4 days ago
ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን (Leenat Charity Foundation) በአሜሪካ የተመሰረተ እና በኢትዮጵያ በተግባር የእርዳታ ስራዎችን እያከናወነ ያለ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው። እስካሁን በደብረ ብርሃን፣ ሻሸመኔ እና ከሚሴ በመድረስ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ሞዴስ፣ ደብተር እና የትምህርት ቁሳቁሶችን በቀጥታ አድርሰናል። በከሚሴ ብቻ ሶስት የተለያዩ ትምህርት ቤቶችን ደርሰን ድጋፋችንን አቅርበናል።
የህክምና ባለሙያና ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን መስራች የሆኑት የእናትፋንታ አስማማዉ እንደገለጹት፤ የበጎ አድራጎት ቡድኑ በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ባደረገው ጉብኝት ለበርካታ አራሶች የንፅህና መጠበቂያዎችን (ሞዴስ) እና ለህፃናት ደግሞ ዳይፐሮችን ያበረከተ ሲሆን በተጨማሪም ፋውንዴሽኑ ለህፃናትና ለአናቶች የምሳ ግብዣ በማዘጋጀት አብሮነቱን አሳይቷል።
የፋውንዴሽኑ ቦርድና የበጎ አድራጎት ቡድን አባላትን ያሳተፈው ይህ ፕሮግራም፣ ድጋፍ የሚሹ አራሶችንና ህፃናትን ለማገዝ የተደረገ በጎ ተግባር መሆኑ ተገልጿል።
ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን በተለይም በገጠር አካባቢዎች ለሚገኙ ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ሞዴሶችን በማቅረብ፣ የጤና ትምህርት በመስጠትና ከኢንፌክሽን ቁጥጥር ጋር የተያያዙ ግንዛቤዎችን በመፍጠር ረገድ በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ ተመላክቷል።
ለወደፊቱም በገጠር አካባቢዎች የሚገኙና የንፅህና መጠበቂያዎችን ለመግዛት አቅም የሌላቸውን ተማሪዎች በዘላቂነት ለመደገፍ፣ የንፅህና መጠበቂያ ሞዴሶችን እዚሁ አገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ትልቅ ፕሮጀክት ተቀርፆ እየተሰራ እንደሚገኝ መስራቿ ገልጸዋል።
በአሜሪካ የተመሰረተውና በኢትዮጵያ በተግባር የእርዳታ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኘው ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን፤ እስካሁን በደብረ ብርሃን፣ ሻሸመኔ እና ከሚሴ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ሞዴስ፣ ደብተር እና የትምህርት ቁሳቁሶችን በቀጥታ ማድረሱ ታውቋል።
👉 ማገዝ ለምትፈልጉ
⚡️Cash | $Enat16
⚡️PayPal & Zelle | +16144056169
⚡️Abyssinia Bank | 266595832
⚡️Commercial Bank | 1000794295305

ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ለሚገኙ ተማሪዎች፣ አራሶች እና ህፃናት ዘለቄታዊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገለጸ
#fastmereja :-በአሜሪካ የተመሰረተው እና በኢትዮጵያ በተግባር የእርዳታ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኘው ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን (Leenat Charity Foundation)፤ በደብረ ብርሃን፣ ሻሸመኔ እና ከሚሴ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስ)፣ ደብተር እና ልዩ ልዩ የትምህርት ቁሳቁሶችን በቀጥታ ማድረሱን አስታወቀ።
የህክምና ባለሙያ እና የፋውንዴሽኑ መስራች የእናትፋንታ አስማማዉ እንደገለጹት፤ ድርጅቱ በከሚሴ ብቻ በሶስት የተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመገኘት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፣ በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ባደረገው ጉብኝት ደግሞ ለበርካታ አራሶች የንፅህና መጠበቂያዎችን እንዲሁም ለህፃናት ዳይፐር ማበርከቱን ገልጸዋል። በተጨማሪም ለህፃናት እና ለአናቶች የምሳ ግብዣ በማዘጋጀት አብሮነቱን አሳይቷል።
ፋውንዴሽኑ በተለይም በገጠር አካባቢዎች ለሚገኙ ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያዎችን በማቅረብ፣ የጤና ትምህርት እና ከኢንፌክሽን ቁጥጥር ጋር የተያያዙ ግንዛቤዎችን የመፍጠር ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ ተመላክቷል።
በቀጣይም በገጠር አካባቢዎች የሚገኙ እና የንፅህና መጠበቂያዎችን ለመግዛት አቅም የሌላቸውን ተማሪዎች በዘላቂነት ለመደገፍ፣ ሞዴሶችን እዚሁ አገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ትልቅ ፕሮጀክት ተቀርፆ እየተሰራ እንደሚገኝ መስራቿ አብራርተዋል።

