20 days ago
ባማኮን ሪልስቴት ለደንበኞቹ የገነባቸውን አፓርትመንቶች አስረከበ
#ethiopia | ባማኮን ሪልስቴት በቦሌ ያስገነባቸውን ዘመናዊ አፓርታማዎች ለባለቤቶቻቸው አስረክቧል።
በግንባታው ዘርፍ ላለፉት 20 አመታት የዳበረ ልምድ ያካበተው ባማኮን ሪልስቴት በቦሌ ሳይቱ የገነባቸውን ዘመናዊ አፓርታማዎች በዛሬው እለት አስረክቧል።
ባማኮን ያስረከባቸው እነዚህ አፓርታማዎች ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ፊት ለፊት የሚገኙ ናቸው።
አፓርታማዎቹ የተገነባበት ቦታ ለአገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ተጓዦች ተመራጭ መኖሪያዎች እንዲሆኑ ታስቦ መሆኑን ተነግሯል።
ቤቶቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ተሰርተው የተጠናቀቁ በመሆናቸው ባለቤቶች ምንም ወጪ አይጠይቃቸውም።
ቤቶቹ ባለቤቶቹ በራሳቸው መኖር አሊያም በቀጥታ አከራይተው ከፍተኛ ገቢ ማግኘት የሚችሉባቸው እንደሆኑ ተጠቅሷል።
በካዛንችስ፣ ባምቢስ አትላስ፣ ፍሬንድሺፕ ፓርክ፣ቦሌ ኤርፖርት ቪው፣በሜክሲኮ እና ቡልቡላ ሳይቶች ላይ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች በታያዘላቸው የጊዜ ቀመር ሰርቶ እያስረከበ ይገኛል።
ባማኮን ሪልስቴት ግንባታዎቹን በታቀደላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ በራሱ በባማኮን ግሩፕ ሥር ካሉ እህት ኩባንያዎች ጋር በጥምረት እንደሚሰራ ገልጿል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #ባማኮንሪልስቴት #አፓርታማ #ግንባታ

Comments