3 months ago
ዓለምን ዳግም ወደ ስጋት የከተተው የቴህራን እና ዋሽንግተን ወታደራዊ ግጭት
**********************
ባለፈው ወር በፓኪስታን አጋዥነት የተደረሰው የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ መፍረሱን ተከትሎ፣ በሁለቱ ኃይላት መካከል ለቀናት የቀጠለው ጥቃት የቀጣናውን የጸጥታና የዓለም አቀፍ የነዳጅ ንግድ መስመር ከባድ ሥጋት ላይ ጥሎታል።
አሁን ላይ ዓለም አቀፍ ሕግጋትን ወደ መጣስ እና የኒውክሌር ተቋማትን ወደ ማጥቃት የተሸጋገረው ይህ አደገኛ ምዕራፍ፣ መላውን ዓለም ወደማይወጣበት ሁለንተናዊ ቀውስ ሊከተው የሚችል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።
የግጭቱ መነሻ የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) ይፋ ባደረገው መግለጫ መሠረት፣ በዮርዳኖስ በሚገኝ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ላይ በተሰነዘረ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ሁለት የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸውንና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን ተከትሎ የተከሰተ ነው።
ዋሽንግተን ለዚህ አጸፋዊ ምላሽ ይሆን ዘንድ በደቡባዊና ደቡብ ምዕራብ ኢራን በሚገኘው የዳርክሆቨይን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ቦታ ላይ ሳይቀር ያነጣጠረ የሚሳኤል ጥቃት ፈጽማለች።
ፔንታገን ጥቃቱን በቀጥታ ከማረጋገጥም ሆነ ከመካድ የተቆጠበ ቢሆንም፣ "አሜሪካ ወታደሮቿን ከጥቃት ለመከላከልና የኢራንን የማጥቃት አቅም ለማዳከም ማንኛውንም እርምጃ ትወስዳለች" ሲል ድርጊቱን በተዘዋዋሪ ተከላክሏል፤ ጥቃቶቹም በዋናነት የኢራንን ወታደራዊ የሎጅስቲክስ መሠረተ-ልማቶች ላይ ያነጣጠሩ መሆቸውን ትሟገታለች።
ይሁን እንጂ የኢራን የአቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ጥቃቱን "የሀገሪቱን የሳይንስ ዕድገትና ነጻነት ለማደናቀፍ የታለመ አረመኔያዊ የሽብር ድርጊት" ሲል በጽኑ ኮንኖታል።
ቴህራን ተቋሙ ሙሉ በሙሉ ለዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ የደኅንነት ጥበቃ ሥርዓት ተገዢና ሰላማዊ መሆኑን በመጥቀስ፣ አሜሪካ ዓለም አቀፍ ሕግን በግልጽ መጣሷን አስታውቃለች።
በአሜሪካ የአየር ጥቃቶች ሳቢያ እስካሁን በኢራን ቢያንስ 50 ሰዎች መገደላቸውንና ከ500 በላይ መቁሰላቸውን የገለጸው የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር፣ በርካታ ድልድዮችና ሲቪል መሠረተ-ልማቶች መውደማቸውን አረጋግጧል።
ለአሜሪካ ጥቃት የኢራን ወታደራዊ ምላሽ ፈጣንና መጠነ-ሰፊ የነበረ ሲሆን፣ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ኃይል "ናስር-2" የተሰኘውንና 20ኛ ምዕራፍ ላይ የደረሰውን የሚሳኤልና የድሮን ጥቃት የሰነዘረ ሲሆን፣ የኢራን መደበኛ ጦር በበኩሉ "ሳዕቃ" የተሰኘውን 15ኛ ምዕራፍ የጥቃት ዘመቻ አካሂዷል።
በጥቃቶቹ በኩዌት የሚገኘው አሊ አል-ሳሌም የአየር ኃይል ሰፈር፣ ካምፕ አሪፍጃን፣ ካምፕ አዳይሪ እና ሚና አብዱላህ የተሰኘው የሎጂስቲክስ ማዕከል በከባድ ሁኔታ ተመተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ በባህሬን የሚገኘው የአሜሪካ አምስተኛ ፍሊት ዋና መሥሪያ ቤት እና በዮርዳኖስ በሚገኘው አል-አዝራቅ የአየር ኃይል ሰፈር ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። ምንም እንኳ የአሜሪካ እና የባሕረ-ሰላጤው አገራት መከላከያ ተቋማት አብዛኞቹን የኢራን ሚሳኤሎችና ድሮኖች ማክሸፋቸውን በይፋ ቢገልጹም፣ የወጡ የሳተላይት ምስሎች ግን የተለየ እውነታ እያሳዩ ነው።
የዋሽንግተን ፖስት የምርመራ ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ በክልሉ በሚገኙ 15 የአሜሪካ ወታደራዊ ይዞታዎች ውስጥ የራዳር ሥርዓቶች፣ የፓትሪዮት መከላከያ መሣሪያዎች እና የመጋዘን ተቋማትን ጨምሮ 228 መዋቅሮች በከፊልም ሆነ በሙሉ መውደማቸውን አረጋግጧል።
ይህ ወታደራዊ መካረር በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲና ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ መናወጥን አስከትሏል። የኢራንን ይፋዊ አቤቱታ ተከትሎ፣ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ባወጡት መግለጫ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች ቁጥር 444 እና 533 መሠረት፣ በሰላማዊ የኒውክሌር ተቋማት ላይ የሚሰነዘር ማንኛውም ጥቃት ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጥስ መሆኑን አስታውሰዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ በበኩላቸው፣ የኒውክሌር ተቋማትን ኢላማ ማድረግ የቀጣናውን ውጥረት ወደማይመለስ አደገኛ አደጋ ሊቀይረው እንደሚችል አስጠንቅቀው፣ የጸጥታው ምክር ቤት በአስቸኳይ እንዲመክርና ሁለቱም ወገኖች ራስን የመግታት እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል።
"የኒውክሌር መሠረተ-ልማቶችን ማጥቃት ቀጣናውን ብቻ ሳይሆን መላውን ዓለም ወደማይወጣበት ሁለንተናዊ ቀውስ ውስጥ የሚከት አደገኛ ድርጊት ነው" የሚለው የሰላም ጥሪ መግለጫ የሁኔታውን አሳሳቢነት በግልጽ ያሳያል።
በፖለቲካው ረገድ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የቃላት መለዋወጥ ይበልጥ ጠንክሯል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋሽንግተን በኩዌትና ባህሬን ላሉት የጦር ሰፈሮቿ ተጨማሪ የአየር መከላከያ ዘዴዎችን በፍጥነት ለማስፈር እያቀደች መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ ኢራን የኒውክሌር ታጣቂ እንድትሆን ፈጽሞ እንደማይፈቅዱ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል፣ የኢራን መንፈሣዊ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ እና የፓርላማው አፈ-ጉባኤ መሀመድ ባቄር ቃሊባፍ፣ ዋሽንግተን ስምምነቱን በተጠቀሰው መሠረት ደጋግማ መጣሷ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ፊርማ ፍጹም ዋጋ ቢስ መሆኑን ያረጋገጠ ነው ብለዋል። የሀገሪቱን ደኅንነት ለማረጋገጥ መላው የኢራን ሕዝብ ቅዱስ ያሉት "አንድነት" እንዲኖረው ጥሪ አቅርበዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዋሽንግተን በኢራን ወደቦች ላይ የባሕር እገዳ ለመጣል መሞከሯን ተከትሎ፣ ቴህራን በበኩሏ የዓለም የነዳጅ ንግድ ወሳኝ የደም ሥር የሆነውን የሆርሙዝ ሰርጥ ሙሉ በሙሉ ዝግ መሆኑን አውጃለች።
ይህንን የባሕረ-ሰላጤው መዘጋት ተከትሎ፣ የዓለም የነዳጅ ዋጋ (Brent Crude) በአንድ ጀምበር ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።
ዓለም አቀፍ የኢነርጂ ተንታኞች ውጥረቱ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ በተለይ በእስያ እና በአውሮፓ አገራት ላይ ከባድ የነዳጅ እጥረትና የዋጋ ግሽበት ሊከሰት እንደሚችልና የንግድ መርከቦች ረጅም ርቀት ወደሚጠይቀው የአፍሪካ አቅጣጫ መስመራቸውን ለመቀየር እየተገደዱ መሆኑን እየገለጹ ይገኛሉ።
ፍጥጫው ወታደራዊ ጡንቻን ከማሳየት አልፎ የዓለምን መደበኛ የኢኮኖሚና የጸጥታ መዋቅር የቀየረ ታሪካዊ ቀውስ ሆኗል።
በሰለሞን ገዳ