30 days ago
ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ የ2019 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የማኅበራዊ ተሳትፎ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ድጋፍ አደርጓል።
ድርጅቱ ድጋፍ ያደረገው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ለሚገኘው የተባበሩት አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው።
ድጋፉም በት/ቤቱ ለሚማሩ 200 ሴት ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የሚሆን የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ቁሳቁስ እንደሆነም ተገልጿል።
በስጦታ ርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኮምፓስ ፕሮፐርቲስ የገበያና ሽያጭ ክፍል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ተኩ "ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ ቃል በገባው መሠረት በዛሬው ዕለት ድጋፉን ያደረገ ሲሆን፣ ወደፊትም ማኅበራዊ ኃላፊነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል" ብለዋል። አክለውም ድርጅታቸው አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለመኖሪያና ለንግድ ቤት ገዢዎች እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ልዩ የበዓል ቅናሽ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።
የወረዳ 03 ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዋኩማ ጎንፋ በበኩላቸው የተደረገውን ድጋፍ አድንቀው፣ ሌሎች ተቋማትም ተመሳሳይ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የትምህርት ቤቱ ም/ርዕሰ መምህር እህቴነሽ ተ/ያሬድ የተደረገውን ደጋፍ በተገቢ መንገድ ለሴት ተማሪዎች እናቀርባለን ብለዋል።
ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ በዘርፉ የካበተ ልምድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያን እና አንቱታን ያተረፉ የቻይና ባለሙያዎችን በማጣመር፣ በጥራት እና በአጭር ጊዜ ግንባታዎችን በማጠናቀቅ በዘርፉ አዲስ መለኪያ ማስቀመጥ የቻለ ተቋም ነው።

1 month ago
የ5ዓመት የፕሮጀክቶች የስምምነት ተፈረመ
በአንድ ልብ ለትውልድ የህፃናት የሴቶች እና የአረጋዊያን መርጃ ድርጅት እና በኦሮሚያ ማረሚያ ተቋማት ኮሚሽን መካከል በሶስት ፕሮጀክቶች ዙሪያ የ5ዓመት የፊርማ ስነ ስራዓት በአዳማ ድሬ 2 ሆቴል ነሃሴ28 ተከናወነ።
በአንድ ልብ ለትውልድ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስራች እና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ማራናታ ተክለሰንበት እንደገለጹት በድርጅታችን ውስጥ ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተድብ ክፍሎችን ካሉበት ችግር ወጥተው ለሃገራቸው ጠጋሚ ዜጋ እንዲሆነ የምንሰራቸው ከ10በላይ ፕሮጀክቶች አሉ ከነዚህ ማሃለ
1.የሻሎም ቤተ መጽሐፍት ፕሮጀክት በ38 ማረሚያ ተቋማት ለስብዕና ግንባታ ትልቅ ድርሻ ያለው ቤተ መጽሐፍትን መክፈት ነው።
2.እኔም ለእህቴ ፕሮጀክት ለ5000 ሴት ተራሚዎች የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ መግዛት ለማይችሉ ጠያቂ ለሌላቸው እህቶቻችን ድጋፍ የሚደረግበት ነው።
3.የህፃናት ፕሮጀክት
ለ1000በማረሚያ ተቋማት ላሉ ህፃናት የፍራሽ ብርድ ልብስ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ። ይህንን ትልቅ ስራ ከዚህ ትልቅ ተቋምጋራ ለመስራት በመፈራረማችን ደስ ብሎናል። እግዚአብሔር ይረዳናል በሚቀጥሉት 5ዓመታት ትውልድን የሚጠቅም ፣የሚለውጥ ስራ እንሰራለን። በዚህ አጋጣሚ የኦሮሚያ ክልል ማረሚያ ተቋማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻፊን እና በስራቸው የሚመሩትን ተቋም ሰራተኞች አመሰግናለው ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል ማረሚያ ተቋማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻፊ በበኩላቸው በአንድ ልብ ለትውልድ ከኛ ተቋም ጋራ ለመስራት ይዞት የመጣው ትልቅ ትርጉም ያለው ስራ ትውልድን ለማነጽ እና ለመርዳት ስፊ ድርሻ አለው። የድርጅቱ መድራች እና ዳይሬክተር የሆኑትን ወ/ሮ ማራናታ ተክለሰንበትን ይህንን ታላቅ ራዕይ ይዘው ወደ ተቋማችን በትልቅ ሃላፊነት ስለመጡ አመሰግናለሁ ብለዋል። በሚቀጥሉት 5ዓመታት በ38ማረሚያ ተቋማት ትልውና ሰፊ ስራ ለመስራት የመግባቢያ ፊራማ በመፈራረማችን ደስ ብሎኛል ብለዋል።

