Logo
YenetaTube
የሩሲያን ቁልፍ ስፍራዎች አመድ አደረግናቸው !/ዘሌንስኪ/
‎
‎ዩክሬን በአንድ ሌሊት ቢያንስ 361 ሰው አልባ አውሮፕላኖች በመጠቀም ሩሲያ ላይ ያነጣጠረ ትልቅ ጥቃት መፈፀሟ ተናገረ ።
‎
‎የዓለም ኃያላን መንግሥታት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በአውሮፓ ውስጥ እጅግ አስከፊውን ግጭት እንዴት ማቆም እንደሚቻል እየተነጋገሩ በሚገኙበት ወቅት ዩክሬን በርካታ ሰዉ አልባ ድሮሎችን በመጠቀም በሩሲያ ሰሜናዊ ምዕራብ በሚገኘው ሰፊው የኪሪሺ ዘይት ማጣሪያና ሌሎች አካባቢዎች ጥቃት መፈፀሟን አልጀዚራ አስነብቧል ።
‎
‎
‎የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከዩክሬን የተነ ቢያንስ 361 ሰው አልባ አውሮፕላኖች ለጥቃት የተላኩ ሲሆን በአብዛኛዎቹ በሩሲያ አየር መከላከያ ዘዴዎች ተጥለዋል ከእነዚህም ውስጥ አራት የአየር ላይ ቦንቦች እና ዩኤስ የተሰራው HIMARS ሚሳኤል ይገኙበታል። ብሏል
‎
‎በዩክሬን ድሮኖች ጥቃት ከተሰነዘረባቸው ኢላማዎች መካከል በሩሲያ ውስጥ ካሉት ሁለት ዋና ማጣሪያዎች አንዱ የሆነው ነዳጅ ማጣርያ መሆኑን የሩሲያ ባለስልጣናት ገልፀዋል ።
‎
‎
‎የሌኒንግራድ ግዛት አስተዳዳሪ አሌክሳንደር ድሮዝደንኮ በኪሪሺ አካባቢ ሶስት ሰው አልባ አውሮፕላኖች ላይ በተወሰደ አፀፋ ምላሽ በነዳጅ ማጣርያዉ አቅራቢያ በመዉደቃቸዉ የተነሳ እሳት መኖሩን ጠቅሰዉ ወዲያዉኑ መጥፋቱን ተናግረዋል። የተጎዳ ሰው የለም ብሏል።
‎
‎የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላን ማዘዣ የነዳጅ ማጣሪያውን ማጥቃቱን አረጋግጦ "የተሳካ ድብደባ አድርጌያለሁ" ብሏል።
‎
‎የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ በምሽት የቪዲዮ ንግግራቸው የኪየቭን ወታደራዊ እና ልዩ አገልግሎት በሩሲያ የነዳጅ ፋብሪካዎች ላይ የረዥም ርቀት ጥቃቶችን አወድሰዋል። ያሉ ሲሆን"በጣም ውጤታማ የሆኑት ጥቃቶቻችን በሩሲያ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ማጣርያ ጣቢያዎቻቸው ላይ ከባድ ጉዳት አድርሰናል " ሲል ዘሌንስኪ ተናግረዋል ።
‎
‎አክሎም "የሩሲያ የነዳጅ ኢንዱስትሪን በከፍተኛ ሁኔታ ገድበዋል, ይህ ደግሞ ጦርነቱን በእጅጉ ይገድባል." ያለዉ ዘሌንስኪ ባለፈው ሳምንት በሩሲያ ሰሜናዊ ምዕራብ ፕሪሞርስክ ወደብ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ለመጀመሪያ ጊዜ ገልጾ “ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ይህ ተረጋግጧል” ብሏል።
‎
‎በተያያዘ ዜና ዩናይትድ ስቴትስ ገቢዋን ለመገደብ እና ከዩክሬን ጋር ያለውን ጦርነት ለማቆም በማሰብ የኢነርጂ ማዕቀቦችን ለማጥበብ ግፊት እያደረገች ሲሆን ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ሩሲያ ላይ የኃይል ማዕቀብ እንዲጨምር በኔቶ ሀገራት ላይ ጫና እያደረገች ትገኛለች ።
‎
‎ትራምፕ ቅዳሜ እንዳሉት ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያ ላይ አዲስ የኃይል ማዕቀብ ለመጣል መዘጋጀቷን ገልፀዉ ሁሉም የኔቶ አገራት የሩሲያ ዘይት መግዛታቸውን እንዲያቆሙ መመሪያ አስተላልፈዋል ሲል ያስነበበው ሮይተርስ የዜና ወኪል ነዉ ።
‎
‎
‎የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.