ትራምፕ፡ "የአሊ ኻሜኒ ልጅ 90 በመቶ ሰውነቱ ተዳክሟል "
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በቅርቡ በተገደሉት የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ ምትክ ስልጣን የያዙት ልጃቸው ሞጅታባ ኻሜኒ "90 በመቶ ሰውነታቸው ተዳክሟል " ሲሉ ተናገሩ።
ትራምፕ የኢራን ወታደራዊ መሪዎች መገደላቸውንና የአገሪቱ የጦር መዋቅር፣ የአየርና የባህር ኃይል ሙሉ በሙሉ መውደሙን ገልጸዋል።
ሞጅታባ ኻሜኒ በየካቲት 21ዱ የአሜሪካና እስራኤል ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ በአደባባይ አልታዩም።
በኻሜኒ ቀብር ላይ ጥቁር ማስክ አድርጎ የታየው ግለሰብ የሞጅታባ ልጅ መሀመድ ጃቫድ መሆኑ ታውቋል።
እርሱም በሳንሱር ጥቃቱ ከባድ የፊት ቃጠሎና ጉዳት እንደደረሰበት ተገልጿል።
Seledadotio

ሞጅታባ ኻሜኒ የአባታቸውን ግድያ ለመበቀል ቃል ገብተዋል❗️
የኢራን አዲሱ የበላይ መሪ አያቶላ ሞጅታባ ኻሜኒ የተገደሉትን አባታቸውን አሊ ኻሜኒን ደም መበቀል የመላው የኢራን ሕዝብ ፍላጎት በመሆኑ የአጸፋው ርምጃ እንደሚወሰድ አስታወቁ።
👉ሞጅታባ ኻሜኒ የአባታቸው ሥርዓተ ቀብር መፈጸሙን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ካለአግባብ የንጹሃንን ህይወት የቀጠፉ ወንጀለኛና ክብር የለሽ ነፍሰ ገዳዮችን ለመበቀል ቃል እንገባለን ብለዋል። ለሳምንት ያህል ሲካሄድ የቆየው የሽኝት ሥነ ስርዓት ተጠናቅቆ የኢራን የቀድሞው መሪ ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።
👉አሜሪካና እስራኤል በኢራን ላይ በሰነዘሩት ጥቃት አሊ ኻሜኒ መገደላቸውን ተከትሎ ኢራን ተከታታይ የአጸፋ ርምጃዎችን መውሰዷ ይታወሳል።
በሌላ በኩል ኢራን የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ለመግደል አዲስ እቅድ ማውጣቷን የሚያሳዩ መረጃዎች ደርሶኛል ስትል እስራኤል በቅርቡ ለአሜሪካ የደህንነት መረጃ ማጋራቷን ተገልጿል። ይህንን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በማህበራዊ ትሰስር ገጻቸው በኩል ኢራን በእሳቸው ላይ የግድያ ሙከራ ካደረገች በሺዎች የሚቆጠሩ ሚሳኤሎችን በኢራን ላይ እንደሚተኩሱ ማስጠንቀቃቸውን የዘገበው አናዶሉ ነው።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በቴህራን የሚገኘው የተግባራዊ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ሞስታፋ ኾሽቼሽም ለአልጀዚራ እንደተናገሩት በቀድሞው ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢራናውያን የበቀል እርምጃ እንዲወሰድ አጥብቀው እየጠየቁ ይገኛሉ። ፕሮፌሰሩ ይህን ያሉት የቀድሞው መሪ የሽኝት ስነ-ስርዓት ከመካሄዱ በፊትም ህዝቡ ቁጣውን ሲገልጽ እንደነበር በማስታወስ ነው።
አዲሱ ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ የአባታቸውን ግድያ ለመበቀል የገቡትን ቃል በተመለከተ ፕሮፌሰሩ ሲያብራሩ፣ ኢራናውያን በየምሽቱ አደባባይ በመውጣት እያሰሙ ያሉት ድምጽ እያደገ ለመጣው የህዝብ የበቀል ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ መሆኑን ገልጸዋል።
"አሜሪካውያን የኢራንን መሪ እና ከፍተኛ ጄኔራሎች መግደላቸው ትክክል ነው፣ ኢራናውያንም ይህን አምነው ዝም ብለው መቀመጥ አለባቸው የሚል ማንም ሰው በዓለም ላይ ይኖራል ብዬ አላምንም" ያሉት ኾሽቼሽም፣ አሜሪካውያን ለፈጸሙት ጥቃት ተገቢውን ዋጋ ካልከፈሉ፣ በአደባባይ እያስጠነቀቁ እንዳሉት አዲሱንም ጠቅላይ መሪ ከመግደል ወደኋላ እንደማይሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።
አሜሪካውያን ከኢራን ጋር ለሚደረግ ለማንኛውም ዓይነት ስምምነት ታማኝ ሆነው ስለማያውቁ፣ በቀጣይ ቀናት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግጭት እና ወታደራዊ ውጥረት መባባሱ ፈጽሞ የማይቀር ጉዳይ መሆኑን ምሁሩ አክለው አስጠንቅቀዋል።

