያዎች ጋር ነበር የሠራችው። እኩል መቆም የግድ ያስፈልግ ነበር። ያንን በብቃት ተወጣችው። እዚያ ላይ ፍጥነቷ እና የኮሜዲ ስሜት የፈጠረችበት መንገድ ልዩ ነበር።”
ከዚያ በኋላ ሙሉዓለም በቁጥር ከሃምሳ በላይ ለሚሆኑ፣ እያንዳንዳቸው ሲጠቀሱ ግን ከተመለከተው የአእምሮ መዝገብ የማይጠፋ የቴአትር ሥራዎች ላይ ድንቅ ትወናዋን አሳየች። ከእነዚያም የአመጻ ልጆች፣ ነጻ ወንጀለኞች፣ ርጉም ሐዋርያ፣ የሌሊት እርግቦች፣ ከአድማስ ባሻገር፣ የቬነሱ ነጋዴ፣ አዙሪት፣ ባለካባ ባለዳባ፣ ነጻ ወንጀለኞች፣ የአመጻ ልጆች፣ ውበትን ፍለጋ፣ ኪሊዮፓትራ ተጠቃሽ ናቸው።
ታዋቂ የሆኑትና ከሁሉም በላይ ጎልተው የሚነሱት ንጉሥ አርማህ እና ውበትን ፍለጋ የተሰኙትም ሳይጠቀሱ አይቀሩም። እነዚህ ሥራዎች በ1994 ዓ.ም በተሰጠው ብሔራዊ ሽልማት ላይ እውቅናና ሽልማት ያስገኟት ሥራዎች ናቸው።
ሙሉዓለም ታደሠ የቴአትር ባለሞያ ብቻ ግን አይደለችም። የፊልምና የሬድዮ ድራማ፣ ማስታወቂያ እና ትረካ፥ ከዚያም አልፎ በማስታወቂያ እና ፊልም ዳይሬክቲንግ እና ፕሮድዩስ በማድረግ ሠርታለች።
እንደውም የማስታወቂያ ባለሞያነቷ ከቴአትር ባለሞያነቷ ጋር እኩያ ነው። “ማስታወቂያ ሥራን ከትያትሩ እኩል ነው የጀመርኹት። የመጀመሪያ ብሔራዊ ቴአትር ስቀጠር ጋሽ ውብሸት ወርቃለማኹ ዐየኝ። ከእርሱም ጋር የሎተሪ ማስታወቂያ ሠራሁ። እንደውም ሕዝብ ከቴአትሩ በፊት ያወቀኝ በማስታወቂያ ነው። ከዚያ ቀጥሎ የአምቦ ውሃ ማስታወቂያ ሠራኹ፥ እንደዚያ እያለ ቀጠለ።” ስትል ታስታውሳለች። ከዚያ ቀጥላም ከሦስት ሺህ በላይ የሚሆኑ የማስታወቂያ ሥራዎችን ሠርታለች።
በማስታወቂያ ሥራ አሁን ድረስ በዘለቀ አብሮነት አብራው የሠራችው የሥራ ባልደረባዋ ሠራዊት ፍቅሬ፣ ከ28 ዓመታት ገደማ በፊት የአዋሽ ባንክ ማስታወቂያን ለመሥራት ሲገናኙ ትውውቃቸው እንደሚጀምር ያስታውሳል። ለሥራው ያላትን ፍቅርና ክብርም አድንቆ፣ ምን ያህል የተመልካችን ቀልብ የሚስቡ ሥራዎች ይሠሩ እንደነበርና፣ ሥራውም ከመስፋፋቱ የተነሳ በጋራ ድርጅት መሥርተው እንደነበርም ያነሳል።
ሙሉዓለም ምንም የማይወጣላቸው በተመልካች ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ የማስታወቂያ ሥራዎችን ብቻ ደግሞ አልነበረም የምትሠራው። በጎን ፊልም ሠርታለች። የመጀመሪያ በቴሌቭዥኝ የቀረበ የፊልም ሥራዋ በ1985 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ለዕይታ የቀረበ ‘ቃል’ የተሰኘ ፊልም ነበር። ቀጥላም ‘የነቀዘች ሕይወት’ የተሰኘው ፊልም ላይ ተሳትፋለች።