3 months ago
የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ከቀረጥ ነጻ ወይም በአነስተኛ ታክስ እንዲገባ እየሰራ እንደሆነ የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን አስታወቀ
በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) የዋጋ ንረት ለማቃለል ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ፤ እንዲሁም በሐገር ውስጥ ለማምረት የሚያስፈልገው ጥሬ ዕቃ ቀረጥ እንዳይከፈልበት፣ ወይም አነስተኛ ታክስ እንዲጣልበት እንዲሁም በገጠር ለሚኖሩ ሴቶች እና ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች ተደራሽ እንዲሆን፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ እንደሆነ የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን አስታወቋል።
ፌዴሬሽኑ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገልጾ፤ ባለሙያዎችን ያካተተ አደረጃጀት በመፍጠር ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
የፌዴሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ገነት ሥዩም እንዳገለጹት፤ ተቋማቸው በዋጋው ውድነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ተፈራርመዋል። በተጨማሪም ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር እየሰራ እንደሆነ ተገልጿል።
በሚካሄዱ አገራዊ መድረኮች ላይም ችግሩን በማንሳት ሰፊ ውይይት እንዲካሄድበት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
በቀጣይ የምርት ጥራቱን ለማስጠበቅ እና የዋጋ ውድነቱን ለመቀነስ ሴቶች ሀገር ውስጥ በሚመረቱ ምርቶች በቀላሉ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚሰሩ ተገልጿል።
ከውጪ የሚገቡ ምርቶችም በዝቅተኛ ታክስ የሚገቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በጋራ እንደሚሰራበት ተመላክቷል።
ፌዴሬሽኑ በተለይም ሴት ተማሪዎች እና ወጣቶች በንጽህና መጠበቂያ እጦት ምክንያት ከትምህርት ገበታ እንዳይስተጓጎሉ ለማድረግ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ዋና ዳይሬክተሯ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ከውጪ የሚገባ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያን ከታክስ ነጻ በማድረግ በዝቅተኛ ዋጋ ተደራሽ እንዲሆን የሚያስችለው እንቅስቃሴ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቀዳሚ አስተባባሪነት ቢጀመርም እስከ አሁን አልተተገበረም።
በስፍራሽ ደመላሽ