Sponsored by
Surafel
3 months ago
ሞጅታባ ኻሜኒ የአባታቸውን ግድያ ለመበቀል ቃል ገቡ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢራን አዲሱ የበላይ መሪ አያቶላ ሞጅታባ ኻሜኒ የተገደሉትን አባታቸውን አሊ ኻሜኒን ደም መበቀል የመላው የኢራን ሕዝብ ፍላጎት በመሆኑ የአጸፋው ርምጃ እንደሚወሰድ አስታወቁ።
ሞጅታባ ኻሜኒ የአባታቸው ሥርዓተ ቀብር መፈጸሙን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ካለአግባብ የንጹሃንን ህይወት የቀጠፉ ወንጀለኛና ክብር የለሽ ነፍሰ ገዳዮችን ለመበቀል ቃል እንገባለን ብለዋል።
ለሳምንት ያህል ሲካሄድ የቆየው የሽኝት ሥነ ስርዓት ተጠናቅቆ የኢራን የቀድሞው መሪ ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።
አሜሪካና እስራኤል በኢራን ላይ በሰነዘሩት ጥቃት አሊ ኻሜኒ መገደላቸውን ተከትሎ ኢራን ተከታታይ የአጸፋ ርምጃዎችን መውሰዷ ይታወሳል።
በሌላ በኩል ኢራን የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ለመግደል አዲስ እቅድ ማውጣቷን የሚያሳዩ መረጃዎች ደርሶኛል ስትል እስራኤል በቅርቡ ለአሜሪካ የደህንነት መረጃ ማጋራቷን ዘገባዎች አመላክተዋል።
ይህንን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በማህበራዊ ትሰስር ገጻቸው በኩል ኢራን በእሳቸው ላይ የግድያ ሙከራ ካደረገች በሺዎች የሚቆጠሩ ሚሳኤሎችን በኢራን ላይ እንደሚተኩሱ ማስጠንቀቃቸውን የዘገበው አናዶሉ ነው።
ቴህራን እና ዋሽንግተን በሁሉም ግንባሮች ላይ የሚደረጉ ውጊያዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ፣ አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የባህር ኃይል እገዳ እንዲነሳ እና የሆርሙዝ ሰርጥ በድጋሚ እንዲከፈት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመው ነበር።
ይሁን እንጂ በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል በሚያልፉ የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት በመሰንዘሩ ምክንያት በሁለቱ ወገኖች መካከል ተቀዛቅዞ የነበረው ውጊያ በድጋሜ እየተባባሰ መምጣቱ ይታወቃል።
በቱርክ በተካሄደው የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) ስብሰባ ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ማብቃቱን መግለጻቸው ይታወሳል።
በዮናስ ጌትነት

የአያቶላሕ ዓሊ ኻሜኒ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ
አሜሪካ እና እስራኤል ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ ላይ የገደሏቸዉ የኢራን የፖለቲካና የኃይማኖት መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻሜኒ ዛሬ ስርዓተ ቀብር ተፈፅሟል።
እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ ጦርነት በከፈቱበት ዕለት የካቲት 28 ቀን 2026 ከኻሜኒ ሌላ ሴት ልጃቸዉን፣ የልጅ ልጃቸውን ፣ አማቻቸውንና 11 ባለሥልጣኖቻቸውን ገድለዋል።
ባለቤታቸውም ክፉኛ ቆስለዉ ቆይተው ሞተዋል።
የኻሜኒ ሥልጣን የያዙት ያሁኑ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒም የዚያን ቀን ቆስለዋል።
ሞጅታባሕ ጠቅላይ መሪነቱን ሥልጣን ቢይዙም እስከ ዛሬ ድረስ ለሕዝብ እይታ አልቀረቡም።
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለአባታቸው በተደረገው የሽኝት ሥርዓትም ሆነ በዛሬው የቀብር ሥርዓት ላይ አልተገኙም።
ኢራንን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት ዓሊ ኻሜኒ ዛሬ የተቀበሩት፤ በሐገሪቱ ሰሜን-ምሥራቅ ቅዱስ የቀብር ሥፍራ ማሻሐድ ዉስጥ ነዉ።
ማሽሐድ የኻሚኔይ የትዉልድ ሥፍራም ናት።
በቀብር ሥርዓቱ ላይ ለመገኘት በመቶ ሺሕ የሚቆጠር የኢራን ሕዝብ የማሻሐድ ከተማን አጥለቅልቋት ውለዋል።

4 months ago
የኢራኑ ፕሬዚዳንት የስራ
መልቀቂያ ማቅረባቸው ተሰማ
የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ለሀገሪቱ የበላይ መሪ ጽህፈት ቤት ይፋዊ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆነ ምንጭ ለኢራን ኢንተርናሽናል ገልጧል። እሁድ ዕለት በተላከው በዚህ ደብዳቤ ላይ ፕሬዝዳንቱና መንግስታቸው በሀገሪቱ ዋና ዋና እና ወሳኝ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ ሙሉ በሙሉ መገለላቸውን ፔዜሽኪያን አጽንኦት ሰጥተውበታል። በዚህም ምክንያት በተፈጠረው ክፍተት የኢስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጦር ውስጥ ያሉ ጽንፈኛ አንጃዎች የሀገሪቱን ጉዳዮች እንዲቆጣጠሩ ዕድል እንደሰጣቸው ምንጩ ጠቁሟል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ በእንዲህ ያለ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መንግስትን መምራትም ሆነ ህጋዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደማይችሉ በመግለጽ፣ በአስቸኳይ ከስልጣናቸው ለመልቀቅ መጠየቃቸውን አስታውቀዋል።
የበላይ መሪው ሞጅታባ ኻሜኒ የፕሬዝዳንቱን መልቀቂያ ይቀበሉት አይቀበሉት እስካሁን ግልጽ ባይሆንም፣ የደብዳቤው ይዘት ግን በከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ ታይቶ የማይታወቅና ጥልቅ የሆነ የስልጣን ክፍፍል መኖሩን በግልጽ ያሳያል። ይህ ክስተት የመጣው በመንግስትና በኢስላማዊቷ ሪፐብሊክ ወታደራዊ-ደህንነት ተቋማት መካከል ለወራት የዘለቀው ውጥረት ከተቀሰቀሰ በኋላ ነው።
ኢራን ኢንተርናሽናል ቀደም ሲል እንደዘገበው፣ የኢስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጦር የፕሬዝዳንቱን በርካታ ስልጣኖች ደረጃ በደረጃ በመገደብ ቁልፍ የመንግስት አካላትን በቁጥጥሩ ስር አውሏል። የውስጥ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ፣ ይህ ሁኔታ የፔዜሽኪያን አስተዳደር በፖለቲካዊና አስፈፃሚ የውሳኔ ማጣት አዙሪት ውስጥ እንዲገባ ያደረገው ሲሆን፣ ይህም ዲፕሎማሲያዊ ድርድሮች ወደፊት እንዳይራመዱና በካቢኔ መዋቅር ላይ የሚፈለጉ ለውጦች እንዳይተገበሩ እንቅፋት ሆኗል።

