16 days ago
#መቼም_የማይረሱ_የምድራችን_በረከት_የሆኑ_ቤተሰቦቻችን
* ሰውን በሕይወት እያለ ማመስገን ይለመድ።
#ethiopia | ሆሳዕና ፎቶ እና ቪድዮ ፕሮዳክሽን — ኤልያስ እና ቅድስትን ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ጀምሮ ነው የማውቃቸው።
የሀድያ እና የከምባታ መዝሙሮችን በቪድዮ ማግኘት የጀመርነውም በዚህ ቤተሰብ አማካይነት ነው። መዝሙሮቻችን በዓለም እንዲሰሙ እግዚአብሔር የተጠቀመባቸው፣ የብዙዎች ድካምና ላብ በኋላ ዛሬ የምናየውን ውጤት እንዲመጣ ያደረጉ ባለውለታዎቻችን ናቸው።
ከአዲስ አበባ ተነስተው እስከ ገጠሩ ድረስ፣ ውስጥ ውስጡን በመግባት፣ እኛ የበላነውን በልተው፣ አብረውን በአዋራ፣ በዝናብና በጭቃ ተጓዝተው፣ ብዙ መዝሙሮችን በጥራት ለመቅረጽ እጅግ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል።
ዛሬ በዙሪያችን ለምናየው ትልቅ ለውጥም ጉልህ ሚና የተጫወቱ ተወዳጅ ቤተሰቦቻችን ናቸው።
ዛሬም በፎቶና በቪድዮ ሥራ ትልቅ ልምድና ስም ያፈሩ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት የሚሰሩ ሰመጥር አንጋፋ ፕሮፌሽናሎች ናቸው።
አሁን ደግሞ ሥራቸውን በማስፋፋት፣ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በደቡብ አፍሪካ፣ ጆሃንስበርግን ማዕከል አድርገው በዘጠኙም ፕሮቪንሶች አገልግሎታቸውን ቀጥለዋል።
ከአብራካቸው የወጡ የሙያ ተተኪዎች
ይህ ቤተሰብ ሙያውን ለቀጣዩ ትውልድ አስተላልፏል።
ናታን ኤልያስ
ሆሳዕና ኤልያስ
ሊረንሶ ኤልያስ
እናመሰግናችኋለን!
ስለ እናንተ እግዚአብሔር ይመስገን።
እንወዳችኋለን!
ሆሳዕና ፎቶ እና ቪድዮ ፕሮዳክሽን ሥራው መዝሙሮችን በመቅረጽ ብቻ አልተወሰነም።
በአዲስ አበባ በተካሄዱ ትላልቅ ኢቨንቶች፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች፣ በተለይም በሀድያ ዞንና በአካባቢው ከተሞች ያለመታከት ገንዘባቸውን፣ ዕውቀታቸውንና ጉልበታቸውን አውጥተው ሰርተዋል።
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ፣ በኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሐውልት ላይ ሰመጥሮቹን ጋዜጠኞች ጌጡ ተመስገን እና ዓለምነ ዋሴን ይዘው በመሄድ ከቦታው ሆነው ዘግበዋል።
የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የእውቅናና የመኪና ሽልማት ሙሉ ፕሮግራምንም በመቅረጽ ለህዝብ አድርሰዋል።
የፕሮፌሰሩ የእልፈት ዜና እንደተሰማ ደግሞ፣ ከአዲስ አበባ ኤርፖርት እስከ ግባተ መሬታቸው ድረስ፣ በተለይም ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሚሊኒየም አዳራሽ የተገኙበትን የፕሮፌሰሩን የመጨረሻ ሰንብት በአለም አቀፍ ደረጃ ለነበሩ የሐዘን ተካፋዮች በቀጥታ ሰርጭት (Live Streaming) አስተላልፈዋል፤ ዜናዎችንም ለሚዲያ ባለሙያዎች በማድረስ ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል።
ሌላም ሌላም…
20+ ዓመታት እናመሰግናችኋለን!
እነዚህን አንጋፋና ተወዳጅ ባለሙያዎች ላለፉት 20 ዓመታት በተለይም የሀድያና የከምባታ ዘማሪያን፣ የዞኑ መንግሥት፣ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እና የዱራሜ ካምፓስ ምን ዓይነት ዕውቅና ወይም ስጦታ ሰጥተዋቸው ይሆን?
እስቲ የምታውቁትን ነገር ኮሜንት አድርጉ።
እንዲሁም አጫጭር ቪድዮዎችን በመቅረጽ በፌስቡክም ሆነ በቲክቶክ ላይ በማጋራት፣ በሕይወት እያሉ ምስጋናችሁን ግለጹ።
ለመሆኑ፣ የመጀመሪያው የቪድዮ ክሊፕ የተቀረጸላችሁ ማን ነው?
ከኢትዮጵያ ተቀርጾ በውጭ ሀገር የምትኖሩ ካላችሁ፣ ቪድዮዎቻችሁን ላኩልን። ቢያንስ በማኅበራዊ ሚዲያ ምስጋናችሁን ተናገሩ።
ሰውን በሕይወት እያለ ማመስገን ይለመድ።
የ20+ ዓመታት ወዳጆቻችሁ

Comments