Sponsored by
Surafel
3 months ago
ኢቭ ሳኒተሪ "ጸደይ ሞዴስ" የሴቶች ንፅህና መጠበቂያን አስተዋወቀ
#fastmereja I ኢቭ ሳኒተሪ ፕሮዳክቶች ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከ10 ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ከ50 በላይ ተማሪዎች የአንድ ዓመት የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. በፍሬንድሺፕ ፓርክ አካሂዷል።
ዛሬ በተካሄደው ፕሮግራም ላይ የድርጅቱ አዲስ ምርት የሆነው "ፀደይ ሞዴስ" ያስተዋወቀ ሲሆን "አንድም ተማሪ በንፅህና መጠበቂያ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታዋ መቅረት የለባትም" በሚል ሃሳብ በሴት ተማሪዎች ላይ የሚታየውን የንፅህና መጠበቂያ አቅርቦት ችግር በመቅረፍ በትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ ለማስቻል ያለመ ነው ተብሏል።
ድርጅቱ ከዚህ ቀደምም በከተማዋ ለሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተመሳሳይ የድጋፍ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ ተገልጿል።
ላለፉት 20 ዓመታት በሴቶችና ህፃናት የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች ኢንዱስትሪ ሲንቀሳቀስ የቆየው ኢቭ ሳኒተሪ ፕሮዳክቶች ማኑፋክቸሪንግ፤ በዕለቱ በተካሄደው የጠዋት መርሃ-ግብር የተማሪዎችን ግንዛቤ ለማሳደግ ታዳጊ ሴቶች በወር አበባ ዑደት፣ በንፅህና መጠበቂያ ምርቶች አጠቃቀም፣ በሴቶች ጤና እና ማብቃት ላይ ያተኮሩ ውይይቶች እና ውድድሮችን በማካሄድ የተለያየ የገንዘብ ሽልማት በመስጠት አጠናቋል።

አዲስ አበባ ውስጥ በጣም ደስስ የሚሉኝ ካፌ እና ምግብ ቤቶች..
1,ያጀት ቁጥር ሁለት ከኤድናሞል ወዳታች ስትወርዱ ያለው እና
2,ሶሻ ..ቦሌ ከዲኤች ገዳ ህንፃ በስተቀኝ ስትታጠፉ signature ህንፃ ላይ ያለው
ለምን? ካላችሁኝ የሴቶች መፀዳጃ ቤት ውስጥ Sanitary pads (ሞዴስ) ስለሚያስቀምጡ!
ጎበዞች እንደዚህ ነው ሰርቪስ መሸጥ ማለት ,ትንሽ ነገር ሊመስል ይችላል ግን ማሰባቸው እራሱ ያስመሰግናቸዋል

