Logo
YenetaTube
“ኢትዮጵያ ችላለች፥ በመተባበራችን ችለናል” የህዳሴ ግድብ ታላቅ የድጋፍ ትዕይንተ ህዝብ በመካሄድ ላይ ይገኛል

“ኢትዮጵያ ችላለች፥ በመተባበራችን ችለናል” የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን አስመልክቶ ታላቅ የድጋፍ ትዕይንተ ህዝብ በመስቀል አደባባይ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በድጋፍ ትዕይንተ ህዝቡ ላይ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የድጋፍ ሰልፉ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ነዋሪዎች የተለያዩ መልዕክቶችን በማንገብ በኅብረ ዜማ ታጅበው ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

ኢዜአ

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.