2 hours ago
🚨🚨🗣️ ቪንሰንት ኮምፓኒ በማንቸስተር ሲቲ ጉዳይ
"እዚያ ባሳለፍኳቸው 11 ዓመታት ውስጥ እንደ ቡድን ላሳካናቸው ነገሮች ሁሉ እኮራለሁ፤ ነገር ግን አሁን እዚህ ባየርን ሙኒክ ስለምገኝ፣ ከዚህ ውጪ ያሉት ጉዳዮች ከእኔ የፍላጎት ክልል ውጪ ናቸው።"
@Bisrat_Sport_433et

26 days ago
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች
🏴ኮትላንድ
8:00 ሬንጀርስ ከ ሴልቲክ
ኢትዮጵያ
10:00 ሲዳማ ቡና ከ ኤግሎን
እስፓንያ
11:15 ሌቫንቴ ከ ባርሴሎና
4:00 ሪያል ሶሴዳድ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ
🏴እንግሊዝ
12:30 ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ማንቸስተር ሲቲ
ጀርመን
12:30 ኤልቨርስበርግ ከ ባየርን ሙኒክ
ጣሊያን
1:00 ናፖሊ ከ ቦሎኛ
3:45 ሳሱኦሎ ከ ጁቬንቱስ
ፈረንሳይ
3:45 ብሬስት ከ ፒኤስጂ
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
🏴ኮትላንድ
8:00 ሬንጀርስ ከ ሴልቲክ
10:00 ሲዳማ ቡና ከ ኤግሎን
11:15 ሌቫንቴ ከ ባርሴሎና
4:00 ሪያል ሶሴዳድ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ
🏴እንግሊዝ
12:30 ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ማንቸስተር ሲቲ
12:30 ኤልቨርስበርግ ከ ባየርን ሙኒክ
1:00 ናፖሊ ከ ቦሎኛ
3:45 ሳሱኦሎ ከ ጁቬንቱስ
3:45 ብሬስት ከ ፒኤስጂ
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
1 month ago
የ2026 የባሎንዶር እጩዎች ይፋ ሆኑ
#ethiopia | የዓለማችን ኮከብ እግር ኳስ ተጫዋቾች የሚሸለምበትና በጉጉት የሚጠበቀው የ2026 የባሎንዶር (Ballon d’Or) ሽልማት ፉክክር በይፋ መጀመሩን ተከተሎ ለዘንድሮው የክብር ሽልማት የታጩ ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ሆኗል።
በታዋቂው የፈረንሳይ እግር ኳስ መጽሔት የሚዘጋጀውና የዓለማችንን ምርጥ የእግር ኳስ ተጫዋች የሚለየው ይህ ታላቅ መድረክ፣ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በየክላቦቻቸው እና በብሔራዊ ቡድኖቻቸው ድንቅ ብቃት ያሳዩ ታዋቂ ኮከቦችንና ተስፋ ሰጪ ተጫዋቾችን በአንድ ላይ አሳታፊ አድርጎ አቅርቧል።
ለ2026 የወንዶች ባሎንዶር ክብር በይፋ የታጩት 30 ተጫዋቾች እነሆ ፦
ጁድ ቤሊንግሃም (ሪያል ማድሪድ)
ፓው ኩባርሲ (ባርሴሎና)
ማርክ ኩኩሬያ (ቼልሲ / ሪያል ማድሪድ)
ኡስማን ዴምቤሌ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ሉዊስ ዲያዝ (ባየርን ሙኒክ)
ብሩኖ ፈርናንዴዝ (ማንቸስተር ዩናይትድ)
ገብርኤል (አርሰናል)
ኤርሊንግ ሀላንድ (ማንቸስተር ሲቲ)
አሽራፍ ሀኪሚ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ሃሪ ኬን (ባየርን ሙኒክ)
ክቪቻ ክቫራትስኬሊያ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ላሚን ያማል (ባርሴሎና)
ሳዲዮ ማኔ (አል ናስር)
ማርኪንዮስ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ላውታሮ ማርቲኔዝ (ኢንተር ሚላን)
ኪሊያን ምባፔ (ሪያል ማድሪድ)
ኑኖ ሜንዴዝ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ሊዮኔል ሜሲ (ኢንተር ማያሚ)
ዦአኦ ኔቨስ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ማይክል ኦሊሴ (ባየርን ሙኒክ)
ዊሊያም ፓቾ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ጁሊያን ኪኖኔዝ (አል ካድሲያ)
ዲክላን ራይስ (አርሰናል)
ሮድሪ (ማንቸስተር ሲቲ / ባርሴሎና)
ፋቢያን ሩይዝ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ዊሊያም ሳሊባ (አርሰናል)
ፌራን ቶረስ (ባርሴሎና / ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ዳዮት ኡፓሜካኖ (ባየርን ሙኒክ)
ቪኒሲየስ ጁኒየር (ሪያል ማድሪድ)
ቪቲንሃ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
የትኛው ተጫዋች ሽልማቱ ይገባዋል ይላሉ?

ከአሰቃቂው ምሽት እስከ ዳግም ተስፋ
የሎሪስ ካሪየስ የትግል ጉዞ
✍️ በጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ
#ethiopia | በ2018 በዩክሬን ኪዬቭ የተካሄደው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ለሪያል ማድሪድ የድልና የክብር፣ ለሊቨርፑል ደግሞ የልብ ስብራት ምሽት ነበር። ነገር ግን ከዚያ ምሽት የበለጠ የተጎዳው የ24 ዓመቱ ጀርመናዊ ግብ ጠባቂ ሎሪስ ካሪየስ ነበር።
በዚያ ታሪካዊ ምሽት ካሪየስ ለሊቨርፑል በጣም ከባድ የሆኑ ሁለት ስህተቶችን ሰርቷል። የመጀመሪያዋ ግብ ከእጁ ላይ በቀረችው ኳስ ከካሪም ቤንዜማ ጋር ተያይዛ ሲሆን፣ በኋላም ጋሬዝ ቤል ከሩቅ የመታትን ኳስ መቆጣጠር ተስኖት ሁለተኛዋ ግብ ሆና ጨዋታው 3-1 በሪያል ማድሪድ እጅ ተጠናቀቀ።
ያ ምሽት ለካሪየስ ግን የአንድ ጨዋታ ሽንፈት ብቻ አልነበረም። በደጋፊዎች ትችት፣ በማህበራዊ ጫናና በስሜታዊ ጉዳት የተሞላ አስቸጋሪ ዘመን መጀመሪያ ሆነ። ብዙዎችም የእግር ኳስ ህይወቱ እዚያው እንደተቋጨ ያህል ተመለከቱት።
ከውድቀት ወደ ዳግም መነሳት
ከሊቨርፑል ከተለየ በኋላ ካሪየስ በተለያዩ ክለቦች አስቸጋሪ ዓመታትን አሳልፏል። ይሁንና ተስፋውን ሳይቆርጥ ለመመለስ ታገለ።
በመጨረሻም ወደ ጀርመኑ ሻልከ 04 መዛወሩ ለካሪየስ አዲስ ምዕራፍ ከፈተለት። በክለቡ ውስጥ ዳግም ራሱን ለማሳየት በጽናት መስራቱን ቀጠለ።
ባለፈው የውድድር ዘመንም በ12 ጨዋታዎች መረቡን ሳያስደፍር በማጠናቀቅ የቀድሞ ብቃቱን ዳግም ማስመስከር ችሏል።
በባየርን ፊት የተገኘ ትልቅ ፈተና
በቅዳሜ ምሽት በቬልቲንስ አሬና በተካሄደው የሊጉ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ፣ ሻልከ ከኃያሉ ባየርን ሙኒክ ጋር ተገናኘ።
ካሪየስም የባየርንን አደገኛ የማጥቃት ኃይል በጽናት ተቋቁሞ፣ መረቡን ሳያስደፍር ጨዋታውን 0-0 አጠናቀቀ። ይህም ለሻልከ ውድ አንድ ነጥብ አስገኘ።
የካሪየስ ታሪክ የሚያስተምረው
የሎሪስ ካሪየስ ጉዞ አንድ ነገር በግልጽ ያሳያል፤ አንድ ስህተት የሰውን ሙሉ ህይወት አይወስንም።
አንድ አሰቃቂ ምሽት ሊያሳፍር ይችላል፤ አንድ ውድቀት ሊያሳምም ይችላል፤ ነገር ግን በጽናት እና በጠንካራ ስነ-ልቦና ከቀጠልን ዳግም መነሳት ይቻላል።
ካሪየስ የግብ ጠባቂነት ታሪክ ብቻ አይደለም—ከውድቀት በኋላ ዳግም ስለመነሳት የሚናገር ህያው ታሪክ ነው።
#loriskarius #schalke04 #liverpool #realmadrid #bayernmunich #football #championsleague #የእግርኳስታሪክ #ጽናት #ዳግምመነሳት