በፊልም ሥራ የበለጠ የደመቀችው ታድያ ያለእረፍት ካገለገለችበት ከብሔራዊ ቴአትር 20 ዓመታት ቆይታ በኋላ የመጨረሻው ሥራዋ የሆነውን ‘ኪሊዮፓትራ’ ሠርታ መልቀቂያዋን ስታስገባ ነው። ምንም እንኳ እረፍት የማድረግ ሐሳብ ይዛ የነበረ ቢሆንም፣ ሥራዎችን መርጣና ተጠንቅቃ የምትሠራው ሙሉዓለም፣ በሰዓቱ የቀረበላትን ‘ሰው ለሰው’ የተሰኘውን ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ መግፋት አልፈለገችም።
ጎን ለጎን እንደ የነቀዘች ሕይወት፣ ስውር ችሎት፣ ስጋ ያጣ ነፍስ፣ አቦጊዳ፣ ቶክሲዶ፣ የሌባው ልጅ፣ ግራና ቀኝ፣ ጥቁርና ነጭ፣ እና ውበትን ፍለጋ (ከቴአትር የተመለሰ) የሚሉና ሌሎች በርካታ ፊልሞችን እየሠራች፣ ለአራት ዓመታት በቆየው ሰው ለሰው ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ላይ ደምቃ ቆየች። ከዚያም የተወሰነ ጊዜ እረፍት ከወሰደች በኋላ ‘እረኛዬ’ በተሰኘው ሌላ ተወዳጅ የቴሌቭዥን ድራማ ላይ ተገኝታለች። ‘አቦጊዳ’ የተሰኘ ፊልም ዳይሬክተርና ፕሮድዩሰርም ሆና ሠርታለች። በዚሁ ፊልም ላይ ደራሲና ተዋናይም ነበረች።
ከዚህ ሁሉ ባሻገር መድረክ በመምራት በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት መካከል ናት። ‘አንድ ብር ለአንድ ወገን’ ከሚለው መርሃ ግብር ጀምሮ የተለያዩ ሀገራዊና ግዙፍ መድረኮችን እንዲሁ በነጻ ጭምር በመምራት አገልግላለች። በሙያዋ በነጻ አገልግሎት የሰጠችባቸው መድረኮችም ከቁጥር በላይ ናቸው። ከዲኬቲ ኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከግሩም ዘነበ ጋር የመራቻቸውን በርካታ መድረኮች አትዘነጋም።
ከእነዚህ አለፍ ሲባል ደግሞ፥ በሬድዮ ድራማም አለችበትም። በብዛት ባይሆንም በተወሰኑ የሬድዮ ድራማዎች መሳተፏን የምታነሳው ሙሉዓለም፣ በቅርብ የሠራችበትንና በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ይቀርብ የነበረውን ‘ወፌ ቆመች’ የተሰኘ የመዓዛ ወርቁ የሬድዮ ድራማ አንዱ መሆኑን ጠቅሳለች።
ሙሉዓለም ሁለገብ የምትባል የጥበብ ባለሞያ ናት። እንዲያም ሆኖ እርሷ ከሁሉ አብልጣ የምትወድደው ትወናን ነው። “በጣም የምወደው፣ የሚያስደስተኝም ትወና ነው። ዳይሬክቲንግ ላይ ችሎታ አለኝ ብዬ አምናለሁ፣ ግን ጭንቀት አልችልም፥ እሱ ያስቸግረኛል።” ትላለች። ከዚህ ባለፈ በሬድዮ የመጽሐፍ ትረካም ‘ሕያው ፍቅር’ የተሰኘውን መጽሐፍ በመተረክ (ከተፈሪ ዓለሙ ጋር) ጀምራ የቶልስቶይ የሆነውን ‘አና ካሪና’ን (ከዓለማየሁ ታደሰ ጋር) እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ መጽሐፍትን በሬድዮ ትረካ አቅርባለች።
