1 month ago
ኢኮኖሚያዊ ነፃነት እና ዘላቂ ልማት
ክፍል ፮
(የመጨረሻ ክፍል)
#ethiopia | በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፣ በምሥራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም፣ መንፈሳዊ አገልግሎቱን ከማስፋፋት ጎን ለጎን የራሱንና የአካባቢውን ማኅበረሰብ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሕይወት በዘላቂነት የሚቀይሩ ስትራቴጂካዊ የልማት ሥራዎችን በስፋት በማከናወን ላይ ይገኛል።
"ኢኮኖሚያዊ ነፃነት እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ተቋም የመሠረት ያህል አስፈላጊ ነው" በሚለው መርሕ መሠረት፣ ገዳሙ በዙይ ሐሙሲት ከተማ የጀመራቸው የንግድና የልማት እንቅስቃሴዎች በገንዘብ ማግኘት ላይ ብቻ የተወሰኑ አይደሉም። ይልቁንም በማኅበረሰቡና በገበያው ላይ ቀጥተኛና አዎንታዊ ተፅዕኖ የመፍጠር ዓላማን ሰንቀዋል።
ገዳሙ በዙይ ሐሙሲት ከተማ ባቋቋማቸው ሦስት ዋና ዋና ሱቆች (የሸቀጣ ሸቀጥ የጅምላና ችርቻሮ፣ የነዋያተ ቅዱሳን መሸጫ፣ እንዲሁም የእህል ሚዛንና መጋዘን) አማካኝነት የአካባቢውን የሸቀጥ ዋጋ በማረጋጋት ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ከዚህ ቀደም የትራንስፖርት መንገድ ሲዘጋ በደላሎችና በቸርቻሪዎች ምክንያት አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ይደረግበት የነበረውን አሠራር በመቀየር እንደ ዘይት፣ ስኳር፣ ፊኖ ዱቄትና ጨው ያሉ መሠረታዊ የሸቀጥ ምርቶች ዋጋ በገዳሙ ፍትሐዊ ተመን ወጥቶለት እንዲወሰን አድርጓል።
ገዳሙ ባስቀመጠው ፍትሐዊ ዋጋ መሠረት የአካባቢው ነጋዴዎችም ዋጋቸውን ለማስተካከል ተገደዋል።
እነዚህ ሱቆች እንደ አርባያ፣ ጎሃላ፣ ሐሙሲት፣ ጣይመን፣ 40 ጠጓርና ቆርቆሮ ያሉ አካባቢዎችን አልፈው እስከ ሰቆጣ ድንበር ድረስ ምርቶችን የሚያከፋፍል ዘመናዊና የተደራጀ አሠራር አላቸው።
ገዳሙ የሚያከናውናቸው ሥራዎች በሙሉ የላቀ የፋይናንስ አያያዝና የቁጥጥር ሥርዓት የተበጀላቸው ናቸው። ለተሳታፊ አባቶችና መነኮሳት የመሠረታዊ አካውንቲንግና የሂሳብ አያያዝ ሥልጠናዎች የተሰጡ ሲሆን፣ የየዕለት ሽያጮች በደብተርና በዘመናዊ ካሽ ቦክስ አማካኝነት ይመዘገባሉ። እንዲሁም የሂሳብ እንቅስቃሴው በልዩ የቁጥጥርና ኦዲት ዲፓርትመንት ይከታተላል።
በተጨማሪም የገዳሙን የፋይናንስ አቅም ከዋጋ ንረት ለመጠበቅ ሲባል፣ በባንክ የሚቀመጠውን ገንዘብ በውስጣዊ አሠራር በማንቀሳቀስ ምርቶች ላይ ማዋል ተችሏል።
በገዳሙ የነዋያተ ቅዱሳን መሸጫ ሱቅ ውስጥ የሚቀርቡት ምርቶች (እንደ ጧፍ፣ ዘቢብ፣ ፎጣዎችና መጻሕፍት ያሉ) መንፈሳዊ አገልግሎትን ለማስፋፋትና ሕገ-ገዳሙን በጠበቀ መልኩ የተደራጁ ናቸው። እያንዳንዱ የገዳሙ ምርት ልዩ ታግ እና ኪው አር ኮድ (QR Code) ያለው ሲሆን፣ ይህም "ገዳማዊ ልማት ለቤተ ክርስቲያን ትሩፋት" የሚለውን እሳቤ በማጎልበት ረጅም ርቀት የሚሄድ ማኅበረሰብና ኔትወርክ ለመገንባት ታስቦ የተሠራ ነው።