5 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ በህይወት እንዳሉ እንደሚያምኑ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ መሪው በመጋቢት ወር መጀመሪያ አካባቢ የተገደሉትን አባታቸውን ለመተካት ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ በአደባባይ ታይተውም ሆነ ድምፃቸው ተሰምቶ አያውቅም።
ኔታንያሁ ከሲቢኤስ የቴሌቪዥን ጣቢያ "60 ሚኒትስ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ስለ አዲሱ መሪ (ታናሹ ኻሜኒ) አካላዊ ሁኔታ እና የአመራር ተጽዕኖ ተጠይቀው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመልሱም፤ "በህይወት እንዳሉ አስባለሁ። ነገር ግን በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳሉ ለመናገር ይከብዳል። የሆነ የመሬት ውስጥ መሸሸጊያ (bunker) ወይም ሚስጥራዊ ቦታ ውስጥ ተደብቀዋል" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ሞጅታባ "ስልጣኑን እና ተጽዕኖውን ለማሳረፍ እየሞከረ ነው" ካሉ በኋላ፣ ነገር ግን ይህ የሞጅታባ ስልጣን ከቀድሞው መሪ (ከአባታቸው አሊ ኻሜኒ) ጋር ሲነጻጸር በእጅጉ ያነሰ መሆኑን ገምግመዋል።

7 months ago
ዘ ቴሌግራፍ ያወጣው አዲስ የድምፅ ቅጂ፤ ሞጅታባ ኻሜኒ እንዴት ተረፉ?
ብሪታንያዊው ጋዜጣ ዘ ቴሌግራፍ ባወጣው አዲስ መረጃ፣ አዲሱ የኢራን መንፈሳዊ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ በቴህራን በተፈጸመው መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ለጥቂት መትረፋቸውን ይፋ አደረገ።
ጋዜጣው እጄ ገብቶኛል ባለው የድምፅ ቅጂ መሠረት፣ ሞጅታባ ኻሜኒ ከሞት የተረፉት በወቅቱ በነበረ "አጋጣሚ" መሆኑ ታውቋል።
እንደ ዘገባው ከሆነ፣ ጥቃቱ የተፈጸመው የካቲት 21 ቀን ረፋድ 3:32 ላይ ሲሆን፣ በአሜሪካና በእስራኤል የተወነጨፉ ባሊስቲክ ሚሳኤሎች የመሪውን መኖሪያ ግቢ በከፍተኛ ሁኔታ ደብድበዋል።
በወቅቱ የጽሕፈት ቤቱ የፕሮቶኮል ኃላፊ የነበሩት ማዛሄር ሆሴይኒ በድምፅ ቅጂው ላይ እንደገለጹት፣ ሞጅታባ ኻሜኒ ጥቃቱ ከመፈጸሙ ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ "አንድ ጉዳይ ለመፈጸም" ወደ ግቢው የአትክልት ስፍራ ወጥተው ነበር።
ይህ አጋጣሚ ሕይወታቸው እንዲተርፍ አድርጓል።
ምንም እንኳን ሞጅታባ ኻሜኒ በእግራቸው ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸው ቢተርፉም፣ ጥቃቱ በቤተሰባቸው ላይ ግን የከፋ ነበር።
ጥቃቱ ሙሉውን የኢራን አመራርና የኻሜኒን ቤተሰብ ለማጥፋት ታቅዶ የተፈጸመ መሆኑን ሆሴይኒ ገልጸዋል።
ሞጅታባ ኻሜኒ ጥቃቱን ቢተርፉም፣ እስካሁን በሕዝብ ፊት አለመታየታቸውና መልእክቶቻቸው በጽሑፍ ብቻ በሀገሪቱ ቴሌቪዥን መተላለፋቸው ስለ ጤንነታቸው ሁኔታ በርካታ ጥያቄዎችን እያስነሳ ይገኛል።

የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት ያሳሰባቸው ትራምፕ ኔቶ እና ሌሎች አገራት እንዲደግፏቸው ጥሪ አቀረቡ
ከፋርስ ባሕረ ሰላጤ አገራት የሚወጣው ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ የሚተላለፍበትን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመጠበቅ ኔቶ እና ሌሎች አገራት እንዲተባበሩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥረት እያደረጉ ነው።
ግዙፍ መርከቦችን ከኢራን ጥቃት ለመጠበቅ የአገራት ጥምረት ለመፍጠር የአሜሪካ መንግሥት ከሰባት አገራት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን የጠቀሱት ትራምፕ ከእነዚህም መካከል ቻይና እንደምትገኝበት ገልጸዋል።
ትራምፕ የሌሎች አገራትን ስም ባይጠቅሱም የኔቶ አባል አገራት “ግዛታቸውን ይከላከላሉ” ብለው እንደሚያምኑ እና አሁን በሆርሙዝ ወሽመጥ የተከሰተው ሁኔታን እንደ ግዛታቸው መመልከት ያለባቸው አገራቱ “ነዳጅ የሚያገኙበት” አካባቢ በመሆኑ እንደሆነ አብራርተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ደግሞ ወሳኙን የሆርሙዝ ወሽመጥ ለመጠበቅ አጋሮቻቸው ድጋፍ የማያደርጉ ከሆነ “የኔቶ የወደፊት ዕጣ በጣም መጥፎ ይሆናል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በተጨማሪም ቻይና ተሳታፊ እንደምትሆን እንደሚጠብቁ፤ ነገር ግን ድጋፍ የማታደርግ ከሆነ ግን በምላሹ ከፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ካር በቅርቡ ሊካሄድ የታቀደውን ስብሰባ ሊያዘገዩት እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ትራምፕ የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ዩናይትድ ኪንግደም የምትሳተፍበት ሁኔታ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር ጋር መነጋገራቸው ተዘግቧል።
ጃፓን በበኩሏ የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመጠበቅ ወደ ፋርስ ባሕረ ሰላጤ ወታደራዊ መርከቦቿን በመላክ የመሳተፍ “ፍላጎት እንደሌላት” የገለጸች ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሯ በዚህ ሳምንት ወደ አሜሪካ በመሄድ ከትራምፕ ጋር እንደሚነጋገሩ ተገልጿል።
በተመሳሳይም አውስትራሊያ ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በጭነት መርከቦች ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ለመከላከል የጦር መርከቦቿን ወደ አካባቢው እንደማታሰማራ በትራንስፖርት ሚኒስትሯ በኩል አሳውቃለች።
አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ ከተሾሙ በኋላ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ኢራናውያንን ደግሞ ሆርሙዝን በመዝጋት እንደሚበቀሉ አመልክተው ነበር።
የዓለም 20 በመቶ የነዳጅ ምርት የሚተላለፍበት ሆርሙዝ ወሽመጥ በጦርነቱ ምክንያት በተፈጠረ ስጋት በዓለም ገበያ ላይ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።
ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚተላለፉ የመርከቦች ቁጥር ከጦርነቱ በፊት ከነበረው የ90 በመቶ ቅናሽ ማሳያቱን የቢቢሲ ቬሪፋይ ዘገባ አመለክቷል።
ከጦርነቱ መጀመር በኋላ አስካሁን ቢያንስ 19 ከባድ መርከቦች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ወድመዋል ወይም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በአካባቢው በተፈጠረው ስጋት ምክንያትም 20 ሺህ የሚጠጉ መርከበኞችን እና የመርከብ ሠራተኞችን የያዙ ግዙፍ መርከቦች ለመንቀሳቀስ ተቸግረው ውቅያኖስ ላይ ቆመው የሚገኙ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት የምግብ እና የውሃ እጥረት እያጋጠማቸው ነው።
BBC

የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ ልጃቸው ሥልጣኑን የመረከቡ ጉዳይ ያሳስባቸው እንደነበር የአሜሪካ የስለላ መረጃ አሳየ
የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ልጃቸው እርሳቸውን ተክቶ ሥልጣን እንዲይዝ የማድረግ ሀሳብ ላይ ጥርጣሬ እንደነበራቸው የአሜሪካ የስለላ መረጃ ማሳየቱን የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ኒውስ ዘገበ።
ይህንን የሚገልጸው የስለላ መረጃ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በዙሪያቸው ላሉ ጥቂት ሰዎች እንደቀረበ ምንጮች መናገራቸውን ዘገባው ያሳያል።
የቀድሞው አያቶላህ ልጃቸው ሞጅታባ ኻሜኒ ብሩህ ጭንቅላት አለው የሚባል ባለመሆኑ እንዲሁም ለመሪነት ብቁ የሆነ ሰው ተደርጎ ባለመታየቱ ሥልጣኑን እንዳይረከብ ስጋት እንደነበራቸው የአሜሪካ ስለላ ትንተና አመልክቷል ተብሏል።
በተጨማሪም አባት በልጃቸው የግል ሕይወቱ ውስጥ ስላለው ችግር ያውቁ እንደነበር መረጃው እንዳሳየ ምንጮቹ ተናግረዋል።
አያቶላህ አሊ ኻሜኒ አሜሪካ እና እስራኤል በከፈቱት ጥቃት መገደላቸውን ተከትሎ ከሳምንት በፊት ልጃቸው ሥልጣኑን ተረክበዋል።
አዲሱ ጠቅላይ መሪ በዚህ ሳምንት የሰጡት የመጀመሪያ መግለጫ በአገሪቱ ቴሌቪዥን ቢነበብም ሥልጣኑን ከተረከቡ ወዲህ እስካሁን አልታዩም።
ሞጅታባ ሳይጎዱ አልቀሩም የሚሉ መረጃዎች ወጥተዋል። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አግራቺ ግን ጠቅላይ መሪ “ጥሩ ጤንነት ላይ” እንደሚገኙ እና “ሁኔታውን ሙሉ በሙሉ እየተቆጣጠሩ” መሆኑን በዛሬው ዕለት ተናግረዋል።

ትራምፕ ጦርነቱ የሚያበቃው “እርግጠኛ ስሆን ነው” አሉ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከእስራኤል ጋር በመሆን በኢራን ላይ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በተመለከተ ፎክስ ኒውስ ከተባለ የአገራቸው ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ በዛሬው ዕለት ቀርቧል።
ፕሬዝዳንቱ በቃለ ምልልሱ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡
ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ጦርነት መቼ እንደሚያበቃ፡ ትራምፕ ጦርነቱ መቼ ማብቃት እንዳለበት ያውቁ እንደሆነ በተጠየቁበት ጊዜ “ይበቃል ብዬ ሳስብ እና እርግጠኛ ስሆን” በማለት መልሰዋል።
በአዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ላይ ስለደረሰው፡ “የተጎዳ ይመስለኛል፤ ነገር ግን በሕይወት ያለ ይመስለኛል”፤ ፕሬዝዳንቱ ጨምረውም ሞጅታባ ኻሜኒ በይፋ ለሕዝብ አልታዩም ብለዋል።
የሆርሙዝ ወሽመጥን በተመለከተ፡ “ማድረግ ካለብን” በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚተላለፉ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን እናጅባለን፤ ነገር ግን ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ይሄዳሉ። ምን እንደሚሆን እናያለን” ብለዋል።
በኢራን ላይ ስለሚፈጸመው ጥቃት፡ “ክፉኛ እንመታቸዋለን” በማለት “እስካሁንም በመጥፎ ሁኔታ አውድመናቸዋል፤መልሰው ለመገንባትም ዓመታትን ይወስድባቸዋል” ሲሉ ገልጸዋል።
ስለ ባሕረ ሰላጤው አጋሮቻቸው፡ ከብዙዎቹ ጋር መነጋገራቸውን እና “ያለው አንድነት ጠንካራ ነው” ብለዋል። አገራቱም እራቸሳውን ለመጠበቅ “ጥሩሥራ እየሠሩ ነው" በማለት አወድሰዋቸዋል።