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የዕጣ ድልድል ዛሬ ይፋ ይሆናል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ2026/27 የውድድር ዓመት የዕጣ ድልድል በዛሬው ዕለት ይፋ ይሆናል፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ከ2024/25 የውድድር ዓመት ወዲህ የቀደመ የጨዋታ ቅርጹን በመቀየር በሊግ ቅርጽ የተሳታፊ ቡድኖችን ቁጥር ወደ 36 በማሳደግ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ያለፉትን ሁለት ዓመታት የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ በተከታታይ ሻምፒዮን በመሆን በመድረኩ አስደናቂ ጊዜ አሳልፏል፡፡
በአዲሱ የውድድር ዓመት ፒኤስጂ ሻምፒዮን የሚሆን ከሆነ በተከታታይ ሦስት ጊዜ የማሸነፍ ክብረ ወሰንን ከሪያል ማድሪድ ጋር የሚጋራ ይሆናል፡፡
ሪያል ማድሪድ በአሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን እየተመራ ከፈረንጆቹ 2016 እስከ 2018 በመድረኩ በተከታታይ ሦስት ጊዜ ሻምፒዮን በመሆን የሚስተካከለው ቡድን የለም፡፡
የስፔኑ ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ መድረክ 15 ጊዜ ዋንጫውን በማሳካት በመድረኩ በርካታ ዋንጫዎችን ያሸነፈ ቀዳሚው ቡድን ነው፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የእሱ ነው የሚባልለት ሪያል ማድሪድ ባለፉት ሁለት ዓመታት ግን ከመድረኩ የተሰናበተባቸው መንገዶች ቡድኑ ላይ ጥያቄ ያስነሱ ነበሩ፡፡
ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ወደ ዋንጫው ለመመለስ የአሰልጣኝ ለውጥ በማድረግ ጭምር የ2026/27 የውድድር ዓመቱን ጀምሯል፡፡
አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆን ወደ ሳንቲያጎ ቤርናባው የመለሰው ሪያል ማድሪድ ቤርናርዶ ሲልቫ፣ ማርክ ኩኩሬላ፣ ኮናቴ፣ ዱምፍሪስ እና ዲዮማንዴን የመሳሰሉ ተጫዋቾችን በነባር የቡድኑ ከዋክብቶች ላይ በመጨመር የቡድኑን ጥልቀት አስፍቷል፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የመድረኩ ንጉስ ሪያል ማድሪድ በታሪኩ 16ኛ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫውን ለማሳካት የሚያደርገው ጉዞ ይጠበቃል፡፡
የጣሊያኑ ክለብ ኤሲሚላን 7 ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን በማሳካት 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ሊቨርፑል እና ባየርን ሙኒክ በተመሳሳይ 6 ጊዜ ዋንጫውን ማሳካት ችለዋል፡፡
ባርሴሎና 5፣ አያክስ 4፣ ማንቼስተር ዩናይትድ 3 እንዲሁም ኢንተርሚላን 3 ጊዜ ሻምፒዮን ሆነዋል።
ቼልሲ፣ ፒኤስጂ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት፣ ቤኔፊካ፣ ጁቬንቱስ እና ፖርቶ ደግሞ ሁለት ጊዜ ዋንጫውን ያሳኩ ቡድኖች ናቸው፡፡
ማንቼስተር ሲቲ፣ ፌይኖርድ፣ ማርሴ፣ ቦርሲያ ዶርትሙንድ፣ አስቶንቪላ፣ ፒኤስቪ አይንዶቨን፣ ክሬቭና ዝቬዝዳ እና ሴልቲክ የመሳሰሉ ቡድኖች ደግሞ በተመሳሳይ አንድ ጊዜ በመድረኩ ከዋንጫው ጋር ተገናገኝተዋል፡፡
በታሪኩ ሁለት ጊዜ ፍጻሜ ደርሶ ዋንጫውን ያጣው አርሰናል ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ለማንሳት የሚያደርገው ጉዞ ይጠበቃል።
በዘንድሮው ውድድር ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊቨርፑል፣ ማንቼስተር ዩናይትድ፣ አርሰናል፣ ማንቼስተር ሲቲ እና የዩሮፓ ሊግ አሸናፊው አስቶን ቪላ ይሳተፋሉ።
ዛሬ የዕጣ ድልደሉ ይፋ በሚደረገው በ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አዲሱ የውድድር ዓመት የትኛው ቡድን ሻምፒዮን ይሆናል የሚለው ይጠበቃል፡፡
እናንተስ በመድረኩ የዘንድሮውን የዋንጫ ቅድመ ግምት ለማን ትሰጣላችሁ? ግምታችሁን አጋሩን።
በወንድማገኝ ጸጋዬ

2 months ago
ጀማል ሙሲሌያ ሜዳ ላይ እራሱን ስቶ ወደቀ
#ethiopia | ባየርን ሙኒክ እና አርቢ ላይፕዚግ ባደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ጀማል ሙስሌያ በጨዋታው 84ኛ ደቂቃ ላይ ራሱን ስቶ ሜዳ ላይ ወድቋል።
ባየርን ሙኒክ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አርቢ ላይፕዚግን ባሸነፈበት የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ሙስሌያ የቡድኑን 3ኛ ግብ አስቆጥሮ ነበር።
በዕለቱ በነበረው ጨዋታ ተጫዋቹ የደም ዝውውር ችግር አጋጥሞት ሜዳ ላይ እራሱን ስቶ እንደወደቀ ተገልጿል።
ዳኛው ጨዋታውን ወዲያውኑ ያስቆሙ ሲሆን የድንገተኛ ህክምና ሀኪሞች ቡድን ወደ ሜዳ ገብተው አስቸኳይ እርዳታ አድርገውለታል ተብሏል።
ተጫዋቹ የህክምና ክትትል ተደርጎለት ለተጨማሪ ህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዱን ነው የተገለፀው።
ተጫዋቹ የደረሰበት የህክምና ችግር ለክፋት የሚሰጥ እንዳልሆነ የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #bayrenmunch #leipzig #friendlymatch #football

3 months ago
የማይቆም የሚመስለው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጉዞ …
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ጥምር አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው በ2026 የዓለም ዋንጫ ውድድር አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል፡፡
በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ ኪሊያን ምባፔ፣ የባሎንዶር አሸናፊው ኦስማን ዴምቤሌ፣ ኦሊሴ፣ ሪያን ሼርኪ፣ ዴዝሪ ዱዌ፣ ኡፓሜካኖ እና ዊሊያም ሳሊባን የመሳሰሉ ከዋክብቶች ይገኛሉ፡፡
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ እየተሳተፉ ከሚገኙ ሀገራት መካከል ውዱ ስብስብ ሲሆን፤ ለ2026 የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮንነት ቅድመ ግምት ተሰጥቷል፡፡
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ ጀምሮ እስከ ሩብ ፍጻሜ ድረስ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች በሙሉ አሸንፏል፡፡
በእነዚህ ጨዋታዎች ተጋጣሚዎቹ ላይ 16 ግቦችን ያስቆጠረው ብሔራዊ ቡድኑ የተቆጠረበት ሁለት ግብ ብቻ ነው፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ ካስቆጠራቸው 16 ግቦች መካከል ስምንቱን ያስቆጠረው የ27 ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋች ኪሊያን ምባፔ ነው፡፡
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ውድ ልጅ የሆነው ኪሊያን ምባፔ አስደናቂ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል፡፡
ኪሊያን ምባፔ በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት በተካሄደው የዓለም ዋንጫ 8 ግቦችን በማስቆጠር በወቅቱ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ወርቅ ጫማውን ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
ኪሊያን ምባፔ በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ ውድድሩ ሳይጠናቀቅ እስከ ሩብ ፍጻሜ ድረስ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ብቻ 8 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፤ በቀጣይ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የግብ መጠኑን ከፍ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ ሦስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
ፈረንሳዊው ኮከብ ኪሊያን ምባፔ በእግር ኳስ ሕይወቱ በዓለም ዋንጫ ውድድር በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 20 ጨዋታዎችን አድርጎ 20 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
ሌላኛው የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች ደግሞ የባሎንዶር አሸናፊው ኦስማን ዴምቤሌ ሲሆን በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ አምስት ግቦችን አስቆጥሮ ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በባየርን ሙኒክ ቤት ድንቅ ጊዜ አሳልፎ ወደ ዓለም ዋንጫ የተጓዘው ኦሊሴ ሌላኛው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አስደናቂው ተጫዋች ነው፡፡
ኦሊሴ በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እስካሁን ድረስ ባደረጋቸው ጨዋታዎች አምስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡
በዚህም በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ በርካታ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻቶ በማቀበል ቀዳሚው ተጫዋች ነው፡፡
ዊሊያም ሳሊባ እና ኡፓሜካኖ ደግሞ የቡድኑ የመከላከል ጥንካሬ ናቸው፡፡
በ57 ዓመቱ አሰልጣኝ ዲዴ ዴሻምፕ እየተመራ አስደናቂ ጉዞ ላይ የሚገኘው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የሚያደርገው እንቅስቃሴ ይጠበቃል፡፡
ዲዴ ዴሻምፕ በተጫዋችነት ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር በፈረንጆቹ 1998 የዓለም ዋንጫን ማሳካታቸው ይታወሳል፡፡
ወደ አሰልጣኝነት ከመጡ በኋላ በፈረንጆቹ 2018 ፈረንሳይን በአሰልጣኝነት እየመሩ የዓለም ዋንጫን ያሳኩ ሲሆን በ2022 ደግሞ የፍጻሜ ተፋላሚ ነበሩ፡፡
አሰልጣኝ ዲዴ ዴሻምፕ በአሰልጣኝነት ሕይወታቸው ለሁለተኛ ጊዜ ፈረንሳይን ሻምፒዮን ያደርጉ ይሆን የሚለው ይጠበቃል፡፡