በዙይ ሐሙሲት ከመንግሥት በተገዛ 800 ካሬ ሜትር አካባቢ ቦታ ላይ የG+3 ሕንፃ ዲዛይን (አርክቴክቸራል፣ ስትራክቸራል፣ ሳኒተሪና ሜካኒካል) ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል። የቦታው የመሬት ጠረጋ እና ኤክስካቬሽን ሥራዎች የተጠናቀቁ ሲሆን፣ የብረት፣ ሲሚንቶ፣ አሸዋና ጠጠር ግብአቶችን በማስገባት የግራውንዱ ግንባታ በጥር 2019 ዓ.ም. ተጀምሮ እስከ ጥር 2020 ዓ.ም. ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ታቅዷል። የዚሁ ማዕከል ግንባታ ሲጠናቀቅ የሸቀጣ ሸቀጥና የነዋያተ ቅዱሳን ሱቆች፣ የእህል መጋዘን፣ ዘመናዊ ዌር ሀውስ፣ እንዲሁም ለአካባቢው ማኅበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ዳቦ የሚያቀርብ ማሽንና የዳቦ ማምረቻ ይኖረዋል።
ከዚሁ ጎን ለጎን ገዳሙ ከዙይ ሐሙሲት ከተማ ባሻገር በአዲስ አበባ ከተማ መካኒሳ አካባቢ ሱቅ በመከራየት የገዳሙን ምርቶች የሚሸጥበት ማዕከል ከፍቷል። በአዲስ አበባ ተጨማሪ ሱቆችን ከመክፈት አልፎ በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ለማስፋፋት አቅዷል።
የኢኮኖሚና ፖለቲካ ማዕከልነትን በመጠቀም ከፍተኛ ተፅዕኖ ለመፍጠርና የገዳሙን የተዘጋጁ የታሸጉ የምግብ ምርቶች (እሴት የተጨመረባቸው/ቫልዩ አድ የተደረጉ የጤፍና ሌሎች ምርቶችን) ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችሉ ማሽነሪዎች ከውጭ ሀገር እንዲገቡ ታዟል። እስከ 2020 ዓ.ም. አጋማሽ ድረስም እነዚህ ምርቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ውጭ ገበያ መግባት ይጀምራሉ።
በአጠቃላይ ገዳሙ በባለሙያዎችና በሠለጠነ የሰው ኃይል የተደገፈ አሠራር በመዘርጋት፣ መንፈሳዊ ተቋማት በራሳቸው ኢኮኖሚ ተደግፈው ማኅበረሰባዊና ሀገራዊ ተፅዕኖ መፍጠር እንደሚችሉ በተግባር እያሳየ ይገኛል።
ምስጋና
ይህንን ዘገባና ሰነድ ለማዘጋጀት እንዲያስችል የላቀ ትብብር ላደረጉ አካላት በሙሉ፤ በተለይም በትሕትና ለተቀበሉን ገዳማውያን መነኮሳት፣ ገዳሙንና የገዳሙን የልማት ሥራዎች ላስጎበኙን አባቶች፣ ለጋዜጠኛ ሙሉቀን አሰፋ፣
ለጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ፣ ከጎንደር አዞዞ ኤርፖርት ወደ ገዳሙ ላደረሱን ሾፌሮቻችን፣ እንዲሁም በጉዞ ላይ ለነበሩ የሚዲያ ባለሙያዎች ጌጡ ተመስገን ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽንስ የከበረ ምስጋናውን ያቀርባል።
ተጠናቀቀ
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#የሙትአንሳማርቅዱስሚካኤልገዳም
#ማዕከላዊጎንደር #ምስራቅበለሳ #getu
#getutemesgen #ጌጡ #eastbelesa
#muteansamarstmichaelmonastery
#centralgondar #ethiopianorthodoxchurch

2 months ago
የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የህንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ
♦️የህንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ 35 ሚሊየን ብር ይፈጃል
♦️ በቀጣይ ሁለት አመት ባልሞላ ውስጥ ይጠናቀቃል
ክፍል ፬
#ethiopia| በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፣ በምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የመጀመሪያና ሁለተኛው የልማት ምዕራፉን አስመልክቶ ይዘንላችሁ የምንቀርበው ተከታታይ ዘገባ አራተኛው ክፍል ደርሷል።