አሁን ደግሞ በአዲስ ሙያ ብቅ ብላለች፣ ይኸውም የቲቪ ሆስት ነው። ‘እሁድ ቤት’ በተሰኘ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥኝ በሚቀርብ ሳምንታዊ መሰናዶ ላይ፣ የተለያዩ አንጋፋና ባለሞያ የሆኑ ሰዎችን በመዘየር፣ ከተዋናይ ሚካኤል ታምሩ ጋር በጋራ በመሆን በቴሌቭዥን መስኮቶቻችን ትታያለች። ከዚህም በተጨማሪ ‘ዞሮ መግቢያዬ’ በተሰኘ በኢቢኤስ እየታየ ባለ ተከታታይ ፊልም ላይ እየሠራች ትገኛለች።
ተዋናይት እመቤት ወልደገብርኤል ስለ ሙሉዓለም ስትናገር፣ ‘የመድረኳ ንግሥት ናት’ ትላታለች። እርግጥም በቴአትር መድረክ ነግሣበት ኖራለች። አልፋም በማስታወቂያና በፊልም ደምቃ፣ ኮከብ ሴት ሆና ትታያለች።
በኢትዮጵያ የጥበብ ዘርፍ በትወና ብዙ እርሷን አርአያ አድርገው የሚከተሉ ወጣቶች አሉ። ከእነዚያ መካከል የሆነችው ተዋናይት ማህደር አሰፋ እንደ ሙያ መምህርት ብቻ ሳይሆን እንደ ጓደኛዋም እንደምታያት ትናገራለች። በበኩሏም ‘ሰው ለሰው’ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ላይ ለትወና እንድትመረጥ (ካስት እንድትደረግ) ያደረገችው ሙሉዓለም መሆኗን አስታውሳ፣ ለሙያውና ለጊዜ ካላት ክብር ጨምሮ አብራት በሠራችበት ወቅት ከሙሉዓለም በብዙ እንደተማረች ትናገራለች።
ሙሉዓለም በነጻ፣ ሙያዊ አገልግሎቷን ከሰጠችባቸውና ለዚያው የእውቅና የምስክር ወረቀት ካገኘችባቸው ባሻገር፥ ከተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ) ጋር ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ (በጊዜው ኮሌጅ) እውቅና አግኝታለች። በቴአትር ምርጥ ተዋናይት በመባል የክብር ዲፕሎማ፣ በ’ሰው ለሰው’ ምርጥ ሴት ተዋናይት፣ በ‘ቶክሲዶ’ በጉማ አዋርድ ምርጥ ረዳት ተዋናይት፣ በ’እረኛዬ’ በምርጥ ፊልም በአሜሪካ ኢምፓክት አዋርድ እንዲሁም ከተለያዩ ድርጅቶች የተለያዩ ሽልማቶችን ተቀብላለች።
ይህ የሙሉዓለም ታሪክ ዛሬ ጥቅምት 15 2018 ሙሉዓለም ታደሰ ለተወዳጅ ሚድያ የሰጠችውን መረጃ መሠረት በማድረግ የቀረበ ነው። አስፋላጊው ማሻሻያ እየተደረገበት በተወዳጅ ሚድያ ዲጂታል ፕላትፎርሞችና በህትመት የሚሰነድ ይሆናል። የመጣጥፉ ባለቤትም ተወዳጅ ሚድያ ሲሆን ፅሁፉን ሲያጋሩ ምንጭ እንዲጠቅሱ የአእምሯዊ ንብረት ህግ ያስገድዳል።

ጥቅምት 14 ዘነበወርቅ ትደምቃለች
ትውልድና ዕድገቴ ዘነበወርቅ እንደመሆኑ መጠን ጥቅምት 14 እንደማንኛውም የአካባቢው ሰው ልዩ ስሜት ይሰጠኛል፡፡