4 months ago
አገር አቀፍ ፈተና እና የሴቶች #የወርአበባ ንፅህና መጠበቂያ
በወር አበባ ምክንያት #ሴት ተማሪ መሸማቀቅ የለባትም!
#ethiopia | እንደሚታወቀው የሰኔ ወር የ 6ኛ; የ 8 ኛ እና የ 12 ኛ ክፍሎች የአገር አቀፍ እና ክልላዊ ፈተናዎች የሚሰጥበት ወቅት ነው።
ከሰኔ ወርም ቀደም ተብሎ የመንግስትና የግል ት/ቤቶች እና የትምህርት ሚኒስቴር; ቢሮዎችና ፅ/ቤቶች ተማሪዎች በጥሩ ውጤት ፈተናዎቹን እንዲያልፉ በትጋት ተማሪዎቻቸውን ያዘጋጃሉ።
የፈተና ቁሳቁሶች; ጥያቄዎች; የመፈተኛ ት/ቤቶች; ፈታኝ መምህራን እና ሌሎችንም ቀድመው ለማዘጋጀት የሚደረገው ርብርብ የሚደነቅ ነው። ለወላጆችም/ለቤተሰቦችም ልጆቻችንን ለፈተናዎቹ በአግባቡ እንድናዘጋጅ ተደጋጋሚ መልእክቶችና ማስጠንቀቂያዎች ይላኩልናል።
በተለይ ፈተናዎቹ ቀናቸው እየቀረበ ሲመጣ ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ ይዘው መምጣት ያለባቸው እና ይዘው ለመምጣት የሚከለከሉ ቁሳቁሶች ለተማሪዎቹም ተደጋግሞ ይነገራቸዋል ለእኛም ለወላጆች/ቤተሰቦች ማስጠንቀቂያ ይላክልናል።
ተማሪዎቹ በፈተና ቦታው ይዘው መምጣት የሚፈቀድላቸው :-
1)እርሳስ ; ላጲስ; መቅረጫ
2)የት/ቤት መታወቂያ እና admission card #ብቻ ነው።
አንድ ትልቅ ነገር ግን ተረስቷል #ሞዴስ !
እንደ አገር ትልቅ ዝግጅት የምናደርግለት አገር አቀፍ ፈተና ላይ ሴት ተማሪዎች በፈተና ወቅት #የወር አበባ ላይ ከሆኑ የንፅህና መጠበቂያ #ሞዴስ እንደሚያስፈልጋቸው መዘንጋት ማለት የፈተናው ዝግጅት; ሂደት እና አፈፃፀም #በስርአተ -ፆታ እይታ እንዳልተቃኘ ማሳያ ነው።
እንኳን ፈተና ተጨምሮበት ይቅርና ወር አበባ ሴት ታዳጊዎች ላይ ከባድ የአካል #ህመም ; #የሆርሞን መዛባት እና #የስነልቦና ጫና ያሳድርባቸዋል።
ስለዚህ የወር አበባ + ፈተና የትምህርት ዘርፉ እና ት/ቤቶች ለሴት ተማሪዎች የተለየ ትኩረት እንዲሰጡ ግድ የሚላቸው ጉዳይ ነው።
ፈተና እየተፈተኑ ድንገት የወር አበባቸው የሚመጣባቸው እና የወር አበባ የሚበዛባቸው /heavy flow period / ሴት ተማሪዎች ቶሎ #ምዴስ መቀየር ወይም መጠቀም ሰላለባቸው በፈተና ወቅት ሞዴስ ይዘው እንዲገቡ ባልተፈቀደበት ሁኔታ ሴት ተማሪዎቹ ከአሁን አሁን ልብሴ ተበላሸ ብለው #ሲሳቀቁ ለፈተናው የሚሰጡት #ትኩረት ይጎዳል ።በዚህም የተነሳ ውጤታቸው ላይ #አሉታዊ ተፅእኖ ያመጣል።
ታዲያ የፈተናው ጣቢያዎች ለሴት ተማሪዎች በመፈተኛ ክፍሎች ውስጥ የድንገተኛ ግዜ #ሞዴስ /emergency sanitary pad / ሊያስቀምጡ ይገባል። አለበለዚያ ፈተናው ለሴት ተማሪዎች #ኢፍትሀዊ ይሆናል።
አንዲትም #ሴት ተማሪ #በተፈጥሮ ምክንያት #ከወንድ ተማሪዎች ወደኋላ መቅረት የለባትም!
የህግ ባለሙያ ሜሮን አራጋው

7 months ago
"በሞዴስ" ውስጥ የተደበቀው ኮኬይን፦ ኡጋንዳዊቷ ተጠርጣሪ በቦሌ ተያዘች
በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 500 ግራም ኮኬይን በረቀቀ መንገድ ደብቃ ለማለፍ የሞከረች ሙኪሳ ስቴላ የተባለች ኡጋንዳዊት በቁጥጥር ስር መዋሏን በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ገልፇል።
ተጠርጣሪዋ እጹን በሴቶች ንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ውስጥ ደብቃ ከማላዊ ወደ ፊሊፒንስ በመጓዝ ላይ ሳለች፣ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጥብቅ ፍተሻ ሊያዝ ችሏል።
ተጠርጣሪዋ ለተጨማሪ ምርመራ ለፌደራል ፖሊስ ተላልፋ መሰጠቷን አገልግሎቱ ገልፇል።
seledadotio