በያዝነው ሕዳር 2018 ዓ.ም. በይፋ የተጀመረው እና በገዳሙ ከእናቶች በዓት ቀጥሎ እየተሰሩ ካሉ ግንባታዎች መካከል የህንጻ ቤተክርስቲያንና የሊቃነ ጳጳሳት ማረፊያ ግንባታዎችን ወቅታዊ የግንባታ እንቅስቃሴ በመጠኑ እንዳስሳለን።
ከምስራቅ በለሳ ወረዳ ዋና ከተማ ከሆነችው ጎሃላ ወደ ዙይ ሐሙሲት በሚወስደው ዋና መንገድ 10 ኪሎ ሜትር እንደተጓዙ በስተቀኝ ታጥፎ ወደ ገዳሙ የሚወስደው የ8 ኪሎ ሜትር መንገድ ቀደም ሲል ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ጭራሽ የማይመች ነበረ። ይህንን ችግር ለመቀየርና መንገዱን 6 ሜትር ያህል በማስፋት ለተሽከርካሪ ክፍት ለማድረግ የህብረተሰቡን ማሳመንና የወሰን ማስከበር ስራዎችን ጨምሮ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል።
የአማራ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ለመንገድ ስራ የሚያገለግሉትን ማሽነሪዎች በነጻ በማቅረብ ፣ እንዲሁም ገዳሙ አስፈላጊውን የነዳጅ፣ የሰራተኞች አበልና የማቴሪያል ማምረት ወጪዎችን በመሸፈን የውሃ ማፍሰሻ ቧንቧዎችን፣ የጎርፍ መከላከያ ድጋፍ ግንቦችንና የጎንዮሽ ማጠናከሪያ ስራዎችን በተሳካ ሁኔታ ማከናወን ተችሏል።
የህንጻ ቤተክርስቲያኑን ግንባታ በተመለከተ ደግሞ ትልቁን ድርሻ የሚይዘውና እጅግ አድካሚው የመሬት መሙላትና የመሰረት ስራ በስኬት ተጠናቋል። ከ900 ሜትር ኪዩብ በላይ የሚሆን መሬት ለመሙላት ከ80 በላይ የከባድ መኪና ጭነት የሚያስፈልግ ቢሆንም፣ በወቅቱ በነበረው የነዳጅ እጥረትና የመለዋወጫ እቃዎች ዋጋ ውድነት ምክንያት መኪኖች ማንቀሳቀስ አልተቻለም ነበር።
ነገር ግን ሙሉ በሙሉ በሰው ኃይል በተደረገው አደካሚ ርብርብ የመሬት መሙላት ስራው ተጠናቆ፣ ለኮለን ለማቆም ቦታው በደንብ መዘጋጀቱን ተመልክተናል።
1,300 ካሬ ሜትር ስፋት ያለውና አጠቃላይ ወጪው 35 ሚሊየን ብር አካባቢ የሚገመተው ይህ ህንጻ ቤተክርስቲያን፣ ለአካባቢው ማህበረሰብ፣ ለመነኮሳቱ እና ለሱባኤ የሚመጡ ምዕመናንን ሙሉ በሙሉ ማስተናገድ የሚያስችል ነው።
በሌላ በኩል ከቤተክርስቲያኑ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘው የሊቃነ ጳጳሳትና የእንግዶች ማረፊያ ግንባታም በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል።
አምስት ዘመናዊ ክፍሎችን የያዘው ይህ ማረፊያ፣ ለሊቀ ጳጳሱ፣ ለአበ ምኔቱና ለእንግዶች የሚሆኑ የየራሳቸው ሳሎንና መጸዳጃ ቤት ያላቸው ክፍሎችን ያካተተ ነው። የህንፃው ዋና መሠረት ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ግንባታው ለጣራ ዝግጁ ሆኖ በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ በትጋት እየተሰራ ይገኛል።
የብሎኬት ማመርቻ፣ የእንጨት መሰንጠቂያና ልዩ ልዩ ማሽኖችን እዚያው በመትከልና መነኮሳቱን በማሰልጠን፣ የብረትና የእንጨት ስራዎች እዚያው እንዲከናወኑ ተደርጓል። በተጨማሪም የቤተክርስቲያኑን ምንጣፍ፣ መንበር፣ ቆርቆሮና ሌሎች የግንባታ ቁሳቁሶችን ቀድሞ በመግዛትና በማከማቸት የግንባታ ወጪውንና የዋጋ ግሽበቱን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ተችሏል።
ቀደምት ክፍሎችን ለማንበብ ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ
ክፍል ፩
https://www.facebook.com/s...