ዘነበወርቅ ያለወትሮዋ በዚህ ቀን ታሸበርቃለች፡፡
ጎዳናዎቿ ነጠላና ነጭ ልብስ በለበሱ ክርስቲኖች ይሞላሉ፡፡ ከለሊት አንስቶ በሊቃውንት አባቶች የሚቀርበው ምስጋናና ዝማሬ መላ አካባቢውን ያደምቀዋል፡፡
የፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮች በተለየ ሁኔታ የተዘጋጁባቸው ዝማሬዎች ሲያቀርቡ አለማጀብ የሚቻል አይደለም፡፡ ተመሳሳይ ልብስ አሰርተው የሚያስተባብሩ የሰፈራችን ወጣቶች ለአላፊ አግዳሚው በፍቅር ፀበል ፃዲቅ ያቀርባሉ፡፡
በየቤቱ ድግስ አለ፤ እናቶች ወደቤታቸው ጋብዘው ብሉልኝ ጠጡልኝ ሲሉ ማነህ? ምንድን ነህ? ጥያቄ አይቀርብም፡፡
ምክንያቱም
ጥቅምት 14 የፃዲቁ አባታችን አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ገብረክርስቶስ ዓመታዊ በዓል ነው፡፡
ይህንን በዓል ለመካፈል አንድ ጊዜ ወደ ዘነበወርቅ የመጣ ሰው ምናልባት ከተፃፈው በላይ ቢገጥመው እንጂ ቅጥፈት ሆኖ አያገኘውም፡፡
ኑ መንፈሳዊ በረከቱን እየተካፈላችሁ በዘነበወርቅ ሰፈር ሰዎች በፍቅር ስትጋበዙ ዋሉ!

1 year ago
የፈተናው ውጤት ምን ይነግረናል?
#ethiopia | እራስህ በቀረጽከው ስርዓት ትምህርት ( Curriculum)ና ባዘጋጀኸው የማስተማርያና የመማርያ ግብአት ላይ ተመርኩዘህ ለአራት ዓመት ያስተማርከው ሀገር ተረካቢ ትውልድ በአምስት መቶ ሺዎች ፈተና ሲወድቅ ድንኳን ጥለህ ማቅ ለብስ በራስህ ውድቀት ማዘንና መጸጸት ሲገባህ በትውልዱ ኪሳራ ላይ መዘባበትና ማላገጥ በውስጥህ የሰረጸ የጥላቻ መንፈስ ካልኖረህ በስተቀር ታዳጊ ልጅ ባለው ሰው አንጀት የሚቻለው አይደለም።
ላለፉት አራት ዓመታት በቢሊዮኖች የወጣበትና በየመድረኩ ሲደለቅለት የከረመው የትምህርት ስርዓት ኩረጃን ከመከላከል ባሻገር እስከ አሁን አንዳችም የፈየደው ነገር እንደሌለ ዘንድሮም አስረግጦ አልፏል። ፈተና ያለፉት ተማሪዎች የፐርሰንትም ሆነ የቁጥር እድገትም በየዓመቱ በሚሊየኖች የሚጨምረው የተማሪዎች አንጻራዊ የተፈታኝ ቁጥር እድገት ተጽኖ እንጂ መሬት የወረደ ወሳኝ የቁጥር ለውጥ እንዳልሆነ ተራ ስሌት የሚያስረዳን ሆኗል።
ከዚህ በላይ የሚያሳስበው ነገር በቀረበው ግርድፍ መረጃ መሰረት ኢንተርናሽናል ት/ቤቶች 85%፣ የግል ት/ቤቶች ከ50% በላይ አዳሪ ት/ቤቶች 100% ማሳለፋቸውና በተቃራኒው በርካታ የአርሷ አደርና የአርብቶ አደር ልጆች የሚማሩባቸው የመንግስት ት/ቤቶች 5% ገደማ ተማሪ ማሳለፋቸው ጉዳይ ነው።