የአባታቸውን መንበር ለመረከብ የተቃረቡት ቀጣዩ የኢራን መሪ ማን ናቸው?
#ethiopia | የኢራን መንፈሳዊ ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒን ለመተካት በሚደረገው የሥልጣን ሽግግር ሂደት ውስጥ የልጃቸው የሞጅታባ ኻሜኒ ስም በጉልህ እየተነሳ ይገኛል።
በሀገሪቱ ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ መዋቅር ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳላቸው የሚነገርላቸው ሞጅታባ፣ በተለይም አባታቸውን ለመተካት ዋነኛው ዕጩ እንደሆኑ የብዙዎች ግምት ነው።
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በሴፕቴምበር 1969 በሰሜናዊ ምስራቅ ማሽሃድ ከተማ የተወለዱት ሞጅታባ፣ ከአሊ ኻሜኒ ስድስት ልጆች መካከል ሁለተኛው ናቸው።
የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቴህራን በሚገኘው ታዋቂው 'አላቪ' ሃይማኖታዊ ትምህርት ቤት የተከታተሉ ሲሆን፣ ገና በ17 ዓመታቸው በኢራን-ኢራቅ ጦርነት ወቅት በውትድርና ውስጥ ለአጭር ጊዜያት ማገልገላቸው ይነገራል።
ይህ የጦርነት ተሳትፎ ለኢራን አገዛዝ መጠናከርና ለምዕራባውያን ያላቸውን ጠንካራ አቋም ለመቅረጽ ትልቅ ሚና እንደነበረው ይታመናል።
ከጦርነቱ በኋላ በ1999 የሃይማኖት ትምህርታቸውን ለመቀጠል ወደ ሺዓ ሥነ-መለኮት ማዕከል 'ቁም' ያቀኑት ሞጅታባ፣ ምንም እንኳን እስካሁን የሃይማኖት መሪዎች የሚለብሱትን የክብር ልብስ (Turban) ባይለብሱም፣ ከበስተጀርባ በኢራን የደህንነትና የፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ትልቅ ስልጣን እንዳላቸው ይነገራል። አሁን ላይ የኢራን ቀጣይ መሪ ማን ይሆናል? ለሚለው ጥያቄ የብዙዎች አይን በሞጅታባ ላይ አርፏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #bisratfm #ኢራን #ሞጅታባ_ኻሜኒ #አሊ_ኻሜኒ #የፖለቲካ_ዜና #መካከለኛው_ምስራቅ #iran #mojtabakhamenei #news

ዶናልድ ትራምፕ የቀጣዩን የኢራን መሪ ምርጫ ላይ "እጃቸው መግባት እንዳለበት" ገለጹ
#fastmereja I የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀጣዩን የኢራን መሪ በመምረጡ ሂደት ላይ በግል መሳተፍ እንደሚፈልጉ በዛሬው ዕለት ለኤክሲዮስ በሰጡት ቃለ ምልልስ አስታወቁ።
ትራምፕ ከኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ ህልፈት በኋላ፣ አዲሱን የሀገሪቱን መሪ በመሰየሙ ሂደት ላይ እሳቸው በግላቸው መሳተፍ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል።
ትራምፕ የሟቹ መሪ ልጅ የሆኑት ሞጅታባ ኻሜኒ የአባታቸው ተተኪ የመሆን ከፍተኛ ዕድል እንዳላቸው ለኤክሲዮስ አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ ሞጅታባ ኻሜኒ የአባታቸውን ቦታ ተረክበው መሪ መሆናቸው "ተቀባይነት የሌለው" ውጤት እንደሆነም ትራምፕ በዚሁ ቃለ ምልልሳቸው አስገንዝበዋል።
ይህ የትራምፕ አስተያየት አሜሪካ በቀጣይ በኢራን የውስጥ ፖለቲካ እና በመሪዎች ሽግግር ላይ ጠንከር ያለ ተጽዕኖ ለማሳደር ያላትን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ተብሏል።

ከኻሜኒ ቀብር በኋላ ተተኪያቸው ይታወቃል፣ እስራኤልም አዲሱ መሪን ዒላማ እንደምታደርግ ዝታለች
የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ መከናወን የሚጀምር ሲሆን፣ የሚተካቸውም አዲስ መሪ ግብአተ መሪታቸውን ተከትሎ ይፋ እንደሚደረግ የአገሪቱ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።
ምርጫውን የሚያከናውነው ምክር ቤት ጽህፈት ቤቶች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ሲዘገብ፤ እስራኤልም ለደኅንነቷ ስጋት ሆኖ የሚቀጥል መሪ ከተመረጠ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃለች።
የጠቅላይ መሪው የቀብር ሥነ ሥርዓት ሦስት ቀናትን እንደሚወስድ እና ከቀብሩ በኋላ የእስላማዊ ሪፐብሊኩ መሪ የሚሰይሙት መንፈሳዊ እና ፖለቲካዊ ሥልጣን ያላቸው መሪዎች በአካል ተሰብስበው ምርጫውን እንደሚያከናውኑ ፋርስ የተባለው የዜና ወኪል ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።
ምርጫውን የሚያካሂደው ምክር ቤት አባላት ለአሜሪካ እና እስራኤል እንዳይጋለጡ "አስፈላጊ የሆነው የደኅንነት ጥበቃ እርምጃዎች በከፍተኛ ደረጃ መወሰዱን” ዘገባዎች እየጠቆሙ ነው።
ነገር ግን 'ቆም' በምትባለው ከተማ የሚገኘው የከፍተኛ ባለሥልጣናቱ ጉባዔ አባላት ጽህፈት ቤት ማክሰኞ እንዲሁም ቴህራን ውስጥ ስብሰባ የሚያደርጉበት ቦታ ዛሬ በእስራኤል እና በአሜሪካ ጥቃት እንደተፈጸመበት ቢቢሲ ፐርሺያ ዘግቧል።
የአያቶላህ ኻሜኒ ቀብር በትክክል የት እንደሚካሄድ እስካሁን ያልተገለጸ ሲሆን፣ የኢራን መገናኛ ብዙኃን ግን ማሻድ በምትባለው ከተማ ውስጥ በሚገኘው ስምንተኛው የሺዓ ኢማም የእምነት ስፍራ ሊሆን እንደሚችል እየዘገቡ ነው።
የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ሦስተኛው ጠቅላይ መሪ ማን እንደሚሆን እየተጠበቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት ኒው ዮርክ ታይምስ የኢራን ባለሥልጣናትን ጠቅሶ የሟቹ መሪ ልጅ ሞጅታባ ኻሜኒ አዲሱ መሪ እንዲሆን ከስምምነት ላይ መደረሱን እና ይፋ እንደሚደረግ ዘግቧል።
ፋርስ ዜና ወኪል ከኻሜኒ ቀብር በኋላ የመሪው ማንነት ይፋ እንደሚደረግ እና የሹመት ሥነ ሥርዓቱም በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚሆን ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ ለአገራቸው ጠላት የሆነ የትኛውም ተተኪ ቢመጣ ዒላማቸው እንደሚሆን ተናግረዋል።
“እስራኤልን የማጥፋት ዕቅድን የሚቀጥል፣ አሜሪካን ላይ የሚዝት፣ የኢራንን ሕዝብ የሚጨቁን የትኛውም ተተኪ በማያጠራጥር ሁኔታ ለመደምሰስ ዒላማችን ይሆናል” ብለዋል የመከላከያ ሚኒስትሩ።
አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት 21/2018 ዓ.ም. በኢራን ላይ በከፈቱት ጥቃት የአገሪቱን ጠቅላይ መሪ ጨምሮ በርካታ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ተገድለዋል።