ክፍል ፪
https://www.facebook.com/s...
ክፍል ፫
https://www.facebook.com/s...
አልተጠናቀቀም .....ይቀጥላል......

የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል ገዳም ድንቅ የልማት ጉዞ
📌 የአባቶች በዓት ግንባታ ተጠናቆ ወደ አገልግሎት ለመግባት ምን ቀረው?
ክፍል ፫
#ethiopia | በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት በምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ታሪካዊው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም፣ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ብቻ ሳይሆን ራሱን በራሱ ለመቻልና ለቀጣዩ ትውልድ የሚመጥን ዘመናዊ መዋቅር ለመዘርጋት ሰፊ የልማት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል። ገዳሙ አጠቃላይ ሶስት ዋና ዋና ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በሁለተኛው ዙር የአባቶችን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችሉ የግንባታ ስራዎች በተጠናከረ ሁኔታ እየተከናወኑ ይገኛሉ።
ባለፈው በክፍል ሁለት የእናቶችን በዓት የደረሰበትን የግንባታ ሂደት የተወሰነውን ማስነበባችን የሚታወስ ነው በዛሬው ክፍል ሶስት በገዳሙ እየተገነባ የሚገኘውን የአባቶች በዓት (ማረፊያ) ያለበትን ወቅታዊ ቁመና፣ የተከናወኑ ስራዎችን እና ወደፊት የሚጠብቁትን ተግባራት እናያለን።
በገዳማዊ ህይወት ውስጥ ለአባቶችም ሆነ ለእናት መነኮሳት ምቹና የተረጋጋ የመኖሪያ ከባቢ መፍጠር መሰረታዊ ጉዳይ ነው። በገዳሙ ሁለተኛ ዙር ግንባታ ውስጥ ትኩረት የተደረገበት ይሄው የአባቶች በዓት ግንባታ፣ አሁን ላይ አብዛኛው መዋቅራዊ አካሉ ተጠናቆ የማጠናቀቂያ ስራ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ አጠቃላይ ዲዛይኑም የገዳሙን ስነ-ስርዓትና ጥንታዊ የህንጻ ጥበብ ባገናዘበ መልኩ የተቃኘ ነው።
ብዙዎች ግንባታው ሲጀመር "ለምን ቅድሚያ ለእናት መነኮሳት ተሰጠ?" የሚል ጥያቄ ያነሱ ነበር፤ ሆኖም ለዚህ ምክንያቱ የቤተክርስቲያን አባቶች በተፈጥሮ እና በባህሪ ወንድ ልጅን እንደ አቅራቢ፣ ጠባቂና መጋቢ አድርገው ስለሚመለከቱትና እናቶች ደግሞ በተፈጥሯቸው ለተለያዩ ማህበራዊና አካባቢያዊ ተጋላጭነቶች የቀረቡ በመሆናቸው ነው። እናቶች መነኮሳት ከምንኩስና ስራቸው በተጨማሪ የተፈጥሮ ኃላፊነቶች ስላለባቸው ቅድሚያ ተሰጥቷቸው በዓታቸው ተጠናቋል፤ አሁን ደግሞ ከዚያ በተቀሰመው መልካም ተሞክሮ የአባቶች በዓት ግንባታ እጅግ በተዋበና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
♦️ የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች
እስካሁን ባለው ሂደት የአባቶች በዓት እያንዳንዱ ክፍል ባለ 12 ካሬ ሜትር ሆኖ አራት መነኮሳትን በነጻነት ለማስተናገድ በሚያስችል ስልታዊ አደረጃጀት ተገንብቷል። ከተለያዩ ገዳማት አድባራት ለልምድ ልውውጥና ለትውውቅ የሚመጡ እንግዶችን በክብር ለመቀበል ይረዳ ዘንድ፣ በማዕከል ላይ የሚገኘው አንደኛው ክፍል ብቻ ባለ 18 ካሬ ሜትር ሆኖ እንዲሰራ ተደርጓል። ይህ ክፍል ለተራ እንግዳ ሳይሆን ለገዳማውያን የእንግዳ መነኮሳት ማረፊያ ተብሎ የተለየ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የህንጻዎቹ የጣራ ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል።
ከዚህ ጎን ለጎን ለአባቶች ንጽህናና ጤና አጠባበቅ የሚያገለግሉ ዘመናዊ መጸዳጃ ቤቶችና የሻወር ክፍሎች ግንባታም ተጠናቆ መገልገያ እቃዎቻቸው በሙሉ ተገዝተው መጋዘን የገቡ ሲሆን፣ አሁን ላይ የመገጣጠም ስራዎች ብቻ ነው የቀሩት።
በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት የተገነቡት ክፍሎች እስከ 64 የሚደርሱ አባቶችን ማስተናገድ የሚችሉ በመሆናቸው አሁን ላለው የመነኮሳት ቁጥር የአባቶች በዓት ሙሉ በሙሉ በቂ ሆኖ ተገኝቷል።
በዚህ ዙር ከተከናወኑት ስራዎች መካከል ሌላው የማምረቻ ሼድ ወይም የገዳሙ የቴክኒክና ምህንድስና ዲፓርትመንት ማዕከል ግንባታ ነው።
ከከተማ ርቆ በሚገኘው በዚህ በረሃ ውስጥ የሚሰበሩና የሚበላሹ በሮችንና የብረት መዋቅሮችን ለመጠገን ወደ ከተማ መመላለስ ከፍተኛ ወጪ ስለሚያስከትል፣ አባቶች ራሳቸው ስኳድራ መለካት፣ መቁረጥና መበየድ እንዲችሉ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል። ቀደም ሲል የሚመጡ ባለሙያዎች የአካባቢው የአየር ንብረትና ለምግብ ሁኔታ የማይመቹ ከመሆናቸውም በላይ ተጨማሪ ወጪ ይጠይቁ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን ገዳሙ በገዛ አቅሙ የእንጨትና የብረት ውጤቶችን ማምረት የሚያስችልበትን ይህንን ሼድ አጠናቆ ማሽነሪዎቹን በሙሉ አስገብቷል።
በተጨማሪም አጋፔ ማዕድ ወይም መነኮሳቱ በጋራ ጸሎት አድርገው፣ ቡራኬ ይዘው ማዕድ የሚቀምሱበት ታላቅ አዳራሽ ግንባታ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታውን ጨምሮ በአብዛኛው አልቋል።
የሊቃውንት ማደሪያ ተብለው የተለዩት ዘጠኝ ክፍሎችም እንዲሁ ግንባታቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በቤተክርስቲያን የስልጣን እርከንና ስርአት መሰረት ካህናቱና ዲያቆናቱ በተለየ መልኩ እንዲያርፉበትና ምልከታቸው በቀጥታ ወደ ቤተክርስቲያኑ እንዲሆን ተደርገው በከፍታ ቦታ ላይ ተገንብተዋል።
♦️ ያጋጠሙ ፈተናዎች
