Logo
Getu Temesgen
አሜሪካ ከ300 የሚበልጡ የደቡብ ኮሪያ ዜጎችን በቁጥጥር ስር አዋለች
#ethiopia | የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ቢሮ ህገወጥ ናቸው ያላቸውን ከ300 የሚበልጡ የደቡብ ኮሪያ ዜጎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

እነዚህ ዜጎች ሀዩንዳይ እና ኤል ጂ በተባሉት የደቡብ ኮሪያ ካምፓኒዎች የሚሰሩ እንደሆኑ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎም ደቡብ ኮሪያ በአሜሪካ የታሰሩ ዜጎቿን ለማስለቀቅ እንደምትሰራ አስታወቃለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቾ ህዩን ባለስልጣናት ጋር ለመወያየት ወደ ዋሽንግተን ሊያቀኑ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

"ዜጎቻችን እንዲለቀቁ የቻልነውን ሁሉ እንሞክራለን" ያሉት ሚኒስትሩ፣ "በጣም ተሰምቶኛል፣ ዜጎቻችንን የማስለቀቅ ከባድ ኃላፊነት እንዳለብኝ ይሰማኛል" ብለዋል። #asiaone #thiqah

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.