አያቶላህ አሊ ኻሜኒ
#ethiopia | የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ መገደላቸውን የኢራን መንግሥት አረጋግጦ 40 የሐዘን ቀናት አወጀ። መሪው እስራኤል እና አሜሪካ ቅዳሜ ዕለት ቴህራን ውስጥ በፈጸሙት ጥቃት መገደላቸውን የአገሪቱ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን አረጋገጡ።
በኢራን ፖለቲካ እና መንፈሳዊ ህይወት ውስጥ ለ37 ዓመታት የመጨረሻውን ቃል ሲናገሩ የቆዩት አያቶላህ ዓሊ ኻሚኒ፣ ዛሬ በታሪክ መዝገብ ውስጥ የሚቀመጥ ትልቅ አሻራ ጥለው አልፈዋል።
"አያ" ማለት ምልክት ወይም አንቀፅ ማለት ሲሆን "አያቶላህ" ማለት ደግሞ "የአላህ ምልክት" ማለት ነው። ይህ ማዕረግ በሺዓ ሙስሊሞች ዘንድ እጅግ የላቀ እውቀትና ስነ-ምግባር ላላቸው መንፈሳዊ መሪዎች የሚሰጥ የክብር ስም ነው።
በወጣትነታቸው የሻህ መሀመድ ሬዛን አገዛዝ በመቃወማቸው ከ6 ጊዜ በላይ ታስረዋል።
በ1979ኙ አብዮት ወቅት በተደረገባቸው የግድያ ሙከራ ቀኝ እጃቸው ጉዳት ደርሶበት እስከ ህይወታቸው ፍፃሜ ድረስ በግራ እጃቸው ብቻ እንዲጠቀሙ ሆኗል።
መጀመሪያ ፕሬዝዳንት፣ በኋላም ከ1989 ጀምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ መንፈሳዊ መሪ በመሆን ኢራንን በኒውክሊየር እና በኢንዱስትሪ ዘርፍ አዘምነዋል።
አያቶላህ ኻሚኒ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሶሪያ፣ የመን፣ ፍልስጤም እና ሩሲያ ጎን በመቆም ጠንካራ የክልላዊ ኃይል ቢገነቡም፣ በሀገር ውስጥ ግን በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በሃሳብ ነፃነት መገደብ በተደጋጋሚ ይተቹ ነበር። ጋዜጠኞችና ፀሐፊዎች መሪውን ተችተዋል በሚል ለእስር መዳረጋቸው የአገዛዛቸው ጥቁር ጥላ ተደርጎ ይነሳል።
አያቶላህ አሊ ኻሜኒ (Ayatollah Ali Khamenei) የዘመናዊቷ ኢራን ተፅዕኖ ፈጣሪ መሪና የሀገሪቱ ከፍተኛ መንፈሳዊ መሪ (Supreme Leader) ናቸው።
አሊ ኻሜኒ ሚያዝያ 19 ቀን 1939 (እ.ኤ.አ) በኢራን የተቀደሰች ከተማ በምትባለው ማሽሃድ ተወለዱ። ቤተሰቦቻቸው እጅግ ሃይማኖተኛና ድሆች ነበሩ።
ገና በለጋ ዕድሜያቸው የሃይማኖት ትምህርት የጀመሩ ሲሆን፣ በቁም (Qom) ከተማ ታዋቂ በሆኑ የሺዓ መሪዎች ዘንድ ተምረዋል።
ከአያቶላህ ኾሜኒ ጋር ያላቸው ግንኙነት፦
የኢራን አብዮት መሪ ከነበሩት አያቶላህ ሩሖላህ ኾሜኒ ጋር የቅርብ ግንኙነት ነበራቸው። በወቅቱ የነበረውን የሻህ መንግሥት በመቃወማቸው በተደጋጋሚ ታስረዋል፣ ተሰደዋል እንዲሁም ተደብድበዋል።
የ1979 አብዮት፦ አብዮቱ ሲፈነዳና የሻህ መንግሥት ሲወድቅ፣ ኻሜኒ የአብዮቱ ምክር ቤት አባል በመሆን ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።
* ፕሬዝዳንትነት (1981-1989)፦ በኢራን-ኢራቅ ጦርነት ወቅት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል። በዚህ ወቅት በደረሰባቸው የግድያ ሙከራ ቀኝ እጃቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ከፍተኛ መሪነት (1989 - አሁን)፦
አያቶላህ ኾሜኒ በ1989 ሲሞቱ፣ አሊ ኻሜኒ የኢራን "ከፍተኛ መሪ" (Supreme Leader) ሆነው ተሾሙ። በኢራን ሕገ-መንግሥት መሠረት ከፍተኛው ስልጣን በእሳቸው እጅ ነው።
የኻሜኒ ርዕዮተ-ዓለምና አቋም
ፀረ-ምዕራባውያን አሜሪካን "ታላቁ ሰይጣን" በማለት ይተቻሉ፤ የምዕራባውያን ባህልና ፖለቲካ በኢራን ላይ ተፅዕኖ እንዳይኖረው በጥብቅ ይከላከላሉ።
ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ (ሊባኖስ፣ ሶሪያ፣ የመንና ኢራቅ) ያላትን ተፅዕኖ ለማስፋት ትልቅ ስራ ሰርተዋል። እንደ ሄዝቦላህ ያሉ ቡድኖች ዋነኛ ደጋፊ ናቸው።
የኢራን የኒውክሊየር ፕሮግራም ለሰላማዊ ዓላማ ነው ቢሉም፣ ከምዕራባውያን ጋር ላለው ፍጥጫ ዋነኛ ምክንያት የእሳቸው ጽኑ አቋም ነው።
አሁን ላይ ዕድሜያቸው የገፋ (86 ዓመት ገደማ) በመሆናቸው፣ ስለ ጤንነታቸውና ስለ ተተኪዎቻቸው ብዙ ግምቶች ይነገራሉ። ሆኖም አሁንም ድረስ የኢራን የጦር ኃይሎች፣ የፍትሕ ሥርዓትና የመንግሥት መዋቅር የመጨረሻ ትዕዛዝ የሚቀበለው ከእሳቸው ነው።
የአያቶላህ አሊ ኻሜኒ ተተኪ ማን ሊሆን ይችላል?
አሊ ኻሜኒ ዕድሜያቸው እየገፋ በመምጣቱ (86 ዓመት)፣ በኢራን ከፍተኛ የፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ተተኪን የመሰየም ጉዳይ እጅግ ሚስጥራዊና አሳሳቢ ሆኗል። ተተኪውን የሚመርጠው "Assembly of Experts" የተሰኘው 88 የሃይማኖት ምሁራን ስብስብ ቢሆንም፣ የሚከተሉት ስሞች በዋነኝነት ይነሳሉ፦
ሞጅታባ ኻሜኒ (Mojtaba Khamenei)፦
የአሊ ኻሜኒ ሁለተኛ ልጅ ናቸው። ምንም እንኳን በይፋ ባይገለጽም፣ ከጀርባ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳላቸውና የሪቮሉሽነሪ ጋርዱን ድጋፍ እንደሚያገኙ ይታመናል። ይሁን እንጂ ስልጣኑ "ቤተሰባዊ" እንዳይመስል ስጋት አለ።