ይህ የሚስረዳን ነገር ቢኖር ስርዓት ትምህርቱ ና የፈተናው ውጤት ከዓመት ወደ ዓመት ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃና በንጽጽር በኑሮ ደረጃቸው አቅመ ደከማ የሆኑ የማህበረሰባችን አካላት ልጆችን ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መገለላቸው ተጠናክሮ የመቀጠሉ ክስተት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ነው።
በዚህ መሰረትም "አዲስ" የተባለለት ስርዓተ ትምህርት ድሃና ሀብታምን ሳይለይ ትምህርትን በአንጻራዊነት በእኩል ደረጃ ለሁሉም ማዳረስ፣ ማስፋፋትና ሚዛናዊ ዉጤትን ማስጠበቅ ሲኖርበት በአጼ ሐይለ ስላሴ ዘመን እንደ ተዘመተበት (Secter Review) ትምህርት በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የአርሶ አደርና የአርብቶ አደር ልጆችን ዳር በማስያዝ ከፍተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ወላጆች ልጆችን ቀጣይነት ባለው መንገድ ባለመብት የሚያደርግና በዚሁ መንገድ ውጤቱ እየተዛባና እያገለለ እንደሚቀጥል እየተዘገበ አለማስደንገጡና አለማወያየቱ አስደማሚ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
በአጠቃላይ የትምህርት ስርዓቱ የአራት ዓመት ግምገማ የተማሪ ጥራትና የቁጥር እድገት ያልታየበት፣ የመማር ማስተማር፣ የተማሪና መምህር ጥመርታ ያልተሰናሰለበት፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የአርሶ አደር፣ የአርብቶ አደር ልጆች በከፍተኛ ደረጃ ከከፍተኛ ትምህርት ተጠቃሚነት ያገለለ፣ ጥግ ያስያዘና በ4 ዓመት ውስጥ ከ2 ሚሊየን በሚበልጡ ወጣቶችን መነሻና መዳረሻ ያሳጣ ሆኗል።
እንደዚህ ዓይነት የትውልድና የሀገር ተስፋን ጥያቄ ላይ የሚጥል ስርዓት ትምህርት ለምን፣ እንዴትና ወዴት በሚሉ መሰረታዊ መስፈርቶች በገለልተኛ አካለትና በባለሙያዎች ኦዲት ተደርጎና ተገምግሞ ወደ ተገቢው አቅጣጫ እንዲያመራ በማድረግ ወጣቱን ከመደናበርና ተስፋ ከመቆረጥ ቤተሰብን ከጭንቀትና ከሐዘን መታደግ ይገባል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ።
በተለይ ደግሞ በየዓመቱ መጨረሻ ላይ በከፍተኛ እርካታና አጀብ ተማሪና ሕዝብን በሚያሳዝን መልኩ የሚዘገበው ከ500 ሺህ የሚልቁ ታዳጊ ልጆች ወድቀትና ኪሳራ ከስሜዊነት ተላቆ ሙያዊ በሆነና በሰከነ መንገድ በጥንቃቄ እንዲዘገብ ሙያ ከባለሙያው ጋር እንዲገናኝ ክንዋኔው ወደ ሚኒስትሩ የሕዝብ ግንኙነት ሊመለስ ይገባዋል።
ሙሼ ሰሙ እንደጻፉት!...

