Logo
YenetaTube
ሳሊኒ ስለ ሕዳሴ ግድቡ ምን አሉ?

“ኢትዮጵያ ይህን ግድብ እንድትገነባ ማንም አልፈለገም

ከ15 ዓመታት በኋላ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እውን ሆነ ያሉት የጣሊያኑ ሳሊኒ (ዊ ቢውልድ) ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ፤ ግድቡን ለመገንባት የነበረውን ውጣ ውረድ እና የተከፈለውን ዋጋ ገልፀዋል።

“ለእኔና ለአገሪቱ ሕልማችን እውን ሆነ። ዛሬ ከዚህ በላይ እንዴት መኩራት ይቻላል?” ያሉት ሳሊኒ፤ ይህን ስኬት እውን ላደረጉ የግንባታውን ሠራተኞች ምስጋና አቅርበዋል።

የህዳሴግድብ ፕሮጀክትን “በዓለም በጣም ደኅንነት የነበረው ፕሮጄክት ነው” ያሉት ሳሊኒ፤ ሆኖም ግን ታላቅ ስኬቶች ዋጋ እንደሚከፈልባቸው ሁሉ በግድቡ ግንባታ ሂደት የሰው ዋጋ መከፈሉን አንስተዋል።

ፔትሮ ሳሊኒ ባለፉት 15 ዓመታት፤ 33 ሠራተኞች በመንገድ አደጋና በሌሎችም ሁኔታዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ አስታውቀዋል። ለዚህ ስኬት ሕይወታቸውን ለሰጡ ሠራተኞች ያላቸውን ከበሬታ የገለፁት ሳሊኒ፤ ለቤተሰቦቻቸውም ትውስታቸው አይጠፋም ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከ10 ሺህ በላይ ሰራተኞች ተቀይረው መስራታቸውን የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ፤ 250 ሺህ ሰዓታት ሠራተኞችን ስለ ደኅንነት ለማሰልጠን እንደዋለ ጠቅሰዋል። 25 ሺህ ወጣቶች በሥራ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደተሰጣቸው ጠቅሰው፤ ይህም ለአገሪቱ ወደፊት መሰረታዊ አበርክቶ ይኖረዋል ሲሉ በሙሉ ልብ ተናግረዋል።

የግድቡን መሠረት ካሳረፉትና በግድቡ ዙሪያ ሥማቸው በጉልህ ከሚነሳው ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር በቅርበት መስራታቸውን የተናገሩት ሳሊኒ፤ ከመለስ ዜናዊ ጋር ያደረጉትን ንግግርም ጠቅሰዋል።

“‘ለዚህ አገር ሕልም አለኝ፤ የተትረፈረፈ የኃይል ሉዓላዊነት። ዓባይ ላይ ፕሮጀክት ልትነድፍልኝ ትችላለህ? ታላቅ ፕሮጀክት፤ ቢያንስ ስድስት ሺህ ሜጋ ዋት የሚያመነጭ እፈልጋለሁ’ አለኝ። ፤በፍጥነት ስራው[አለኝ]’፤ ከአንድ ዓመት በኋላ ሕይወቱ አለፈ” በማለት የግድቡ ውጥን እንዴት እንደተጠነሰሰ ገልፀዋል።

ከኢትዮጵያ ጋር በግድብ ግንባታ እስከ ቤተሰባቸው ታሪካዊ ትስስር እንዳላቸው በስሜት የገለፁት ፔትሮ ሳሊኒ፤ ኢትዮጵያ በምን ያህል ፈተና ውስጥ ተከባ ሕዳሴን እንደገነባችም ዘርዝረዋል።

“አገሪቱ ይህን ግድብ እንድትገነባ ማንም አልፈለገም። ማንም ገንዘብ ለማቅረብ አልፈለገም። ብዙ ፖለቲካዊ ጉዳዮች፤ ብዙ ችግሮች [ነበሩ]፤ ቀላል መፍትሔ አልነበረም። ነገር ግን ኢትዮጵያዊያን ችግር ፈሪ አይደሉም። አይበገሬ ናቸው። መገዳደር ወይም ጠላት ሲገጥማቸው ጥረታቸውን በእጥፍ ይጨምራሉ፤ ማግኘት ያለባቸውን ያገኛሉ” ብለዋል።

ቢቢሲ-

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.