ምባፔ፣ ዴምቤሌና ኦሊሴ - አስፈሪው የፊት መስመር
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ እየተካሄደ በሚገኘው 23ኛው የዓለም ዋንጫ ውድድር የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋቾች አስደናቂ ጊዜ እያሳለፉ ነው፡፡
በዓለም ዋንጫ እየተወዳደሩ ከሚገኙ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ውዱ ስብስብ ነው፡፡
በዚህ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ውድ ስብስብ ውስጥ ደግሞ ኪሊያን ምባፔ፣ ኦስማን ዴምቤሌ እና ኦሊሴን የመሳሳሉ ምርጥ ተጫዋቾች ይገኙበታል፡፡
ሁለቱ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከዋክብት ኪሊያን ምባፔ እና ኦስማን ዴምቤሌ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ከከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች መካከል ይገኛሉ፡፡
ኪሊያን ምባፔ በ23ኛው የዓለም ዋንጫ በሦስት የምድብ ጨዋታዎች አራት ግቦችን አስቆጥሮ ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻቶ አቀብሏል፡፡
በ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የወርቅ ጫማውን የወሰደው ኪሊያን ምባፔ በድጋሚ የወርቅ ጫማውን ለማሸነፍ እየተፋለመ ነው፡፡
ኪሊያን ምባፔ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በምድብ ጨዋታዎች ያስቆጠራቸውን አራት ግቦች ጨምሮ በአጠቃላይ በዓለም ዋንጫ ያስቆጠራቸውን ግቦች 16 አድርሷል፡፡
በዚህም ኪሊያን ምባፔ የምን ጊዜም የዓለም ዋንጫ 2ኛ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋች ሆኗል፡፡ በቀጣይ በሚደረጉ ጨዋታዎች ተጫዋቹ ምን ያህል ግብ ያስቆጥራል የሚለው ይጠበቃል፡፡
ሌላኛው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የሆነው ኦስማን ዴምቤሌ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ከከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች መካከል አንዱ ነው፡፡
የባሎንዶር አሸናፊው ተጫዋች ኦስማን ዴምቤሌ በሦስት የምድብ ጨዋታዎች አራት ግብ አስቆጥሮ አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻቶ አቀብሏል፡፡
ዴምቤሌ በ2026 የዓለም ዋንጫ ሐትሪክ መስራት ከቻሉ ሦስት ተጫዋች መካከል አንዱ ሲሆን÷ ፈረንሳይ ኖርዌይን 4 ለ 1 ስታሸንፍ ሐትሪክ መስራቱ ይታወሳል፡፡
ዴምቤሌ በ32 ደቂቃ ኖርዌይ ላይ የሰራው ሐትሪክ በዓለም ዋንጫ ታሪክ 2ኛው ፈጣን ሐትሪክ ሆኖም ተመዝግቦለታል፡፡የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋች ኤሪክ ፕሮብስት በ1954 የዓለም ዋንጫ በ24 ደቂቃ ሐትሪክ መስራቱ የሚታወስ ነው፡፡
ተጫዋቹ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ለወርቅ ጫማው በቀጣይ ጨዋታዎች የሚያደርገው ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል፡፡
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በባየርን ሙኒክ ቤት ደምቆ ወደ ፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ያቀናው ኦሊሴ የፊት መስመሩ ሌላኛው ኮከብ ነው፡፡ኦሊሴ በምድብ በተደረጉ ሦስት ጨዋታዎች ሦስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
ሦስቱ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋቾች በዚህ የዓለም ዋንጫ እስካሁን ድረስ በጋራ 14 ግቦች ላይ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡
ይህ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ጥምረት በ2026 የዓለም ዋንጫ ለተጋጣሚዎቹ ፈታኝ ሆኗል፡፡ በቀጣይ በሚደረጉ ጨዋታዎችም የእነዚህ ሦስት ተጫዋቾች ጥምረት ተጠባቂ ነው፡፡

5 months ago
ለ3ኛ ተከታታይ የውድድር ዓመት የፈረንሳይ ሊግ ሻምፒዮን - አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ስፔናዊው አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ለተከታታይ 3ኛ የውድድር ዓመት ከፒኤስጂ ጋር የፈረንሳይ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ ችለዋል፡፡
በፈረንጆቹ 1970 ስፔን ውስጥ በዛሬው ዕለት የተወለዱት አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ የአሰልጣኝነት ስራቸውን የጀመሩት በባርሴሎና ቢ ቡድን ነው፡፡
ከባርሴሎና ቢ ቡድን በመቀጠል ሮማ እና ሴልታቪጎን ያሰለጠኑት አሰልጣኙ በፈረንጆቹ 2014 የባርሴሎና ዋናውን ቡድን ተረክበዋል፡፡
በካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በነበራቸው የአሰልጣኝነት ቆይታ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ፣ የስፔን ላሊጋ፣ የስፔን ሱፐር ካፕ፣ ኮፓ ዴል ሬይ፣ የዓለም ክለቦች ዋንጫ እና የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዋንጫዎችን አሳክተዋል፡፡
ከባርሴሎና ጋር ከተለያዩ በኋላ የስፔን ብሔራዊ ቡድንን ከፈረንጆቹ 2018 እስከ 2022 አሰልጥነው በ2023/24 ወደ ፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ አቅንተዋል፡፡
የፓሪሱን ክለብ በ2023/24 ከተረከቡ ወዲህ የዘንድሮን ጨምሮ ለተከታታይ ሦስት የውድድር ዓመታት የሊጉን ዋንጫ ማሳካት ችለዋል፡፡
ፒኤስጂ በታሪኩ 14ኛ የፈረንሳይ ሊግ ዋንጫውን ያሳካ ሲሆን÷ በኤንሪኬ እየተመራ ደግሞ ያለፉትን ሦስት ተከታታይ የውድድር ዓመት ሻምፒዮን ሆኗል፡፡
ፒኤስጂ በሀገር ውስጥ ውድድር ስኬታማ ቢሆንም በአውሮፓ መድረክ ግን ተፎካካሪ ለመሆን እና ዋንጫ ለማንሳት የኤንሪኬን ፓሪስ መድረስ ይፈልግ ነበር፡፡
ፒኤስጂ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ለማሳካት ሊዮኔል ሜሲ፣ ኔይማር ጁኒየር እና ኪሊያን ምባፔ የመሳሳሉ ተጫዋቾችን ቢያጣምርም ማሳካት እንዳልቻለ ይታወቃል፡፡
ከስፔናዊው አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ፓሪስ መድረስ በኋላ ግን የክለቡ የዘመናት ጥያቄ ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ምላሽ ማግኘቱ ይታወሳል፡፡
አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ የፈረንሳዩን ክለብ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የዘመናት ሕልም መፍታት የቻሉ ሰው ናቸው፡፡
ፒኤስጂ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን በፈረንጆቹ 2024/25 የውድድር ዓመት ሲያሳካ አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ በክለቡ ያመጡት ለውጥ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡
አሰልጣኙ በአንድ ተጫዋች ላይ ጥገኛ ያልሆነ እንደ ቡድን የሚጫወት ጠንካራ ስብስብ በመገንባት ክለቡን ለዚህ ታላቅ ክብር አብቅተዋል፡፡
አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ አሁን የፈረንሳዩን ክለብ ፒኤስጂን በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ መድረክ ለተከታታይ የውድድር ዓመት ለፍጻሜ ማድረስ ችለዋል፡፡
የአሰልጣኝ ኤንሪኬ ቡድን በዚህ የውድድር ዓመት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተጋጣሚዎቹ ላይ 44 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን÷ በዚህም በውድድር ዘመኑ በመድረኩ በርካታ ግቦችን በማስቆጠር ቀዳሚው ሆኗል።
ቡድኑ በዚህ የውድድር ዓመት በመድረኩ ባየርን ሙኒክ፣ ሊቨርፑል፣ ቼልሲ እና ባርሴሎናን የመሳሰሉ ቡድኖችን ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
ፒኤስጂ በአሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ እየተመራ ለተከታታይ የውድድር ዓመት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ያሳካ ይሆን የሚለው የሚጠበቅ ሲሆን÷ በፍጻሜው ከአርሰናል ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በሀንጋሪ ቡዳፔስት ፑሽካሽ አሬና ስታዲየም ይደረጋል።

Sponsored by
Surafel
5 months ago
የአርሰናል እና የፒኤስጂ ጨዋታን የሚዳኙት ዳኛ ታወቁ
#ethiopia | በጉጉት ለሚጠበቀው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ፍልሚያ፣ በአርሰናል እና በፒኤስጂ መካከል የሚደረገውን ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ መታወቃቸው ተረጋግጧል።
ጀርመናዊው የ42 ዓመቱ ዳኛ ዳንኤል ሴበርት ይህንን ታላቅ ጨዋታ በመሐል ዳኝነት እንዲመሩ በኃላፊነት ተሰይመዋል።
ከ20 ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ ወደ ፍጻሜው የተመለሱት መድፈኞቹ፣ በግማሽ ፍጻሜው አትሌቲኮ ማድሪድን በድምር ውጤት በመርታት ነው ለዚህ ደረጃ የበቁት።
ክለቡ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ወደ ለንደን ለመውሰድ ቆርጦ ተነስቷል።
የአምናው ውድድር አሸናፊው የፈረንሳዩ ክለብ፣ በግማሽ ፍጻሜው ባየርን ሙኒክን በማሸነፍ ለፍጻሜው ደርሷል።
ፒኤስጂ ክብሩን አስጠብቆ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት ሻምፒዮን ለመሆን ይፋለማል።
ይህ ተጠባቂ የፍጻሜ ጨዋታ በሀንጋሪ ቡዳፔስት በሚገኘው ፑሽካሽ አሬና ስታዲየም ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#championsleague #arsenal #psg #uclfinal #danielsiebert #footballnews #ethiopia

የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ ኦዌን ሃርግሪቭስ በቲኤንቲ ስፖርት ላይ ቀርቦ አርሰናል በቀጣይ ከፓሪስ ሴንት ዠርመን ጋር ስለሚኖረው ጨዋታ እና የማሸነፍ እድል ተከታዩን አስተያየት ሰጥቷል፡
"አርሰናል ያለምንም ጥርጥር የማሸነፍ እድል አለው። ባላቸው የተከላካይ ክፍል እና ግብ ጠባቂ እጅግ ድንቅ ናቸው። ዴክላን ራይስ በተከላካይ አማካይ ስፍራ ላይ እየተጫወተ ሲሆን፣ እዚያ ቦታ ላይ ደግሞ አስደናቂ ብቃቱን እያሳየ ነው። ጨዋታው እጅግ አጓጊ ይሆናል። ፒኤስጂ ከባየርን ሙኒክ ጋር ከነበረው ጨዋታ ይበልጥ አጥቅቶ እንደሚጫወት ይጠበቃል፤ ነገር ግን አሁን የምናየው አርሰናል የተለየ ነው። ባለፉት ሶስት ወይም አራት ሳምንታት ውስጥ ከገጠማቸው አነስተኛ መዋዠቅ (ማሽቆልቆል) አሁን ላይ ያገገሙ ይመስለኛል። አሁን በራሳቸው ያምናሉ። ቡካዮ ሳካ በትልልቅ እና ወሳኝ ሰዓቶች ላይ ትልልቅ ግቦችን ይዞ ተመልሷል። እድሉ አላቸው፤ ማድረግ ያለባቸው በራሳቸው ማመን ብቻ ነው።"
ባየርን ሙኒክ 1 - 1 ፓሪስ ሴንት ዠርመን (በድምር ውጤት 5-6)

ፒኤስጂ ለአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፒኤስጂ በድምር ውጤት ባየርን ሙኒክን በማሸነፍ ለአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ደርሷል።
ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም በተደረገው የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ፒኤስጂ እና ባየርን ሙኒክ 1 ለ 1 ተለያይተዋል።
የፒኤስጂን ግብ ኦስማን ዴምቤሌ ጨዋታው በተጀመረ ሶስተኛ ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥር፤ የባየርን ሙኒክን የአቻነት ግብ ሃሪ ኬን ከመረብ አሳርፏል።
በዚህም ፒኤስጂ በድምር ውጤት 6 ለ 5 በማሸነፍ የፍጻሜ ተፋላሚ ለመሆን በቅቷል።
የአምና የመድረኩ አሸናፊ ፒኤስጂ ለተከታታይ የውድድር ዓመት ዋንጫውን ለማንሳት የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ትናንት አርሰናል አትሌቲኮ ማድሪድን በድምር ውጤት 2 ለ 1 በማሸነፍ ከ20 ዓመታት በኋላ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን ማረጋገጡ ይታወቃል፡፡

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ለማመን የሚከብድ ጅምር በአሊያንዝ አሬና! ጨዋታው በተጀመረ ገና በ3ኛው ደቂቃ ፒኤስጂ ባስቆጠረው አስደንጋጭ መብረቃዊ ግብ ባየርን ሙኒክን በሜዳው ክፉኛ አስደንግጧል።
በሜዳው ላይ ኑኖ ሜንዴዝ በትንሹ መንሸራተቱን ተከትሎ ማይክል ኦሊሴ አምልጦታል። ይሁን እንጂ ሜንዴዝ አስቀድሞ የቢጫ ካርድ ሰለባ በመሆኑ፣ በእነዚህ ሁለት ተጫዋቾች መካከል የሚኖረው ፍልሚያ በቀጣዮቹ ደቂቃዎች እጅግ አጓጊ እንደሚሆን ይጠበቃል።
የስፖርት ተንታኙ ፊል ማክኑልቲ ከሙኒክ ስታዲየም ሆኖ ይህንን ግብ ሲገልጸው "ገዳይ... ፈፅሞ ገዳይ የሆነ ማጥቃት ነው!" ብሎታል። ይህ ፒኤስጂ ባለፉት 12 ወራት በተደጋጋሚ ሲያሳየን የነበረው ዓይነተኛ የመብረቅ ፍጥነት ያለው የመልሶ ማጥቃት ስልት ነው።
ጆርጂያዊው ኮከብ ኽቪቻ ክቫራትስኬሊያ ኳሱን ይዞ በፍጥነት ወደ ፊት ሲያፈተልክ፣ የፒኤስጂው አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ሌሎች ተጫዋቾችም ወደ ፊት እንዲገፉ በእጃቸው ምልክት ይሰጡ ነበር። ምንም የሚያሳስብ ነገር አልነበረም፤ ክቫራ በድንቅ እይታ ያቀበለውን ኳስ ኡስማን ዴምቤሌ እጅግ ማራኪ በሆነ አጨራረስ መረቡ ላይ አሳርፎታል።
ይህ ግብ ቢቆጠርባቸውም የባየርን ሙኒክ ደጋፊዎች ግን እስካሁን ዝምታን አልመረጡም፤ ስታዲየሙ አሁንም በደጋፊዎች ጩኸት እየተናወጠ ይገኛል።
ክቫራትስኬሊያ በአንድ የቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ውድድር ላይ በተከታታይ 7 ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር ወይም ለግብ የሚሆን ኳስ በማቀበል የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆን ታሪክ ሰርቷል።
ከየካቲት 2025 የፒኤስጂ የመጀመሪያ ጨዋታው አንስቶ በቻምፒየንስ ሊጉ ከእሱ የተሻለ ግብ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያደረገ ተጫዋች የለም። በአጠቃላይ 21 (13 ግቦች እና 8 አሲስቶች) በማስመዝገብ ከባየርኑ ሃሪ ኬን ጋር እኩል ተቀምጧል።
ጨዋታው ገና 13 ደቂቃ ላይ ቢሆንም፣ ይህ የፒኤስጂ ፈጣን ግብ የባየርንን የተስፋ ጉዞ እጅግ አዳጋች አድርጎታል!
ጨዋታው እንዴት የሚያልቅ ይመስላችኋል?
ባየርን ሙኒክ 0 - 1 ፒኤስጂ (በድምር ውጤት፡ 4-6) | (ጨዋታው ከተጀመረ በ15ኛው ደቂቃ ላይ ናቸው)

ባየርን ሙኒክ ወይስ ፒኤስጂ - ማን የፍጻሜ ተፋላሚ ይሆናል?
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ባየርን ሙኒክ በሜዳው ፒኤስጂን ያስተናግዳል፡፡
የጀርመኑ ክለብ ባየርን ሙኒክ በውድድር ዓመቱ የሦስትዮሽ ዋንጫ ሕልሙን ለማሳካት የሚያደርገውን ጉዞ ለማጠናከር የሚያደርገው ፍልሚያ ተጠባቂ ነው፡፡
ባየርን ሙኒክ በዚህ የውድድር ዓመት አስፈሪ የፊት መስመር ጥምረት ያለው ቡድን መሆኑን በሁሉም ውድድሮች እያሳየ ይገኛል፡፡
ሙኒክ በውድድር ዓመቱ እስካሁን ድረስ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ 42 ግቦችን እንዲሁም በቡንደስሊጋው ደግሞ 116 ግቦችን ተጋጣሚዎቹ ላይ አስቆጥሯል፡፡
የአምና የመድረኩ አሸናፊ ፒኤስጂ ለተከታታይ የውድድር ዓመት ዋንጫውን ለማንሳት የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሮ ለመቀጠል ይፋለማል፡፡
ፒኤስጂ በውድድር ዓመቱ እስካሁን ድረስ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ 43 ግቦችን ተጋጣሚዎቹ ላይ አስቆጥሯል፡፡
በዚህም በ2025/26 የውድድር ዓመት በመድረኩ በርካታ ግቦችን ተጋጣሚዎች ላይ በማስቆጠር ቀዳሚው ክለብ ነው፡፡
ሁለቱ ቡድኖች በፓርክ ደ ፕሪንስ ያደረጉትን የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ፒኤስጂ 5 ለ 4 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት በአሊያንዝ አሬና የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ የ38 ዓመቱ ፖርቹጋላዊ ዳኛ ጇ ፒንሄሮ በመሐል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል፡፡
የሁለቱ ቡድኖች የድምር ውጤት አሸናፊ በፍጻሜው ከአርሰናል ጋር ይገናኛል፡፡
አርሰናል አትሌቲኮ ማድሪድን በድምር ውጤት 2 ለ 1 በማሸነፍ ከ20 ዓመታት በኋላ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን ማረጋገጡ ይታወቃል፡፡