ግንባታው በተወሰነ መልኩ የጊዜ መጓተት ያሳየው በሀገሪቱ ባለው አጠቃላይ የሲሚንቶ ምርትና አቅርቦት እጥረት ምክንያት ሲሆን፣ ይህንን ክፍተት ለመሙላት የገዳሙ አስተዳደር ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሲሚንቶ በስፋት ወደ ገዳሙ ማስገባት የሚጀመር ሲሆን፣ ግንባታው መሰረቱና መዋቅሩ አስቀድሞ ያለቀ ስለሆነ የልስን ስራው ብዙ ጊዜ የሚወስድ አይሆንም። የልስን ስራው በከፍተኛ ፍጥነት ተጠናቆ ባለሙያዎች አስቀድመው ወደተዘጋጁበት የቻክ (የጂብሰም) ስራ በቀጥታ ይሸጋገራሉ።
ይህ የጂብሰም ስራ እንደተጠናቀቀ የቀሩት የቀለም ስራዎችና የውስጥ ምንጣፎችን የማንጠፍ ስራዎች በፍጥነት የሚከናወኑ ይሆናል። ለክፍሎቹ የሚያስፈልጉ ምንጣፎች፣ መጽሐፍ ቅዱሶችና ዳዊቶች በሙሉ ቀደም ብለው ተገዝተው የገቡ በመሆናቸው፣ እነዚህ የማጠናቀቂያ ስራዎች ተጠናቀው ህንጻዎቹን ወደ አገልግሎት ማስገባት ብቻ ነው የሚጠበቀው።
ይህ ተግባር ከአካባቢው ጥበቃና ውበት ጋር አብሮ የሚሄድ በመሆኑ፣ ክፍሎቹ ሲጠናቀቁ ዙሪያቸውን በችግኞችና በአጸዶች የመሸፈንና የማስዋብ ስራ በእናት በአባቶች
መነኮሳትና የጋራ ተሳትፎ በስፋት ይከናወናል።
♦️ በቀጣይ በአባቶች በዓት የሚሰሩ ታላላቅ እቅዶች
ገዳሙ በአሁኑ ወቅት ከአንድ መቶ በላይ መነኮሳትን የያዘ በመሆኑ፣ ወደፊት ለሚመጡት ተጨማሪ መነኮሳትና የአብነት ተማሪዎች የሚሆን የመኖሪያ ቤት መስራት የሚቻለው ገዳሙ የኢኮኖሚ ነጻነቱን ሲያረጋግጥ ብቻ ነው። ስለሆነም ወደፊት የሚመጡ መነኮሳት በዚህ በማምረቻ ሼድና በተዘረጉት የልማት ማሽነሪዎች ተጠቅመው በራሳቸው አቅም ተጨማሪ በዓታትን እንዲገነቡ ይደረጋል። ይኸውም ዘመኑን የዋጀና ለቀጣዩን ትውልድ የሚሆን ጠንካራ የልማት መሰረት ለመጣል ታስቦ የተዘጋጀ ስትራቴጂ ነው።
ሁሉም ፕሮጀክቶች የሚከናወኑት በእኩል ደረጃ ሲሆን፣ አላማው ቤተክርስቲያኑን ብቻውን መጨረስ ሳይሆን የአባቶችን መረጋጋትና የገዳሙን የውስጥ ኢኮኖሚ አብሮ ማሳደግ ነው። አባቶች በዓት አጥተው በየበረሃው እንዳይበተኑና የካህናት ደሞዝ፣ የዕጣን፣ የጧፍና የዘቢብ ወጪዎችን በራስ አቅም ለመሸፈን እነዚህ የልማት ፕሮጀክቶች ወደፊትም በስፋት ይቀጥላሉ። ገዳሙ እንደ ከተማ አድባራት ከምዕመናን ሙዳየ ምጽዋትና ሕዝባዊ የገንዘብ ማሰባሰብ ብቻ የሚተዳደር ባለመሆኑ፣ ራሱን እንዲችል ማድረግ የወደፊቱ ትልቁ ግብ ነው።
በተጨማሪም በአባቶች በዓት ዙሪያ የሚገኘውን ገደላማ ቦታ ለማቋረጥና መነኮሳቱ እንዲሁም ቀላል እንስሳት በቀላሉ ከቦታ ቦታ እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ፣ በብረት የሚሰራ ዘመናዊ ተንጠልጣይ ድልድይ የመገንባት ስራ ወደፊት የሚሰራ ይሆናል።
ቀደምት ክፍሎችን ለማንበብ ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ
ክፍል ፩
https://www.facebook.com/s...
ክፍል ፪
https://www.facebook.com/s...
ገና በቀጣይ ቦታው ድረስ ሂደን የተመለከትነውን የህንጻ ቤተክርስቲያኑ ግንባታ ከምን እንደደረሰ ፣ በገደሙ በቅርበት በሚገኘው ዙ ሐሙሲት ከተማ ትኩረቱን ትምህርት እና ጤና ላይ አድርጎ በግንባታ ላይ ስለሚገኘው ግዙፍ ኘሮጀክት የምንነግራችሁ ይሆናል።

Comments