***
እራስህ በቀረጽከው ስርዓት ትምህርት ( Curriculum)ና ባዘጋጀኸው የማስተማርያና የመማርያ ግብአት ላይ ተመርኩዘህ ለአራት ዓመት ያስተማርከው ሀገር ተረካቢ ትውልድ በአምስት መቶ ሺዎች ፈተና ሲወድቅ ድንኳን ጥለህ ማቅ ለብስ በራስህ ውድቀት ማዘንና መጸጸት ሲገባህ በትውልዱ ኪሳራ ላይ መዘባበትና ማላገጥ በውስጥህ የሰረጸ የጥላቻ መንፈስ ካልኖረህ በስተቀር ታዳጊ ልጅ ባለው ሰው አንጀት የሚቻለው አይደለም።

የ50 ሚሊዮን ብር እና የ25 ሚሊዮን ብር የሎተሪ አሸናፊዎች ተገኝተው ሽልማታቸውን በይፋ ተረከቡ ።
የቤትና መኪና ሽልማት ከተጨማሪ ገንዘብ ጋር ያሸነፉም እንዲሁ ሽልማታቸውን ተረክበዋል።
ከደብረ-ብርሀን 10ኪሎ ሜትር በምትርቀው ሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስትያን ለንግስ ሄዳ በቆረጠችው የሚሊየን ትኬት የ50 ሚሊዮን ብር ዕድለኛ ያደረጋት ወጣት የሽቱ ምስጋናው ትባላለች፡፡
ትውልድና ዕድገቷ ጎንደር ከተማ የሆነው ወጣት የሽቱ ምስጋናው በጎንደር ከተማ ውስጥ የሸቀጣ ሸቀጥ ነጋዴ ናት፡፡
የሽቱ ምስጋናው የ50 ሚሊዮን ብር ቼኳን በዛሬው ዕለት ተረክባለች፡፡
ካሳ አለሙ አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ ኮንስትራክሽን ድርጅት ውስጥ በወር የ1500 ብር ተቀጥሮ የሚሰራ የጥበቃ ሰራተኛ ነው፡፡
ለበርካታ አመታት ስራ አጥ ሆኖ አሳልፏል። በዚህ ሁሉ መካከል ግን ሎተሪ ከመቁረጥ “ደከመኝ” ብሎ አያውቅም።
በአንድ የተባረከ ቀን አዲስ አበባ በተለምዶ 24 በሚባለው አከባቢ ከአንድ ሎተሪ አድራሽ በ200 ብር የሚሊየን ሎተሪ ሲቆርጥ ዕድል አይኗን ጥላበት ነበር።
ግንቦት 29/2017ዓ.ም የሚሊዮን ሎተሪ ዕጣ በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አዳራሽ ሲወጣ ሁለተኛው የ25 ሚለዮን ብር ዕጣ ለሱ ነበር የወጣው።
የ25 ሚሊዮን ብር ዕድለኛ ካሳ አለሙ አባይ።
የሚሊየን ሎተሪ የ2ኛ ዕጣ አሸናፊ ወጣት ካሳ አለሙ ቅዳሜ ሀምሌ 19 ቀን በስካይ ላይት ሆቴል በተካሔደ ስነ ስርዓት የ25 ሚሊዮን ብር ቼኩን ተረክቧል፡፡
ባሸነፍከው የ25 ሚሊየን ብር ዕጣ ምን ለማድረግ ተዘጋጀህ ሲባል ቤትና መኪና የመጀመሪያዎቹ ቀድሚ ሰጥቶ የሚያከናውናቸው እንደሆኑ ገልፆ በቶሎ ስራ እንደሚጀምርም አጫውወቶናል።
በቶምቦላ ሎተሪ የቤትና መኪና አሸናፊዎችም የታወቁ ሲሆን እንዲሁ ሽልማታቸውን ተረክበዋል።
የአንደኛ እጣ አሸናፊው አቶ ነጋልኝ አበራ በጨፌ ዶምሳ የፍርድ ቤት ዳኛ ሲሆኑ የአንደኛውን ዕጣ የቤት ቁልፍ ዕድለኛ ሆነው ሽልማታቸውን ተረክበዋል።
አቶ ነጋልኝ በቶምቦላ ሎተሪ በ1ኛ ዕጣ በአዲስ አበባ አፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት አጠገብ የሚገኘውን ባለ 3መኝታ ቤት ቁልፉን ተረክቧል፡፡ በተጨማሪም በየወሩ 60 ሺህ ብር ለ3 ዓመታት ይከፈለዋል፡፡