የባቫሪያኑ ፊት አውራሪዎች…
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የባየርን ሙኒክ የፊት መስመር ተጣማሪዎቹ ሀሪ ኬን፣ ሉዊስ ዲያዝ እና ማይክል ኦሊሴ በሀገር ውስጥ ውድድሮችና በአውሮፓ መድረክ አስደናቂ ጉዞ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ይህ የባቫሪያኑ ጥምረት በዚህ የውድድር ዓመት ያስቆጠራቸው ግቦች 100 የደረሱ ሲሆን÷ የሪያል ማድሪዶቹ ኪሊያን ምባፔ፣ ቪኒ ጁኒየር እና ቫልቬርዴ በ71 ግቦች በሁለተኛነት ይከተላሉ፡፡
በቪንሴንት ኮምፓኒ የሚመራው ባየርን ሙኒክ በቡንደስሊጋው ብቻ እስካሁን 116 ግቦችን (በአማካይ በአንድ ጨዋታ ከሦስት በላይ ግቦችን) ያስቆጠረ ሲሆን፥ አራት ጨዋታዎች እየቀሩት የሊጉ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወቃል፡፡
በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ላይ የሚገኘው የጀርመኑ ክለብ በአስፈሪ የማጥቃት እንቅስቃሴ ለተጋጣሚዎቹ የተከላካይ መስመር ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፡፡
በውድድሩ በዚህ ዓመት እስካሁን ባደረጋቸው 13 ጨዋታዎች በኬን፣ ዲያዝና ኦሊሴ የሚመራው የባቫሪያኑ የፊት መስመር በተጋጣሚዎቹ ላይ 41 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
ባየርን ሙኒክ ባለፈው ሳምንት በመድረኩ በፒኤስጂ 5 ለ 4 በተሸነፈበት የግማሽ ፍጻሜው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሦስቱም ተጫዋቾች ግብ ማስቆጠራቸው ይታወሳል፡፡
በሁሉም ውድድሮች በጋራ በዚህ የውድድር ዓመት ብቻ እስካሁን 100 ግቦችን ያስቆጠሩ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 54ቱ ግቦች በእንግሊዛዊው ኮከብ ሀሪ ኬን የተቆጠሩ ናቸው፡፡
ባለፈው ክረምት በ75 ሚሊየን ዩሮ የዝውውር ሂሳብ ሊቨርፑልን ለቅቆ ወደ ባየርን ሙኒክ ያቀናው ኮሎምቢያዊው ኮከብ ሉዊስ ዲያዝ 26 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል፡፡
20 ጊዜ ኳስና መረብን ያገናኘው ፈረንሳዊው ኮከብ ማይክል ኦሊሴ ከቀኝ መስመር እየተነሳ ከሚያስቆጥራቸው ግቦች በተጨማሪ ያለቀላቸውን ኳሶች አመቻችቶ በማቀበል ወሳኝ ተጫዋች መሆኑን እያስመለከተ ይገኛል፡፡
ይህ የባየርን ሙኒክ የፊት መስመር ጥምረት ከአስር ዓመታት ወዲህ በአንድ የውድድር ዓመት 100 እና ከዚያ በላይ ግቦች በማስቆጠር ሦስተኛው ጥምረት ሆኗል፡፡
ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ 2015/16 የውድድር ዓመት ሊዮኔል ሜሲ፣ ሉዊስ ሱዋሬዝ እና ኔይማር በባርሴሎና 131 እንዲሁም ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ካሪም ቤንዜማ እና ጋሪዝ ቤል በሪያል ማድሪድ በጋራ 100 ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል፡፡
ሙኒክ በሻምፒየንስ ሊግ ለ7ኛ ጊዜ ሻምፒዮንነትን እያለመ ወደ ፍጻሜው ለመሻገር በሚያደርገው ጉዞ በዛሬ ምሽቱ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ የሦስቱ ተጫዋቾች ሚና ከወዲሁ ይጠበቃል፡፡
በኃይለማርያም ተገኝ

አርሰናል ከ20 ዓመታት በኋላ ለሻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ አርሰናል አትሌቲኮ ማድሪድን 1 ለ 0 አሸንፏል።
የአርሰናል ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ቡካዮ ሳካ በመጀመሪያው አጋማሽ አስቆጥሯል።
ወደ ስፔን አቅንቶ የመጀመሪያውን ዙር ጨዋታ 1 አቻ አጠናቅቆ የተመለሰው አርሰናል፥ በድምር ውጤት 2 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ፍጻሜው አልፏል።
በዚህም አርሰናል ከ20 ዓመታት በኋላ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚ ሆኗል።
አርሰናል በፍጻሜው ከባየርን ሙኒክ እና ፒኤስጂ አሸናፊ ጋር ይፋለማል።

አርሰናል ከአትሌቲኮ ማድሪድ…
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ አርሰናል በሜዳው ኢምሬትስ ምሽት 4 ሰዓት ላይ አትሌቲኮ ማድሪድን ያስተናግዳል፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን በታሪካቸው አንድም ጊዜ ማሳካት ያልቻሉት ሁለቱም ቡድኖች ወደ ፍጻሜው ለማለፍ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
በኦፕታ ቅድመ ትንበያ መሰረት ለዋንጫው ቀዳሚውን ግምት ያገኘው አርሰናል እና ከቀሩት አራት ቡድኖች ዝቅተኛውን ቅድመ ግምት ያገኘው አትሌቲኮ ማድሪድ የሚያደርጉት ጨዋታ ነው፡፡
በሪያድ ኤር ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም በተደረገው የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሩት ግብ 1 አቻ በሆነ ውጤት መለያየታቸው ይታወሳል፡፡
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ለዋንጫው ቅድመ ግምት በማግኘት ቀዳሚው ክለብ ቢሆንም ተጋጣሚው አትሌቲኮ ማድሪድ ብርቱ ተፎካካሪ መሆኑን በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ አሳይቷል፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን በታሪኩ ማሸነፍ ያልቻለው አርሰናል ለፍጻሜ መድረስ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን ወቅቱም በፈረንጆቹ 2006 ነበር፡፡
አርሰናል ከፈረንጆቹ 2006 በኋላ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ መድረክ የፍጻሜ ተፋላሚ ለመሆን በዛሬው ጨዋታ የሚያደርገው ፉክክር ይጠበቃል፡፡
በ2024/25 የውድድር ዓመት በመድረኩ እስከ ግማሽ ፍጻሜ የተጓዝ አርሰናል በዚህ የውድድር ዘመን በሻምፒየንስ ሊጉ የሚያደርገው ጉዞ ተጠባቂ ነው፡፡
በአርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒ የሚመራው አትሌቲኮ ማድሪድ በበኩሉ በታሪኩ ሦስት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ላይ መገኘት መቻሉ ይታወሳል፡፡
አትሌቲኮ ማድሪድ በተለያዩ ጊዜያት በመድረኩ ፍጻሜ ላይ መድረስ ቢችልም ዋንጫውን ግን አንድም ጊዜ ማንሳት አልቻለም፡፡
አትሌቲኮ ማድሪድ ለመጨረሻ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚ የሆነው በፈረንጆቹ 2016 እንደነበር አይዘነጋም፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ለማሳካት በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ የዛሬውን ጨዋታ አሸንፎ ለፍጻሜ ለመድረስ ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
ለዚህም በሳምንቱ መጨረሻ በተደረገው የስፔን ላሊጋ ጨዋታ አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒ ለአብዛኛው የቡድኑ ቋሚ ተሰላፊ ተጫዋቾች እረፍት ሰጥተዋል፡፡
የአትሌቲኮ ማድሪድ የፊት መስመር ተጫዋች ዩሊያን አልቫሬዝ ለጨዋታው ብቁ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ካይ ሃቨርትዝ እና ጁሪየን ቲምበር በአርሰናል በኩል በጉዳት ለጨዋታው የማይደርሱ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
በኢምሬትስ ስታዲየም የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ጀርመናዊው ዳኛ ዳንኤል ሴበርት በመሐል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል፡፡
የሁለቱ ቡድኖች የድምር ውጤት አሸናፊ በነገው ዕለት ጨዋታቸውን ከሚያደርጉት ባየርን ሙኒክ እና ፒኤስጂ ድምር ውጤት አሸናፊ ጋር በፍጻሜው ይገናኛል፡፡
በአቤል ነዋይ