ኮኬይን በረረቀ መንገድ ደብቃ ለማስተላለፍ የሞከረች ተጠርጣሪ በቦሌ ዓለም- አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር ዋለች
ሙኪሳ ስቴላ የተባለች ኡጋንዳዊት ግለሰብ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ ውስጥ በረቀቀ መልኩ 500 ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ ዕጽ ደብቃ ለማስተላለፍ ስትሞክር በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡
ከማላዊ ዋና ከተማ ሊሎንጌ ተነስቶ ፊሊፒንስ ማኒላ መዳረሻው የሆነው አውሮፕላን በቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ትራንዚት ሲያደርግ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአቪዬሽን ደኅንነት ባለሙያዎች ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በዘመናዊ መሣሪያዎች ባከናወኑት ጥብቅ ፍተሻና ቁጥጥር ኮኬይኑ ከእነተጠርጣሪዋ መያዙን መረጃው ጠቁሟል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አደገኛ ዕጽዋት ቁጥጥር እና ወንጀል ምርመራ ዘርፍ አባላትም ለተጨማሪ ምርመራ እንደተረከቡት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል፡፡
በተጨማሪም በተከታታይ ቀናት ከለንደን በአዲስ አበባ በኩል ወደ ኬንያ በሚጓዝ አውሮፕላን 86 ኪሎ ግራም ደረቅ ጫት እንዲሁም ከኢጣሊያ ሚላን በቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ ኮንጎ ኪንሻሳ በሚበር አውሮፕላን 17 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም ጫት በሕገ-ወጥ መንገድ ለማዘዋወር ሙከራ ሲደረግ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአቪዬሽን ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር መዋሉም ተመላክቷል፡፡
በያዝነው ሳምንት መጀመሪያም ከ 4 ኪሎ ግራም በላይ ኮኬይን በቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር መዋሉን ያስታወሰው መረጃው፤ ኢትዮጵያ የብዙ አፍሪካ ሀገራት መተላለፊያ ከመሆኗም ባሻገር በመካከለኛው ምሥራቅ የተፈጠረውን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ ተመራጭ የትራንዚት ማዕከልነቷ በመጠናከሩ ከሰላማዊ ተጓዦች ጋር ተቀላቅለው በሕገ-ወጥ ተግባራት የሚሰማሩ በመኖራቸው እንደ ወትሮው ሁሉ በከፍተኛ ዝግጁነት ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ ያደረገውን ሪፎርም ተከትሎ የላቁ ቴክኖሎጂዎች መጠቀም መቻሉ፤ የሰው ኃይል አቅም መገንባቱ እንዲሁም ግልጽ አሠራር መዘርጋቱ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚተላለፉ አደንዛዥ ዕጾችና ሌሎችንም ሕገ-ወጥ ቁሶች በከፍተኛ ደረጃ ለመቆጣጠር ማስቻሉን ያመለከተው መረጃው፤ በቀጣይም በተዘረጋው የአሠራር ስርዓት መሰረት የሚወሰዱ ተመሳሳይ የቁጥጥር እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጧል፡፡
#ኢዜአ

11 months ago
🎈 መልካም ልደት ለኔ ህዳር 2 🎂🎂
''በልደቴ አንድ ሞዴስ ለእህቴ'' 🎈🎈🎈
#ethiopia | በዕድሜ ላይ ዕድሜን ጨምሮ አመታትን በምህረቱ ያሻገረኝ አምላክ ምስጋና ይግባዉ እና በቅርቡ ትንሽ ለየት ባለሁኔታ ከእናንተ ጋር ልደቴን ላከብር አቅጃለሁ።
በሀዋሳ ማረሚያ ተቋም ከ100 በላይ ሴት ታራሚዎች በህግ ጥላ ዉስጥ ይገኛሉ። እነዚህም እህቶቼ የተፈጥሮ ግዴታ ነዉና በከፍተኛ ሁኔታ የሞዴስ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቆሶች እየቸገራቸዉ ይገኛል ።
ስለሆነም ''በልደቴ አንድ ሞዴስ ለእህቴ'' በሚል ቻሌንጅ ጓደኞቼ ለልደቴ ልትሰጡኝ ያሰባችሁትን ስጦታ በሞዴስ ቀይራችሁ እንድትሰጡኝ እና በዕለቱም ማለትም #ህዳር 2/2018 ዓ.ም በጋራ ሆነን በማረሚያ ተገኝተን እህቶቻችንን እንድንደግፋቸዉ በታላቅ አክብሮትና ፍቅር እጠይቃለሁ ።
የንፅሕና መጠበቂያዎችን በዓይነት ባህል አደራሽ ክፍለከተማ የወጣቶች ማዕከል በመገኘት ለበጎ ልቦች በጎ አድራጎት ማህበር የምናሰባስብ ስለሆነ እዚያ ማምጣት ይችላሉ።
ወይንም ያሉበት ቦታ ድረስ መጥተን እንረከባለን።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር
+251-902-917695 ይደዉሉ።
መልካም ልደት ለኔ ፤ ( ቤቲ )
''በልደቴ አንድ ሞዴስ ለእህቴ''

Comments