የ50 ሚሊዮን ብር ተሸላሚን ጨምሮ በቶምቦላ ሎተሪ የቤት እና የመኪና ዕድል ከተጨማሪ ገንዘብ ጋር ያሸነፉ ሌሎች የሎተሪ አሸናፊዎች በዛሬው ዕለት ማለትም ቅዳሜ 19/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል ‹‹ሚሊየነሮቹ›› የሚል ስያሜ በተሰጠው መርሀ ግብር በይፋ ሽልማታቸውን ተረክበዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዘንድሮው የእንቁጠጣሽ ሎተሪ ከ66 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት በተለያዮ ዕጣዎች አጠቃሎ ለዕድለኞች አቅርቧል፡፡
በአንደኛ ዕጣ ከቀረበው የ20 ሚሊዮን ብር ዕጣ በተጨማሪ በሁለተኛ ዕጣ የ10 ሚሊየን ብር፣ በሶስተኛ ዕጣ ደግሞ የ5 ሚሊዮን ብር ዕጣን አጠቃሎ በጥቅሉ የ66 ሚሊዮን ብር ሽልማት በእንቁጣጣሽ ሎተሪ እድለኞችን ይጠብቃል።
ይህንን የሎተሪ ዕድል በቴሌብር እና በ ethiolottery.et ላይ በመግዛት ባለዕድል ይሁኑ፡፡
ለበለጠ መረጃ በ +251977717272
+251950189808 እና
+251950199808 ይደውሉ!
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት!

ህይወት የሚያከብሯትን ታከብራለች!
#ethiopia | “ዛሬ የአትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ልጅ ሜላት ሀይሌ፣ በአባቷ ልዩ ባህርያትና ጠቃሚ ልማዶቹ ላይ በፃፈችው "ዳይሴክቲንግ ሀይሌ/ የሀይሌ ሀይሎች /" የተሰኘ መፅሐፍ፣ በደራሲዋ ሜላት ሀይሌ ግብዣ ቀድሜ ለማንበብ እድለኛ በመሆኔ፣ አትሌት ኃይሌ፣ ባለቤቱ ወ/ሮ ዓለምና መላው ቤተሰቡ በተገኙበት፣ ለአለማቀፍና ለአገር አቀፍ የሚዲያ አካላት በሀይሌ ግራንድ ገለፃ አድርገናል::
ይህ መፅሐፍ በአትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ መርሆዎች ላይ የተመሰረቱ ህይወት ቀያሪ በርካታ ትምህርቶች አሉት:: አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ራሱን የዓላማው እስረኛ በማድረግ፣ በጥብቅ መርህ ህይወቱን መምራቱ፣ በአትሌቲክስ ብቻ ሳይሆን በቢዝነስም አሁን ለደረሰበት ዓለም አቀፍ ስኬት አብቅቶታል::
አትሌት ሀይሌ ገ /ስላሴ ህይወትን አክብሯልና ህይወትም አክብራዋለች::
ጀግና አባቶች ለሴት ልጆቻቸው ዋና አሰልጣኝ ናቸው፡፡
አባት 'ጀግና' ያላት ሴት ልጅ ሁልጊዜ ጅግና ነች::
ሜላት ሀይሌ እግዚአብሔር እጅግ የረዳውንና ጀግናውን አባትሽንና እናትሽን አጥንተሽ፣ ይሄን መፅሐፍ ለአንባቢ በማበርከትሽ ያንቺ ትውልድና ልጅ አሳዳጊዎች በሙሉ ያመሰግኑሻል::
እኔም ይህን ድንቅ መፅሐፍ እንዳነበውና ለሚዲያ ገለፃ እንዳደርግ ስለሰጣችሁኝ ዕድል በጣም አመሰግናለሁ፡፡ “
አክባሪያችሁ
ፍሬዓለም ሺባባው

Comments