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ፒኤስጂ ባየርን ሙኒክን በጎል ናዳ አሸነፈ
#ethiopia | በፓሪስ ፓርክ ዴ ፕሪንስ ስታዲየም የተካሄደው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ እጅግ አስደናቂ እና በጎሎች የታጀበ ምሽት ነበር።
ዘጠኝ ጎሎች የተቆጠሩበት ይህ ፍልሚያ የእግር ኳስ አፍቃሪዎችን ቀልብ የገዛ ሲሆን ፒኤስጂ ባየርን ሙኒክን 5 ለ 4 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ ለሁለተኛው ዙር ጨዋታ መጠነኛ ብልጫ መያዝ ችሏል።
ጨዋታው እንደተጀመረ ሃሪ ኬን በፍፁም ቅጣት ምት ባየርን ሙኒክን ቀዳሚ ቢያደርግም ፓሪሶች በክቫራትስኬሊያ እና በጆአኦ ኔቬስ አማካኝነት ተከታታይ ጎሎችን በማስቆጠር መሪነቱን ተረክበዋል።
ባየርኖች በሚካኤል ኦሊሴ ጎል አቻ መሆን ቢችሉም በመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ላይ ኡስማን ዴምቤሌ በቪዲዮ ረዳት ዳኛ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ወደ ጎል በመቀየር ፒኤስጂን 3 ለ 2 መሪ አድርጎ ወደ እረፍት አምርተዋል።
ከእረፍት መልስ ፒኤስጂዎች ብልጫቸውን በማስፋት በክቫራትስኬሊያ እና በዴምቤሌ አማካኝነት ተጨማሪ ጎሎችን አስቆጥረው ልዩነቱን ወደ ሶስት አሳድገው ነበር።
ሆኖም የጀርመኑ ሀያል ክለብ ባየርን ሙኒክ ተስፋ ሳይቆርጥ በመታገል በኡፓሜካኖ እና በሉዊስ ዲያዝ አማካኝነት ሁለት ጎሎችን በማከታተል የጎል ልዩነቱን ወደ አንድ ማጥበብ ችሏል።
ፒኤስጂ በዚህ ጨዋታ ያስመዘገበው ውጤት በታሪኩ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን በተለይም ክቫራትስኬሊያ ክለቡን ከተቀላቀለ በኋላ እያሳየ ያለው ድንቅ ብቃት ለቡድኑ ስኬት ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል።
ባየርን ሙኒክ ምንም እንኳን በሜዳው ቢሸነፍም ያስቆጠራቸው አራት ጎሎች ለሁለተኛው ዙር ጨዋታ ትልቅ ተስፋ የሚሰጡት ናቸው።
የሁለቱ ቡድኖች ወሳኝ የሁለተኛ ዙር ፍልሚያ ረቡዕ ግንቦት 6 ቀን በሙኒክ አሊያንዝ አሬና የሚካሄድ ይሆናል።
#ucl #psg #bayernmunich #championsleague #football #sports #goal #paris #munich #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) በፓርክ ዴ ፕሪንስ ስታዲየም ሰማይ ስር ዘጠኝ ጎሎች የተቆጠሩበትና የኳስ አፍቃሪውን እስትንፋስ የገታ ድንቅ የምሽት ፍልሚያ ተካሂዷል። የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ የውድድሩ ባለቤት የሆኑት ፒ.ኤስ.ጂዎች ባየርን ሙኒክን 5 ለ 4 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ ለዳግም ፍልሚያው ቀጭን ብልጫ ይዘው እንዲወጡ አስችሏቸዋል። ጨዋታው ገና በጅማሬው ትኩሳት የነካው ሲሆን፣ ሉዊስ ዲያዝ በዊሊያም ፓቾ ላይ በሰራው ጥፋት የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ሃሪ ኬን ወደ ጎል በመቀየር የጀርመኑን ኃያል ክለብ ቀዳሚ አደረገ። ሆኖም ፓሪሶች ምላሽ ለመስጠት ብዙም አልዘገዩም፤ ኽቪቻ ክቫራትስኬሊያ ከግራ መስመር ኳሷን ይዞ በመግባት ድንቅ ጎል በማስቆጠር ውጤቱን ሲያሰክን፣ ብዙም ሳይቆይ ጆአኦ ኔቬስ በግንባር በመግጨት ፓሪሶችን መሪ አደረጋቸው። ባየርኖች ግን ተስፋ ሳይቆርጡ በሚካኤል ኦሊሴ ግሩም ጎል ጨዋታውን ወደ አቻነት መለሱት። አጋማሹ በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅ ሲመስል፣ በአምስተኛው ደቂቃ የጭማሪ ሰዓት ላይ አልፎንሶ ዴቪስ ኳስ በእጅ ነክቷል በሚል አወዛጋቢ የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (VAR) ውሳኔ ለፒ.ኤስ.ጂ የፍፁም ቅጣት ምት ተሰጥቶ ኡስማን ዴምቤሌ ኳሷን ከመረብ ጋር በማገናኘት ባለቤቶቹን በመሪነት ወደ እረፍት እንዲያመሩ አደረገ።
ከእረፍት መልስ ፓሪሶች የጨዋታውን የበላይነት ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩ ሲሆን፣ ክቫራትስኬሊያ እና ዴምቤሌ ተከታትለው ባስቆጠሯቸው ጎሎች ፒ.ኤስ.ጂ የሶስት ጎል ልዩነት እንዲኖረው አደረጉ። ባየርን ሙኒክ ሙሉ በሙሉ ተሸንፈው የወጡ ቢመስሉም አስደናቂ የሆነ የአሸናፊነት መንፈስ በማሳየት፣ ዳዮት ኡፓሜካኖ የአፅናኝ ጎል ሲያስቆጥር ሉዊስ ዲያዝ ደግሞ ከሃሪ ኬን የተላገለትን ግሩም ኳስ ተጠቅሞ አምስተኛውን ጎል በማስቆጠር የጎል ልዩነቱን ወደ አንድ ዝቅ አደረገው።
ፒ.ኤስ.ጂ ባለፉት ዘጠኝ የሻምፒዮንስ ሊግ ጥንቃቄ የሚጠይቁ ጨዋታዎች በእያንዳንዱ ከሁለት ጎል በላይ በማስቆጠር አዲስ የውድድሩን ታሪክ ያስመዘገበ ሲሆን፣ በተለይ ክቫራትስኬሊያ ጥር 2025 ክለቡን ከተቀላቀለ በኋላ በሻምፒዮንስ ሊግ ብቻ በ20 ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ ከማንኛውም ተጫዋች የላቀ ሆኗል። ባየርን ሙኒክ በበኩሉ ቡንደስሊጋውን አስቀድሞ የጠቀለለ ቢሆንም፣ በኬን፣ ኦሊሴ እና ዲያዝ የሚመራውና በጋራ ከ100 በላይ ጎሎችን ያስቆጠረው የአጥቂ መስመሩ አሁንም ለዳግም ፍልሚያው ትልቅ ተስፋ ሰጥቶታል። ይህ አስደናቂ ፍልሚያ በፓሪስ 5 ለ 4 መጠናቀቁ ረቡዕ ግንቦት 6 በሙኒክ የሚደረገውን የሁለተኛ ዙር ጨዋታ እጅግ ተጠባቂ እና አጓጊ አድርጎታል።

9 ግቦች በተቆጠሩበት ጨዋታ ፒኤስጂ ባየርን ሙኒክን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ፒኤስጂ ባየርን ሙኒክን 5 ለ 4 አሸንፏል።
ለባለሜዳው ክለብ ፒኤስጂ ክቫራስኬሊያ እና ዴምቤሌ እያንዳንዳቸው ሁለት ግቦች ሲያስቆጥሩ ቀሪዋን ግብ ኔቬሽ ከመረብ አሳርፏል።
የባየር ሙኒክን ግቦች ኬን (በፍጹም ቅጣት ምት)፣ ኦሊሴ፣ ኡፓሚካኖ እና ሉዊስ ዲያዝ አስቆጥረዋል።
ለፍጻሜ የሚያልፈውን ቡድን የሚለየው የመልስ ጨዋታ በቀጣዩ ሳምንት ረቡዕ በአሊያንዝ አሬና ይደረጋል።

6 months ago
አርሰናል ድል ቀንቶታል!
#ethiopia | በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ አርሰናል ስፖርቲንግ ሊዝበንን 1 ለ 0 አሸንፏል። መድፈኞቹን ለድል ያበቃችውን ብቸኛ ግብ ካይ ሀቨርትዝ በሁለተኛው አጋማሽ አስቆጥሯል።
ትላንት በኤፍ ኤ ካፕ መውጣታችን ቢያሳዝነንም፣ በሻምፒዮንስ ሊጉ የተመዘገበው ድል ትልቅ ተስፋ ሰጥቶናል።
ባየርን ሙኒክ ማድሪድን አንበረከከ!
በሌላ ታላቅ ፍልሚያ ባየርን ሙኒክ ሪያል ማድሪድን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ለባየርን ሉዊስ ዲያዝ እና ሀሪኬን ግቦቹን ሲያስቆጥሩ፣ ለማድሪድ ኪሊያን ምባፔ ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል።
#getu #arsenalvictory #championsleague #kaihavertz #bayernmunich #realmadrid #አርሰናል #ባየርን #ሰበርዜና #ሻምፒዮንስሊግ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

7 months ago
ባየርን ሙኒክ፣ ሊቨርፑል እና አትሌቲኮ ማድሪድ የሩብ ፍፃሜን ተቀላቀሉ
ትናንት ምሽት በተደረጉ የአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ ጨዋታዎች ባየርን ሙኒክ አታላንታን 4 ለ 1 (በድምር ውጤት 10 ለ 2) በማሸነፍ በቀላሉ አልፏል።
ሃሪ ኬን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር፣ ካርል እና ዲያዝ ቀሪዎቹን አክለዋል።
ሊቨርፑል በበኩሉ ጋላታሳራይን በአንፊልድ 4 ለ 0 በመርታት (በድምር 4 ለ 1) ተከታዩን ዙር ተቀላቅሏል።
ሳላህ፣ ሶቦስላይ፣ ኤኪቲኬ እና ግራቨንበርች የሊቨርፑልን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።
አትሌቲኮ ማድሪድ ምንም እንኳን በቶተንሃም 3 ለ 2 ቢሸነፍም፣ በመጀመሪያው ጨዋታ በነበረው 5 ለ 2 ሰፊ ውጤት ምክንያት በድምር 7 ለ 5 ማለፉን አረጋግጧል።
እነዚህ ሶስት ቡድኖች ባርሴሎና፣ ፒኤስጂ፣ ሪያል ማድሪድ፣ ስፖርቲንግ እና አርሰናልን በመቀላቀል ለታላቁ ፍልሚያ ተዘጋጅተዋል።