* አሊሬዛ አራፊ (Alireza Arafi)፦ ታዋቂ የሃይማኖት ምሁርና የ"Assembly of Experts" አባል ናቸው። በሃይማኖታዊ መዋቅሩ ውስጥ ተቀባይነት ያላቸው በመሆኑ እንደ ገለልተኛ ተተኪ ሊታዩ ይችላሉ።
መሀመድ ባገር ቃሊባፍ (Mohammad Bagher Ghalibaf)፦
የፓርላማው አፈ ጉባኤና የቀድሞ የጦር አዛዥ ናቸው። የሪቮሉሽነሪ ጋርድ አመራሮች ይበልጥ "ወታደራዊና ተግባራዊ" መሪ ከፈለጉ የእሳቸው ስም ሊነሳ ይችላል።
የኢራን ሪቮሉሽነሪ ጋርድ (IRGC) ምንድነው?
ይህ ድርጅት በኢራን ውስጥ ከወትሮው ጦር ሰራዊት (Army) ጎን ለጎን የሚንቀሳቀስ ነገር ግን እጅግ ኃያል የሆነ የጦር ኃይል ነው።
ዋነኛ አላማው የኢስላማዊ አብዮቱን መርሆዎች መጠበቅና የመንግስቱን ህልውና ማረጋገጥ ነው።
የቁድስ ኃይል (Quds Force) የሪቮሉሽነሪ ጋርድ ክፍል ከሀገር ውጭ ያሉ ምስጢራዊ ስራዎችንና እንደ ሄዝቦላህ፣ ሀማስ እና ሁቲ ያሉ ቡድኖችን የማሰልጠንና የማስታጠቅ ኃላፊነት አለበት።
ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ፦ ሪቮሉሽነሪ ጋርዱ የጦር ኃይል ብቻ አይደለም፤ በኢራን ውስጥ ግዙፍ የግንባታ፣ የነዳጅ እና የኮሙኒኬሽን ኩባንያዎችን ይቆጣጠራል። ይህም በሀገሪቱ ፖለቲካ ላይ የማይናወጥ አቅም ሰጥቶታል።
አሁን ባለው የኢራንና እስራኤል ጦርነት ውስጥ ሪቮሉሽነሪ ጋርዱ ዋነኛ ተዋናይ ነው። እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ስትሰነዝር ኢላማ የምታደርገው የዚህን ኃይል የጦር ሰፈሮችና የሚሳኤል ማከማቻዎችን ነው።
የእስራኤል ጥቃት ኢላማዎች ምን ነበሩ?
የእስራኤል አየር ኃይል በኢራን ላይ የሰነዘረው ጥቃት በሦስት ዋና ዋና ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነበር፡-
* የአየር መከላከያ ሥርዓቶች (S-300)፦
ኢራን ከሩሲያ ያገኘቻቸውን እና ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን ለመጠበቅ የተተከሉ የአየር መከላከያ ራዳሮችን እና የሚሳኤል ባትሪዎችን እስራኤል መጀመሪያ ኢላማ አድርጋለች። ይህን ያደረገችው የኢራንን ሰማይ ለቀጣይ ጥቃቶች ክፍት ለማድረግ ነው።
* የሚሳኤል ማምረቻ ተቋማት፦
በቴህራን አቅራቢያ የሚገኙ እና ለባሊስቲክ ሚሳኤሎች ጠንካራ ነዳጅ (Solid Fuel) የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ተመተዋል። ይህም ኢራን ሚሳኤሎችን በፍጥነት የመተካት አቅሟን ለወራት ወይም ለዓመታት እንደሚያዳክምባት ይገመታል።
* የሪቮሉሽነሪ ጋርድ (IRGC) የጦር ሰፈሮች፦
በኢራቅ እና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኙ የሎጅስቲክስ ማዕከላት ጥቃት ደርሶባቸዋል።
የኢራን ሪቮሉሽነሪ ጋርድ (IRGC) የሰጠው ምላሽ
ጥቃቱን ተከትሎ ከኢራን ከፍተኛ አመራሮች የተሰጡት ምላሾች መጀመሪያ ላይ የጥቃቱን መጠን "ዝቅ አድርጎ የመመልከት" (Downplaying) ዝንባሌ ቢታይባቸውም፣ በኋላ ግን ማስጠንቀቂያዎች እየጠነከሩ መጥተዋል፦
* አያቶላህ አሊ ኻሜኒ፦
"ጥቃቱ ሊጋነንም ሆነ ዝቅ ተደርጎ ሊታይ አይገባም" በማለት፣ ኢራን ብሄራዊ ክብሯን ለመጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ እንደምትወስድ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ገልጸዋል።
ጄነራል ሆሴን ሳላሚ (የIRGC ዋና አዛዥ)፦
እስራኤል ለፈጸመችው "ስህተት" አስደንጋጭ እና የማይታሰብ ዋጋ እንደምትከፍል ዝተዋል። የሪቮሉሽነሪ ጋርድ አመራሮች "True Promise III" (እውነተኛ ቃል ኪዳን 3) በሚል መጠሪያ ሦስተኛ ዙር የሚሳኤል ጥቃት ለመሰንዘር መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
አዲሱ የኃይል ሚዛን (The Red Line)
ይህ ጥቃት በመካከለኛው ምስራቅ ለብዙ ዓመታት የነበረውን "በተኪ መዋጋት" (Proxy War) ደንብ ሰብሮታል። አሁን ሁለቱ ሀገራት በቀጥታ አንዱ በሌላው ምድር ላይ ጥቃት መፈጸም የጀመሩበት አዲስ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን።
የእስራኤል መልዕክት፦ "ኢራን ውስጥ የትኛውንም ቦታ መድረስ እንችላለን፤ የኒውክሊየር እና የነዳጅ ማዕከላትን ደግሞ ለቀጣይ ጥቃት አስቀምጠናል" የሚል ነው።
የኢራን ስጋት፦ ተጨማሪ ጥቃት መሰንዘር እስራኤልን ወደ ኒውክሊየር ተቋማት ጥቃት እንድትሸጋገር ሊገፋፋት ይችላል የሚል ስጋት በቴህራን አለ።
#አያቶላህኻሚኒ #ኢራን #መካከለኛውምስራቅ #ታሪክ #መንፈሳዊመሪ #አብዮት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #alikhamenei #iran #middleeasthistory

Comments