የግዙፎች ፍልሚያ፦ ሪያል ማድሪድ ከማንቸስተር ሲቲ በድጋሚ ተገናኙ! ⚔️⚽
ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. በኒዮን ስዊዘርላንድ በወጣው የ2018ቱ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ16ቱ ድልድል፣ መላው ዓለም በጉጉት የሚጠብቀው ፍልሚያ ይፋ ሆኗል።
"የአውሮፓ ነገስታቱ" ሪያል ማድሪዶች ካለፉት ዓመታት ባላንጣቸው ማንቸስተር ሲቲ ጋር በድጋሚ ተፋጠዋል።
የ16ቱ ድልድሎች፦
🔵 ማንቸስተር ሲቲ 🆚 ሪያል ማድሪድ (የዓመቱ ትልቅ ጨዋታ!)
🔴 አርሰናል 🆚 ባየር ሌቨርኩሰን (የአርቴታ እና ካስፐር ጁልማንድ ታክቲካዊ ጦርነት)
🔵 ፒኤስጂ 🆚 ቼልሲ (የድሮው ትውውቅ ተመለሰ)
🔴 ሊቨርፑል 🆚 ጋላታሳራይ
🔵 ባርሴሎና 🆚 ኒውካስል ዩናይትድ
⚪️ ቶተንሃም 🆚 አትሌቲኮ ማድሪድ
🔴 ባየርን ሙኒክ 🆚 አታላንታ
🟢 ስፖርቲንግ ሊዝበን 🆚 ቦዶ ግሊምፕት
📅 የጨዋታ ቀናት፦
የመጀመሪያ ጨዋታዎች መጋቢት 1 እና 2 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚከናወኑ ሲሆን፣ የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ መጋቢት 8 እና 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ይደረጋሉ።
seledadotio

8 months ago
በጀርመን የባቡር ትኬት አሳላፊው በጭካኔ ተገደለ፤ አባቱም በድንጋጤ ህይወታቸው አለፈ
በጀርመን ባየርን ግዛት ውስጥ የሚገኘው የሙኒክ ከተማ ነዋሪዎች በአሰቃቂ ክስተት ድንጋጤ ውስጥ ወድቀዋል። የ36 ዓመቱ የባቡር ትኬት ተቆጣጣሪ ሰርካን ሲ. ሥራውን እያከናወነ ባለበት ወቅት ትኬት በሌለው መንገደኛ ተደብድቦ መገደሉ ተሰምቷል።
📍 ክስተቱ እንዴት ነበር?
ሰርካን ሲ. በባቡር ውስጥ መደበኛ የትኬት ፍተሻ እያደረገ ባለበት ወቅት፣ ትኬት ያልቆረጠ አንድ ግለሰብ ፍተሻውን በመቃወም ጥቃት ሰንዝሮበታል። በደረሰበት ከባድ ድብደባ ምክንያት ሰርካን ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። ሟቹ በባልደረቦቹና በጓደኞቹ ዘንድ ተወዳጅ፣ ሰላማዊና ለስራው ታማኝ የነበረ የቤተሰብ መጋቢ ነበር።
💔 በሀዘን ላይ ሌላ ሀዘን
የልጃቸውን መገደል የሰሙት የሰርካን አባት፣ በደረሰባቸው ከፍተኛ ድንጋጤ በልብ ድካም ተዝለፍልፈው ወድቀዋል። በሚያሳዝን ሁኔታ እርሳቸውም ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።
በአሁኑ ወቅት ቤተሰቡ በአንድ ቀን ሁለት የምሰሶ ሰዎችን በማጣቱ ከፍተኛ ሀዘን ላይ ይገኛል።
🗞️ ዘገባዎች ምን ይላሉ?
እንደ BILD ዘገባ ከሆነ፣ የሰርካን ዘመዶች ሁኔታው "ሊታመን የማይችል" እንደሆነባቸውና መላው ቤተሰብ በከፍተኛ የስነ-ልቦና ስብራት ውስጥ እንዳለ ገልጸዋል።
የጀርመን የባቡር ሰራተኞች ማህበርም በሰራተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ተደጋጋሚ ጥቃት በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲያገኝ ጥሪ አቅርቧል።
🔍 የተጠርጣሪው ሁኔታ
ፖሊስ ጥቃቱን ፈጽሟል የተባለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን፣ በግድያ ወንጀል ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል።

11 months ago
ሚኬል አርቴታ አማትሪያን…
#ethiopia | የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አማትሪያን የተወለደው በፈረንጆቹ 1982 በስፔን ሳን ሴባስቲያን ሲሆን፤ የእግር ኳስ ህይወቱ ጅማሬና ዕድገት በካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ነው፡፡
በባርሴሎና የታሰበውን ያክል የጨዋታ ጊዜ ባለማግኘቱ ወደ ፈረንሳዩ ክለብ ፓሪስ ሴን ዠርመ በማቅናት 18 ወራትን በውሰት አሳልፏል፡፡
በእግር ኳስ ተጫዋችነት ጉዞው እንደሌሎች ስፔናዊያን የመሃል ሜዳ ሞተሮች መፍካት ባይችልም ለስኮትላንዱ ሬንጀርስ፣ ለስፔኑ ሪያል ሶሴዳድ እንዲሁም ለእንግሊዞቹ ኤቨርተንና አርሰናል ክለቦች ተጫውቷል።
በተለይም በመርሲሳይዱ ኤቨርተን በነበረው የስድስት ዓመታት ቆይታ በተጫዋችነት ዘመኑ ጥሩ ጊዜ አሳልፏል።
ለሀገሩ ስፔን በተለያየ የእድሜ እርከን ለታዳጊ ቡድን የተጫወተው ሚኬል አርቴታ፤ ለዋናው ብሔራዊ ቡድን የመጫወት እድል አላገኘም።
በተጫዋችነት ዘመኑ ደምቆ መታየት ያልቻለው ሚኬል አርቴታ በአሰልጣኝነት ዘመኑ ስኬታማ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል።
በማንቼስተር ሲቲ ቤት የስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጓርዲዮላ ረዳት በመሆን የአሰልጣኝነት ህይወትን በፈረንጆቹ 2016 የጀመረው አርቴታ፤ በኢቲሀድ በቆየባቸው ሶስት አመታት ሁለት የፕርሚየር ሊግ፣ አንድ የኤፍኤ እና ሁለት ካራባኦ ዋንጫዎች አንስቷል።
በ2019 የመድፈኞቹ አሰልጣኝ የነበሩት ስፔናዊው ኡናይ ኤምሪ ስንብትን ተከትሎ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ሚኬል አርቴታን የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን ይፋ አደረገ፡፡
በወቅቱ መድፈኞቹ የዝቅታ ዘመናቸው ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ሹመቱ ስህተት እንደነበር ብዙዎች ትችታቸውን ሰንዝረው ነበር፡፡
አርቴታ በወቅቱ በክለቡ ያለው የስራ ባህል ደካማ መሆኑንና ቡድኑ አቅጣጫ ማጣቱን በመግለጽ በቡድኑ ስብስብ ውስጥ የተነሳሽነትና የፍላጎት ማጣት ችግር ነበረባቸው ያላቸውን በማሰናበት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ የሚወጡ ተጫዋቾችን እንደሚፈልግ በግል ተናገረ፡፡
በዚህ የማይስማሙ ተጫዋቾች ሊገነባ ለሚፈልገው የስራ ባህል እንቅፋት እንደሚሆኑበት በመግለጽ አብሮ ለመቀጠል እንደሚቸገር በድፍረት የተናገረው አርቴታ፤ በቅጥሩ የመጀመሪያው ዓመት የእንግሊዝ ኤፍኤ ዋንጫን በማንሳት ጅማሮውን አሳመረ፡፡
በዚህ ሂደት የወቅቱ የቡድኑ ኮከብ ተጫዋቾች የነበሩትን ሜሱት ኦዚል፣ ፒየር ኤምሪክ ኦባሚያንግና ሌሎችንም ከቡድኑ ያስወጣበት መንገድ አነጋጋሪ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በአርቴታ ውጥን እምነቱን ያሳደረው የአርሰናል ቦርድ በክለቡ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በርካታ ሚሊየን ፓውንድ ፈሰስ በማድረግ ለአሰልጣኙ ድጋፉን አሳይቷል፡፡
መድፈኞቹ ከታሪካቸው በተቃራኒ የበይ ተመልካች ሆነውበት ወደ ነበረው ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ዳግም ተሳታፊ ብሎም ተፎካካሪ እንዲሆኑ ማድረግ የቻለው አሰልጣኙ፥ የሊጉ ተፎካካሪና ለዋንጫ ተገማች ቡድን በመገንባት ድንቅ የእግር ኳስ አዋቂ መሆኑን እያስመለከተ ይገኛል፡፡
ባለፉት ጥቂት አመታት በአርቴታ እየተመራ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ያወጣው አርሰናል የሊጉን ዋንጫ ባለማሳካቱ ከፍተኛ ትችት ሲቀርብበት ቢቆይም በዚህ ውድድር ዘመን የሊጉን ዋንጫ ለማሳካት ዓልሞ እየሰራ ነው።
ከ2022/23 የውድድር ዘመን ጀምሮ ባሉት ሶስት አመታት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ አስልጣኙ ላይ ያለውን ጫና ከባድ እንደሚያደርጉበት በብዙዎች ዘንድ እየተገመተ ይገኛል፡፡
በየዓመቱ እየተሻሻለ የመጣው አርሰናል በ2025/26 የውድድር ዓመት 11ኛ ሳምንት ላይ ከማንቼስተር ሲቲ በአራት ነጥብ ከፍ ብሎ በ26 ነጥቦች ሊጉን እየመራ ሲሆን፤ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ላይ ያደረጋቸውን አራት ጨዋታዎች በሙሉ በማሸነፍ በባየርን ሙኒክ በግብ ክፍያ ተበልጦ ከምድቡ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የባለፉት ጥቂት ዓመታት ልምዶችን በማንሳት በዚህ የውድድር ዘመንም የፔፕ ጓርዲዮላው ማንቼስተር ሲቲ የሊጉን ዋንጫ ከኋላ በመነሳት ያነሳል የሚሉ ድምጾች ቢበራከቱም አርቴታና ሰራዊቱ ግን ብቸኛ አማራጫቸው ዋንጫውን የግላቸው በማድረግ 22 አመት የሞላውን የቡድኑ የዋንጫ ረሃብ ማስታገስ የቤት ስራ አለባቸው፡፡
አርሰናል በብዙ መመዘኛዎች ወደ ክፍታ ያመጣው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሊጉን ዋንጫ በማንሳት የልሂቃን አሰልጣኞችን ጎራ ለመቀላቀል እየተጋ ነው።
በታክቲክ መረዳት ልህቀቱ፣ ጫናን በመቋቋም ብቃቱ እና ከመገኛኛ ብዙሃን ጋር ባለው መልካም ግንኙነት የሚወደሰው ሚኬል አርቴታ አማትሪያን በአርሰናል ታሪክ ረጅም ዓመታትን ያሰለጠነ ስምንተኛው አሰልጣኝ በመሆን ቀጥሏል፡፡
#fmcsport

1 year ago
የ2025/26 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድል እጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት በሞናኮ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
በዚህ መሰረትም፡-
የአርሰናል ተጋጣሚዎች፡- ባየርን ሙኒክ፣ ኢንተርሚላን፣ አትሌቲኮ ማድሪድ፣ ክለብ ብሩዥ፣ ኦሊምፒያ ኮስት፣ ስላቪያ ፕራግ፣ ካይራት አልማቲ እና አትሌቲክ ቢልቫኦ
የቼልሲ ተጋጣሚዎች፡- ባየርን ሙኒክ፣ ባርሴሎና፣ ቤንፊካ፣ አታላንታ፣ አያክስ፣ ናፖሊ፣ ፓፎስ እና ካራባግ
የሊቨርፑል ተጋጣሚዎች፡- ሪያል ማድሪድ፣ ኢንተር ሚላን፣ አትሌቲኮ ማድሪድ፣ አይን ትራክት ፍራንክፈርት፣ ፒ ኤስ ቪ፣ ማርሴ፣ ካራባግና ጋላታሳራይ፣
የማንቼስተር ሲቲ ተጋጣሚዎች፡- ሪያል ማድሪድ፣ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ፣ ባየር ሌይቨርኩሰን፣ ቪያሪያ፣ ናፖሊ፣ ቦዶ ግሊምት፣ ጋላታሳራይ እና ሞናኮ
የሪያል ማድሪድ ተጋጣሚዎች፡- ማንቼስተር ሲቲ፣ ሊቨርፑል፣ ጁቬንቱስ፣ ቤንፊካ፣ ማርሴይ፣ ኦሊሚፒያ ኮስት፣ ሞናኮና ካይራት አልማቲ
የባየርን ሙኒክ ተጋጣሚዎች፡- ቼልሲ፣ ፒ ኤስ ጂ፣ ክለብ ብሩጅ ፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን፣ አርሰናል፣ፒ ኤስ ቪ፣ ዩኒየን ኤስ ጂና ፓፎስ ሆነዋል፡፡
Seledadotio

ከንግስና እስከ ባላንጣነት - የቀድሞው የፓሪስ ንጉስ
#ethiopia | በፓርክ ዴ ፕረንስ "ምባፔ ንጉሳችን፥ ኩራታችን ነህ" ተብሎ ቢዘመርለትም ወደ ማድሪድ መኮብለልን ሲመርጥ "ከእኛ ይልቅ ገንዘብን መርጠሃል" ተብሎ በራሳቸው በፒኤስጂ ደጋፊዎች ተብጠልጥሏል፡፡
በስተመጨረሻ ከክለቡ ፒኤሰጂ ጋር የመለያየቱ ነገር ቁርጥ ሲሆን በደጋፊዎች በክብር መሸኘቱ ይታወሳል፡፡
የተወደሰበትን የቀድሞ ክለቡን በተቃራኒ ሊገጥም በሎስ ብላንኮዎቹ ማልያ ወደ ሜዳ የሚገባው ኪሊያን ምባፔ ከፓሪሱ ክለብ ጋር ያላሳካው የሀገር ውስጥ ዋንጫ የለም፡፡
ነገር ግን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግን በፓሪስ ማሳካት ባለመቻሉ ባለ ትልቁን ጆሮ ዋንጫ በማለም ነበር የሻምፒየንስ ሊግ ንጉስ ወደ ሆነው ማድሪድ የኮበለለው፡፡
አዲስ የእግር ኳስ ህይወትና አዲስ ፈተና እፈልጋለሁ በማለት ከፓሪሱ ክለብ መለያየት እንደሚፈልግ ሲገልጽ፥ በክለቡ ደጋፊዎችና አመራሮች ብዙ ትችትን አስተናግዷል፡፡
ሆኖም ነገሮች የተገላቢጦሽ ሆነው ምባፔ ሪያል ማድሪድን በተቀላቀለበት ዓመት ፒኤስጂዎች ታሪካዊውን የሻምፒየንስ ሊግ ድላቸውን ማጣጣም ቻሉ፡፡
በግማሽ ፍጻሜው አርሰናልን በደርሶ መልስ አሸንፈው የሙኒኩን ትኬት ሲቆርጡ፥ ደጋፊዎች "ያለ ኪሊያን ምባፔ የተሻልን ነን" በማለት በስታዲየም ሲዘምሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ተጫዋቹ በቀድሞ ክለቡ የሻምፒየንስ ሊግ ድል ማግስት ከክለቡ በመልቀቁ ይጸጽተው እንደሆን ተጠይቆ "የምጸጸትበት ምክንያት የለም ለክለቡ ማድረግ የምችለውን አድርጌያለሁ፥ አሁን ስላለሁበት የእግር ኳስ ምዕራፍ ነው የማስበው" በማለት ነበር በቀድሞ ክለቡ ድል መደሰቱን የገለጸው፡፡
ኪሊያን ምባፔ በፈረንጆቹ 2020 ፒኤስጂ በባየርን ሙኒክ ተሸንፎ ዋንጫውን ካጣበት የማድሪዱ የሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በኋላ በሰጠው አስተያየት፥ "ከዚህ ክለብ ጋር ይህንን ክብር ማሳካት እፈልጋለሁ ቢልም አብዝቶ የተመኘው ሳይሰምር ወደ ስፔን አቅንቷል፡፡
በዓለም የክለቦች ዋንጫ ለፍጻሜ ለማለፍ በሚደረገው የሪያል ማድሪድ እና የፒኤስጂ ትንቅንቅ ምባፔ የቀድሞ ክለቡ ላይ ግብ ለማስቆጠር ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
በአስደናቂ ብቃት ላይ የሚገኘው የሊዊስ ኤንሪኬ ቡድን በውድድሩ እስካሁን ባደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች የተቆጠረበት ግብ አንድ ብቻ ሲሆን ይህም በውድድሩ አነስተኛ ግብ የተቆጠረበት ክለብ ያደርገዋል፡፡
በአራት ጨዋታዎች ምንም ግብ ያልተቆጠረበት የሻምፒየንስ ሊጉ ባለክብር ዛሬ ምሽትስ በኪሊያን ምባፔ በሚመራው የሎስ ብላንኮዎቹ የፊት መስመር ግብ ሳያስተናግድ መውጣት ይችላል ወይ የሚለው ይጠበቃል፡፡
ኪሊያን ምባፔ በ2017 ከሞናኮ ወደ ፒኤስጂ ከተዘዋወረ በኋላ ለፓሪሱ ክለብ በሁሉም ውድድሮች 308 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ በመጫወት 256 ጊዜ ኳስና መረብን አገናኝቷል።
ምባፔ ያልተከፈለኝ 55 ሚሊየን ዩሮ አለ በማለት በቀድሞ ክለቡ ፒኤስጂ ላይ ባለፈው ግንቦት ወር ክስ መስርቶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፥ አሁን ላይ ጉዳዩን በንግግር ለመፍታት ክሱን ማቋረጡ ነው የተነገረው።
ዛሬ ምሽት 4፡00 ላይ ኪሊያን ምባፔ ከቀድሞ ክለቡ ጋር የሚገናኘውና በፍጻሜው ቼልሲን የሚገጥመውን ክለብ የሚለየው የሪያል ማድሪድ እና ፒኤስጂ ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

Comments